21 days ago
የመኖሪያ ቤት እጥረትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቅረፍ ይሠራል፦ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
**************
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ላለፉት ቀናት በድሬዳዋ ባካሄዳቸው የተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች የ50ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን አጠቃልሏል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ ኮርፖሬሽኑ የወርቅ እዮቤልዩውን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በድሬዳዋ በተለያዩ መርሀ ግብሮች በማክበሩ አመስግነዋል።
ድሬዳዋ ከለውጡ ወዲህ ሰላምና አንድነቷን አስጠብቃ በማስቀጠል የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳ ያላቸው የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኗን ገልጸዋል።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዚህ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃይለብርሃን ዜና፣ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 8 ዓመታት ዕድሜና ልምዱን የሚመጥኑ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ገቢውን ከ30 እጥፍ በላይ አሳድጓል ብለዋል።
በቀጣይም አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የመኖሪያ ቤት እጥረትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቅረፍ ይሠራል ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወጠነውን 1.5 ሚሊዮን ቤቶች የመገንባት ዕቅድ በውጤታማነት ለመተግበር በትኩረት እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የኮርፖራሽኑ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እውነቱ ወርቅነህ፣ ኮርፖሬሽኑ ካጋጠመው ውድቀት በመነሳት ባለፉት 8 ዓመታት ባከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች የቤቶች ግንባታ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል መሆን ችሏል ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን ከአዲስ አበባ በመቀጠል ከግንቦት 10 እስከ 17 በድሬዳዋ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲያከብር ቆይቶ ነው በዛሬው ዕለት አጠቃልሏል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ethiopia #housingcorporation #50years #goldenjubilee #diredawa #ebc

Comments