Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀድሞው " የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ " የአሁኑ " የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን " መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም በቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተፈጽሟል።

በ1996 ዓ/ም ህፃን ልጃቸውን በደም ካንሰር የተነጠቁት አቶ ወንዱ "ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን" በሚል ለ22 ዓመት አገልግሎት የሰጠውን የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዳሽንን መስርተው ለበርካቶች ወገኖቻቸው ደርሰዋል።

አቶ ወንዱ፣ ለአንድ አመት ከ10 ወር ከካንሰር ህመም ጋር ታግለው ህክምና ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ኢትዮጵያን አልፎ ለአፍሪካ እና ዓለም ሀገራት መድረስ የሚችል ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ችግር ለመፍታት ያለመ "ጤናማ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል" የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጸው በመስራት ላይ ነበሩ። ይህንኑ ፕሮጀክት ከግብ ለማድረስ ፋውንዴሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

አቶ ወንዱ በቀለ የ3 ልጆች አባት ነበሩ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia "ታሞ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ባልጠበቅነው ሁኔታ በድንገት ነው ያረፈው" - የሟች ቤተሰብ ልጃቸው ህፃን ማቲዎስን የካንሰር በሽታ ሲነጥቃቸው በልጃቸው ስም የህክምና ተቋም ያቋቋሙት "‎የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ፋውንዴሽኑና ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ቤተሰባቸው በሰጡን ገለጻ፣ አቶ ወንዱ በቀለ ሕይወታቸው…
17 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.