7 months ago
በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሥራ ሰዓት ስልክ መጠቀም ተከለከለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ባደረገው አዲስ የአሰራር ለውጥ (ሪፎርም)፣ ሰራተኞች በሥራ ሰዓት የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይችሉ አስታወቀ። እንደ አዲስ አበባ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) ዘገባ፣ ይህ መመሪያ በተለይ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ክፍል ውስጥ በሚሰሩ ባለሙያዎች ላይ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል።
ባለሙያዎች ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ስልካቸውንና የግል ቦርሳቸውን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሎከር ውስጥ ቆልፈው የማስቀመጥ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
ሰራተኞች ደንበኛ እያስተናገዱ ስልክ በመነካካት (social media በመጠቀም) የሚባክነውን ጊዜ ለማስቀረትና ለተገልጋዮች ተገቢውን ክብር ለመስጠት የታለመ ነው።
በቢሮው ውስጥ የሚያገለግሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ደንበኛ ፊት ስልክ መጠቀም ለተገልጋዩ ምቾት አይሰጥም ነበር፤ አሁን ግን ትኩረታቸውን ሥራቸው ላይ ብቻ በማድረጋቸው አገልግሎቱን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን ችለዋል።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሃኑ እንደተናገሩት፣ ይህ አሰራር "ቆይ ስልክ ላንሳ" ወይም "መልዕክት ልመለስ" የሚሉ ሰበቦችን በማስቀረት የተገልጋዮችን እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል።
ይህ ዲጂታል አሰራርን ከሥራ ስነ-ምግባር ጋር ያቆራኘው አዲስ መመሪያ፣ ቢሮውን የቀልጣፋ አገልግሎት ተምሳሌት እንደሚያደርገው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #tradebureau #publicservice #workethics #mobileban #ethiopianews #efficiency

8 months ago
የ580 ኪ.ሜ የፓስፖርት እንግልት አበቃ!
ሚዛን አማን አዲስ ቅርንጫፍ ተከፈተ!
#ethiopia | "ፓስፖርት ለማውጣት የሚደረገው የረጅም ርቀት ጉዞ ታሪክ ሆኗል"
ለረጅም ዘመናት የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከ580 ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጪ ሲዳረጉ ለነበሩ በሚዛን አማን እና አካባቢዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ቅርንጫፍ ዛሬ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ስራ ጀምሯል።
የአዲሱ አገልግሎት እና የተቋሙ ማሻሻያዎች:
✅ ቅርበት: አገልግሎቱ በደጃችሁ መጥቷል፤ እንግልት ቀርቷል።
✅ የቆይታ ጊዜ: የፓስፖርት የአገልግሎት ዘመን ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ ብሏል።
✅ ተደራሽነት: ይህ ቅርንጫፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተከፈቱት 15 አዳዲስ ቅርንጫፎች አንዱ ነው።
አገልግሎቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ተገልጋይ በተቋሙ ድረ-ገጽ www.immigration.gov.et በመግባት፣ በመመዝገብ እና ቀጠሮ በመያዝ በሚዛን አማን ቅርንጫፍ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላል።
ይህ እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና ይድረስ!
#mizanaman #passport #immigration #publicservice #southwestethiopia #goodnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለሦስት ተቋማት በውክልና ተሰጠ
#ethiopia | የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት (ICS) የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባዎችን በውክልና እንዲሰጡ ከተመረጡ የመንግሥት ተቋማት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ።
🤝 ውክልና የተሰጣቸው ተቋማት፦
አገልግሎቱ በአዲሱ አዋጅ መሰረት የሚከተሉትን ተቋማት በውክልና መርጧል፦
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፦ እስከ ወረዳ በሚገኙ መዋቅሮች የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስራዎችን በሙሉ በውክልና ያከናውናል።
የጤና ሚኒስቴር፦ በተመረጡ ወሳኝ ኩነቶች (እንደ ልደት) ላይ የማሳወቅና የምዝገባ ሂደቶችን ያመቻቻል።
የመከላከያ ሚኒስቴር፦ በተቋሙ ስር ያሉ ወሳኝ ኩነቶችን የማሳወቅ ፈቃድ ተሰጥቶታል።
🚀 "ዲጂታል ምዝገባ ለዲጂታል ኢትዮጵያ"
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደገለጹት፣ ይህ የምዝገባ ሥርዓት ዘመናዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ለሀገራዊ ፖሊሲ ቀረፃ ወሳኝ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ፦
ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በተበለጸገ አዲስ ሶፍትዌር አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል።
ምዝገባው ለዲጂታል ማንነት መታወቂያ (Digital ID) እና ለ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ስኬት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
#ethiopia #immigration #civilregistration #digitalidentity #digitalethiopia2030 #ics #publicservice #addisababa

Sponsored by
Surafel
Comments