በፌስቡክ ገጻቸው የሲዳማ ክልልን ህዝብ በተለይ ወጣቶችን ይቅርታ ጠየቁ የተባሉት የቀድሞ አፈጉባኤ " ፌስቡክ ገጼ ተጠልፎ ነው " አሉ።
በሰሞኑን የሲዳማ ክልል መንግሥት ምስረታ ሂደት ከክልል ፕሬዝዳንት አንስቶ ከፍተኛ የአመራር ለውጦች የተደረጉ ሲሆን፣ በዚህም ሂደት የክልሉ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሌላ ሰው ተተክተዋል።
ይህ ከሆነ በኋላ በወ/ሮ ፋንታዬ የፌስቡክ ገጽ ላይ "ይቅርታ" በሚል ርዕስ በስልጣን ዘመናቸው ለሰሯቸው ስህተቶችና በእሳቸው ዝምታ ለተፈጠሩ ልዩ ልዩ ጥፋቶች የሲዳማን ሕዝብ በተለይም ወጣቶችን ይቅርታ መጠየቃቸውን የሚገልጽ ፅሁፍ ወጥቷል።
በርካቶችም ይህንኑ መረጃ በማጋራት የሳቸው ተከታዮችና የስራ ባልደረቦቻቸው ጭምር አስተያየት ሲሰጧቸው የነበረ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀድሞ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በስልክ አግኝቶ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቋቸዋል።
ወ/ሮ ፋንታዬ " አካውንቱ አሁን ላይ የኔ አይደለም፣ ተጠልፎብኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" እኔ በአመራር ለውጡ ቅሬታ የለብኝም " ያሉት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ " አካውንቱ ከዚህ ቀደም የኔ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ተጠልፎብኛል " ሲሉ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ከሲዳማ ክልል የአመራሮች ለውጥ ጋር በተያያዘ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ፥ " በቀድሞ የክልሉ አመራሮች ጊዜ ከላይ እስከ ታች ለጠፉ ጥፋቶች ፣ በልማት ወደኋላ መቅረት ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ በክልሉ ተንሰራፋ ሙስና እና በዛ ለመጣው ጥፋት ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባ ነበር " ሲሉ እየገለጹ ናቸው።
በተለይ ደግሞ ከወጣቶች የስራ አጥነት ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ የሚነሳው ቅሬታ የበዛ ነው።
አሁን ላይ ክልሉን አዲስ አመራሮች ተረክበው እየመሩት ይገኛሉ። ረጅም ጊዜ የአመራርነት ልምድ ያላቸውና በፌዴራል መ/ቤት የነበሩት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው ወደ ስራ ገብተዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ወደ ፌዴራል ሄደው የፌዴራሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia አቶ ደስታ ሌዳሞን በመተካት የሲዳማ ክልልን በፕሬዚደንትነት እንዲመሩ የተሾሙት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ማናቸው ? በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ከዚህ ቀደም የሲዳማ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። በትምህርት ዝግጅታቸው፦ - የመጀመሪያ ዲግሪ በሕዝብ ጤና ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ…

12 hours ago