Logo
FastMereja
በወተት ተዋጽኦዎች አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ ህብረተሰቡ አስፈለጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ!
#fastmereja :- ህብረተሰቡ የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎችን በሚገዛበት ወቅት በተገቢው ማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጣቸዉን ሳያረጋግጥ መግዛት ለከፍተኛ የምግብ ወለድ በሽታዎች እና ለጤና እክሎች እንደሚያጋልጥ ተገለጸ።

የወተት ተዋጽኦዎች በፍጥነት በጥቃቅን ተህዋሲያን (ባክቴሪያዎች) ሊበላሹ የሚችሉ በመሆናቸው በበቂ ቅዝቃዜ (ከ 4°C በታች) ሳይጠበቁ ሲቀሩ በፍጥነት የመበላሸት እና የምግብ መመረዝ (Food Poisoning) የማስከተል እድላቸው ከፍተኛ ነው።

የተጠቃሚዎችን ጤና ለማረጋገጥ እና ከብክለት ለመጠበቅ ህብረተሰቡ በሚገዛበት ወቅት እነዚህን ነጥቦች እንዲያስተውል ይመከራል፡

የማቀዝቀዣውን ሁኔታ ማረጋገጥ ምርቶቹ የተቀመጡበት ማቀዝቀዣ በበቂ ሁኔታ ማቀዝቀዙንና በአግባቡ እየሰራ መሆኑን ማየት፤ የአገልግሎት ማብቂያ ቀን (Expiry Date) ማየት የጽሁፍ መረጃውን በማንበብ ጊዜያቸው ያላለፈባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ

እንዲሁም የማሸጊያ ደህንነትን መፈተሸ፡ ያበጡ፣ የተቀደዱ ወይም የአየር መግቢያ ያላቸውን ማሸጊያዎች አለመጠቀም፤ የግዢ ጊዜን ማሳጠር፡ ምርቶቹን ከገዙ በኋላ ወደ ቤት እስከሚደርሱ በሙቀት ውስጥ የሚቆዩበትን ጊዜ ያህል ማሳጠር እና ወዲያውኑ ፍሪጅ ውስጥ ማስገባት እና መጠቀም እንደሚገባ ተገልጿል

ህብረተሰቡ ጥራትና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የወተት ምርት ሲያጋጥመው ወደ 8482 በነፃ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.