45 mins. ago
የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና እርዳታ ትግራይ ደርሷል።
የህክምና አቅርቦቶችንና መሳሪያዎችን የጫኑ ስምንት ተሽከርካሪዎችን የያዘ ኮንቮይ መቐለ ደርሷል።
ይህ እርዳታ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በአይደር፣ መቀሌ፣ ማይቾው፣ መኮኒ፣ አላማጣ እና ሱሁል-ሺሬ ላሉ ሆስፒታሎች እንዲሁም በጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ሌሎች የጤና ተቋማት ይሰራጫል።
ይህ እርዳታ ለተጎዱ እና ድንገተኛ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ሌሎች ሰዎች አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።
Seledadotio

13 hours ago
አርሰናልንና ሌቨርኩሰንን ያገለገለው ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ግራኒት ዣካ የሐሰት የኮቪድ-19 የክትባት ማስረጃ በማቅረብ በተከሰሰበት የወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ከባድ የገንዘብና የእስራት ቅጣት ተጣለበት።
የተሰጠውን የፍርድ ውሳኔ መሠረት በማድረግ ግራኒት ዣካ 136,000 ፓውንድ (መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መቀጮ) እንዲከፍል የተወሰነበት ሲሆን፣ በተጨማሪም የ2 ዓመት በይደር የሚቆይ የእስራት ቅጣት (Suspended Sentence) ተፈርዶበታል።
ይህ ማለት ተጫዋቹ የ2 ዓመቱን የይደር ጊዜ በሚያልፍበት ወቅት ተመሳሳይ ወንጀል ካልፈጸመ ወደ ማረሚያ ቤት አይገባም።
የክሱ መነሻ እንደሚያስረዳው፣ ዣካ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በነበረበት ወቅት የክትባቱን መጠን ሳይወስድ (ሳይከተብ)፣ «ተከትቤያለሁ» በማለት የሐሰት የክትባት ሰነድና ማስረጃ በማዘጋጀት እንዲሁም ያንን ማስረጃ ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረቡ ነው የተከሰሰው።
የፍርድ ቤቱ ማጣሪያ ሰነዱ ሕጋዊ እንዳልሆነና የተጭበረበረ መሆኑን በማረጋገጡ በሕግ ፊት ጥፋተኛ ተብሏል።
ይህ ውሳኔ በስፖርቱ ዓለም እና በደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በተለይም በወቅቱ የስፖርት ተቋማትና መንግሥታት ያወጧቸውን የጤና ደንቦችና ፕሮቶኮሎች መጣስ፣ የትኛውም ያህል ታዋቂ ተጫዋች ቢሆን ከሕግ ተጠያቂነት አያመልጥም የሚል መልእክት አስተላልፏል።
ዣካና የሕግ ቡድኑ በይግባኝ ደረጃ የሚወስዱት እርምጃ ካለ ወይም ከተጫዋቹ ወገን የሚሰጥ ተጨማሪ መግለጫ ወደፊት የሚጠበቅ ይሆናል።

22 hours ago
በወተት ምርትና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮችን ለመቆጣጠር አዲስ ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ ነው
#ethiopia | በወተት ምርት፣ አያያዝና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራትና የንፅህና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት ባካሄደው ጥናት ከወተት እርባታ ሼዶች እስከ ችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ድረስ የንፅህና ጉድለቶች መኖራቸውን መለየቱን ገልጿል።
በእርባታ ቦታዎች አላቢዎች ተገቢውን የደንብ ልብስ አለመልበሳቸውና የንፅህና አጠባበቅ ክፍተቶች መኖራቸው በጥናቱ ከተለዩ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም ላሞች ሲታመሙ የሚሰጣቸው መድኃኒት ከሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ ሳይወጣ ወተቱ ለገበያ የሚቀርብበት ሁኔታ መኖሩ ተመልክቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ጸጋ ለማ እንደገለጹት፣ ወተት ለማለብ፣ ለማጠራቀምና ለማጓጓዝ ተገቢውን የምግብ ደህንነት መስፈርት የማያሟሉ የፕላስቲክ ጀሪካኖች በስፋት እየተጠቀሙ ነው። ይህም ለማፅዳት አስቸጋሪ በመሆኑ በወተት ጥራትና ደህንነት ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ወተት ውስጥ ውሃ በመጨመር ተፈጥሯዊ ይዘቱን የማዛባት ሕገወጥ ድርጊት በአንዳንድ አካላት እየተፈጸመ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።
ኮሚሽኑ እነዚህን የምግብ ደህንነትን የሚጎዱ ተግባራት ለመቆጣጠር፣ ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድና በወተት ምርት ሰንሰለት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል አዲስ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለማስጸደቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ረቂቅ ደንቡ ጸድቆ ወደ ተግባር ሲገባ፣ ከእርባታ ጀምሮ እስከ ምርት ማጓጓዝ፣ ማከማቸትና ለሸማቾች ማቅረብ ድረስ ባለው የንግድ ሰንሰለት ውስጥ የጥራትና የንፅህና መስፈርቶችን ለማስጠበቅ አስፈላጊ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
ይህም ለህብረተሰቡ ጤናማ፣ ጥራቱ የተጠበቀና ደህንነቱ የተረጋገጠ ወተት እንዲደርስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
ፋሲል አረጋይ — አሐዱ

1 day ago
አዲስ የታሰረ የቃል ኪዳን ተስፋ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር
****************
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማካሄዷን ተከትሎ፣ አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል።
ይህ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ የተበሰረበትና የሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ ውሳኔ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ላለፉት ዓመታት የተጣሉትን የዕድገትና የተስፋ መሠረቶች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የመደመር እይታ ያለፉ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላትና የቀጣይ ትውልድን ተስፋ በማገናኘት ሀገራዊ አንድነትንና ትብብርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ላለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተመዘገቡት ስኬቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ራዕይ ሌሎች ማሳያዎች ናቸው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት በተመሰረተበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችንና ግቦችን አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን፣ ኅብረትንና ትብብርን ማስፈን፣ ጥራትን መሠረት ያደረገ መዋቅራዊ ሽግግር ማድረግ እንዲሁም የትምህርት፣ የጤና እና የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በጥራት ማሳደግ ዋነኛ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ወደ 65 በመቶ፣ የጤና መድኅን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ፣ እንዲሁም የተማሪዎች የምገባ ሽፋን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ የተያዙ አበይት ግቦች መሆናቸውን አንሥተዋል።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምስረታ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበርና የሕዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የሰላም፣ የፍትሕና የልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ የቃል ኪዳን መስመር ይከፍታል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #medemergovernment #statebuilding

ዋናው ነገር ጤና! ⚡️
በአውቶቢስ ተራ እና ፈረንሳይ መካከል ከተደረገው የቀበና ካፕ የደርቢ ጨዋታ ጀርባ 'ዋናው' ከእግር ኳስ ጨዋታው በላይ የሆነን ታላቅ የወጣት አቅም እያነቃቃ ይገኛል።
ዋናው የስፖርት ትጥቅ | የውድድሩ አጋር! 🏆
🔗ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
⭐️| #wanawsportwear |
በኢትዩጵያ የተመረተ

አንድ የኢቦላ ሞት በኬንያ መመዝገቡ አህጉራዊ ስርጭት ሊሰፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጠረ፡፡
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት እያየለ መምጣቱ ተገልጿል።
በተለይም በኬንያ አንድ ሰው በኢቦላ ምክኒያት ህይወቱ በማለፉ የበሽታው ስርጭት ከታሰበው በላይ ሊሆን ይችላል የሚለውን ስጋት አባብሶታል።የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በኬንያ ህይወቱ ያለፈው ሰው ኢቦላ ከተከሰተበት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መነሻውን ያደረገ ሲሆን ግለሰቡ በየብስ ወደ ዩጋንዳ ከተጓዘ በኋላ በአውሮፕላን ወደ ኬንያ ናይሮቢ መግባቱ ተገልጿል።
ይህ ሁኔታ ቫይረሱ በሰዎች እንቅስቃሴ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ሊሰራጭ የሚችልበትን አደጋ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ከወረርሽኙ ነፃ መሆኗን ያስታወቀችው ዩጋንዳ በእርግጥ ከበሽታው ነፃ መሆኗን በተመለከተም ጥያቄ አስነስቷል።የኢቦላ ወረርሽኙ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተነስቶ በአካባቢው በመስፋፋት ከፍተኛ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ማድረጉን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል። በወረርሽኙ ቢያንስ 4 ሺህ 148 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 8 ሺህ 300 በላይ የተጠረጠሩ የበሽታው ተጠቂዎችም ተመዝግበዋል።
የበሽታው ወረርሽኝ ወደ ዩጋንዳም ተሻግሮ የነበረ ሲሆን በሀገሪቱ 20 የሚጠጉ ታካሚዎች መመዝገባቸውን ተከትሎ በሐምሌ ወር ከኢቦላ ነፃ መሆኗ ተገልጾ ነበር። በኬንያ የተመዘገበው ሞት ግን በክልሉ ያለውን የበሽታውን ስርጭት በተመለከተ አዲስ ስጋትን ፈጥሯል።
በዚህም የተነሳ ኬንያ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው የመግቢያ በሮች ላይ የጤና ምርመራን እያጠናከረች መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። በተለይም ከተጠቂ አካባቢዎች የሚመጡ ሰዎችን መከታተልና የበሽታውን ምልክቶች በፍጥነት መለየት ላይ ትኩረት ተደርጓል።
የኬንያው የኢቦላ ሞት በክልሉ የበሽታውን ስርጭት በጥብቅ የመከታተል፣ የጤና ምርመራን የማጠናከርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይስፋፋ የጋራ ጥረት የማድረግ አስፈላጊነትን አጉልቶ አሳይቷል።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል Photo

Sponsored by
Surafel
1 day ago
በወተት ላይ የሚታየውን የጥራት ችግር ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ደንብ በሂደት ላይ መሆኑ ተገለጸ
👉 ረቂቅ ደንቡ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከእርባታ እስከ ገበያ ያለውን የንግድ ሰንሰለት ጥራት ለማስጠበቅ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል
በወተት ምርት ፣ አያያዝና ስርጭት ላይ እየታዩ ያሉ የጥራት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የህግ ማዕቀፍ ለማስጸደቅ በሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በ 2018 በጀት ዓመት በተደረገ ጥናት ከወተት እርባታ ሼዶች ጀምሮ እስከ ችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ድረስ የንፅህና ጉድለቶች መኖራቸው እንደተረጋገጠ አስታውቋል።
በእርባታ አካባቢዎች አላቢዎች ተገቢውን የደንብ ልብስ አለመልበስና የንፅህና አጠባበቅ ክፍተት መታየቱ እንዲሁም ላሞች ሲታመሙ የሚወስዱት መድኃኒት ከሰውነታቸው ሳይወጣ ወተቱ ለገበያ መቅረቡ በጥናቱ ከተለዩት አበይት ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ለወተት ማለቢያ ፣ ማጠራቀሚያ እና ማጓጓዣነት የአሉሚኒየም እቃዎችን መጠቀም ሲገባ ለጤና ጠንቅ በሆኑና ለማፅዳት አስቸጋሪ በሆኑ የፕላስቲክ ጀሪካኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ጸጋ ለማ ተናግረዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ ከዚህም ባሻገር በአንዳንድ አካላት ወተት ውስጥ ውሃ በመጨመር የወተቱን ተፈጥሯዊ ይዘት የማዛባት ህገወጥ ድርጊት መስተዋሉን አክለዋል።
እነዚህን ከምግብ ደህንነት አንፃር ፈፅሞ ተቀባይነት የሌላቸውን ድርጊቶች በህግ አግባብ ለመቆጣጠርና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ኮሚሽኑ አዲስ የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ለማስጸደቅ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ አዲስ የሚወጣው ረቂቅ ደንብ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከእርባታ እስከ ገበያ ያለውን የወተት ሰንሰለት ጥራት በማስጠበቅ ጤናማና ደህንነቱ የተረጋገጠ ምርት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
#አሐዱ_ሬዲዮ

መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በወተት ምርት ፣ አያያዝና ስርጭት ላይ እየታዩ ያሉ የጥራት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የህግ ማዕቀፍ ለማስጸደቅ በሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።

በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

በቅድሚያ ለረዳኝ ላገዘኝ በመንገዴ ሁሉ ከኔ ጋራ ለነበረ ክብር ለሆነኝ ለአምላኬ ከፍ ያለ ምስጋናዬ ይድረሰው!!🙏🏾🙏🏾🙏🏾
ክቡራትና ክቡራን - በድጋሚ ለማገልገል እድል ያገኛችሁ እንዲሁም አዲስ ለተሾማችሁ የካቢኔ አባላት እንኳን ደስ አላችሁ!! በጋራ በታላቅ ፍቅር በትብብርና በአብሮነት መንፈስ ለነበረን ቆይታ ከልብ እያመሠገንኩ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
ላለፉት ስምንት (8) አመታት በሚኒስትርነት ወደ ትልቅ የሀገርና የህዝብ ሀላፊነት በመምጣት በታማኝነት ለማገልገል እንዲሁም የተቻለኝን ሁሉ ማበርከት እንድችል ታላቅ ዕድል በማግኘቴ ክብር ይሰማኛል ! ለዚህም መንግስትን ፓርቲዬንና መላው ህዝባችንን በታላቅ ክብር አመሠግናለሁ🙏🏾
በተለይ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይም በቀድሞ የካቢኔዎ አባል ሆኜ ለ2 ጊዜ የማገልገል ዕድል ስለሰጡኝ ለዚህም እምነት ስላሳደሩብኝ በነጻነት እንድሰራና ሀላፊነቴን እንድወጣ ስላበረታቱኝ ስለደገፉኝ ከልብ አመሠግናለሁ!! ፈጣሪ ረጅም እድሜ ጤናን ጥበብና ሞገስን ይስጥዎ🙏🏾
ለስራዬ መቃናት ድጋፍና ትብብር ስታደርጉልኝ ለነበራችሁ የምወዳችሁ ቤተሰቦቼ የስራ ሀላፊዎችና ባልደረቦቼ የአጋር አካላት እንዲሁም መላው ማህበረሰባችን አክብሮቴን ምስጋናዬንና ፍቅሬን ከልቤ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ 🙏🏾
በቀሪ ዘመኔም ፈጣሪዬ በፈቀደልኝ ሁኔታ ሁሉ አገሬንና ህዝቤን አገለግላለሁ!!
ክብር ይስጥልኝ! አመሠግናለሁ! 🙏🏾🙏🏾🙏🏾
ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የቀድሞ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
1. ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል፡፡
@YeneTube FikerAssefa

የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር

15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

2 days ago
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ተካሂዷል
ለሚንስትርነት ስፍራው እጩዎች በጠ/ሚ አማካኝነት አቀርበዋል
👉አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
👉ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
👉ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር
👉 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በድጋሚ የትምህርት ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር
👉አቶ መሀመድ እድሪስ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
👉 አቶ አዲሱ አረጋ የግብርና ሚኒስትር
👉 ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር
👉 ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
👉 ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድና ቀጠናዊ ስትትር ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ለባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር
👉 አቶ አወሉ አብዲ የስራና ክህሎት ሚኒስትር
👉 አቶ በረከት ፍስሃፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
👉 አቶ ሳዳት ነሻ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
👉 አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር
👉 ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
👉ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
#ዳጉ_ጆርናል

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም የኃይል አቅርቦት የተቋረጠባቸው እና የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡፡
ከጠዋት 12፡00 - ቀኑ 8፡00
👉እህል በረንዳ፣ አማኑኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው
👉 አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ፣ ኮልፌ 18 ድልድዩ ድረስ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ ሙስና ሰፈር፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብና አካባቢው፣ እና አካባቢው
ከቀኑ 8፡00 - ምሽት 4፡00
👉አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤ/ክ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስኪድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት አካባቢ፣ ኮልፌ ወ.8 ፅህፈት ቤት እና አካባቢው፣

ከምሽት 4፡00 - ጠዋት 12፡00

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።
የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

በደቂቃዎች ውስጥ የቆዳ ካንሰርን የሚለየው
አስገራሚው የኤ.አይ (AI) ሥርዓት!
በዩናይትድ ኪንግደም ብራድፎርድ በሚገኘው ሴንት ሉክስ ሆስፒታል የቆዳ ሕክምና ቡድን አጠራጣሪ የቆዳ እብጠቶችን እና የጤና መጓደሎችን በፍጥነት ለመመርመር አዲስ የኤ.አይ (AI) ሥርዓትን በሥራ ላይ ማዋሉ ተሰማ። «DERM» (Deep Ensemble for the Recognition of Malignancy) የተሰኘው ይህ ዘመናዊ ሥርዓት፣ አጠራጣሪ የቆዳ እብጠቶችን ሦስት ፎቶዎች ብቻ በመውሰድ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ውጤት ማቅረብ ያስችለዋል።
የሕክምና ባለሙያዎች ይህ ቴክኖሎጂ ታካሚዎች ረጅም ሰዓት በሰልፍ የሚጠብቁበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ይናገራሉ። አልሚው አካል «ስኪን አናሊትክስ» (Skin Analytics) እንዳገለጸው ከሆነ፣ ቴክኖሎጂው ካንሰር እንዳልሆነ በመለየት ረገድ እስከ 99.9 በመቶ ትክክለኛነት አለው፤ ሆኖም በሂደቱ ውስጥ ሐኪሞች ሁልጊዜም በንቃት ይሳተፋሉ።
ይህ የጤና ዘርፍ ፈጠራ የካንሰር ምርመራን ፈጣን እና ቀለል በማድረግ በብዙዎች ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ቴክኖሎጂው ከጊዜ ወደ ጊዜ በሕክምናው መስክ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ይህ ክስተት በግልጽ ያሳያል።

የአቦቦ ወረዳ ፖሊስ በአደረገው ክትትል የጂን አልኮል መጠጦች ተያዘ
በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ የተከለከለ የአልኮል መጠጥ ይዘው የሚዘዋወሩ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር የወረዳው ፖሊስ በአደረገው ክትትል 180 የጂን አልኮል መጠጦች ተይዘው እንዲወገዱ ተደርጓል።
የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋዉሩ ግለሠቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጌራ ገልፀዋል።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጌራ በተጨማሪ እንደገለጹት አልኮል ለጤና ጠንቅ በመሆኑ ህብረተሠቡ ይሄን የአልኮል ዝውውር ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች ሲያጋጥሟቸው ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ የአፍና የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለፀ
በአገሪቱ የአፍና የጥርስ ጤና ችግሮች በስፋት የሚታዩ ቢሆንም በዘርፋ የህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አስታውቋል።
በማህበረሰቡ ዘንድ ከሚስተዋሉ የጥርስ ጤና ችግሮች መካከል በዋናነት የህፃናትና የአዋቂዎች ጥርስ መበስበስ፣ የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ሕመም፣ የጥርስ መርገፍ እንዲሁም የአፍና የከንፈር ካንሰር ይገኙበታል።
በሆስፒታሉ የጥርስና ማክሲሎፌሻል ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የፊትና መንጋጋ ቀዶ ጥገና ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ጥርስን እስከ ማጣት ሊያደርስ የሚችለው የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ህመም 18.7 በመቶ ስርጭት ሲኖረው የጥርስ መርገፍ ደግሞ 1.8 በመቶ ስርጭት እንዳለው ተናግረዋል።
የሕክምና ኮሌጁም ከመደበኛው የጥርስ ህክምና በተጨማሪ የአፍ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ጥገና ሕክምናን እንደሚሰጥ ገልጿል።ተቋሙም በየቀኑ ከ90 እስከ 140 የሚደርሱ ታካሚዎችን በማስተናገድ ሕክምናን እየሰጠ መሆኑን ዶክተር አዲስ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2022 የታተመውና በ2018 አ/ም የተሰበሰበው መረጃን ያካተተው የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙት 1 ሺህ 745 የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ብቻ ናቸው።በዘርፋ የተሰማሩ የባለሙያዎችን ቁጥር አስመልክቶ ወቅታዊና የተጠናቀረ መረጃ ባለመኖሩ በአሁኑ ወቅት ያለው ቁጥር ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተር አዲስ ገልጸዋል።
በሰብል አበበ

የኢትዮጵያን የውጪ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር እና የደመኝነት እይታ ያላቸውን የሚመክር ስራ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ተናገሩ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የፌዴሬሽን ምክርቤት 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
በንግግራቸውም የ2019 ዓ.ምን ዋና ዋና ትኩረቶች የዘረዘሩ ሲሆን በአንደኛነት ሰላም ለኢትዮጵያ እድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጠና እና ከማንኛውም ጊዜ በላይ ህብረትን፣ ትብብርንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግርም የሚደረግ ሲሆን ትምህርት፣ ጤናና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማእከሉ ያደረገ ልማት እንደሚፋጠንም አረጋግጠዋል።
ለእድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብአቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል ሲሉም ገልፀዋል።
የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን መስራትም ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል ብለዋል።
በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ኩነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋና እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚደረግም አክለዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ተነሳሽነቶች ያሉትና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም እነዚህን ዋና ዋና ትኩረቶች መሰረት በማድረግ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ ምርታማነት ይመዘገብባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት መካከል የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ እንደሚያድግ ገልፀዋል።
የውሃ ተጠቃሚነትም በስፋት እንዲዳረስ የሚደረግ ሲሆን የጤና መድህን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲያድግ እና የደን ሽፋን ደግሞ አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማእከላት ቁጥር እንዲበራከቱና ከፍ እንዲሉ፣ የተማሪዎች ምገባ ሽፋንም 70 በመቶ እንዲያድግ ይደረጋል ብለዋል።
የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ እንዲዘምንና በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችንና ያለፉትን የስራ ክንዋኔዎች በሚገባ የተነተነ፣ መልካሙንና ክፍተቶችን የለየ እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ይበልጥ የሚያስከብርና ፈጣን እድገቷን የሚያረጋግጥ እንደሚሆን ገልፀዋል።
እነዚህን እውን ለማድረግም በተያዘው አመት አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን መከተሉ ከማንኛውም ጊዜው በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የአመቱን እቅድ ለመፈጸም የሚመደቡ አካላት የህዝብን ፍላጎት ያስቀደሙ፣ የዛሬንና የወደፊት ራእያችንን ጭምር የሚያመለከቱ እንዲሁም ዋዛ ፈዛዛ ልምምድን የሚጠየፉ እና ትጋት ያላቸው አገልጋዮች እንዲሆኑ እንደሚጠበቅ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ

በጎረቤት ኬንያ የኢቦላ ቫይረስ ታካሚ ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
#ethiopia | የኬንያ መንግሥት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይኖር በነበረ ኬንያዊ ዜጋ ላይ በ«ቡንዲቡግዮ» የቫይረስ ዝርያ የተያዘ የኢቦላ ታካሚ መገኘቱን አስታወቀ።
ግለሰቡ በዲአር ኮንጎ እያለ በበሽታው ተይዞ በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና ሲከታተል ከቆየ በኋላ፣ በኡጋንዳ ካምፓላ በኩል ወደ ናይሮቢ ተጓዞ ትናንት ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታውን ሥርጭት በቁጥጥር ስር ለማዋልና ተጨማሪ የታመሙ ሰዎችን በፍጥነት ለመለየት ከኬንያ፣ ዲአር ኮንጎ እና ኡጋንዳ መንግሥታት ጋር በመተባበር ከታካሚው ጋር የተገናኙ ሰዎችን የመከታተል፣ የምርመራና የቅኝት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

የ18 ቁጥር ማዞሪያ ቀለበት መንገድ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል ተባለ
በአዲስ አበባ ከመርካቶ በመሳለሚያ በኩል ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደውን የመንገድ ግንባታ ለማፋጠን የ18 ቁጥር ማዞሪያ ቀለበት መንገድ ከቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው ለትራፊክ እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።የመንገዱ ፕሮጀክት በ18 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ የላይና የታች የትራፊክ ማሳለጫ ድልድዮችን የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም ከጦር ኃይሎች፣ ከ3 ቁጥር ማዞሪያና ከአየር ጤና ወደ ዊንጌት፣ ሸጎሌና አዲሱ ገበያ የሚጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች በኮካና ልደታ አደባባዮች፣ በአማኑኤልና አብነት በኩል ወይም በሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ በሚገኙ አማራጭ መንገዶች እንዲጓዙ ተመላክቷል። ከአዲሱ ገበያና ከሸጎሌ ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ ወይም ጦር ኃይሎች የሚጓዙ ከባድ መኪኖች ደግሞ በዊንጌት አደባባይ በላይኛው መተላለፊያ ድልድይ እንዳይጠቀሙ ተገልጿል።
ቀላልና መካከለኛ ተሽከርካሪዎች ግን በተዘጋጁት የውስጥ ለውስጥ አማራጭ መንገዶች መጓዝ እንደሚችሉ የባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በተጨማሪም ከአሸዋ ሜዳና ቡራዩ በ18 ቁጥር ማዞሪያ በኩል ወደ ዊንጌት የሚጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎችም ትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ በአንፎ አደባባይ፣ በዓለም ባንክ ወይም በቀራንዮ አደባባይ በኩል የጉዞ መስመራቸውን እንዲያስተካክሉ ተመክረዋል።
ባለሥልጣኑ በአማራጭ መንገዶች ላይ ትራፊክን የሚያውክ መኪና ማቆም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ገልፆ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ምልክቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስቧል።የመንገዱ መዘጋት ጊዜያዊ በመሆኑ በቀጣይ የሚሰጡ ተጨማሪ መመሪያዎችንና ማሻሻያዎችን የመንገድ ተጠቃሚዎች በትኩረት ሊከታተሉ ይገባል ሲሉ አቶ እያሱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Yenetube Fikerassefa

#ebola⚠️
በጎረቤት ሃገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ግለሰብ መሞቱ ሲረጋገጥ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳውቋል።
• የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ " በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች በሙሉ የቀጠሉ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያው ከውጭ የገባ የኢቦላ (ቡንዲቡግዮ) ቫይረስ በሰው ላይ መገኘቱና የታካሚው ሕይወት ማለፉ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ ላለፉት ሰባት ዓመታት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ዲ.አር.ሲ) ይኖር የነበረ የኬንያ ዜጋ ነው።
ግለሰቡ ከዲ.አር.ሲ በየብስ ጉዞ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ካመራ በኋላ፣ ኦክቶበር 3 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) በአውሮፕላን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ ተገልጿል።
በሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም፣ በብሔራዊ የቫይሮሎጂ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ (NVRL) እና በኬኤምአርአይ (KEMRI) በተደረገ ምርመራ በቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ (Bundibugyo Ebola Virus) መያዙ ተረጋግጦ ሕይወቱ አልፏል።
ኬንያ ከሟቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን የቤተሰብ አባላት፣ የጤና ባለሙያዎችና አብረውት የተጓዙ መንገደኞችን የመለየትና በለይቶ ማቆያ የማስገባት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ኬንያ ላይ በሽታው መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን እንደሚመስል የጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሰጡን ምላሽ በወረርሽኞች ዙሪያ ሁሌም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን የተለመዱና የአየር እና የየብስ መግቢያዎቻችን ላይ ሁሌም የሚሰሩ የምርመራ ስራዎች አሉ እነዛን በሙሉ እየተሰሩ የቀጠሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዶ/ር መቅደስ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ማንቂያ ደወል ሲያሰማና ሀገራት በሽታው መግባቱን ይፋ ሲያደርጉ፣ ከእነዚያ ሀገራት በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻና የክትትል ስራዎች ወዲያውኑ እንደሚተገበሩ አመልክተዋል።
"እኛ ሁልጊዜ ዝግጅት ላይ ነን፤ ስክሪን እንሰራለን፣ በአየርም በየብስም ያለው ይሰራል" ያሉት ሚኒስትሯ "ዘ ሞመንት ደብሊው ኤች ኦ (WHO) አክቲቬት ሲያደርግና አገሮች ዲክሌር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ ከዛም አገር የሚመጡት ላይ ተመሳሳይ ነገሮችን ኢንፎርስ ይደረጋል፤ የተለመዱ ስራዎች ስላሉን እነዛን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል" ብለዋል።
ቫይረሱ ከዚህ ቀደም በዲ.አር.ሲ እና በዩጋንዳ በታየበት ወቅት ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፣ አሁን በሽታው ወደ ኬንያ መግባቱ ሲረጋገጥም የዝግጅት ደረጃው ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።
"ገና ዲአርሲ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ዩጋንዳም ሲመጣ፣ አሁን ደግሞ እዚህኛውም(ኬንያ) ሲመጣ ደረጃው እያሻሻለ እየጨመረ የሚሰሩ ስራዎች ጀምረናል። ከባለድርሻ አካላት ጋር፣ የድንበር አካባቢ (ክሮስ ቦርደር) ከሚሰሩት ጋር በመረጃ መነባበብ፣ ቅድመ ዝግጅት፣ ቅኝትና ምላሽ እነዚህን በሙሉ አክቲቬት አድርገናል፤ በዛ መልክ ላይ ነው ያለነው" ሲሉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ አቋምና ዝግጁነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም

በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የመኖሪያ ቤት ምግብ ሽያጮች ላይ የጤና ስጋት ጥቆማ ከደረሰ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካይነት የኦንላይን የምግብ ማዘዣዎችን በመቀበል፣ በግል መኖሪያ ቤቶችና በድብቅ ቦታዎች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ላይ የጤናና የደህንነት ስጋት መኖሩ ከተጠቆመ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
ተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርተፊኬት) ሰጥቶ እውቅና ከሰጣቸው ህጋዊ የምግብና የጤና ተቋማት ውጭ በኦንላይንና በመኖሪያ ቤቶች ደረጃ በድብቅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተቋሙ አስቀድሞ የማወቅና የመቆጣጠር አሰራር እንደሌለው ለአሐዱ የተናገሩት የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው
ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የቤት ለቤት የምግብ ዝግጅትና ሽያጮች ላይ በህብረተሰቡ በኩል የጥራት፣ የደህንነት ወይም የጤና ስጋት መኖሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ከደረሱ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማውን መሰረት በማድረግ የተገለጹትን ቦታዎች በመፈተሽና በመቆጣጠር አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
ማንኛውም የምግብ ዝግጅትና ማቅረብ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ አካል አስቀድሞ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመቅረብ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል ብለዋል።
አስፈላጊውን ደረጃ አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይይዙ ምግብ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በራሱ ህገ-ወጥነት በመሆኑ፣ በጥቆማ በሚደረጉ ፍተሻዎች ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አሳስበዋል።
አክለውም ፤የባለስልጣኑ ባለሞያዎች መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ ህጋዊ ተቋማትን በቀጣይነት በዓመት አራት ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንደሚያከናውኑባቸው ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም በጤናና በምግብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚፈጥሩ መሰል ህገ-ወጥ አሰራሮችን ሲታዘብ ጥቆማ በመስጠት መተባበር እንዳለበት ጠቁመዋል።
በወልደሐዋርያት ዘነበ

አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ ከፈተ።
በቱርኪዬ ከጤና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ስመጥር የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ ቢሮ መክፈቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው በቱርክ ስለሚገኙ ልዩ የህክምና አገልግሎቶች እና የህክምና አማራጮች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በሀገር ቤት ሆነው ከሀኪሞች ጋር በቀጥታ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት ይሰጣልም ተብላል።
ማዕከሉ፤ የታካሚዎችን ነባር የህክምና መረጃዎችን ግምገማ ከማከናወን እና ተጨማሪ የባለሙያ ምክር ከመስጠት ጀምሮ እስከ ህክምና ዕቅድ ዝግጅት፣ የጉዞ ዝግጅት ማስተባበር እና ከህክምና በኋላ የሚደረግ ክትትል ድረስ ባሉት ሂደቶች ሁሉ ለታካሚዎች ድጋፍ እንደሚሰጥ የአጂባድም ኸልዝኬር ግሩፕ የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የጤና መረጃ መዓከሉ ትኩረት ከአደረገባቸው የጤና ዘርፎች ውስጥ የኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ፣ የኩላሊትና ጉበት ንቅለ ተከላ ፣ የሜዲካልና ራዲዬሽን ኦንኮሎጂ ወይም ካንሰር፣ እና አይ.ቪ.ኤፍ እንዲሁም የፅንስና ማህፀን ህክምናዎች ይገኙበታል ተብሏል።
ቢሮው ለታካሚዎች አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በኢትዮጵያና በቱርክ ሀኪሞች መካከል የልምድ ልውውጥ፣ የስልጠናና የልዩ ሙያ እድሎችን በማመቻቸት የሁለቱን ሀገራት የጤና ትብብር ያጠናክራል ሲሉ ሚስተር ኢሊያስ ጨምረው ተናግረዋል።
አጂባደም በዓለም ዙሪያ 30 ሆስፒታሎችና 15 ክሊኒኮች ያሉት ሲሆን፣ ይህ የአዲስ አበባው ማዕከል በዓለም አቀፍ ደረጃ 52ኛው የመረጃ ቢሮው መሆኑም ተገልፃል።

3 days ago
ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አሁን ባለው የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ 150 ክፍሎች ያሉት አዲስ ‘Hilton Garden Inn’ እና የጤናና ደህንነት ማዕከልን (Wellness facility) በ55 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ይህ ግንባታ አዲስ አበባ በህዳር ወር 2020 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2027) ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የከተማዋን የእንግዳ ማስተናገድ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ከተማዋ ለጉባኤው ከ80,000 በላይ የውጭ ልዑካንን የምትጠብቅ ሲሆን፣ አሁን ያላት የሆቴል መኝታ አቅም ግን 25,000 ገደማ ብቻ ነው። በመሆኑም የዚህ አዲስ ሆቴል ግንባታ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2027 ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ታቅዷል።
የፕሮጀክቱ ስምምነት ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመ ሲሆን፤ የዲዛይን እና ግንባታ ሥራውን ‘ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ’ ተረክቦታል። ‘ዚያስ አርክቴክቸር እና ኢንጂነሪንግ’ ደግሞ የፕሮጀክቱ አማካሪ ሆኖ ተሰይሟል።
በተያያዘ ዜ ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ ከሆልዲንግሱ ጋር ያለው ስራ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአውትሶርሲንግ አገልግሎቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመና 3,000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ማዕከል በ25.56 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት የሚያስችል ተጨማሪ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህ የBPO ፕሮጀክት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማብዛት፣ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አቅም ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ጥራትን ማዕከል ያደረገው የመደመር መንግሥት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ብሩህ መጻኢ ዕድል በጽኑ መሠረት ላይ ገንብቶ ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚቻለው ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ልማት ሲረጋገጥ ነው።
የመደመር መንግሥትም በተለያዩ ዘርፎች ሕዝብን ማዕከል ያደረጉ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግሮችን ሲያከናውን ቆይቷል።
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ዘርፎች ላይ ያጠነጠነ፤ ዜጋን የልማቱ ዋና ተጠቃሚና ባለቤት ያደረገ የፖሊሲ እና የተግባር ርምጃን የወሰደ አካሄድ ነው።
ለአብነትም የትምህርት ሀገርን ተረካቢ ትውልድ የሚቀረጽበት ዋና ማዕከል እንደመሆኑ መጠን፣ በመደመር መንግሥት ትልቅ የመዋቅር ለውጥ ከተደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።
ቀደም ሲል የነበረውን የትምህርት ቤቶችን ቁጥር የማብዛት ብቻ ትኩረት ወደ ትምህርት ጥራት፣ የምዘና ሥርዓት ጥብቅነት ብሎም የትምህርት ፍኖተ- ካርታን እስከ ማሻሻል የተጓዘ ስር ነቀል አቋምን ተከትሏል።
የሀገር አቀፍ እንዲሁም ክልላዊ ፈተናዎች ከስርቆትና ማጭበርበር እንዲጸዱ መደረጉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቁልፍ ርምጃ ሆኗል።
የቅድመ-መደበኛ፤ ሀገር በቀል እውቀቶች፤ የዜግነትና ግብረ-ገብ ትምህርት መስፋፋት እንዲሁም የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ስልጠናዎች ትግበራ ትውልዱን ለዘመኑ ዝግጁ የሚያደርጉ ውሳኔዎች ናቸው።
የተማሪዎች ምገባ መርሐ-ግብር ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና የማቋረጥ ምጣኔም እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
እነዚህ ታሪካዊ ርምጃዎች ትምህርትን በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራትና በትውልድ ግንባታ ሚዛን ለመለካት የተደረጉ ታላቅ ውሳኔዎች ናቸው።
ጤናማ ዜጋ ለሀገር እድገትና ምርታማነት መሠረት እንደመሆኑ መጠን፤ በተመሳሳይ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ሽፋንን ከማስፋት ባለፈ ጥራቱን ለማሳደግ ያለመ መዋቅራዊ ለውጥ ተካሂዶበታል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተዳራሽነትን በማስፋት የዜጎችን የሕክምና ወጪ ጫና መቀነስ ከመቻሉም ባሻገር የላቀ የሕክምና ማዕከላት ግንባታ፣ የሆስፒታሎች ደረጃ ማሻሻያ እና የእናቶችና ሕፃናት ጤና ጥበቃን የማጠንከር ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።
የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓትን ማዘመን እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሕክምና መረጃ አያያዝን በመዘርጋት፤ ዜጎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኙ ተችሏል።
የኢኮኖሚ እድገት ትርጉም የሚኖረው በኢኮኖሚያዊ አቅም ውስንነት ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሲደግፍ ነው።
በዜጋ ተኮር ማህበራዊ ዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎች ክብርና ሰብአዊነትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው።
የከተሞች የሴፍቲኔት ፕሮግራሞች፣የሴቶች፤ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ አሰራሮችን ዘርግተዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመኖሪያ ቤቶች እድሳት፣ የምገባ ማዕከላት መመስረትና የዜጎችን ኑሮ የማሻሻል ዘመቻዎች ማህበራዊ ፍትሕንና አንድነትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ስኬትን አስመዝግበዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ እዳሉት÷ "ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፤ ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል፡፡"
ይህ የሚያሳየው፤ የመደመር መንግሥት የተከተለው ብሎም በቀጣይ የሚከተለው የልማት አቅጣጫ፤ ቁጥርና ስፋትን መሠረት ያደረገውን የተለምዶ አካሄድ ወደ ጥራት፣ ውጤታማነት እና የዜጎችን ሕይወት ማሻሻልን የትኩረት ማዕከሉ ወደ አደረገው እይታ ያሻገረ ነው።
ትምህርትን፣ ጤናን እና አጠቃላይ ማህበራዊ ዘርፉን በጥራት ማደራጀትና ማጠናከር ሰብዓዊ ልማትን ተጨባጭ ከማድረጉም በላይ የሀገር የመበልጸግ ርዕይን እውን ለማድረግ መዋቅራዊ መሠረት ጥሏል።
#የመደመር_መንግሥት
በመልካም ፈቃዱ

ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
በነባራዊ ሁኔዎች የተቃኙ የመደመር መንግሥት አቅጣጫዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት በ2019 ዓ.ም ትኩረት የሚሰጣቸውን ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ይፋ አድርጓል።
አቅጣጫዎቹ ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት ያለውን ሀገራዊ እድገት ብሎም የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው፡፡
እነዚህ አቅጣጫዎች ሀገራዊ አንድነትን ከመገንባት ጀምሮ፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ፣ የአገልግሎት ዘርፉን ማዘመን እና የዲፕሎማሲ ተጽዕኖን ማሳደግ የሚያስችሉ አጠቃላይ የፖሊሲ ግቦችን ያካተቱ ናቸው።
ሰላም ለሀገር ሕልውና፣ ለልማት እና ለዜጎች ሁለንተናዊ እድገት መሰረት መሆኑን በጥልቀት በመገንዘብ፣ በ2019 ዓ.ም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል።
በዚህም የሀገርን ዘላቂ ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን አንድነት የሚያጠናክር እና ከልዩነቶች ይልቅ የጋራ እሴቶችን የሚያጎላ አሰራር ይተገበራል። ይህም በማንኛውም መስክ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ ሀገራዊ ሕልውናን እና ልማትን ማዕከል ያደረጉ ይሆናሉ።
ሀገራዊ ኢኮኖሚው እና ማህበራዊ የአሰራር እይታው ከብዛት ወይም ከቁጥር ባሻገር በጥራት ላይ የተመሰረተ ሽግግር እንዲያደርግ ይደረጋል።
በየዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ዘላቂነትን፣ ምርታማነትን እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማዕከል በማድረግ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች እርስ በርስ እየተደጋገፉ የሚራመዱበት አጠቃላይ ሀገራዊ ሽግግር እውን ይሆናል።
ባለፉት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ጥበቃ ዘርፎች የተመዘገቡትን የተደራሽነት ወይም የስፋት ስኬቶች ወደ ላቀ ጥራት የማሸጋገር ትኩረት ቀጣይ ተልዕኮ ነው።
ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን አስተማማኝ እና ዘላቂ ይሆን ዘንድ መሰረታዊ ግብዓቶች ማለትም ለኢንዱስትሪና ለግብርና ዘርፍ የሚሆኑ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም ይጎልብታል።
ታላላቅ ፕሮጀክቶችን የትራንስፖርት፣ የኃይል እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን መገንባት፣ ማስፋፋት እና ማዘመን በራስ አቅም ይከናወናል።
በዚህም ቀደም ብለው በስኬት እንደተጠናቀቁት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ ይደረጋል።
የፋይናንስ አጠቃቀምን እና የፕሮጀክት አፈጻጸምን በዘመናዊ አሰራር የታገዘ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው።
ሀገራዊ ዕዳን በሥርዓት እና በኃላፊነት ማስተዳደር፣ የመንግሥትን ወጪና ገቢ በጥብቅ ዲሲፕሊን መቆጣጠር እና የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግና የሕዝብ አገልግሎትን ቀላልና ቀልጣፋ ማድረግ የዚህ ዓመት ሌላኛው አንኳር አጀንዳ ነው።
ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እና አዳዲስ ወዳጆችን ማፍራት፣ ለአፍሪካ ቀንድ እና ለቀጣናው ሰላም፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ እድገት ግንባር ቀደም በመሆን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲያዊ ምሕዳርም ከተራ ተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚሸጋገርበት መንገድ ም በቀጣይ የሚተገበር ነው፡፡
የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ፣ ኢትዮጵያን በጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መሰረት ላይ ለማቆም ያለመና ሕዝባዊ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ አጠቃላይ ሀገራዊ የልማት ጥሪ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በሩሲያ ሪፖርት የተደረገውን አደገኛ የሳንባ ቸነፈር ጉዳይ አስመልክቶ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር "በጣም በቅርብ ሰዓታት ውስጥ" የስልክ ውይይት እንደሚያደርጉ ማክሰኞ ዕለት አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣አሜሪካ በሩሲያ የተከሰተውን የዚህን በሽታ ስጋት በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለችው መሆኑን ገልጸዋል። ከፑቲን ጋር ስለሚያደርጉት ውይይት ሲጠየቁም፣ "በጣም በቅርብ የተያዘ የስልክ ቀጠሮ አለኝ። እስካሁንም ቢሆን ጥልቅ ውይይቶች እያደረግን ሲሆን፣ ምናልባትም ነገ ስለዚህ ጉዳይ ዝርዝር መረጃዎችን ይፋ እናደርጋለን" ብለዋል።
ዋሽንግተን ይህን አሳሳቢ የጤና ስጋት በቅርበት እየመረመረችው መሆኑን የጠቆሙት ትራምፕ፣ አሜሪካ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለሩሲያ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግም በንግግራቸው አረጋግጠዋል።

ስለ ወተት የተደረገው ጥናት ምንድነው የሚለው ?
የጥሬ ወተት ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ከእርባታ ሼድ እስከ ሽያጭ ባለው ሂደት አንዳንድ ለጤና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ፣ በከተማዋ 11 ክፍለ ከተሞች ስለወተት ጥራት ደህንነትና የግብይት ስርዓት ጥናት መደረጉን ነግረውናል።
በዚህም " ከእንስሳት እርባታ ሼዶች ጀምሮ እስከ ምርት መሸጫ ድረስ ባለው ሂደት ለጤና ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉ ጥናቱ ጠቁሞናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከውሃ ባሻገር ለጤና ጠንቅ የሆነ "ባዕድ ኬሚካል" ጥሬ ወተት ላይ እንደሚጨመር ስሞታ ይቀርባል፤ "ኬሚካል" እንደሚጨመር ጥናቱ አሳይቷል ? ብለን ስንጠይቃቸው፣ "በጥናት ያረጋገጥነው በዋናነት ከፍተኛ ውሃ የሚጨምሩ አንዳንድ ነጋዴዎችና አርቢዎች እንዳሉ ነው" ብለዋል።
በጥናቱ " ወተቱ ዋናውን ይዘቱን እንዲያጣ የሚያደርጉ ችግሮች እንዳሉ አይተናል። ከማህበረሰቡ በኩል ግን 'ባዕድ ኬሚካል' የሚጠቀሙ እንዳሉ ጥቆማዎች ይመጣሉ። ያንን በቀጣይ ጥናት መመለስ ያስፈልጋል " ሲሉም ተናግረዋል።
ጥናቱ " በተጨባጭ የወተት አያያዛችን ለጤና ስጋት የሚያስከትል ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ቁጥጥር መደረግ አለበት " በሚል ኮሚሽኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያጠናው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ለ " ካንሰር " የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር ወተት ላይ መገኘቱን ጥናቱ በተጨባጭ አሳይቷል ?
ም/ኮሚሽነሩ፣ " በተጨባጭ ጥናቱ ይሄን አመላክቷል ሳይሆን አሁን ላይ ያለው የወተት አያያዝ ስርዓታችን ከሚፈለገው ስታንዳርድ አንጻር ሙሉ አይደለም ፤ ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረግ አለበት " የሚል ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ በዋነኛነት በየሱቁ የሚገዛው ወተት " በሁለት፣ ሦስት ቀንም አይረጋም፤ ችግሩ ምንድን ነው ? " በማለት ህብረተሰቡ ቢሮ ድረስ እየሄደ ጥቆማ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
" በጭምጭምታ ደረጃ ወተቱ ላይ ኬሚካል እንደሚጨመርበት ነው የምንሰማው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ኬሚካሉ ደግሞ በጣም ከባድ ነው ወተቱን እንዳይረጋ ቢያደርግም በጊዜ ሂደት በጤና ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ሀኪሞች ያነሳሉ። በጊዜ ሂደት እነዚህ ነገሮች በከተማዋ በተጨባጭ ካሉ ካንሰር ሊያስከትል የሚችል ስጋት ሊያስከትል ይችላል " ብለዋል።
የተስተዋሉ ክፍተቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?
የወተት አያያዝን በተመለከተ በእንስሳት እርባታ ሸዶች የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ችግር ያለባቸው መሆኑንም ጥናቱ ማሳየቱን ገልጸዋል።
በእርባታ ቦታ ለላሞች የህክምና አሰጣጥ አንዲት ላም ህክምና ካገኘች ከስንት ጊዜ በኋላ ነው መታለብ ያለባት ? የሚለውን በሳይንሱ መሰረት አለመተግበር መስተዋሉን ገልጸዋል።
" የመድኃሃቱ ቅሪት እያለ አብሮ ወተቱን የማለብ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ፣ የግንዛቤ ክፍተትም አለ " ሲሉ ተናግረዋል።
በመታለብ ላይ ያለች ላም በበሽታ ብትጠቃ መድኃኒት እንደሚሰጣት፣ መድኃኒቱ በላሚቷ ሰውነት ውስጥ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር እንዳለ፣ የመድኃኒቱ ቅሪት የሚጠፋው ሀኪሞች በሚያስቀምጡት አግባብ በተለያዩ ጊዜ እንደሆነና የሀኪም ትዕዛዝ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
" የመድኃኒቱ ቅሪት ከላሚቷ አካል ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፋ ወተት ታልቦ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ግን የመድኃኒቱን ቅሪት ሰው እንዲመገበው እያደረግን ነው ማለት ነው " ብለው፣ ይህን በተመለከተ ዝርዝር ማዕቀፍ እየወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም፣ መኖ በተመለከተ በተለይ ከአቀማማጡ ጋር በተያያዘ "አፍላ ቶክሲን" የመፈጠር እድሉ ሰፊ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ረገድ ክፍተቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
" ከምንም በላይ የወተት ማለቢያ መሳሪያዎች ለምግብ ተስማሚ አለመሆናቸውን " የተናገሩት ፀጋ፣ በተለምዶ ወተት የሚገዛው በሃይላንድ፣ የሚጓጓዘውም ለማጽዳት አስቸጋሪ በሆኑ ጀርካዎች መሆኑን አንስተዋል።
በጊዜ ሂደት የፕላስቲኩ ፍቅፋቂ ከፀሐይ፣ ሙቀት ጋር ሲገናኝ የሚለቀቁ ነገሮች እንዳሉና ከፍተኛ የጤና ስጋት እንደሚያስትከሉ ሳይንሱ እንደሚያረጋግጥ ገልጸው፣ " እኛም በጥናታችን እነዚህ ነገሮች እየተተገበሩ እንደሆነ አይተናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
(ተጨማሪ ይኖረናል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም

የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች አቶ ወንዱ በቀለ የዐይን ብሌናቸውን ለገሱ
የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለአቶ ወንዱ በቀለ ቤተሰቦች የምስጋና የክብር ምስክር ወረቀት አበርክቷል።
የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ነበር።
አቶ ወንዱ በቀለ በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ቁጥጥር እና በሕፃናት ሕክምና ድጋፍ ዙሪያ የሚሰራው "ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" (የቀድሞው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ።
በሙያቸው የቢዝነስ አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ፣ የበጎ አድራጎት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደረጋቸው ልጃቸው ሕፃን ማቲዎስ ወንዱ በደም ካንሰር ሕመም ምክንያት በሕፃንነቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ነበር።
የልጃቸውን ሕልፈት መታሰቢያ በማድረግ ሚያዝያ 9 ቀን 1996 ዓ.ም (በ2004 እ.ኤ.አ) ድርጅቱን መሠረቱ።
ተቋሙ በካንሰር ለተያዙ አቅም የሌላቸው ሕፃናትና ወላጆቻቸው የምክር፣ የመጠለያ፣ የሕክምና ቁሳቁስ እና የፋይናንስ ድጋፍ ይሰጣል።
በተጨማሪም፤ የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥብቅ የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎች በሀገሪቱ እንዲወጡ ከጤና ሚኒስቴር እና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ከፍተኛ የፖሊሲ ሙግት አድርገዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ሆነው ከቱርክ ስፔሻሊስቶች የሕክምና አስተያየት የሚያገኙበት ቢሮ ተከፈተ!
#fastmereja :-በቱርክ በጤና አገልግሎት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑ ተቋማት አንዱ የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ (Acıbadem Healthcare Group) በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ በዛሬዉ እለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ይህ ማዕከል፣ አጂባደም በዓለም ዙሪያ ከከፈታቸው ተመሳሳይ ቢሮዎች 52ኛው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማዕከሉ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቱርክ ሳይጓዙ በሀገር ውስጥ ሆነው በአፍ መፈቻ ቋንቋቸው ስለ ሕክምና አማራጮች፣ ስለሚገመቱ ወጪዎችና የጊዜ ሰሌዳዎች ሙሉ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ስለመሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪም ማዕከሉ የታካሚዎችን ነባር የህክምና ሰነዶች በመገምገም ከቱርክ ስፔሻሊስቶች ሁለተኛ የሕክምና አስተያየት (second opinion) ማቅረብ፣ የሕክምና ቪዛ እና የጉዞ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም ሕክምና ተጠናቆ ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የክትትል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአጂባደም የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ እንደገለጹት፣ ቢሮው ለአገልግሎት ፈላጊዎች መረጃ ከመስጠት ባለፈ ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ጋርበመተባበር የልምድና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
በዕለቱ በቦታው የተገኙት ታዋቂው የጉበት ንቅለ-ተከላ እና ሄፓቶቢሊየሪ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ፕሮፌሰር አሊ አዘርም ቀደም ሲል በቱርክ ሕክምና አድርገው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ ከሀገር ውስጥ ሀኪሞች ጋርም ቀጣይነት ባለው ሙያዊ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በቱርክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያ፣ ኔዘርላንድስ እና መቄዶንያ 30 ሆስፒታሎችንና 15 የተመላላሽ ክሊኒኮችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ታካሚዎችን ያስተናግዳል።

Comments