2 days ago
" የኦቶና ሆስፒታል በተገቢው ሁኔታ መልሶ አለመገንባቱና አለመጠገኑ ታካሚዎችን ለአላስፈላጊ እንግልት እየዳረጋቸው ነው " - ነዋሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች
ከአንድ ዓመት በፊት በድንገተኛ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የኦቶና ሆስፒታል አሁንም ድረስ ተገቢው ጥገናና መልሶ መገንባት ስላልተደረገለት ታካሚዎች ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እና እንግልት እየተዳረጉ ስለመሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዲገጸል ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ታካሚዎች እና የጤና ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ፣ የተቋሙ መልሶ አለመገንባት አጠቃላይ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ እክል ስለመፍጠሩ ያስረዳሉ።
ታካሚዎች ምን አሉ ?
ለረጅም ዓመታት በሕክምና ተቋሙ ይመላለሱ እንደነበር የገለጹት የመጀመሪያው ታካሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " በቃጠሎው ምክንያት በርካታ የአገልግሎት ክፍሎች ተዘግተው በመቆየታቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ መጨናነቅ ፈጥሮ ቆይቷል " ብለዋል።
በእንዲህ ያለው ሁኔታ በርካታ ሰዎች ለሕክምና መጥተው ሳይታከሙ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ መመልከታቸውን ገልጸው " እኔም ብሆን የኢኮኖሚ አቅም ውሱንነት ስላለብኝ ባለሙያዎችን እየለመንኩ ለመታከም ተገደጃለሁ " ብለዋል።
አክለውም " ሆስፒታሉ ' ፈጥኖ ይታደሳል፣ ይጠገናል ' በሚል በተስፋ ስንጠባበቅ ብንቆይም፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት የተሻለ የጥገና እርምጃ አለመወሰዱ እጅግ አሳዝኖናል፤ ታካሚዎችንም ለከፍተኛ እንግልት ዳርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡት ሁለተኛው የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፤ " ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ይሰጣቸው የነበሩና በቃጠሎው ምክንያት ሙሉ በሙሉ የቆሙ በርካታ የምርመራ ዓይነቶች አሉ " ብለዋል።
ቀጥለውም " በቅርቡም አንድ የቤተሰብ አባሌን ለማሳከም ወደ ሆስፒታሉ በሄድኩበት ወቅት፣ ከቃጠሎው በፊት እዚያው ይሰጡ የነበሩ ነገር ግን አሁን ላይ የቆሙ ምርመራዎችን ለማድረግ ሁለት ጊዜ ወደ ሌላ የግል ተቋም እንዲሁም ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭምር ለመሄድ ተገደድናል " ሲሉ አስረድተዋል።
የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ምን አሉ ?
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ሁለት የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " ተቋሙ በድንገተኛ ቃጠሎ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ በሕክምና አገልግሎቱ ላይ ሰፊ ክፍተት ተፈጥሯል። የታካሚዎች እንግልትና ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ተገቢና እኛም የምንጋራው እውነታ ነው " ብለዋል።
አክለውም " ለሆስፒታሉ መልሶ መገንባት ከፌዴራል ተጠሪ መስሪያ ቤት (ከጤና ሚኒስቴር) ጀምሮ እስከ ክልል አካላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ድረስ ከፍተኛ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ቢደረግም፣ ብዙም ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች እስካሁን ጥገናውና ግንባታው ሳይከናወን መቅረቱ አሳዛኝ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ከሰሞኑ የተቃጠለውን ሕንፃ የማፀዳዳት ስራዎች እየተከናወኑ ነው " ያሉት ሁለቱ የጤና ባለሙያዎች " ሆስፒታሉ በአስቸኳይ ተጠግኖ የሕብረተሰቡን እንግልት ቢያስቀር ጥሩ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።
ባለድርሻ አካላት ምን አሉ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ፦
- ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣
- ከወላይታ ሶዶ ጤና መምሪያ
- ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ስልክ ባለማንሳት እንዲሁም በሰሞኑ በተደረገው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአመራር ለውጥና ሽግሽግ ምክንያት የስራ ኃላፊዎች በመቀያየራቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
ተጨማሪ ሙከራዎችን አድርገን ምላሻቸውን ለማቅረብ እንሞክራለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia ፎቶ ፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የተከሰተው የእሳት አደጋ በህዝቡ ብርቱ ጥረት በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደተቻለ ተገልጿል። በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል። መንስኤው እየተጣራ ነው ተብሏል። #wolaitazoneadministration #tikvahethiopiafamilywolaitasodo…

Comments