Logo
FastMereja
ሜትሮ ኬተሪንግ የኢቢኤስ ፕሮግራም አቅራቢ ጥበብ ሰለሞንን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ
​ #fastmereja I በምግብ ዝግጅት የኬተሪንግ አገልግሎቶች ዘርፍ የሚታወቀውና ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈው "ሜትሮ ኬተሪንግ"፤ ታዋቂዋን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ጥበብ ሰለሞንን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በሜትሮ ቤከሪ እና ፐጀዘወፔስትሪ ስር ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ ቆየት ብሎም የተለያዩ ስራዎችን በመስራት አሁን ላይ በትልልቅ ተቋማትና ኮርፖሬት ድርጅቶች ውስጥ የኬተሪንግ አገልግሎቱን በሰፊው በማዳረስ ላይ ይገኛል።

የድርጅቱ ባለቤት ​አቶ ፍጹም ተስፋዬ ባደረጉት ንግግር በምግብ ጥራት፣ በንፅህና እና በጤናማነት አጠባበቅ አሰራሩ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜትሮ ኬተሪንግ፤ ከምግብ ጋር በተያያዙ በርካታ ስራዎች ላይ ትልቅ አሻራ ማሳረፉን ገልጸዋል።

የአምባሳደር መመረጥም ተቋሙ ለህብረተሰቡ የሚያደርሰውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ከደንበኞች ጋር ያለውን ቁርጠኝነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል።

​በቀጣይም ተቋሙ በምግብ ዝግጅት እና በኬተሪንግ አገልግሎት መስጫዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አዳዲስ መርሆችን በመቅረጽ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ የገለጹት የስራ ሃላፊዎች፣ በሂደቱም የድርጅቱን ዕድገትና ስኬት ከህዝብ ጋር ለማስተዋወቅ አርቲስት ጥበብ ሰለሞን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደምታበረክት ተማምነዋል።

በ2013 ዓ.ም ስራ የጀመረው ሜትሮ በሲኤምሲ እና አያት ቅርጫፍ ያለው ሲሆን በልዩ ሁኔታ አምባሳደር አከባቢ በሚገኘው ግዙፉ በንግድ ባንክ ህንጻ ላይ ሶስተኛውን ቅርጫፍ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.