በሁሉም ክፍለከተሞች በተካሔደ የዳሰሳ ጥናት ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ ንጥረ-ነገሮች በጥሬ ወተት ላይ መገኘታቸው ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት በጥሬ ወተት ላይ ከውሀ እስከ ለካንሰር አጋላጭ መርዛማ ባእድ ንጥረ-ነገሮች ተጨምረው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ፀጋ ለማ፣ ጥናቱ በጥሬ ወተት ላይ ቁጥጥር ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት እንደተከናወነ ጠቅሰው፤ "በየመንደሩ ለሽያጭ የሚቀርበው ጥሬ ወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች መበራከታቸው ተረጋግጧል" ብለዋል።
በወተት ላይ የሚጨመረው ውኃ ወተቱ ሊኖረው የሚገባውን አስፈላጊ ንጥረ ነገር እንዳይዝ እንደሚያደርግ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ከውኃ ባለፈ ወተቱ ሳይበላሽ የሚቆይበትን ጊዜ ከ4 እስከ 5 ቀናት ለማስረዘም ሲባል የሚጨመሩ ንጥረ-ነገሮች የሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እና መርዛማ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የተደረጉ የቁጥጥር ሥራዎች እንደሚያሳዩት በወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ንጥረ-ነገሮች የማኅበረሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ የሚያጋልጡና እንደ ካንሰር ላሉ ከባድ የጤና ችግሮች የሚያጋልጡ ናቸው።
ይህንን ተከትሎ የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር ኮሚሽኑ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ፀጋ አስታውቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ

7 hours ago