3 months ago
"ኢትዮ ሆም- ኤክስፖ 2026" በለንደን ሊካሄድ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም እና በአካባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራችሁ የቤት ባለቤት የመሆን ህልማችሁን እውን የምታደርጉበት ትልቅ መድረክ ተዘጋጅቶላችኋል።
በለንደን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት እና ከኤድማርቬንቸርስ ጋር በመተባበር ልዩ የሪል ስቴት ኤክስፖ አዘጋጅተዋል።
ኤክስፖው ለምን ይለያል?
ተሳታፊ የሪል ስቴት አልሚዎች በግንባታ አፈጻጸማቸውና በህጋዊነታቸው በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ተመርጠውና ተጣርተው የሚቀርቡ በመሆናቸው ስጋትን ያስቀራል።
የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የንግድ ባንኮች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የፖሊሲ አውጪ የመንግስት አካላት በአንድ መድረክ ይገኛሉ።
አዳዲስ የመንግስት ፖሊሲዎችና የባንክ ብድር አማራጮች ላይ የፓናል ውይይቶችና ሰፊ መረጃዎች ይሰጣሉ።
ከኤክስፖው በኋላም ለሚፈጠሩ ውሎችና ግብይቶች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል የክትትል ስርዓት ተዘርግቷል።
ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም
(May 23-25, 2026)።
ለንደን ከተማ፣ ዩናይትድ ኪንግደም
በዩናይትድ ኪንግደም የምትገኙ ወገኖቻችን በዚህ ታላቅ ኤክስፖ ላይ በመሳተፍ የቤት ባለቤትነት ጥያቄያችሁን በህጋዊና በአስተማማኝ መንገድ እንድትመልሱ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #ethiohomeexpo2026 #ethiopiandiaspora #realestateethiopia #londonevents #investinethiopia #homeownership #ethiopianembassylondon #addischamber #የቤትባለቤትነት #ለንደን #ሪልስቴት #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

10 months ago
በታክስ እና ጉምሩክ ዙርያ የሚወጡ ህጎችና አሰራሮች ፍትሀዊ፣ግልፅና የሚተነበዩ እንዲሆኑ ተጠየቀ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተቋቋመባቸው አላማዎች አንዱ የፖሊሲ አድቮኬሲ ስራዎችን በማካሄድ ለንግድና ኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ ባለፉት ጊዜያት በርካታ የምክክር መድረኮችን በማመቻቸት ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት እንዲመክሩና የተሻሉ የንግድ ህጎችና ፖሊሲዎች እንዲወጡና እንዲተገበሩ ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል፡፡
የዚህ አንድ አካል የሆነው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ በታክስና ጉምሩክ ሪፎርም ፣ ትግበራና ተግዳሮቶች ዙርያ ትኩረቱን በማድረግ ተካሂዷል፡፡
“የታክስ እና የጉምሩክ ሪፎርም አተገባበር በግሉ ዘርፍ ላይ ያለው ተጽእኖ” በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የመጀመሪያው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ አዲስ ቻምበር ከአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጲያ እና ከአለም አቀፉ የግል ኢንተርፕራይዞች ማእከል ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።
የምክክር መድረኩ የሚመለከታቸው የገንዘብ ና የገቢዎች ሚኒስቴር ሀላፊዎች ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አመራሮች ፣ የአዲስ ቻምበር እና የአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላትን በማገናኘት በግብር እና በጉምሩክ ስርአት፣ አስተዳደርና አተገባበር ዙርያ ሰፊ ሃሳቦች የተንሸራሸሩበት መድረክ ነበር፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አለምወርቅ ደረሰ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ የሪፎርምና የለውጥ ስራዎች መስራቱን ጠቅሰው መስሪያ ቤታቸው ለንግዱ ህብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት እጅግ ቀላል፣ ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።
የግሉ ዘርፍ የሚያነሳቸውን ተግዳሮቶችም በተደራጀ እና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተቀራርቦ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ጠቁመዋል ።
የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሀፊ መሠረት ሞላ (ዶ/ር) በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የግብር እና የጉምሩክ ጉዳይ ከበርካታ አመታት ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ችግር መሆኑን ተናግረው እንዲህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት ምክር ቤታቸው ወሳኝ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ፤ የፖሊሲ ግብአቶች የሚሰበሰቡበትና አመቺ ፖሊሲዎች እንዲወጡና ተግባራዊ እንዲደረጉ ምክር ቤቱ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል መላኩ እንደተናገሩት አባል ኩባንዎቻቸውና መላው የንግዱ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ውስጥ የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በማስታወስ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ማክሮ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጤናማ፣ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ እና ሊተነበይ የሚችል የግብር እና የጉምሩክ ስርአት መኖር ወሣኝ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ለውይይት የሚሆኑ ጹሁፎች ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን እና አግሉ ዘርፍ በሚመለከታቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የቀረቡ ሲሆን ሰፋ ያሉ ሀሳቦችና ግብአቶች ቀርበውበታል፡፡
ከተነሱ ሀሳቦችና ምልከታዎች መካከል የኢትዮጵያ የታክስ ምጣኔ ከጥቅል አመታዊ ምርት ጋር ሲነጻጸር ከአመት አመት እየቀነሠ መምጣቱ፤ የታክስ እና ጉምሩክ ሪፎርሞች ከተቋማት ብቃትና ፤ከሰለጠነ የሰው ሀይል አንጻር ክፍተቶች እንዳሉበት፤ የታክስ እና ጉምሩክ አስተዳደርና አተገባበሮች ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱ አለመሆናቸው፤ የታክስ ፖሊሲ ለውጦችን በየጊዜው ከሚለዋወጠው ኢኮኖሚ ጋር በማነጻጸር ለውጥ ያለማድረግ ክፍተቶች መሆናቸውን በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ በምክክር መድረኩ ከተነሱት ሀሳቦች መካከል የቅንጅታዊ አሰራር መጓደል፤ የታክስ ከፋዮችን መብት ሊያስከብር የሚችል ነፃና ገለልተኛ ተቋም አለመኖር፤ የታክስ ግጭት አፈታት ረጅምና አሰልቺ መሆን በዋናነት ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡
በግብር ይግባኝ ችሎት በቂ የግሉ ዘርፍ ተወካይ እንዲኖርና በግብር ይግባኝ ክርክር ወቅት ቅድሚያ የሚከፈለው የ 50 በመቶ መጠን ወደ 20 በመቶ ዝቅ እንዲል እንደ ምክረ ሀሳብ ተጠይቋል ።
በአጠቃላይ “የታክስ እና የጉምሩክ ሪፎርም አሠራርና አተገባበር በግሉ ዘርፍ ላይ ያለው አንድምታ” በሚል የተካሄደው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ከንግዱ ማህበረሰብና ከሚመለከታቸው ሀላፊዎች በርካታ ምላሾችና ምክር ሀሳቦች የተዳሰሱበት ሲሆን በተለይ የኢትዮጵያ የታክስ እና ጉምሩክ አሠራር እና አተገባበር ቀልጣፋና ለንግድ አሰራር አስቻይ እንዲሆን አሁን ያለው ፖሊሲ፣ ሕግና መመሪያ ወደፊት ከሚታሰበው የግል ዘርፉ ሚና አኳያ መቃኘት እንዳለበት፤ ሪፎርሞቹን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችሉ ብቁ ተቋማት፤ ወጥ ስትራቴጂና ዝርዝር ህጎች በስራ ላይ ማዋል ፤ በታክስ አሰባሰብ ሂደት ውስጥ ቴክኖሎጂን መጠቀም፤ ፍትኃዊና ተጠያቂነት ያለበት የታክስና ጉምሩክ ስርአትን መፍጠርና ግንዛቤ እንዲያድግ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል ፡፡
በመጨረሻም በምክክር መድረኩ መፈታት አለባቸው የተባሉ ተግዳሮቶችን በማጠናቀር ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማቅረብ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ክትትል እንደሚደረግ አዲስ ቻምበር ገልጿል፡፡
አዲስ ቻምበር በቀጣይም ከአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያና ከአለም አቀፉ የግል ኢንተርፕራይዞች ማእከል ጋር በመተባበር በተለያዩ የፖሊሲ አድቮኬሲ ጉዳዬች ዙሪያ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች በተከታታይ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል ።
#advocacy
#addischamber

11 months ago
የኢትዮ- ቱርክ የቢዝነስ ፎረም
የኢትዮጵያና የቱርክ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነትን የሚያጠናከር የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተጀመረ
ዛሬ በቱርኩ የአለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም/ World Cooperation of Industries Forum-WCI Forum/ / እና በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አማካኝነት የተሰናዳው ስምንተኛው የ ደብሊው ሲአይ / WCI የቢዝነስ ፎረም ዛሬ ተጀምሯል፡ ፡
በንግድ ፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን፤ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ ፕሬዚዳንት ዘሀራ መሀመድ፤ የዲፕሎማቲክ እና የንግዱ ማህበረሰብ እና ሌሎች ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡ ፡
በመድረኩ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ መሰረት ሞላ የኢትዮጵያ እና የቱርክ አመታዊ የንግድ ልውውጥ መጠን እ.አ.አ በ2023 ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መብለጡን ተናግረው ሁለቱ ሀገራት ካላቸው እምቅ አቅም አንፃር ከዚህ በላይ መሰራት እንዳላበት ገልፀዋል ፡፡
አዲስ ቻምበርም የሀገራቱን የንግድ ማህበረሰብ በማቀራረብ እና ትስስር በመፍጠር የኢትዮጵያን ንግድና ኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ እንደሚቻልና ለዚህም አዲስ ቻምበር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡ ፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን/ዶ/ር/ እንዳሉት ኢትዮጵያ የቱርክ ባለሀብቶች ዋነኛ መዳረሻ መሆንዋን ጠቅሰው አሁንም ካለቸው ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እና አቅም አንፃር የቱርክ ባለሀብቶች በሰፊው በየዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡ ፡
በቱርክ ኤምባሲ የንግድ ካውንስለር የሆኑት ጣሃ አልፕሬን በበኩላቸው ኢትዮጵያና ቱርክ ረዥም ታሪካዊ ግንኙነት ቢኖራቸውም የየንግድ ልውውጣቸውን እና የኢንቨስትመንት መጠናቸውን አሁንም ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የቱርክ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙና የኢትዮጵያም አቻዎች በቱርክ ያለውን የገበያ እድል እንዲያማትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በንግድ ፎረሙ ላይ ከ 200 በላይ የአዲስ ቻምበር አባላትና ከ 20 በላይ ግዙፍ የቱርክ የንግዱ ማግበረሰብ አባላት ተገኝተው የንግድ ለንግድ ግንኙነት አድርገዋል፡ ፡
የኢትዮ ቱርክ የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ለ2 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡

Comments