የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር መቐለ ዉስጥ ተወያዩ::
የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በቅርቡ የትግራይ ክልል ርዕሰ-መስተዳድርነታቸውን መልሰው ከተረከቡት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር መቐለ ዉስጥ ተወያዩ። የ89 ዓመቱ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ወደ መቐለ የተጓዙት የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተፈራረሙትን ግጭት የማቆም ሥምምነት አፈጻጸም የመከታተል ኃላፊነት የተጣለባቸውን ወታደራዊ ባለሙያዎች አስከትለው ነው።
የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ኦባሳንጆ እና አብረዋቸው ከተጓዙ ልዑካን ተገናኝተው መነጋገራቸውን በፌስቡክ ፎቶግራፎች አስደግፎ ባሠራጨው መልዕክት አስታውቋል።
ከቅርብ ወራት ወዲሕ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የህወሓት ልዩነት እየተካረረ ነዉ። ህወሓት በጳጉሜ 2012 በተካሔደ ምርጫ የተቋቋመ የክልል ምክር ቤቱን ወደ ሥራ በማስመለስ ደብረፅዮን ርዕሰ-መስተዳድርነቱን እንዲረከቡ አድርጓል።
ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ "ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የአፍሪካ ኅብረትን ጥረት እንዲደግፉ" በኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ዳግም የተሾሙት ከአንድ ወር ገደማ በፊት ነበር። የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ከጥቅምት 2013 እስከ ጥቅምት 2015 የተካሔደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ግጭት በማቆም ሥምምነቱ እንዲገታ የአፍሪካ ኅብረትን አደራዳሪነት መርተዋል።
DW Amharic #amharic

4 days ago