በኬንያ የመጀመሪያው የኢቦላ ቫይረስ ታካሚ ሕይወት አለፈ
ኬንያ የመጀመሪያውን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የገባ የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ ማረጋገጧንና ታካሚውም ሕይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትሩ አደን ዱአሌ ገለፁ።
ለሰባት ዓመታት በኮንጎ የኖረው ይህ የኬንያ ዜጋ፣ በኡጋንዳ አድርጎ በመስከረም 23 ቀን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ኤርፖርት በጃምቦጄት በረራ ገብቷል።
ከኤርፖርት ቀጥታ ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል በመሄድ በለይቶ ማቆያ ቢደረግም ህይወቱ አልፏል።
የኬንያ የጤና ባለስልጣናት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከሟቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን 28 ሰዎች (የቤተሰብ አባላትና የጤና ባለሙያዎችን) ለይተው ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።
ኢቦላ በበሽታው ከተያዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ወይም ደም ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ፣ በሀገሪቱ በኤርፖርቶችና ድንበሮች ላይ ጥብቅ የጤና ቁጥጥር እየተደረገ ነው።
Seledadotio

2 days ago