3 days ago
♦️1:45 ደቂቃ በቶሮንቶ ሠማይ ስር
♦️FIFA እና Destination Toronto በጋራ የሠጡኝ ወርቃማ የጉብኝት ዕድል(ክፍል አንድ)
♦️ቶሮንቶን ከሜዳ ውጪ(Off the Pitch)
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ወደ ሌላ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮኛል FIFA እና Destination Toronto ለአለም ዋንጫ ዘገባ ከመጡ ኢንተርናሽናል ጋዜጠኞች ዛሬ የጉብኝት ዕድል ሠጥተውናል፤እኔም ይሄን ዕድል ካገኙት ጋዜጠኞች ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሆኜ ቶሮንቶን ከእግር እስከራሷ የማየት ዕድል አግኝቻለሁ ከ1:45 ደቂቃ በላይ በዘለቀው የጉብኝት መርሃ ግብር የማውቃት የሚመስለኝ ነገር እንደማላውቃት የተረዳሁበትን አስገራሚ ጉብኝት አድርጌ በግርምት እጄን አፌ ላይ ጭኜ ተመልሻለሁ።ታሪክን፣ጥንታዊነትንና ዘመናዊነትን በውስጧ ሸሽጋ የያዘችው የኢኮኖሚ፣የቢዝነስ ከተማና ከ170+ አገሮች የመጡ ሰዎች የሚኖሩባት ባህላዊውን ከዘመናዊነት ጋር አጣምራ የያዘች ተወዳጅ ከተማ ናት።
በአንድ ጎዳና ላይ እየተራመዱ ብዙ ቋንቋዎችን ከሠሙ በትክክልም እርስዎ ያሉት ቶሮንቶ ነው፤ምክንያቱ ደግሞ ከ170 በላይ ሀገሮች የሚኖሩባት ብቻ ሳይሆን የተለየ ቋንቋ የሚነገርባት ዓለምን በአንድ ቦታ ሠብስባ የያዘች ከተማ ናትና።
በምሽት የካናዳ ምልክት ተደርጎ ከሚወሠደው፣ቶሮንቶን ልዩ ውበትና ድምቀት የሚያላብሳት CN Tower በሚፈልቀው ብርሃን፣በLake Ontario የባህር ዳርቻ ከወዳጅ ወይም ከፍቅረኛ ጋር የፍቅር ማር የሚቆረጥባት ከአለማችን ለኑሮ ምቹና ሠላማዊ ተብለው ከሚጠሩ ሀገሮች አንዷ፣ በዓመት ከ25–30 ሚሊዮን፣በበጋ ወቅት ደግሞ ከ150,000 በላይ ቱሪስቶች በቀን የምትጎበኘው የቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ቶሮንቶን በToronto Double-Decker አውቶብስ አናት ላይ ተቀምጬ ታዘብኩትን የዛሬ የ1:45 ደቂቃ ጉብኝቴን በወፍ በረር ላስቃኛችሁ።
የተሳፈርንበትን Double-Decke Bus የሚዘውረው የህይወቱን ግማሽ ክፍል ለካናዳ የገበረው አቶ ፍቅሩ ብርሃኔ መሆኑ በጉብኝቴ የቤተሠብነት ስሜት እንዲሠማኝ ያደረገ ሲሆን በጣፍጭ አንደበቱ ታሪካዊ ቦታዎች የፍትፍት ያህል ፈትፍቶ ሲያጎርሠን የነበረውን አስጎብኚያችንን MASHAALን ከልብ ላመሠግነው ወደድኩ፤በቅድሚያ የጉብኝታችን መነሻ ስለነበረው
♦️University of Toronto
ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ ዕድሜ ጠገብ ነው፤የኛውን የቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የአሁኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ123 ዓመት ዬበልጠዋል፤የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ76 ዓመት አዛውንት ሲሆን ዕድሜ ጠገቡ University of Toronto ደግሞ የ199 ዓመት አረጋዊ ነው፤እንደ አስጎብኚያችን MASHAALከ102 በላይ ተማሪዎችን እቅፍ ድግፍ አድርጎ በውስጡ ይዟል፤ዩኒቨርስቲውን ከአለማችን የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ከ175 የዓለማችን ሀገሮች የመጡ ተማሪዎች መዳረሻ ብቻ ሳይሆን በባችለር፣በማስተርስና በፒኤችዲ ፕሮግራሞች በመታቀፍ ከህልማቸው የሚገናኙበት ትልቁ የዕውቀት ፋብሪካም ነው፤
በሚመደብለት ከ3.62 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በካናዳ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ቀዳሚ የሆነው University of Toronto ካሉት ከ16ሺ የበለጡ ስታፎች ከ9ሺ በላዩ አስተዳደሩን የሚዘውሩ አመራሮች መሆናቸው ቶሮንቶን ያለ አዋዜ አጣጥሞ እንደበላት በቃሉ የሚሠጠው መረጃ ከሚያሳብቅበት አስጎብኚያችን MASHAAL መረዳትም ተችሏል።
ከዓለማችን ምርጥ 30 ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት University of Toronto የአለምን በዕውቀታቸው እንዳሻቸው ከሚዘውሩ በዕውቀቱ የታጠቁ ሙሁራንን ከማፍራቱ በተጨማሪ የካናዳን ኢኮኖሚ በፍይናንስ ከሚያግዙ ተቋማት መካከልም አንዱ ነው፤በዚህም መሠረት ከ15 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በላይ ወደ ካናዳ ፈሰስ መመድረጉ ይሄ ገቢዎች ነው?ወይስ ኢትዮ ቴሌኮም የሚል ጥያቄ ማስመዘዙ አልቀረም"
♦️TTC የቶሮንቶ ከተማ የልብ ምት
Toronto Transit Cooperation በምህፃረ ቃል TTC የደም ስር ወይም የከተማዋ የልብ ምት ቢባል ቃሉ አልተጋነነም፤በተለይም ለToronto እና አካባቢው ያበረከተው ጥቅም ከመጓጓዣነትም በላይ የሕይወት አገልግሎት ነው። ከተማዋን የሚያንቀሳቅስ ደም መስመር ተደርጎም ይቆጠራል፤TTC የከተማው የደም ሥር ነው።በቀላል አማርኛ
እንደ ደም ሥሮች ደምን ወደ ሰውነት ክፍሎች እንደሚያደርሱ ሁሉ TTC ሰዎችን ወደ ሥራ፣ ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ ሆስፒታል፣ ወደ ገበያ እና ወደ መዝናኛ ቦታዎች በየቀኑ በማመላለስ ህይወት በቶሮንቶ የቀለለ እንዲሆን እንዳደረገ በጉብኝታችን ወቅት ተረድተናል።
በቅርቡ የወጣ ጥናት እንደሌለ ነገር ግን የ2025ትን ጥናት መነሻ አድርጎ እንደ ነገረን አስጎብኚያችን MASHAAL መረጃ ከሆነነ የቶሮንቶን ከተማ ከጫፍ ጫፍ ለማገናኘት ማልደው የሚሠማሩት የTTC በእኛ ሀገር አጠራር የካናዳ አንበሳ አውቶቢስ አገልግሎት ከ2000 በላይ ቀይና ነጭ አውቶቢሶችን 250 የሚጠጉ ነኤሌክትሪክ፣ከ200 በላይ ረዣዥም ባሶችን ቶሮንቶ ትጠቀማለች።
የTTC የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ባይካድም ትራፊክን ይቀንሳል፣መኪና መግዛት፣ ነዳጅ መሙላት እና ፓርኪንግ መክፈል ከሚጠይቀው ወጪ ይልቅ ብዙ ጊዜ ይቀላል፤ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እና ወደ ንግድ ማዕከላት እንዲደርሱም ከማገዙም በላይ ለሁሉም ተደራሽ በመሆን በኩል መኪና የሌላቸው፣ ተማሪዎች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ከተማው እንዳያገላቸው ይልቅ እንዲጠቀሙበት ትልቅ ዕድል ይሠጣል።ይህ ነፃና የተመቻቸ የትራንስፖርት ፍሠት ያለ TTC የባቡር አገልግሎት የተሳለጠ ይሆን ነበር ብሎ ለስህተት ይዳርጋል።ምክንያቱም የTTC ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት በዓመት ወደ ከ180 ሚሊዮን በላይ በቀን ደግሞ በየቀኑ ከ 690,000 በላይ ወይም 1ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ከአንደኛው የከተማው ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በማመላለስ የቶሮንቶ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጉብኝቴ አሳይቶኛል።
♦️በቶሮንቶ ከ110 ካሬ ኪ.ሜ. በላይ የሚሸፍን የተፈጥሮ ሸለቆዎች ያለባት ከተማ
አብዛኛው ሠው ስለ ቶሮንቶ ሲያስብ ከፊቱ ቀድሞ የሚመጣበት ወይም የካናዳና የቶሮንቶ መለያ አድርጎ የሚወስደው CN Tower ን ነው፤ከትናንቱ የሚዲያ ጉብኝቴ የተረዳሁት ትልቁ ቁምነገር ግን ቶሮንቶን ከሌሎች ትልልቅ ከተሞች የሚለየው የRavine System (የተፈጥሮ ሸለቆዎች አውታረ መረብ) ያለበት ከተማ መሆኑ ነው እላለሁ።ከላይ ለማነሳት እንደሞከርኩት ብዙ ሰዎች ስለቶሮንቶ ሲያስቡ የመጀመሪያው የሚያስታውሱት CN Tower ን ነው፣ ነገር ግን የቶሮንቶ እውነተኛ ልዩነት በከተማው መሃል ውስጥ የሚያልፉ የተፈጥሮ ሸለቆዎች መኖራቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን?በሚገርማችሁ ሁኔታ በከተማው ውስጥ በአጠቃላይ 110 ካሬ ኪ.ሜ. የሚሸፍን የሸለቆ ስርዓት አለ፤
ይህ ደግሞ የከተማውን 17% በላይ እንደሚሸፍን የአስጎብኚያችን መረጃ ይጠቁማል፤በዓለም ላይ ቀከተማ ውስጥ ካሉ የሸለቆ ስርዓቶች ትልቁ በመሆንም ቶሮንቶን ከፊት ያስቀምጣታል።ስለዚህ በቶሮንቶ አንድ ሰው በዳውንታውን ውስጥ ያሉ ቁመተ መለሎ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች መካከል ሲሆን ከ10 ደቂቃ በኋላ በዱር ውስጥ እንዳለ ሊሰማው ቢችል አይፈረድበትም፤ይሄንን የታዘቡ ደግሞ ቶሮንቶን “city within a park” (በፓርክ ውስጥ ያለች ከተማ) ብለው እስከመግለፅ የተገደዱት።
ቶሮንቶ ሰማይን የሚነኩ ሕንፃዎችና የተፈጥሮ ዱር በአንድ ቦታ የሚገናኙባት ከተማ መሆኗ በእርግጥም የተለየች ከተማ የሚል ስያሜ እንዲሠጣት ያስገድዳል።።
የክፍል አንድ የወፍ በረር ጉብኝቴ ይሄንን ይመስላል፤በክፍል ሁለት ትዝብቴ ቀ1:45 ደቂቃ በፈጀው ጉብኝቴ የካናዳዊያን ምልክት ተደርጎ ስለሚወሠደው CN Tower፣ስለ ሮያል ኦንታሪዮ ሙዚየም፣ቶሮንቶንስላጥለቀለቁት ላይብረሪዎች፣የፍቅር ማር ስለሚቆረጥባትና የመዝናኛ ዋነኛ የልብ ምት ስለሆነችው Lake Ontario እና በካናዳ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የጉብኝት ባሳችንን Double-Decke ከሚዘውረው ኢትዮጵያዊ ህይወትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቃረምኩትን አካፍላችኋለሁ፤FIFA እና Destination Toronto በጋራ ይሄን ዕድል ስለሠጡኝ ከልብ አመሠግናለሁ🙏🙏...(ይቀጥላል)....
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከከናዳ ቶሮንቶ

4 days ago
ዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያ የደኅንነት አቅም ላይ ሙሉ እምነት አላት - አምባሳደር ዳረን ዌልች
**********************
የዩናይትድ ኪንግደም በአፍሪካ አህጉር ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለውን፣ የላቀ የሰነድ ማጭበርበር (ፎርጀሪ) መመርመሪያ የኤቪዬሽን ደኅንነት ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አበርክታለች።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፣ ይህ የቴክኒክ ድጋፍ የሁለቱን ሀገራት የጠበቀ ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በእንግሊዝ ሀገር የተመረተው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መደረጉንም አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።
ይህም ዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያ የደኅንነት አቅም ላይ ያላትን ሙሉ እምነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አክለዋል።
ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቁልፍ የዓለም አቀፍ መተላለፊያ ማዕከል መሆኑን ያነሱት አምባሳደሩ፣ የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች የእንግሊዝ ዜጎችን ጨምሮ የዓለምን ማኅበረሰብ ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን የላቀ ጥረት አድንቀዋል።
"ሁላችንም ደኅንነታችን እስካልተረጋገጠ ድረስ የማንም ደኅንነት የተጠበቀ አይሆንም" በማለትም የጋራ ደኅንነትን ፅንሰ-ሀሳብ አስምረውበታል።
ይህ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እና ትብብር ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎችን ለመከላከል እንዲሁም የጉዞ መስመሮችን ከሕገ-ወጥ ድርጊቶች ነጻ ለማድረግ የላቀ ሚና ይጫወታል።
አምባሳደሩ እንዳብራሩት የሁለቱ ሀገራት አጋርነት በደኅንነት ዘርፍ ብቻ ሳይወሰን፤ በጤና፣ በትምህርት እና በኢኮኖሚ ልማት ጭምር ሰፊ መሠረት ያለው ነው።
በቀጣይም በቢሾፍቱ በሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን እና ግንባታ ላይ የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
አውሮፕላን ማረፊያው በዓለም ላይ ካሉ ደኅንነታቸው እጅግ ከተጠበቁ ተርሚናሎች አንዱ እንዲሆን በጋራ ለመሥራት ዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላትም አምባሳደሩ ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ወደ ሂትሮው፣ ማንችስተር፣ ጋትዊክ እና ግላስኮ የሚደረጉ ዕለታዊ እና መደበኛ በረራዎች የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ይበልጥ እያሳደጉት መሆኑን አምባሳደሩ አንስተዋል።
የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጠው ይህ የደኅንነት ትብብር ውጤታማነቱ ታይቶ በቀጣይም ተጨማሪ የቴክኖሎጂ ድጋፎች እንደሚደረጉ አመላክተዋል።
#ethiopia #uk #cooperation #aviationsecurity #aviationtech #ethiopianairlines #boleairport #niss #ebc

2 months ago
የአፍሪካ ድምፅ በቻይና
የሕግ ባለሙያው ቴዎድሮስ ጌታቸው በባዎ (BOAO) ፎረም
#ethiopia | ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያና አማካሪ ቴዎድሮስ ጌታቸው (TP)፣ አፍሪካን ወክለው በቻይና ሄይናን ግዛት በተካሄደውና 25ኛ ዓመቱን ባከበረው ታላቁ የኢንቨስትመንት ፎረም (Boao Forum) ላይ የጥናት ጽሁፋቸውን አቅርበዋል።
ታሪካዊ ውክልና
በአህጉር ደረጃ ተመርጠው በ"Rule of Law" ፓነል ላይ ከአውሮፓና እስያ ታዋቂ መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
አብረውት የተሳተፉ ታዋቂ ሰዎች
የቀድሞው የስሎቬንያ ፕሬዝዳንት ዳኒሎ ቱርክ፣ የዓለም አቀፉ ሜዲዬሽን ተቋም (IOMed) ዋና ፀሃፊ ቴሬሳ ቼንግ እና የBRILSA ፕሬዝዳንት ዋንግ ጁፌንግ።
ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥቦች
የኢትዮጵያና የአፍሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ዕድሎች፣ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ፈተናዎች፣ እና የነፃ ንግድ ቀጠናዎች አስፈላጊነት።
ተሳታፊዎች
የሲንጋፖር፣ አዘርባጃን፣ ስሪላንካና ካዛኪስታን መሪዎችን ጨምሮ ከ60 ሀገራት የተወከሉ 2,000 ልዑካን።
"multilateral cooperation እና Rule of Law ለዓለማችን ወቅታዊ ፈተናዎች ቁልፍ መፍትሄዎች ናቸው!" — ቴዎድሮስ ጌታቸው
#getu #lawandinvestment #internationaltrade #boaoforum #ethiopia #africarising #legalexcellence #hainan #china #tewodrosgetachew #ኢትዮጵያ #ንግድ #ህግ #ባዎፎረም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago
Melat will be elected. Ethiopia will prevail!
ሜላት በወገኖቿ ድጋፍ ትመረጣለች! 🇺🇸
Ethiopians living in the DMV area will participate in the Melat Congress on Sunday, March 15, from 4:00 PM to 6:00 PM. Ethiopians at home and around the world will be watching your cooperation and dedicated efforts live. There is no doubt that your actions will inspire and amaze the world. With the strong support of her people, Melat will be elected. Ethiopia will prevail!
ሜላት በወገኖቿ ድጋፍ ትመረጣለች!
— ለዲ ኤም ቪ (DMV) ነዋሪዎች የቀረበ ጥሪ
በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ (DMV) የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሆይ! ለሜላት የኮንግረስ ጉዞ የሚደረገው ታሪካዊ የድጋፍና የርብርብ መድረክ ለፊታችን እሁድ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም (March 15, 2026) ቀጠሮ ተይዞለታል።
የመርሐ-ግብሩ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
📅 የቀጠሮ መረጃ
ቀን፦ እሁድ ማርች 15 (March 15)
ሰዓት፦ ከቀኑ 10:00 (4:00 PM) እስከ ምሽቱ 12:00 (6:00 PM)
ትኩረት፦
ለሜላት የኮንግረስ መግባት የሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያና የድጋፍ ርብርብ።
🌍 የዓለም ሕዝብ ዓይን በእናንተ ላይ ነው!
ይህ መርሐ-ግብር በሀገር ቤትና በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ስርጭት (Live) የሚከታተሉት በመሆኑ፦
የዲ ኤም ቪ (DMV) ነዋሪዎች ያላችሁን አንድነትና አቅም ለዓለም የምታሳዩበት ልዩ አጋጣሚ ነው።
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ የሚደረገውን ጥረት የምታግዙበት ታሪካዊ ወቅት ነው።
💪 "አለምን የሚያስደምም ተግባር እንደምትፈፅሙ አያጠራጥርም!"
ሜላት በወገኖቿ ድጋፍና ብርታት የኮንግረስ መቀመጫን እንደምትይዝ ሙሉ እምነት ተጥሎባችኋል። ይህ ርብርብ የግለሰብ ስኬት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ድምፅ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲሰማ የሚያደርግ ትልቅ ድል ነው።
ድል ለሜላት!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
#melatforcongress #dmvethiopians #ethiopiansinusa #supportmelat #unity #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

6 months ago
📣ደሞዝተኛ እናድርግዎ !
📱 የLinkedIn አካውንቶን በማከራዬት በሳምንት ከ 1500 እስከ 4000 ብር ድረስ መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ ?
💥 መስፈርቶች ፦
✔️ከተከፈተ 1 ዓመት እና ከዛ በላይ።
📱 100+ Connection
📱 300+ Connection
📱 500+ Connection
📱 1000+ Connection
💬 በውስጥ መስመር ➡️
linkedin_ethiop ያግኙን
📱 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️ linkedin_ethiopiaa
😀ስልክ ፦ +251934848429
🤝 Stable • Trusted • Long-Term Cooperation!

Sponsored by
Surafel
7 months ago
📣ደሞዝተኛ እናድርግዎ !
📱 የLinkedIn አካውንቶን በማከራዬት በሳምንት ከ 1500 እስከ 4000 ብር ድረስ መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ ?
💥 መስፈርቶች ፦
📱 100+ Connection
📱 ከተከፈተ አንድ ዓመት እና ከዛ በላይ

የኢትዮጵያ"የሀይል ማስፋት" (Power Projection)፡በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዲፕሎማሲ ጥረት...!
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia | በቅርቡ የተከናወነው በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የG-20 የኢትዮጵያ ተሳትፎ እንዲሁም የማሌዥያና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት፣የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እየተከተለው ያለውን የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ "የሀይል ማስፋት"ስትራቴጂ ቁልፍ ማሳያዎች ናቸው።ይህ ስትራቴጂ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ በማስፋት፣ለሀገር ውስጥ ዕድገት የሚያስፈልገውን ሀብትና ዕውቀት ለመሳብ ያለመ መሆኑን ያሳያል።
🔴 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ራዕይ፦
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋናነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (Economic Diplomacy) እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።ከዓለም ደቡብ (Global South) አገሮች በተለይም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር አዲስና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መገንባት፤ በሁሉም ወገን የሀገርን መሰረታዊ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እና ማረጋገጥ አጋርነትን ማስፋትን ያካትታል።
የ"ብልጽግና" ጽንሰ-ሀሳብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሙሉ ከብልጽግና ራዕይ ጋር የተሳሰሩ ሲሆን፣ የውጭ ግንኙነት በዋናነት ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲያገለግል ለማድረግ ያለመ ነው።
🔴የቡድን ሀያ አባለ ሀገራት (G-20) ተሳትፎ፦የብዙ-ዋልታ ዓለምን (Multipolar World) መቀበል ኢትዮጵያ በG-20 ስብሰባ ላይ እንደ ልዩ እንግዳ መሳተፏ፣በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ተዋናይ አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ጥረት ያሳያል።በዓለም የፋይናንስ እና የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ።ክቡር ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ እንደሚገልጹት፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ዋና መስሪያቤት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካን አጠቃላይ ጥቅም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በማንሳት፣ የሀይል ማስፋት ጥረቷን ከአህጉራዊ ሚናዋ ጋር አጣምራለች።
🔴 የእስያ መሪዎች ጉብኝት፦የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት ድልድይ የማሌዥያ እና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት የዶ/ር ዐቢይ የዲፕሎማሲ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ነው።ከእነዚህ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የእስያ "ነብሮች" (Asian Tigers) ጋር ግንኙነት መፍጠር የኢትዮጵያን የመበልፀግ የማደግ ስትራቴጂ ለመደገፍ ወሳኝ ነው።
🖊እንደ መውጫ ስልታዊ ትኩረት የሀይል ማስፋት ትርጉም⁉️
ሲንጋፖር የላቀ የሎጅስቲክስ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የከተማ ልማት (Smart City)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልምድ ሽግግር፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ፈተና ለመቅረፍ ዘመናዊ የንግድ መስመሮችን መገንባት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል ።( በሀገራችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይጠቀሳል ።
ማሌዥያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) በኤሌክትሮኒክስና በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሳብ፣ የዘይትና ዘይት ነክ ምርቶች ንግድ በማጠናከር የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የንግድ አጋሮች ማጎልበትን ያሳያል ።( Industrial Park Development cooperation ስር የሚከናወኑ የእውቀት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መጥቀስ ይቻላል ።)
🔴የማጣቀሻዎች (Reference )
1️⃣Abiy Ahmed (PhD). Medemer: A Collective Journey. (የዶ/ር ዐቢይ የፍልስፍና መሰረት ለዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጂያቸው።)
2️⃣ Minister's Office. Official Press Releases on G20 and Bilateral Visits. (የጉብኝቶቹን ዓላማ እና የተደረጉትን ስምምነቶች ለመረዳት።)
3️⃣Think Tank Analysis. ISS, Chatham House or Brookings papers focused on Ethiopia's shift in foreign policy towards Asia and Global South engagement.
ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የሀይል ማስፋት እቅድ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ኢኮኖሚን ማዕከል ባደረገ እና በብዙ-ዋልታ ትብብር ላይ በተመሰረተ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ እየተመራ መሆኑን ያሳያል ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

መልህቁን የሚደግፉ ሌሎች ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር ጥያቄን ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት አንፃር ከዚህ በፊት አጭር ሀሳብ ማቅረቤ ይታወሳል።ሀሳቡን ይበልጥ ለማዳበር እና በተለይም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ምንም ግንዛቤ ሌላቸው ሰዎች ይረዳ ዘንድ ሌሎች ንድፈ-ሐቦች ምን ይላሉ የሚለውን ለመመልከት የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ወረቀቶችን እና (Article Review) ለማድረግ ሞክሪያለሁ፤እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪዩን አለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንደ አጠና ሰው በተጨማሪም የተለያዩ ከፍተኛ ሥልጠናዎችን፤አለምአቀፍ ጉዳዬችን እንደ ሚከታተል ባለሙያ በድጋሚ ሌሎች መልህቁን ሊደጋፉ የሚችሉ ህልዩቶችን ተመልክቻለሁ ።
እንደ አንድ ዜጋ የሀገር እና የብሔራዊ ጥቅም (National Interest )ጉዳይ ሲነሳ በምንም ሁኔታ እና አስተሳሰብ ወደ ጎን የሚተው ነገር እንዳልሆነ አምናለሁ።ይህ አጀንዳ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አማካኝነት በመንግስት ደረጃ መነሳቱ በዘላቂነት አጥተነው(በሆነ ዘመን) የነበረውን እድል እና ባለቤትነት በትውልድ ቅብብሎሽ መሳካቱ እንደማይቀር በማመን(በኢትዮጵያ ልጆች፥ለታላቁ ህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ ገንብተን እንደጨረስነው ሁሉ)ይህም የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ የሚጠይቅ እንደመሆኑ ታሪክ ስንመረምር ደግሞ የጥንት ስልጣኔዎች ከአክሱም(አዱሊስ)ጀምሮ የኢትዮጵያ መርከቦች በቀይ ባህርና ወደብ ናኝተውበታል።እኛ የጥንት ህዝቦች እና የአባቶቻችን ልጆች ነን ለዚህም እንደ ሀገር ልጅነት በጋራ እና በትብብር በመቆም መስራት ይጠበቅብናል።
በዛሬው አጭር ሀሳቤ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በማቅረብ ይበልጥ መረዳትን ለማሳደግ እና በተለይ በአንዳንድ የመረጃ ምንጮች የሚተላለፉ ጥሬ መረጃዎች በእውቀት እና በግንዛቤ ላይ ያልተመሰረቱ እና የተሳሳቱ መሆኑን ባደረኩት ቅኝት ለመረዳት ችያለሁ።
ዛሬ የምንመለከተው የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ህልዮቶች መሰረት በማድረግ እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች መልካምድራዊ አቀማመጥ እና የኢኮኖሚ ጥቅሞች በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ሚና መሰረት በማድረግ እንፈትሻለን:-( ሌሎች በመስኩ የምርምር ስራ የሰራችሁ ሊቃውንት ሀሳባችሁን ወደ መድረክ በልዩ ልዩ አማራጮች በማቅረብ ለሀገር እና ለብሔራዊ ጥቅም የሚደረጉ ጥረቶችን በእውቀትና ሳይንስ ተኮር በሆኑ አስረጂዎች በማቅረብ ለሀገር እና ለህዝብ ያላችሁን አጋርነት አሳዩ)። (የተረዳነውን እናስረዳ)
🔴.የባህር ኃይል ፅንሰ-ሀሳብ (Sea Power Theory/ Mahanian Thought):-ይህ ንድፈ-ሀሳብ የሚያጠነጥነው የሀገር ልማትናብልጽግ እንዲሁም ኃይል የሚወሰነው በባህር ላይ ባለ ቁጥጥር እና አጠቃቀም ላይ ነው ብሎ ያምናል።የባህር መንገድን መቆጣጠር እና ነፃ የባህር ላይ ንግድ ማካሄድ ለብሔራዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል።ይህ ንድፈ ሀሳብ ለጥያቄው በተለያ መንገድ ድጋፍ ይሰጣል።ኢትዮጵያ ለንግድ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ቀይ ባህርን መድረስ፣መጋራት መፈለጓ፣የባህር በር እንደ "ህልውና ጉዳይ"(Existential Matter) መታየቱ፣ይህ ንድፈ-ሐሳብ እንደሚደግፈው፣አንድ ሀገር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ለመፍጠር ተሰሚነትን ለማሳደግ የባህር ላይ አቅም (Sea Power) ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።
🔴.የሪምላንድ ፅንሰ-ሀሳብ (Rimland Theory - Spykman):-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ በአህጉር ዳርቻ የባህር ጠረፎችን(ሪምላንድን) የሚቆጣጠር ሀይል የአለምን እጣ ፈንታ ይወስናል የሚል እምነት አለው።የባህር ዳርቻ አካባቢዎች በየብስ እና በባህር ኃይሎች መካከል ድልድይ በመሆናቸው ስልታዊ ጠቀሜታ አላቸው የሚል እይታ አለው።አስረጅ ሲያቀርብ ቀይ ባህር ከአፍሪካ ቀንድ፣ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእስያ ጋር የሚያገናኝ "ወሳኝ የንግድ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ መስመር"(Chokepoint)በመሆኑ፣በዚያ አካባቢ ተሳትፎና እንቅስቃሴ ማድረጉ የኢትዮጵያን አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሚና ለማሳደግ ስልታዊ ጠቀሜታ አለው።
🔴.ጂኦ-ኢኮኖሚክስ(Geo-economics):-የዚህ ንድፈ ሀሳብ መነሻ የሀገሮች ተሰሚነት፣ስልጣንና ግንኙነት በዋነኛነት የሚወሰነው በኢኮኖሚ አቅማቸው እና ንግድን በሚጠቀሙበት መንገድ ነው።የንግድ መስመሮችን እና የገበያ ተደራሽነትን መቆጣጠር ከወታደራዊ ኃይል የበለጠ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል ይላል።ለኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር አቅርቦት ጥያቄን ሲያስረዳ ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና (As the gateway to the Suez Canal and Bab el-Mandab)፣ለኢትዮጵያ ነፃ የባህር በር ማግኘቷ የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ወደ ውጭ መላክን ለማሳደግ እና በሌሎች ሀገሮች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
🔴.ዓለም አቀፍ የህግ እና ትብብር ንድፈ-ሐሳቦች:-እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ትብብር እና የህግ ማዕቀፎችን አስፈላጊነት ያመለክታሉ።የዓለም አቀፍ ሊብራሊዝም እና ተቋማዊነት (International Liberalism and Institutionalism)ሀገሮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመመርኮዝ በትብብር (Cooperation) እና በዓለም አቀፍ ተቋማት (እንደ የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ኮንቬንሽን-UNCLOS) አማካኝነት ግጭቶችን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን ይችላሉ የሚል እይታ አለው ።
🔴.የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት (UNCLOS) እና የባህር-በር የሌላቸው ሀገራት መብቶች:-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ (በህጉ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ) ይህ ኮንቬንሽን (A landlocked Country) የተዘጉ ወይም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባህር የመድረስ መብት (Right of Access to and from the Sea) እና በጎረቤት ሀገራት በኩል በነጻ የመጓጓዝ መብት (Freedom of Transit) እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል (አንቀጽ 125-127)። ይህ መርህ ታዲያ የኢትዮጵያን ወደብ የመጠቀም ፍላጎት "በዓለም አቀፍ ህግ የተደገፈ" መሆኑን ያረጋግጣል።
✍️እንደ መውጫ ⁉️:-
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ "የባህር ኃይል እና የጂኦ-ኢኮኖሚክስ" ንድፈ-ሐሳቦች በሚደግፉት መሠረት ለብሔራዊ ጥቅም እና ህልውና ወሳኝ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ፣ "የሊብራሊዝም እና ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች" (እንደ UNCLOS) ይህንን ጥያቄ በሰላማዊ እና በትብብር መንገድ ለመፍታት መነሻ መሆን እንደሚችሉ ያመለክታሉ።

11 months ago
የኢትዮ- ቱርክ የቢዝነስ ፎረም
የኢትዮጵያና የቱርክ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነትን የሚያጠናከር የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተጀመረ
ዛሬ በቱርኩ የአለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም/ World Cooperation of Industries Forum-WCI Forum/ / እና በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አማካኝነት የተሰናዳው ስምንተኛው የ ደብሊው ሲአይ / WCI የቢዝነስ ፎረም ዛሬ ተጀምሯል፡ ፡
በንግድ ፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን፤ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ ፕሬዚዳንት ዘሀራ መሀመድ፤ የዲፕሎማቲክ እና የንግዱ ማህበረሰብ እና ሌሎች ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡ ፡
በመድረኩ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ መሰረት ሞላ የኢትዮጵያ እና የቱርክ አመታዊ የንግድ ልውውጥ መጠን እ.አ.አ በ2023 ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መብለጡን ተናግረው ሁለቱ ሀገራት ካላቸው እምቅ አቅም አንፃር ከዚህ በላይ መሰራት እንዳላበት ገልፀዋል ፡፡
አዲስ ቻምበርም የሀገራቱን የንግድ ማህበረሰብ በማቀራረብ እና ትስስር በመፍጠር የኢትዮጵያን ንግድና ኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ እንደሚቻልና ለዚህም አዲስ ቻምበር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡ ፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን/ዶ/ር/ እንዳሉት ኢትዮጵያ የቱርክ ባለሀብቶች ዋነኛ መዳረሻ መሆንዋን ጠቅሰው አሁንም ካለቸው ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እና አቅም አንፃር የቱርክ ባለሀብቶች በሰፊው በየዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡ ፡
በቱርክ ኤምባሲ የንግድ ካውንስለር የሆኑት ጣሃ አልፕሬን በበኩላቸው ኢትዮጵያና ቱርክ ረዥም ታሪካዊ ግንኙነት ቢኖራቸውም የየንግድ ልውውጣቸውን እና የኢንቨስትመንት መጠናቸውን አሁንም ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የቱርክ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙና የኢትዮጵያም አቻዎች በቱርክ ያለውን የገበያ እድል እንዲያማትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በንግድ ፎረሙ ላይ ከ 200 በላይ የአዲስ ቻምበር አባላትና ከ 20 በላይ ግዙፍ የቱርክ የንግዱ ማግበረሰብ አባላት ተገኝተው የንግድ ለንግድ ግንኙነት አድርገዋል፡ ፡
የኢትዮ ቱርክ የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ለ2 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡
#addischamber

Comments