ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ስትቀጣ፤ ለ1,655 ዜጎች ደግሞ ምህረት አደረገች።
ሳዑዲ አረብያ በዚህ ሳምንት 4 ኢትዮጵያውን በሞት ስትቀጣ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 1655 ዜጎቿ በምህረት እንዲለቀቁ ማደረጓን አስታውቃለች።
የበሳዑዲ የሞት ቅጣት ተበይኖባቸው ፍርዳቸውን በተለያዩ እስር ቤቶች ሆነው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም ከቤተሰቦቻቸው አንዱ ለዶቼቬለ ተናግሯል።
በሳዑዲ አረብያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መረጃ መሠረት ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ሁለት ኢትዮጵያውያን በናጅራን ግዛት፣ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያውያን በአሲር ግዛት በስቅላት ተገድለዋል።
አራቱም ኢትዮጵያውያን በሞት የተቀጡት ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕፅ ይዘው በመግባታቸው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ እስር ቤት የሚገኙ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምህረት እንዲሰጣቸው ማድረጉን በዚሁ ሳምንት አስታውቋል።
በሳዑዲ አረብያ በስቅላት ስለተገደሉትም ሆነ በምኅረት ስለተለቀቁት ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ዶቼቬለ ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነበያት ጌታቸው የእጅ ስልክ ላይ ቢደውልም ስልካቸው አልተነሳልንም። #dw
Seledadotio

15 hours ago