16 hours ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ዘመናዊ የፎረንሲክ፣ የዲኤንኤ እና የሥነ ምረዛ ምርመራ ልሕቀት ማዕከል ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት https://youtu.be/7IOsXMF14...
4 days ago
የእንጦጦ-ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
#fastmereja | የፊታችን ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 ቀን 2026 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተከናወነው የእንጦጦ-ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል። ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ የተጎሳቆለ እና ለአደጋ የተጋለጠ የነበረው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ፣ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ ውብ እና ማራኪ ገጽታን ተላብሷል። ይህ ፕሮጀክት የከተማዋን "ሳምባ" በሆነው ደን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ታሪክ እና የስራ ባህል የሚያንጸባርቁ ቅርሶችና ሐውልቶች ተካተውበታል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ይዘቶች፦
ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 597 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ 9.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻን ይሸፍናል።
15 ሄክታር መሬት በአረንጓዴ ተሸፍኗል። በውስጡም 210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ የአበባ ጋርደን እና የእጽዋት ጋርደን የተካተቱበት ነው።
የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፦
6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ።
8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ።
22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ።
4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ።
39 ቼክ ዳሞች የተገነቡ ሲሆን፣ ሁለት አዳዲስ ድልድዮች እና ሶስት ነባር ድልድዮችም እድሳት ተደርጎላቸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ለብዙኃን አገልግሎት እንዲሰጥ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባውን የከተማ መናፈሻ፣ የከተማው ነዋሪ እንዲጠቀምበት እና እንዲንከባከበው ጥሪ አቅርቧል። ፕሮጀክቱ ለመዝናኛ፣ ለንግድ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።

5 days ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ሰጡ
ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚወዳደሩበት ምርጫ ጣቢያ በአካል ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

u12e8u121du122du132b u12abu122du12f5u1295 u121bu1263u12a8u1295 u1218u1265u1275u1295 u12a0u1208u1218u1320u1240u121d u1290u12cd -u12a8u1295u1272u1263 u12a0u12f3u1290u127d u12a0u1264u1264","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[],"color_ranges":[]},"id":"UzpfSTEwMDA2NDMyNTY2NjA0NDpWSzoxNjI3OTU3MjcxNjQxNzQz
የምርጫ ካርድን ማባከን መብትን አለመጠቀም ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Sponsored by
Surafel
10 days ago
አዲስ አበባ ባለፉት 5 ዓመታት የልማት አብዮት አካሂዳለች - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መዲናችን አዲስ አበባ ባለፉት 5 ዓመታት የልማት አብዮት አካሂዳለች አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በባለፉት 10 ቀናት ብቻ 11 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል።
ለአብነትም ፦
1. በኢንዱስትሪ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፤ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ይህ ፓርክ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው።
2. የማህበራዊ ልማት (የመኖሪያ ቤቶች)፤ ሶስቱ የበጎነት መንደሮችን በአዲስ ከተማ፣ በኮልፌ ቀራንዮ እና የካ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ የመኖርያ ቤቶች ለሀገር ባለውለታዎች፣ ለአቅመ ደካማዎች እና ለአካል ጉዳተኞች የማስተላለፍ ስራ ተሰርቷል፡፡
3. የመዝናኛ እና የህዝብ ፓርኮች ፤በአዲስ ከተማ (አስኮ አዲስ ሰፈር) በ30 ሺህ ካሬ ሜትር እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ እና የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች ተመርቀዋል። እነዚህ ማዕከላት ህፃናትን፣ ወጣቶችን እና አረጋውያንን ያካተቱ፣ ማህበረሰቡ በጋራ የሚጠቀምባቸው ናቸው።
4. የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የግብይት ማዕከላትን የማስፋት ስራ አካል የሆነው 7ኛው የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል፣ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
5. ዘመናዊ የገበያና የትራንስፖርት ማዕከል፤ አይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የአድዋ የገበያ ማዕከል እና ዘመናዊ የትራንስፖርት ተርሚናል ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። የዚህ ማዕከል ሱቆች እና ካፍቴሪያዎች ለፒያሳ ልማት ተነሺዎች በዕጣ ተላልፈዋል።
6. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ3 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ፣ 16 ሱቆችን እና 18 ሼዶችን የያዘ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ማዕከል አገልግሎት ክፍት ተደርጓል ።
7. የስፖርት እና የወጣቶች ማዕከል፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየም፣ 5 ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ 95 የህፃናት መጫወቻዎች፣ 6 የህፃናት ማቆያ (Daycare) ማዕከላት፣ ካፍቴሪያዎች እና አምፊ ቲያትሮችን ጨምሮ ለወጣቶች ተጠቃሚነት የሚያገለግሉ መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
8. በልደታ ክ/ከተማ ለትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ሁለት ት/ቤቶች እና ሶስት የህፃናት ማቆያ ማእከል ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረገዋል ።
9. የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎች ለነበሩ 400 ነዋሪዎቻችን መነሻ ካፒታልና የመስሪያ ቁሳቁስ በማሟሟላት ከተረጂነት ወደ የስራ እድል ተጠቃሚነት እንዲሸጋገሩ ተደርጓል።
10. 7ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በላፍቶ ክፍለ ከተማ ተመርቋል።
11. ዘመናዊ የጤና አገልግሎት ፤ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ የተደገፈው እና እጅግ ዘመናዊ የሆነው የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለምርቃት በቅቷል።
አንዳንዶች እነዚህ ፕሮጀክቶች ለምርጫ ተብሎ እንደተከናወነ ያነሳሉ ያሉት ከንቲባዋ፤ ነገር ግን እውነታው ቀድሞ ያልተሰራ ለምርጫም ሊደርስ አይችልም፤ ተሰርቶም ለምርጫ ከዋለ ዋናው ህዝቡና ሀገር ተጠቃሚ ይሁን እንጂ ችግር የለውም ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምረቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
#ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #pmabiy #digitalethiopia #healthcareethiopia #addisababa
11 days ago
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘው ዘመናዊው የላፍቶ ሆስፒታል ተመረቀ
#fastmereja በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ የተደገፈው እጅግ ዘመናዊው የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ግንባታው በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና 17 ዘመናዊ ሕንጻዎችን ያቀፈው ይህ ግዙፍ የሕክምና ማዕከል፣ 500 አልጋዎችን የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በተለይም የካንሰር እና የልብ ሕክምናዎችን በላቀ ደረጃ በመስጠት ዜጎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ውጭ አገር የሚያደርጉትን ጉዞና የውጭ ምንዛሬ ወጪን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት፣ ይህ የሕክምና ማዕከል በምሥራቅ አፍሪካ ብቸኛና ልዩ የሚያደርጉትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚደገፉና የ2026 ምርት የሆኑ የረቀቁ የሕክምና መሣሪያዎችን በውስጡ አካትቷል። ከእነዚህም መካከል በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የPET-SCAN የቅድመና ድህረ ካንሰር ምርመራ ማሽን፣ የሂሊየም ትነትን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀረው የMRI- 3 Tesla መሣሪያ፣ ልብ አንድ ጊዜ መትታ ሳትጨርስ ሙሉ ምርመራ የሚያከናውነው ፈጣን የCT Scan (640 Slice) ቴክኖሎጂ፣ እና የልብና የአንጎል ደም ሥር ችግሮችን በአጭር ጊዜ ለይቶ የሚያክመው የካዝ ላብ (Cath Lab) ይገኙበታል።
በተጨማሪም የጡት ካንሰርን በቅድሚያ ለመመርመርና የናሙና ምርመራ ለመውሰድ የሚያስችለው 3D ማሞግራፊ፣ ሙሉ በሙሉ ከሰው እጅ ንክኪ ነጻ የሆነውና የሰውን ስህተት የሚያስቀረው የመጀመሪያው የሮቦቲክ ላቦራቶሪ (TLA) ሥርዓት፣ እንዲሁም ዘመናዊ የአልትራሳውንድ እና የዲጂታል ኤክስሬይ ማሽኖች በሆስፒታሉ ውስጥ ተሟልተዋል። ማዕከሉ በሰዓት 80 ሜትር ኩብ ኦክስጂን የማምረት አቅም ያለው የሜዲካል ጋዝ ማምረቻ ፕላንት፣ የራሱ የውኃ ጉድጓድ፣ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕላንት እና 18 ዘመናዊ የአስከሬን ማቀዝቀዣዎች ያሉት ሲሆን፣ በሆስፒታሎች የሚያጋጥመውን የኢንፌክሽን ችግር ለመከላከል ሲባልም ግድግዳዎቹና ወለሎቹ ባክቴሪያን ሙሉ በሙሉ በሚከላከል (Anti-bacterial) ቁስ መገንባታቸው ተረጋግጧል። ለፕሮጀክቱ መሳካት ሌት ተቀን ለደገፉ አመራሮችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"ሶስት ልጆች አሉኝ፤ ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጅ አሉኝ። አያትም ሆኛለሁ። የመጀመሪያዋ ሴት ልጄ ሁለት ቆንጆ ወንድ ልጆችን ወልዳለች። ወንድ ልጄም ተምሮ አሁን ሁለተኛ ዲግሪውን አጠናቅቆ በግል ስራው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ሁለቱም ተምረው የጨረሱት ልጆች በጣም ጎበዞች ናቸው። አሁን እኔን ይረዱኛል። እኔ (ጊዜ በማጣት ምክንያት) ማንበብ ያልቻልኩትን መጽሐፍ፣ እነሱ አንብበው ማጠቃለያውን በመጻፍ 'ይህ መረጃ እንደ አመራር ይጠቅምሻል፣ አንብቢው' ይሉኛል። እንዲህ ያለ ቤተሰብ አለኝ። ባለቤቴም በጣም ጥሩ እና የሚደግፈኝ ሰው ነው። ሶስተኛዋ ልጄ የአምስት ዓመት ልጅ ናት። እሷም አሁን በፈጣሪ እርዳታ እየደረሰች ነው።"
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢቢሲ ኦሮሚኛ ጋር ባደረጉት ቃለምልል
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢቢሲ ኦሮሚኛ ጋር ባደረጉት ቃለምልል
Sponsored by
Surafel
11 days ago
11 days ago
ስልጣን በምርጫ የሚገኝ እንጂ እንደ ቅርጫ የሚከፋፈል አይደለም - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስልጣን በምርጫ የሚገኝ እንጂ በጉልበት ወይም እንደ ቅርጫ የሚከፋፈል አይደለም አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባዋ በዛሬው ዕለት በመዲናዋ የተካሄደውን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የምናፀናበትና የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት ሕዝቡ መሆኑን የምናስመሰክርበት ነው ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ያለበት በሕዝብ ይሁንታ ብቻ ነው የሚል ጽኑ እምነት እንዳለው ገልጸው፥ አንዱና ዋናው ግባችን ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ማድረግ ነው ብለዋል።
በእስካሁኑ ጉዞ ብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ስልጣን የሚመነጨው በሕዝብ ይሁንታ መሆኑን በማመን ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ እያራመዱ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን የፓርቲዎችን ሀሳብ በክርክርና በሌሎች መንገዶች ለህዝብ እንዲደርስ በማድረግ ፅኑ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት ሀሳባችንን ለሕዝባችን አድርሰናል ያሉት ከንቲባዋ፥ ሕዝቡ ጥሩ ዳኛ እንደሆነ በማመን በፅናት ውሳኔውን እንጠብቅ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የተካሄደው የተሳትፎ ሂደት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማፅናት የጀግንነት አውድ ነው‼️
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ማልደው ወደ መስቀል አደባባይ የተመሙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያሳዩት እንቅስቃሴ፣ ብልጽግናን ከመደገፍ ባለፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማፅናት የጀግንነት አውድ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የከተማዋ ነዋሪዎች “በምርጫ ብቻ!” የሚለውን ታላቅ መልዕክት ለዓለም ማስተላለፍ መቻላቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም የነዋሪዎቹ የሁል ጊዜ የአብሮነት መልዕክት ሀገር ማፅናት መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ለታየው ፅኑ አቋምና አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል።
Seledadotio

12 days ago
ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
7ኛው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።
የማዕከሉን ለአገልግሎት መብቃት አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ ባለ 6 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ አደራጅተን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጋችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ለዘመናት በተንዛዛ አሰራር እጅ መንሻ እየተጠየቀ ዜጎችን ሲያማርር የነበረውን የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥ ችግር ስርነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመፍጠንና መፍጠር መርህ፤ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ የዘመነና ፍትሃዊ ለማድረግ አንድ ተብሎ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት 7ኛው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ለአግልግሎት ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።
የማዕከላቱ መበራከት አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ህዝብ ወደ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ በተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ በማድረግም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ብለዋል።
ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንዲሁም የምናልመውን ብልጽግና እውን እንዲሆን ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ነው ያሉት።
ኑ በሚቀርባችሁ ማዕከል ያለምንም መንገላታት በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቀሙ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

13 days ago
Sponsored by
Surafel
13 days ago
በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ በመገንባት አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለን ስንነሳ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ መገንባትን ቅድሚያ በመስጠት ነው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በቦሌ ክፍለከተማ የተገነቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
በይፋ ተመርቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት መሰረተ ልማቶች አምስት ስፖርት ማዘውተሪያዎችን፣ 95 የህጻናት መጫዎቻዎች፣ ስድስት የህጻናት ማቆያዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ አንፊ ትያትሮችን ያካተተ ነው፡፡
በተለይም ካፒቴን አበራ ለሚ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በ4ሺህ 900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ማስረከባቸውን ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
ስታዲየሙ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየምና የእቃ ማከማቻ መጋዘንንና ያካተተ ነው ብለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ስታዲየሙን ገንብተው ያስረከቡን ካፒቴን አበራ ለሚ አመስግነው የአካባቢው ነዋሪዎች ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ትላንት ምሽት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ፓርኩ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ስድስት የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን እንዲሁም ሰባት የህፃናት መጫወቻዎችን ያካተተ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ሰፊ አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶች፣ ስድስት ካፌቴሪያዎች፣ ሦስት አንፊ ቲያትሮች፣ ልዩ ልዩ መናፈሻዎች እና በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እውን የሆነው ግዙፍ ፕሮጀክት በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፓርኩ መሳካት በጋራ በመሆን ድንቅ ስራ ላከናወኑት ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#addisababa #lemikura #greendevelopment #riversidepark #ethiopianbroadcastingcorporation

16 days ago
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት አይተን የተመኘናቸውን ነገሮች ከአሰብነው በላይ ማሳካት ችለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የቆሻሻ መጣያ የነበረና ያለ አግባብ ተይዞ የቆየ ስፍራ ወደ ዘመናዊ የጋራ መገልገያ ኢኮ ፓርክ በመቀየር ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜና በጥራት ተጠናቅቆ ለውጤት በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት እኛም እንዲህ ባደረግን የሚል ምኞት እንደነበር አንስተዋል።
አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ የራሷን ከተሞች በላቀ ደረጃ በማልማት ላይ መሆኗን አክለዋል።
ታታሪ ሕዝብ፣ ለም መሬትና ያልተጠቀምንበት ሰፊ ሀብት አለን ያሉት ከንቲባዋ፤ በልማት ሥራዎች ሀገራችን አሁን ላይ ከሌሎች ሀገራት የተሻሉ ውጤቶችን እያስመዘገበች መሆኗን ተናግረዋል።
ኢኮ ፓርኩ በውስጡ ፋውንቴይን፣ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የህጻናት መጫወቻ፣ አምፊ ቲያትር፣ ዘመናዊ ካፍቴሪያ፣ ሱቆች፣ የጁስ ባር፣ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት እንዲሁም የእግር ጉዞ የሚደረግበት ሰፊ መንገድ ተሟልተውለት በጥራት መገንባቱን ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት የትውልድ ግንባታ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የመክፈል አቅም የሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችና ሕፃናት በእኩልነት ስሜት የሚዝናኑበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ቀደም ሲል ቦታው የቆሻሻ መጣያና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጠ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ግን ለአእምሮ ምግብ የሚሆን ጤናማ አካባቢ መፈጠሩን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ይህን የጋራ ሀብት እንዲንከባከቡና እንዲጠብቁ አደራ ብለው፤ ለፕሮጀክቱ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የክፍለ ከተማው አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#ethiopia #addisababa #addisecopark #ebc

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከልን ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልክዕክት፥ መንግስት ለህዝብ የገባውን ቃል ይፈጽማል፤ የማይሰራውን ቃል አይገባም ብለዋል፡፡
ማዕከሉ የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እንዲቻል ምርትን በብዛት ለማቅረብና የግብይት ማዕከላትን ለማስፋት የሚያከናውነው ስራ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለከተማዋ 7ኛው ሲሆን፥ ለለሚ ኩራ፣ ለቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች አማካይ በሆነው ሰሚት ዋና መንገድ ላይ መገንባቱ ነው የተገለጸው፡፡
ዘመናዊ ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ያላቸው 221 መጋዘኖች፣ የችርቻሮ ሱቆች፣ ሱፐር ማርኬቶች እና ወፍጮ ቤቶችን ያካተተው ማዕከሉ በአንድ ጊዜ 250 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ እንዳለው ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡
በገበያ ማዕከሉ ማህበረሰቡ ለዕለት ፍጆታ የሚጠቀምባቸውን የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የበርበሬና የቅመማቅመም ምርቶችና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የአንድ ማዕከል የግብይት ስርዓት እውን አድርገናል ነው ያሉት።
በማዕከሉ የሚቀርቡ ምርቶች ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እንዳላቸው የገለጹት ከንቲባዋ፥ ዋጋ የሚያንረውን ህገወጥ የደላላ ሰንሰለት በመበጣጠስ ከአምራቹ ያልተቋረጠ ምርት በማቅረብ የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልል ነው ብለዋል።
ከተለያየ ቦታ በኮሪደር ልማት የተነሱ ነዋሪዎችንና የገበያ ማዕከሉ ያረፈበትን መሬት ለልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች በማዕከሉ ሱቅ እንዲያገኙ መደረጉን አንስተዋል፡፡

u12a8u1295u1272u1263 u12a0u12f3u1290u127d u12a0u1264u1264 u1260u12a0u12f2u1235 u12a2u12ae u1353u122du12ad u121du122du1243u1275 u1225u1290-u1225u122du12d3u1275 u120bu12ed u12ebu1235u1270u120bu1208u1349u1275 u1218u120du12d5u12adu1275 #adanechabiebie #addisecopark #addisababa #ethiopia ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ኢኮ ፓርክ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት #adanechabiebie #addisecopark #addisababa #ethiopia
16 days ago
በአስኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመረቀ
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሕዝብ መዝናኛና አረንጓዴ ስፍራዎችን ለማስፋፋት የጀመረውን ፕሮጀክት አካል በማድረግ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን ፓርክ ዛሬ በይፋ አስመርቋል።
ይህ በአስኮ አዲስ ሰፈር የተገነባው ሁለገብ ፓርክ፣ ከዚህ ቀደም የአካባቢውን ነዋሪዎች ለአደጋና ለብክለት ይዳርግ ከነበረ የቆሻሻ መጣያነት ወደ ንጹህና መንፈስን የሚያድስ ስፍራነት የተቀየረ የልማት ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።
ፓርኩ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት ተገቢው ጥራት ተሰጥቶት የተገነባ ሲሆን፣ በውስጡ በርካታ ዘመናዊ የአገልግሎት መስጫዎችን አካቷል።
ከእነዚህም መካከል ውብ የውሃ ፏፏቴ (ፋውንቴይን)፣ መደበኛ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የባህልና የኪነጥበብ ዝግጅቶች ማቅረቢያ አምፊ ቲያትር፣ ዘመናዊ ካፌዎች፣ የጁስ ባሮችና የተለያዩ ሱቆች ይገኙበታል። በተጨማሪም ሰፊ መኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ)፣ ንጽህናቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የሻወርና የመጸዳጃ ቤት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ የሚያደርጉባቸው ሰፋፊ መንገዶች ተሟልተውለታል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፓርኩን በይፋ ለሕዝብ ክፍት ባደረጉበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና መላው የከተማዋ ማኅበረሰብ ይህንን ከፍተኛ ወጪና እሴት የተጨመረበትን ሁለገብ መዝናኛ ፓርክ በአግባቡ እንዲጠቀሙበትና የጋራ ንብረታቸው አድርገው እንዲንከባከቡት አደራ ብለዋል።

17 days ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆችን ለተጠቃሚዎች አስተላለፉ
************
ዛሬ በአደስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ቁጥር 3 የበጎነት መንደር የተገነባውን 44 የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ያሉት ባለ አምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
17 days ago
ከንቲባ አዳነች 44 የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆች ያሉትን ባለአምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 44 የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ያሉትን ባለአምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ቁጥር 3 የበጎነት መንደር የተገነባውን 44 የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ያሉት ባለአምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል ብለዋል።
ገብስ ተራ ቀደም ብሎ እጅግ የተጎሳቆለ፣ ለመኖር ምቹ ያልሆነና ባረጁ እና በደቀቁ ቤቶች የተሞላ፣ በተደጋጋሚ በእሳት አደጋ የሚጠቃ፣ ለአቅመ ደካማ እናቶች የማብሰያና የመጸዳጃ አገልግሎት አስቸጋሪ የነበረበት መንደር መሆኑን አስታውሰዋል።
በዚህ መንደር የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 377 የመኖሪያ ቤቶች ያላቸው 5 ህንጻዎች መገንባት መቻሉን የገለጹት ከንቲባዋ÷ ነዋሪዎቻችንም ከዛ አስከፊ አኗኗር ተላቀው ክብራቸውን በሚመጥን ፅዱ፣ ዘመናዊ አኗኗር የሚፈጥር፣ ልጆች ቦርቀው የሚጫወቱበት እና ደረጃውን በጠበቀ መኖሪያ መንደር እንዲኖሩ በማድረጋችን በጣም ደስ ብሎናል ነው ያሉት።
ይህንን የበጎነት መንደር ግንባታ ላይ በክትትል እና ድጋፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን ከምንም በላይ ልበ ቀና ባለሃብቶች በገንዘባቸው ላደረጉት ድጋፍ በነዋሪዎቹ ምስጋና አቅርበዋል።

18 days ago
አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ጋር የተፈረመው ስምምነት፤ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ በቱሪዝም (ስፖርት ቱሪዝምን) ጨምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia | አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ጋር የተፈረመው ስምምነት፤ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ በቱሪዝም (ስፖርት ቱሪዝምን) ጨምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
18 days ago
አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ እና የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የባህልና የታሪክ ልውውጥ የሚያጠናክር ነው፡፡
በተጨማሪም በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ የስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ በቱሪዝም ልማት የሁለቱን ከተሞች ትብብር ያጠናክራል ነው ያሉት፡፡

አዲስ አበባ እና የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የእህትማማች ከተሞች (Sister Cities) ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ (ስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ) በቱሪዝም እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
#ethiopia #azerbaijan #addisababa #baku #sistercities #ebc

አዲስአበባውያን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ
📌በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረግነው ጉብኝት ለከተሞቻችን ልማት ትልቅ ልምድ የቀሰምንበት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም አቀፉ የከተሞች ፎረም ጎን ለጎን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረግነው ጉብኝት ለከተሞቻችን ልማት ትልቅ ልምድ የቀሰምንበት ነው አሉ፡፡
በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ በባኩ ከተማ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን እና የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ የባኩ ከተማ የከተማ እድሳት ሂደት የአዲስ አበባን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችን ተሞክሮ የሚያንፀባርቅ ነው።
ጉብኝቱ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የጀመርናቸውን የከተማ ልማት፣ የቅርስ እድሳትና ጥበቃ ስራዎችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ትልቅ ልምድ የተቀሰመበት ነው ብለዋል።
አሮጌና ጎስቋላ የነበረውን ስፍራ ሙሉ በሙሉ በማፍረስና እንደ አዲስ በመገንባት እንዲሁም ጥንታዊቷ ከተማ በመባል የሚታወቀውን የከተማዋ ክፍል በጥንቃቄ በማደስ ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
ይህ የከተማ እድሳት ሂደት የኢትዮጵያን ተሞክሮ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸው፥ ታሪክና ቅርሶችን ጠብቆ በማደስ ጎስቋላ አካባቢዎችን በአዲስ መልክ እየገነባን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ለአብነትም በፒያሳ እና አራት ኪሎ ያሉ ጥንታዊ ሕንፃዎችን፣ የመጀመሪያውን ሲኒማ ቤት፣ የመጀመሪያውን ማዘጋጃ ቤት፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን እንዲሁም የተለያዩ ሐውልቶችን እድሳት ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር እንደ ሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና የጎንደር ፋሲል ቤተ መንግሥት የመሳሰሉትን ታላላቅ ቅርሶች በማደስ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
እጅግ ጎስቋላና ለመኖር ምቹ ያልነበሩ መንደሮችን በማፍረስ ዘመናዊና ምቹ በሆነ መልኩ መገንባታቸውን ጠቅሰው፥ በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በተሳካ ሁኔታ የተተገበረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዚሁ ራዕይ ዋነኛ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።
ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ምቹ፣ ማራኪ፣ አረንጓዴና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በማስፋት፣ ለእግረኛና ለብስክሌት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን በመፍጠር እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ በመቀየር እጅግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

19 days ago
በዓለም አቀፉ የከተሞች ፎረም የሀገራችንን እና የመዲናችንን እያስተዋወቅን እንገኛለን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
************
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአዘርባጃን መዲና ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው ዓለም አቀፍ የከተሞች ፎረም (13th World Urban Forum) ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
ፎረሙ “ቤት ለሁሉም፤ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጠንካራ ከተሞች እና ማህበረሰቦች” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤውም ዓለም አቀፋዊ የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት፣ ዘላቂ የከተማ ልማት፣ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ከተሞችን መገንባት፣ የአየር ንብረት እና የመኖሪያ ቤት ግንኙነቶች፣ መልሶ ግንባታ እንዲሁም ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በዋናነት እየተመከረባቸው መሆኑን በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ ጠቃሚ የልምድ ልውውጥና የመስክ ጉብኝቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ የጠቆሙት ከንቲባዋ ፤ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከውይይቶቹ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እና የመዲናዋን አዲስ አበባን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም መሠረት በዛሬው ዕለት በተከፈተው ኤክስፖ ላይ መንግሥት ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገልጽ ልዩ ፓቪልዮን (ቡዝ) በማዘጋጀት፤ የተከናወኑ ዘላቂ የከተማ ልማት ሥራዎችን በጽሑፍ፣ በቪዲዮ እና በቪርቹዋል ሪአሊቲ ቴክኖሎጂዎች ለታዳሚዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እየተሠራ ይገኛል።
#worldurbanforum #mayoradanechabiebie #ethiopia #addisababa #bakuazerbaijan #ethiopianbroadcastingcorporation

የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ የሚለካው ያልተጠቀምንባቸውን ሀብቶች የልማት ማዕከል በማድረግ ጭምር ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ የሚለካው ያልተጠቀምንባቸውን ሀብቶች የልማት ማዕከል በማድረግ ጭምር ነው አሉ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ‘ገላን ጉራ የብልጽግና አሻራ!’ በሚል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ ስፋትና ጥልቀት የሚለካው የከተማዋን እምብርት በማስዋብ ብቻ ሳይሆን፣ ትናንት በአግባቡ ያልተጠቀምንባቸውን ሀብትና አካባቢዎችን ዓይናችንን ገለጥ በማድረግ ተመልክተን የልማትና የዕድገት ማዕከል በማድረግም ጭምር ነው ብለዋል።
ከ5 ዓመት በፊት ምንም የሚታይ መሠረተ ልማት ያልነበረው የገላን ጉራ አካባቢ ዛሬ ላይ የታሪክ ምዕራፉ ተቀይሮ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ከፍታና መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳይ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስተጋብር ማዕከል ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
ዛሬ በዚህ ስፍራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው በማለት ተናግረዋል።
ለአብነትም:-
1. በአዲስ አበባ የመጀርያው እና ትልቁ ባለ 325 ሜትር ርዝመት እና 60 ሜትር ስፉት ዘመናዊ ድልድይ፣
2. 21.73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው (ቃሊቲ ቀለበት -ቱሉዲምቱ እና ቃሊቲ ቀለበት - ቂሊንጦ አደባባይ) የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደርን ያሳለጠ እና ቀጥታ ከአየር መንገድ ካርጎ የሚያገናኝ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት፣
3. የከተማችንን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለማቃለል አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል የሆነ 60 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣
4. ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን የገነባነው ምቹና የተቀናጀ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የሚገኝበት፣
5. የኅብረተሰባችንን ጤና በላቀ ደረጃ ለመጠበቅ በከተማችን በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የገላን ትሯማ ሆስፒታል ግንባታ፣
6. በአካባቢው ለዚሁ ልማት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ለለቀቁልን አርሶ አደሮች የተቀናጀ ዘመናዊ የግብርና ልቀት ማዕከል ግንባታ፣
7. መንፈስን የሚያድሱ ሰፋፊ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ፓርኮች እንዲሁም
8. የስፖርት ማዘውተርያዎችና የልጆች መጫወቻዎች፣ ለእናቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር የእንጀራ ፉብሪካ ግንባታ እና የመሳሰሉት የብልፅግና አሻራዎች ደምቀው አካባቢውን ከመሐል ከተማ የበለጠ ተመራጭ አድርገውታል ብለዋል በመልዕክታቸው።

Comments