20 days ago
በካፋ ዞን የተመረቁት ሞዴል የገጠር መንደሮች የገጠርን ሕይወት ወደ ዘመናዊነት ያሸጋገሩ አዲስ ተስፋዎች
*********************
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የተገነቡት ሞዴል የገጠር መንደሮች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ርክብክብ መደረጋቸው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የነበረውን ባህላዊ የኑሮ ዘይቤ ወደ ዘመናዊነት የሚያሸጋግር ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል።
በዞኑ በጨና እና ሺሾንዴ ወረዳዎች በመንግስት፣ በተጠቃሚዎች እና በግል ባለሀብቶች የተቀናጀ ድጋፍ ተገንብተው የተመረቁት እነዚህ መንደሮች፣ ዜጎች በአካባቢያቸው ሆነው የተረጋጋና ዘመናዊ ሕይወት እንዲመሩ መደላድል ፈጥረዋል።
በሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተበሰረው የሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ የዜጎችን ሕይወት በተጨባጭ በመቀየር በገጠር ዘመናዊነት እንዲሰርጽ አድርጓል።
የመደመር መንግሥት የሕዝብን ሕይወት የሚያሻሽሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ መንግስትም ለዚህ ስኬት የተቀናጀ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የመንደሮቹ መገንባት የገጠር ሽግግርን በማሳደግ በኅብረተሰቡ የኑሮ ዘይቤ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩንና አሁን ላይ ይህ ልማት በ16 ወረዳዎች በተሟላ ሁኔታ መፈጸሙን አብራርተዋል።
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው የመንደሮቹ መገንባት ዜጎች በገዛ አካባቢያቸው ዘመናዊ የኑሮ ሁኔታን እንዲመሩ ማስቻሉን ገልጸዋል።
በጣቢያው የተገኙ የሞዴል ገጠር መንደር ተጠቃሚዎችም ቀደም ሲል ረዥም ርቀት ተጉዘው ያገኙ የነበሩትን መሠረታዊ አገልግሎቶች አሁን በአቅራቢያቸው ማግኘት መቻላቸውን ገልጸው፣ ይህም ከዘመናዊነት ባሻገር ማህበራዊ መስተጋብራቸውን ይበልጥ እንዳጠናከረው ተናግረዋል።
በሰለሞን ባረና
#kaffazone #modelvillages #ruraldevelopment #southwestethiopia #ethiopiadevelopment

1 month ago
ቃልን በተግባር የመለወጥ እውነተኛ ማረጋገጫ ከ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ እቅድ እስከ ታሪካዊው የሞርጌጅ ፋይናንስ ስምምነት
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ከጉባ ብስራቶች እና ሀገራዊ የማንሰራራት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የቤት ልማት ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ነበር።
በባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶች መገንባታቸውን በወቅቱ ያሳወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ደግሞ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በመንግሥት፣ በግል እንዲሁም በመንግሥትና የግል አጋርነት ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።
ይህንን ግብ ለማሳካት የ3D ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ዘመናዊ አሠራሮችን ማስገባት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት ፋብሪካዎችን ማጠናቀቅ እና የሞርጌጅ ሥርዓት በመዘርጋት ዜጎች በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ወይም በተመጣጣኝ ዋጋ የሚከራዩበት መፍትሔ እንደሚበጀው ተናግረው ነበር።
ይህ በምክር ቤት የተገባው ቃል ሳይዘገይ በፍጥነት ወደ ተጨባጭ ተግባር መለወጡን የሚያሳይ ታሪካዊ እርምጃ ዛሬ ተወስዷል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ተፈረሟል።
በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመውና በIFC በኩል እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚደረግበት ይህ ታላቅ ተቋም፣ በባንክ ዘርፉ የሚታየውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን በመቅረፍ ተደራሽ የቤት መግዣ ብድር እንዲኖር ያስችላል።
ይህም የተመጣጣኙን 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ግብ የሚያሳካ፣ የግል ዘርፉን ተሳትፎ የሚያሳድግ እና ኢትዮጵያ ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ስኬታማ ጉዞ የሚያፋጥን ትልቅ የፖሊሲ እና የተግባር ውጤት ነው።
#housingethiopia #mortgagefinance #ethiopiadevelopment #ifcethiopia #economicgrowth

2 months ago
አዳማን ያደመቀው አዳማ ሲቲ አሬና
#adamacityarena #adama #ethiopia #smartcityadama #corridordevelopment #ethiopiadevelopment
5 months ago
ከስንዴ እስከ አረንጓዴ አሻራ ዓለምን ያስደመሙት የስኬት ምስጢሮች
#pmabiyahmed #ethiopiadevelopment #aiethiopia #ethiopiatourism
Sponsored by
Surafel
5 months ago
የሚፈጥርና የሚሰራ ዜጋ መፍጠር ነው ዓላማችን ➡️
https://youtu.be/8RhS67wUS... #gelanguraindustrialpark #ethiopiadelivers #pmabiyahmed #ethiopiadevelopment
5 months ago
5 months ago
ዓለም መጤ አይፈልግም የማትሰለቸን ኢትዮጵያ ናት
https://youtu.be/viRi8qm-u... #gelanguraindustrialpark #ethiopiadelivers #pmabiyahmed #ethiopiadevelopment
Comments