4 months ago
ዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያ የደኅንነት አቅም ላይ ሙሉ እምነት አላት - አምባሳደር ዳረን ዌልች
**********************
የዩናይትድ ኪንግደም በአፍሪካ አህጉር ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለውን፣ የላቀ የሰነድ ማጭበርበር (ፎርጀሪ) መመርመሪያ የኤቪዬሽን ደኅንነት ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አበርክታለች።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፣ ይህ የቴክኒክ ድጋፍ የሁለቱን ሀገራት የጠበቀ ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በእንግሊዝ ሀገር የተመረተው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መደረጉንም አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።
ይህም ዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያ የደኅንነት አቅም ላይ ያላትን ሙሉ እምነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አክለዋል።
ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቁልፍ የዓለም አቀፍ መተላለፊያ ማዕከል መሆኑን ያነሱት አምባሳደሩ፣ የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች የእንግሊዝ ዜጎችን ጨምሮ የዓለምን ማኅበረሰብ ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን የላቀ ጥረት አድንቀዋል።
"ሁላችንም ደኅንነታችን እስካልተረጋገጠ ድረስ የማንም ደኅንነት የተጠበቀ አይሆንም" በማለትም የጋራ ደኅንነትን ፅንሰ-ሀሳብ አስምረውበታል።
ይህ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እና ትብብር ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎችን ለመከላከል እንዲሁም የጉዞ መስመሮችን ከሕገ-ወጥ ድርጊቶች ነጻ ለማድረግ የላቀ ሚና ይጫወታል።
አምባሳደሩ እንዳብራሩት የሁለቱ ሀገራት አጋርነት በደኅንነት ዘርፍ ብቻ ሳይወሰን፤ በጤና፣ በትምህርት እና በኢኮኖሚ ልማት ጭምር ሰፊ መሠረት ያለው ነው።
በቀጣይም በቢሾፍቱ በሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን እና ግንባታ ላይ የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
አውሮፕላን ማረፊያው በዓለም ላይ ካሉ ደኅንነታቸው እጅግ ከተጠበቁ ተርሚናሎች አንዱ እንዲሆን በጋራ ለመሥራት ዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላትም አምባሳደሩ ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ወደ ሂትሮው፣ ማንችስተር፣ ጋትዊክ እና ግላስኮ የሚደረጉ ዕለታዊ እና መደበኛ በረራዎች የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ይበልጥ እያሳደጉት መሆኑን አምባሳደሩ አንስተዋል።
የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጠው ይህ የደኅንነት ትብብር ውጤታማነቱ ታይቶ በቀጣይም ተጨማሪ የቴክኖሎጂ ድጋፎች እንደሚደረጉ አመላክተዋል።
#ethiopia #uk #cooperation #aviationsecurity #aviationtech #ethiopianairlines #boleairport #niss #ebc

9 months ago
✅ ተገኝተዋል! | "ፓስፖርታችንን በክብር ተረክበናል!"
#ethiopia | የጠፉት 5 ፓስፖርቶች፣ መታወቂያዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ለባለቤቶቹ ተመለሰ! 👏
ትናንትና ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ወድቆ በወንድማችን ዲንሰፋ በሽር (Dinsefa Beshir) እጅ ገብቶ የነበረው የካናዳ እና የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እንዲሁም ጠቃሚ ሰነዶች ዛሬ ለባለቤቶቹ ተመልሰዋል።
ከ9 ዓመታት በኋላ ከካናዳ፣ ባለቤቱን እና ልጆቹን ይዞ ለሦስት ሳምንት ለእረፍት ወደ ሀገር ቤት የገባው አቶ ሚኪያስ ንብረቱን ተረክቧል።
ዲንሰፋ በሽር፤
ለአቶ ሚኪያስ የስፖርት ትጥቅ መሸጫ ሱቁ ድረስ በመጥራት፡-
4 የካናዳ ፓስፖርት
1 የኢትዮጵያ ፓስፖርት
የካናዳ መኖሪያ ፈቃድ፣ መንጃ ፈቃድ እና ዶላሩን ጨምሮ ምንም ሳያጎድል አስረክቧል።
የክብር ምስጋና!
ይህ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ እና ቤተሰቡ ከጭንቀት እንዲገላገል መረጃውን #ሼር (SHARE) ላደረጋችሁ የጌጡ ተመስገን ሚዲያ ቤተሰቦች በሙሉ "ምስጋና ውሰዱ" ተብላችኋል!
በጎነት ለራስ ነው!
ክብር ለወንድማችን ዲንሰፋ! 🙏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #honesty #goodnews #lostandfound #boleairport #getutemesgenmedia

‼️ አስቸኳይ፡ ቦሌ ኤርፖርት የጠፋ ንብረት ተገኝቷል ‼️
#ethiopia | ዛሬ ጠዋት ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት (Bole Int. Airport) እንግዳ ለመቀበል በሄድኩበት ሰዓት የወደቀ ቦርሳ አግኝቻለሁ። ቦርሳውን ስንከፍተው በውስጡ የበርካታ ቤተሰቦች ህይወት የሆነ ወሳኝ ሰነዶችን ይዟል።
የተገኙት እቃዎች ዝርዝር፦
✅ 4 የካናዳ ፓስፖርት (የትውልደ ኢትዮጵያውያን)
✅ 2 የካናዳ መኖሪያ ፈቃድ (Residence Permit/PR) 🆔
✅ 1 የኢትዮጵያ ፓስፖርት
✅ የተወሰነ የካናዳ ዶላር (ገንዘብ) 💵
✅ ሌሎች ከትንሽ ቦርሳ ጋር ያሉ ንብረቶች...
እባካችሁ እነዚህ ሰነዶች የጠፉባቸው ሰዎች ምን ያህል ተጨንቀው ሊሆን እንደሚችል አስቡት! ባለቤቶቹ በእጃቸው ላይ ያለውን የጉዞ ወይም የኑሮ ዕቅድ ሳያስተጓጉሉ እንዲረከቡ ይህንን መረጃ #ሼር (SHARE) በማድረግ እንተባበር።
📞 ንብረቱን ለመረከብ በዚሁ ስልክ ይደውሉ፦
ዲንሰፋ በሽር (Dinsefa Beshir)
0911695276
በጎነት ለራስ ነው!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#lostandfound #boleairport #passports #canada #ethiopia #share

Comments