21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ባህል) የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ"አምባሳደር አሸንዳ" ማዕረግ ተሸላሚ የነበረችውን ወጣት ዜማ እምብዛን ከክብር ማዕረጓ ማንሳቱን ያስታወቀበት ይፋዊ መግለጫ፣ በባህል ልማት ስም የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት ተቋማትን ሚና እና የአስተሳሰብ አድማስ በድጋሚ በትዝብት መድረክ ላይ የሚጥል ሆኗል። ቢሮው ውሳኔውን ያስተላለፈው ወጣቷ «አሸንዳ ኢትዮጵያ» በሚል መጠሪያ ባህሉን ለማስተዋወቅ መሞከሯን እንደ ትልቅ ወንጀልና የሕዝብን እሴት የመጣስ ተግባር ቆጥሮት ነው። ይህ እርምጃ ባህላዊ ቅርሶችን ከማሳደግና ዓለም አቀፋዊ አድማሳቸውን ከማስፋት ይልቅ፣ ጥበብንና ባህልን በፖለቲካዊ ቅጥሮች ውስጥ የመሸበብ አደገኛ ዝንባሌ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
አሸንዳ ዕድሜ ጠገብ የሆነ፣ የማንነት፣ የነጻነትና የሴቶች ክብር መገለጫ የሆነ እምቅ የሕዝብ ቅርስ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ የማስተዋወቅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም፣ ዋና ዓላማው ቅርሱ ከክልላዊ ወሰን አልፎ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ፣ አልፎ ተርፎም በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገብ መሥራት መሆን ነበረበት። ሆኖም ግን፣ወጣቷ አምባሳደር የቅርሱን አድማስ ለማስፋት እና ከሌሎች ወገኖች ጋር ድልድይ ለመፍጠር «ኢትዮጵያ» የሚለውን ስም በማካተቷ ብቻ ማዕረጓን መንጠቅ፣ ከተቋማዊ ራዕይ ማነስ እና ባህልን የፖለቲካ ፍጆታ ከማድረግ የሚመነጭ እጅግ ጠባብ አካሄድ ነው።
የባህልና ቱሪዝም ቢሮው በመግለጫው ላይ ወጣቷን «የሕዝቡን ባህላዊ እሴቶች የማይወክል ተግባር ፈጽማለች» ሲል ቢከስም... በተግባር ግን ራሱ ቢሮው የትኛውን ባህላዊ እሴት እየጠበቀ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ባህል የሰዎች መገናኛ፣ የፍቅርና የሰላም መድረክ እንጂ ሰዎችን ማግለያና መቅጫ መሣሪያ አይደለም። ወጣት ዜማ እምብዛ ለአሸንዳ በዓል ሰፊ ዕውቅና ለመስጠት ያሳየችውን ተነሳሽነት በበጎነት ከመደገፍና ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ከመምራት ይልቅ፣ እንደ ፖለቲካ ወንጀለኛ ቆጥሮ በይፋ ማዋረድና ማዕረግ መንሳት፣ በክልሉ ጥበብና ባህል ላይ የተጣለ ትልቅ ጥላሸት ነው።
ይህ ክስተት የሚያሳየው ትልቁ እውነት፣ የታሪክና የባህል ተቋማት ከዘመኑ የፖለቲካ ውጥረት እና ከልሂቃኑ መከፋፈል ራሳቸውን ማላቀቅ አለመቻላቸውን ነው። የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ይህንን መሰል የተሳሳተ ውሳኔ በማሳለፍ... አሸንዳን ለዓለም ከማስተዋወቅ ይልቅ በጠበበ የፖለቲካ አጥር ውስጥ መልሶ አግቷታል። ተቋማት የሕዝብን ውብ ባህል ወደ ኋላ ከመጎተት እና በወጣቶች የፈጠራ አቅም ላይ ሳንሱር ከመጣል ተቆጥበው፣ ጥበብ ያለ አንዳች የድንበር ገደብ እንድታብብ የነጻነት አየር ሊፈጥሩላት ይገባል የሚለው የብዙኃኑ ጥያቄና የዚህ ክስተት ዋነኛ ማሳያ ነው።

29 days ago
ቁጥሮች ይናገራሉ፡- ዓመታት ይታዘባሉ
**********************
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዘመናት ውዝፍ ስራዎችንና የባከኑ ታሪካዊ እድሎችን በሚያካክስ መልኩ እጅግ አስደናቂና ግዙፍ የኢኮኖሚ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች።
ለዘመናት ሀገራችን የተጓዘችው የኤሊ ጉዞ በድህነት አዙሪት ውስጥ እንድትቀር አድርጓት ቆይቷል። ሆኖም፣ የመደመር መንግሥት ይህንን የተደራረበ የኋላ ቀርነት ችግር ለመቅረፍና የባከነውን ጊዜ ለማካካስ፣ የተለመደውን አዝጋሚ ጉዞ በመተው "የዝላይ ስትራቴጂን" (Leapfrogging)፣ የፈጠራ (Innovation) እና የፍጥነት (Speed) መንገድን አጥብቆ መከተል እንዳለበት ያምናል።
ይህን የፍጥነትና የፈጠራ እሳቤ በተግባር በማረጋገጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ መሰረት፣ ሀገራችን አሁን ላይ የ17፣ የ27 ዓመታት እና ከዚያም በላይ የሆኑ የትናንት ታሪኮችን በአንድ አመት ገደማ ያጠቃለለችበት የብልጽግና ምዕራፍ ላይ በኩራት ደርሳለች ብለዋል።
የ17 ዓመታት ስኬት በአንድ ዓመት መቋጨት በውጭ ንግድ (ኤክስፖርት) ዘርፍ ኢትዮጵያ ዘንድሮ 11 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ሀገራዊ ታሪክን የቀየረ ግዙፍ ክንውን አስመዝግባለች።
ይህ አሃዝ ዝም ብሎ ስሌት ሳይሆን፣ ከ1984 እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት 17 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ካገኘችው አጠቃላይ የኤክስፖርት ገቢ ጋር እኩል የሆነ ነው።
በተለይም የኢትዮጵያ አንጡራ ሀብት በሆነው በቡና ኤክስፖርት ዘርፍ፣ ኢትዮጵያ ለ17 ዓመታት ወደ ውጭ ልካ ያገኘችው አጠቃላይ የዶላር መጠን 3.3 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ሲሆን፣ ዘንድሮ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 3.1 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት የ17 ዓመቱን አዝጋሚ ጉዞ በአንድ አመት የፍጥነት ዝላይ ማሳካት ችላለች።
ይህ እመርታዊ ለውጥ (Nonlinear growth) የተገኘው ዘመናትን የፈጀውን የደረጃ በደረጃ ጉዞ በመዝለል፣ አዳዲስ አሰራሮችን በማፍለቅና አቅምን አሟጦ በመጠቀም ነው።
የ27 ዓመታት ውጤት በአንድ ዓመት ሲገለጥ በማዕድን ዘርፍ በተለይም የወርቅ ኤክስፖርትን ስንመለከት ውጤቱ ይበልጥ አስደማሚና የፈጠራን ሃያልነት የሚያሳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
ከ1984 እስከ 2011 ዓ.ም ባሉት 27 የውድቀትና የመከራ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የላከችው አጠቃላይ የወርቅ መጠን 3.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ በአንድ አመት ገደማ ብቻ ወደ 5.5 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት የ27 ዓመቱን ታሪክ በአንድ አመት መብለጥ መቻሏ የዝላይ ስትራቴጂን ተግባራዊነት ያረጋግጣል።
በሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብም የኢኮኖሚ አሻጋሪነት ራዕይ ደምቆ ይታያል። በ27 ዓመታት ውስጥ የተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ 1 ትሪሊዮን ብር ገደማ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ዘመናዊ አሰራርንና ፈጠራን በማቀናጀት ዘንድሮ በአንድ አመት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ በማስገባት የ27 ዓመቱን ጥረት 150 በመቶ በአንድ አመት መሰብሰብ ተችሏል።
ይህ የሚያሳየው፣ የመደመር መንግሥት ተስፈንጥሮ ከፍታ ላይ ለመድረስ ያለውን ስነ-ልቦናዊና የተግባር ዝግጁነት ነው።
ከ20 እጥፍ በላይ ያደገው አቅም እና የማይበገር ማክሮ ኢኮኖሚ ከእነዚህ የዘመናት ስኬቶችን ወደ አንድ አመት ካመቁ ውጤቶች ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ራሷን ከድንገተኛ አለም አቀፍ ንዝረቶች የምትጠብቅበት የውጭ ምንዛሬ ክምችቷ (Reserve) ከጥቂት አመታት በፊት ከነበረው አቅም ከ20 እጥፍ በላይ በማደግ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጫናዎችን የመቋቋም አቅሟን አፈርጥማለች።
ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ፣ መንግሥት ይህንን ሁሉ ስኬት ያመጣው የሀገርን ሉዓላዊነትና የነገ ትውልድ ነጻነትን አደጋ ላይ ከሚጥል እዳ በመራቅ፣ ላለፉት 8 ዓመታት አንድም ዶላር የንግድ ብድር (Commercial Loan) ሳይበደር መሆኑ ውጤቱን ይበልጥ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ያደርገዋል።
በዚህም የተጠናና የተናበበ ሁሉን አቀፍ ጥረት፣ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ10.2 እስከ 10.3 በመቶ ያድጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም በአፍሪካ ትልቁ ዕድገት ሆኖ በኩራት ተመዝግቧል።
በአጠቃላይ፣ እነዚህ አስደማሚ ቁጥሮች እና ድንቅ ስኬቶች ኢትዮጵያ የመደመር መንግሥት በሚከተለው የ"ፍጥነት፣ ፈጠራ እና ዝላይ" አስተሳሰብ የዘመናትን የተከማቸ የድህነት እዳ በአጭር ጊዜ ማካካስ እንደምትችል በተግባር ያረጋገጡበት ግዙፍ ማሳያ ናቸው።
የብዙ አስርት አመታትን ስራ በአንድ አመት በማጠናቀቅ፣ "ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ" ከሆነው የድህነት አዙሪት በሀይል ተፈንጥራ ወጥታለች።
ቁጥሮቹ የሚመሰክሩት ይህንን እውነት ነው፤ ኢትዮጵያ ወደ ተጨባጭ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ ወደማይቀለበስበት ምዕራፍ መሸጋገሩን የዘመናችን ታሪክና አመታት በትዝብትና በአድናቆት እያዩት ይገኛሉ።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ

2 months ago
ሕወሓትን የተቃወሙት የ76 አመት አዛውንት ታሰሩ‼️
በትግራይ ክልል የእንደርታ ተወላጅ የሆኑት የ76 ዓመቷ ነባር ታጋይ አኸዛ ሕሉፍ፣ በክልሉ ስላለው የፍትህ እጦት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና የፖለቲካ ብልሽት አስመልክተው ከሶስት ቀናት በፊት የሰጡት ቃለመጠይቅ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው መታሰራቸው ተሰማ።
የወረዳ 70 እንደርታ የፈለግማያት ጣቢያ ነዋሪ የሆኑት እናት ለምን ተነፈስሽ? ለምንስ ተናገርሽ?” በሚል ዛሬ መታሰራቸውን ተረጋግጧል። እንደ መረጃዎች ገለጻ ለእስራታቸው ዋነኛ ምክንያት የሆነው “ለምን ልጆች ወደ ጦርነት ይገባሉ?” በማለት ሰላማዊ ጥሪ ማቅረባቸውና እንደሌሎቹ የጦርነት ነጋሪት ለመጎሰም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ የቀድሞው ህወሓት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አፋኝ ህግ ማውጣቱ በሚታወስበት በዚህ ወቅት የ76 ዓመት አዛውንት በአመለካከታቸው ማሰሩ ከፍተኛ ቁጣንና ትዝብትን እየቀሰቀሰ ይገኛል።
እስካሁንም እናት አኸዛ ሕሉፍ በታጣቂዎች ተወስደው የት ቦታ እንደታሰሩና አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አለመታወቁ ተገልጿል።
Seledadotio

⌚️ የሰከንድ ስሌት እና የ"ሩት ቢር" ናፍቆት ጥበብ በክንድ ላይ ስትመለክ!
በአሁኑ ዘመን የሰዓት አገልግሎት ጊዜን ማወቅ ብቻ አይደለም ጊዜውን የሚቆጥረው አካል ማንነት፣ የውበት ምርጫ እና ምናልባትም "የኪስ አቅም" ማሳያ ጭምር እንጂ።
ሰሞኑን በዲጂታሉ ዓለም የብዙዎችን አይን የሳበውና መነጋገሪያ የሆነው የስዊዘርላንዶች እጅግ ረቂቅ የእጅ ጥበብ ውጤት የሆነው Rolex GMT-Master II "Root Beer"ሰዓት ነው።
ይህ ሰዓት እንዲሁ ተራ የሰከንድ መቁጠሪያ አይደለም በስፖርታዊ ጥንካሬው እና በቅንጦት ውበቱ የብዙዎችን ልብ የሰረቀ የሰዓት አምራቾች ቁንጮ ነው።
የ"ሩት ቢር" ቀለም እና የቅንጦት ጥበብ
ይህ ሞዴል "Root Beer" የሚለውን ስም ያገኘው ከባህላዊው መጠጥ ቀለም ጋር በሚመሳሰለው ከሴራሚክ (Cerachrom) ከተሰራው ቡናማ እና ጥቁር ጠርዙ የተነሳ ነው።
ሰዓቱ የትዕግስት፣ የጥራት እና የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ውጤት ነው።
* *ሁለት ዓለም በአንድ ክንድ ላይ**
ይህ ሰዓት የተሰራው በተለይ በተደጋጋሚ ለሚጓዙ ሰዎች በመሆኑ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያዩ ሀገራትን የሰዓት ቀጠናዎች መቁጠር ይችላል።
የEverose ወርቅ እና የብረት ቅይጥ
ሮሌክስ የራሱን የፈጠራ መብት የተጠቀመበትን የሮዝ ወርቅ (Everose Gold) እና ልዩ ብረትን አቀናጅቶ የሰራው በመሆኑ፣ በሩቅ ሲመለከቱት እንኳ ማራኪነቱ አይን ይበላል።
ይህንን ሰዓት ልዩ የሚያደርገው ውበቱ ብቻ አይደለም ወደ ገበያው ሲመጣ የሚጠይቀው አስገራሚ የገንዘብ መጠን ጭምር ነው።
በሮሌክስ መደብሮች ውስጥ ሰዓቱን ለማግኘት እጅግ ረጅም የጥበቃ ዝርዝር (Waiting List) ያለ ሲሆን በዓለም አቀፍ የግራጫ ገበያ (Grey Market) ላይ ደግሞ ዋጋው እስከ አስር ሺዎች አሜሪካ ዶላር ድረስ ይተመናል።
የዚህን ሰዓት ዋጋ ወደ እኛ ሀገር የመግዛት አቅም እና የወርሃዊ ደሞዝ ስሌት ስንመዝነው ነገሩ ሌላ ታሪክ ይወልዳል።
በአንድ በኩል ጥበብን የሚያደንቅ አይን እንዲህ ያለውን ውድ ዕቃ በክንድ ላይ ማየቱ "የእውነትም ያምራል!" ሊያስብል ይችላል።
በሌላ በኩል ግን የኑሮው ፈተና እና የኪስ አቅሙ ሁኔታ ፈታኝ በሆነበት ምድር ላይ እንዲህ ያሉ የቅንጦት ቁንጮዎች በአደባባይ ሲታዩ "የቁጥሮቹ ስሌት እንዴት ይሆን?" የሚል የብዙዎችን የማወቅ ጉጉትና የትዝብት ጥያቄ መቀስቀሱ አልቀረም።
ታዲያ ጊዜው የቴክኖሎጂ ነውና ሰዓቱ ራሱ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያየ ሀገር ሰዓቶችን እንደሚቆጥረው ሁሉ ሰዓቱን የሚያዩ ሰዎችም በአንድ ጊዜ ሶስት የተለያየ ሀሳቦችን ቢያሰላስሉ አይገርምም አንደኛው የሰዓቱን ውበት ያደንቃል፣ ሁለተኛው ዋጋውን ሰምቶ ይደመማል፣ ሶስተኛው ደግሞ "ይህንን የመሰለ ወርቅ በደሞዝ ወይንስ በምን?" ብሎ በዝምታ ይተክዛል።
ያም ሆነ ይህ ሰዓቱ ግን አሁንም ስራውን በትክክል እየሰራ ነው ሰከንዶችን ያለ ማቋረጥ ይቆጥራል ጊዜ ደግሞ ሁሉንም ነገር ..

Sponsored by
Surafel
2 months ago
♦️በተተኮሠበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ ባለፈው የቀድሞ አትሌት ይሄይስ ታደለው ዙሪያ የተጠናከረ ልዩ ዘገባ
♦️በአትሌቶች መካከል ያለውን የአጉል ባህልና ዕምነት፣የመጠራጠርና የመጠፋፋት ባህል እንደወረርሽኝ ተዛምቶ ለተጨማሪ አደጋ ከመጋለጣችን በፊት ይታሰብበት
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
♦️የሟችና በገዳይነት የተጠረጠረው አትሌት ማንነት
በሚያሳዝን ሁኔታ ሁለቱም የነገ ውጤታማ አትሌቶች ይሆናሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ወጣቶች ነበሩ፤ጉዳዩ በህግ የተያዘ በመሆኑና በማስረጃ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በተለይ ለሀትሪክ እንደገለፁት በገዳይነት ተጠርጥሮ በህግ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አትሌት ደረሠ ረታ ከደብረብርሃን የተገኘ በመቀጠል በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አሁን በመጨረሻ ደግሞ ለፌዴራል ፖሊስ የሚሮጥ አትሌት ሲሆን በጣም ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አትሌት እንደነበረም ነው ለአትሌቱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች የሚናገሩት።እንደ እነዚሁ ምንጮቻችን አገላለፅ አትሌቱ ከአንድ ዓመት በፊት በጉያንግ በተካሄደው ውድድር 2:12:00 በሆነ ሠዓት በመግባት የተሻለ ሠዓትና ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን የቅርብ ምርጥ ሠዓቱም 2:13:00 እንደሆነ ነው የሚሠማው።
በተተኮሠበት ጥይት ህይወቱ ያለፈው አትሌት ይሄይስ ታደለው በበኩሉ ከአማራ ክልል (ሠሜን ሸዋ)የተገኘ አትሌት ሲሆን በጉዳት ምክንያት ከውድድር ርቆ ባለቤቱን አትሌት ወርቅነሽ ዓለሙን እንደ አሠልጣኝ ሆኖ ከማሠራት ውጪ በአሁን ሠዓት በአትሌትነት እየሮጠ አይደለም።
♦️እስከመገዳደል ያደረሳቸው ምን ይሆን?
ሁለቱን ከአንድ ክልል የመጡ አትሌቶችን እስከመገዳደል ያበቃቸውን ትክክለኛውን ከእነሱና ከፈጣሪ ውጪ የሚያውቅ ሠው ፈልጎ ማግኘት አይቻልም፤ነገር በመካከላቸው ለገላጋይ ያስቸገረ አለመግባባት እኔዳላቸው ቀአሠልጣኝቻቸውና በቤተሠብቻቸው እኔዲሁም አትሌት በሆኑት ሚስቶቻቸው ጭምር ይታወቃል።የፀባቸውን መነሻ በትክክል መግለፅ ባይቻልም ከአጉልጰባህል ወይም አምልኮ ጋር ተያይዞ ባለቤቴና እኔ ላይ ይሄን አስደርገሃል የሚለው ዋነኛው የግጭታቸውና እስከመገዳደል ያደረሠ ችግር እንደሆነ በዙሪያ ያሉ ሠዎች ይናገራሉ፤ይህ ከድሮም ጀምሮ በአትሌቶች ዙሪያ የሚሠማው አጉል ባህል ወይም የአምልኮ ነገር ዛሬ ወደ አዲሶቹ ትውልዶችም ተሸጋግሮ አብሮ ልምምድ ያለመስራት፣አብሮ በህቴል እኔደጓደኛ አትሌት ክፍል ያለመጋራት፣አብሮ ያለመብላትና አብሮ በአንድ አውሮፕላን አልሄድም እስከማለት አስፈሪ ውሳኔ ላይ ተደርሶ የቡድን ስሜት ከአትሌቲክሱ እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል።
♦️ለሽማግሌና ለአስታራቂዎች ያስቸገሩት ሟችና ገዳይ
በሁለቱ አትሌትች መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ያልመጣ አስታራቂ ሽማግሌ፣የሁለቱም አሠልጣኞች ፍቅሩና ኢማና መርጊያን ጨምሮ፣የቅርብ ጓደኛ በመጨረሻም ቤተሠብች የሁለቱንም አለመግባባት ለመፍታት ዳገት ቢወጡ ቁልቁል ቢወርዱ ሊሳካ አልቻለም፤አሠልጣኞችም ነገሩ ከብዷቸው ሁለቱም ሴት አትሌቶች በተለያየ አሠልጣኝ የተለያየ ቦታ እንዲሠሩ እሰከማድረግ ደርሠዋል፤በውስጥ የተቋጠረው ቂም በሽማግሌም፣በገላጋይ አልፈታም ብሎ በመጨረሻም ድምዳሜው የአንደኛው ህይወት በአንደኛው እጅ መጥፋት ሆኗል።
♦️የአትሌቱ ህይወት ስላለፈበት አጋጣሚ
ገዳይ እንዴትና የት፣በምን ሁኔታ የሟችን ህይወት ነጠቀ የሚለው ብዙዎች ለማወቅና እርግጠኛ መሆን የሚፈልጉበት ጥያቄ ነው፤በገዳይነት የተጠረጠረው አትሌት ደረሠ ረታ በውስጡ በተፈጠረ አንዳች ስሜት ተነሳስቶ ወደ ሠንዳፋ የልምምድ ቦታ ድንገት አመራ፤በዛች ቀን የተደገሠለትን ድግስና ከሞት ጋር ቀጠሮ እንዳለው ለሠከንድም ቢሆን ያላሠበው የቀድሞ አትሌት ይሄይስ ታደለው ባለቤቱን አትሌት ወርቅነሽ ዓለሙን ከፊት ሆኖ እያሠራ እያለ በድንገት በተተኮሠበት ጥይት ይህቺን ዓለም ዳግም ላይመለስባት ለዘለዓለሙ አሸልቧል።በገዳይነት የተጠረጠረው ከፊቱ በርካታ የአትሌቲክስ የስኬት ዓመታት እንዳሉት የሚነገርለት በግድያ የተጠረጠረው አትሌት ደረሠ ረታ ከግድያው በኋላ ራሱን ለማሸሽ ጥረት ቢያደርግም በአካባቢው በነበሩ አርሶ አደሮች ጥረት ተይዞ አሁን ሠንዳፋ በሚገኘው ማረሚያ ቤት በህግ ጥላ ስር ውሎ ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።
♦️"በጣም ተፈታተነኝ፣በጣም ታገለኝ"የሚል አጭር ቃል የተነፈሠው ገዳይ
በግድያ ተጠርጥሮ በህግ ጥላ ስር የሚገኘው አትሌት ደረሠ ረታ ከግድያው በኋላ በተለይ ዛሬ ከሟች አትሌት ይሄይስ ታደለው የቀብር ስነ-ስርዓቱ ከተፈፀመ በኋላ የቅርብ ወዳጆቹ ለምን እንደዚህ አይነት ውሳኔ እንደወሠነ ጠይቀውት ከገጠመው ያልታሠበ ፈተና ውስጥ የወደቀው አትሌቱ በፀፀት ውስጥ ሆኖ "በጣም ተፈታተነኝ፣በጣም ታገለኝ"የሚል አጭር ቃል ከመናገር የዘለለ መተንፈስ እንዳልቻለ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ገልፀዋል።
♦️የአትሌት ይሄይስ ታደለው የመጨረሻ ስንብት
የአትሌት ይሄይስ ታደለው የቀብር ስነ-ስርዓቱና የአስከሬን ሽኝት ዛሬ ከቀኑ በ6:00 በሚኖሩበት ሠንዳፋ በኬ ማርያም ቤተክርስቲያን የአትሌቱ ቤተሠቦች፣ጓደኞች፣አሠልጣኞች፣አትሌቶችና የስፖርት ቤተሠቦች በተገኙበት በክብር አርፏል።በጉዳት ምክንያት ከአትሌቲክስ ርቆ ባለቤቱን በማሠራት የሚያሳልፈው አትሌት ይሄይስ ታደለው እንደዋዛ ይህቺን ዓለምና አትሌቲክሱንም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሠናብቷል።
♦️ለኢት.አ.ፌዴሬሽንና ለአትዮጵያ አትሌቶች ማህበር መልዕክት
የኢት.አ.ፌዴሬሽንና የአትዮጵያ አትሌቶች ማህበር እስከአሁን በአሳዛኙ ክስተት ዙሪያ የተነፈሱት ነገር አለመኖሩ ትዝብትን ፈጥሯል፤እንደ ሀገርም እንደ አትሌቲክሱ ዓለምም ትልቅ ስብራትና ልብ ሠባሪ አጋጣሚ ነው፤ሁለቱም አካላት በአትሌቶቹ መካከል የተፈጠረውን ግድያ ወደ ሌሎች እንዳይዛመትና በዚሁ እንዲያበቃ በይፋ በመግለጫ ጭምር ማውገዝና ማስተማር ይጠበቅባቸዋል።ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ምክንያቶች የጠፋውን ውዱን የሠው ልጅ ህይወት መለስ ብሎ ላስታወሠ በጎረቤት ኬንያ በጥይት አረር ህይወታቸው የተነጠቁ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና የአትሌቶች ህይወት እንደዋዛ መነጠቁን በትዝታ ፈረስ ወደኋላ ሄዶ ላስታወሠ ጉዳዩ ቢያሳስበው አይፈረድበትም፤ይሄ በአትሌቶች መካከል ያለውን የአጉል ባህልና ዕምነት፣የመጠራጠርና የመጠፋፋት ባህል እንደወረርሽኝ ተዛምቶ ለተጨማሪ አደጋ ከመጋለጣችን በአሠልጣኞችና በአትሌቶች አእምሮ ላይ ስራ ይሠራ።

በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት ለምርጫ ገለጸ
የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (CECOE / ኅብረት ለምርጫ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርቱ፣ በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ ከአንድ እስከ 10 የሚሆኑ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ገለጸ።
እንዲሁም በስምንት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሳይገኝ እና የመራጭነት ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ መፈቀዱንም ኅብረቱ በምርጫ ትዝብት ጊዜያዊ ሪፖርቱ ላይ አስታውቋል።
ኅብረቱ ከታዘባቸው 2,506 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ2,458 ጣቢያዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት የተከለከለ ሰው እንዳልነበር መታዘቡን ጠቅሷል፤ ይሁንና በ46 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ከ1 እስከ 10 ግለሰቦች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸው ተገልጿል።
በሁለት ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸውን የኅብረቱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የኢጋድና የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸውን ዛሬ ረፋድ በቀጥታ ስርጭት ለዓለም ይፋ አድርገዋል። የኢጋድና አፍሪካ ኅብረትን ታዛቢነት እውቅና እሰጣለሁ ያለው የአውሮፓ ኅብረትም አዲስ መግለጫ ይዞ ብቅ ብሏል። #ethiopia #generalelection #igad #au
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
2 months ago
በጋና "ባሕሩን እከፍላለሁ" በማለት የሙሴን ታሪክ ለመድገም የሞከረው ግለሰብ ለትዝብት ተዳረገ
ራሱን "ነቢይ" አድርጎ የሚጠራውና በተደጋጋሚ ስለ ዓለም ፍጻሜ ትንቢት በመናገር የሚታወቀው ኤቦ ኖህ (እውነተኛ ስሙ ኢቫንስ ኢሹን) የተባለ ጋናዊ፣ በባሕር ማዕበል ተመትቶ ሲወሰድ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ሰሞኑን በጋና የባሕር ዳርቻ ላይ የተከናወነው ይህ ክስተት፣ ግለሰቡ የነቢዩ ሙሴን ታሪክ በመምሰል ሁለቱን እጆቹን ወደ ባሕሩ ዘርግቶ "ባሕሩን ለመክፈል" ሲሞክር ያሳያል።
ሆኖም ግን፣ ሳይታሰብ የመጣ ከባድ ማዕበል ክፉኛ ከመታው በኋላ በውሃው ፍሰት ተገፍቶ ሲወሰድና ሊወድቅ ሲል በምስሉ ላይ ታይቷል።
ይህ የተቀረጸ ምስል በቲክቶክ እና ኤክስ ላይ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን፣ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን በትዝብት እየተመለከቱት ይገኛሉ።
ኖህ ከዚህ ቀደም "እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 25 ቀን 2025 ዓለም ትጠፋለች" የሚል ትንቢት ተናግሮ የነበረ ሲሆን፣ የጋና ባለሥልጣናትም የሕዝብ ሽብር በመፍጠር ወንጀል ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ስር አውለውት እንደነበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የምርጫ ትዝብት ሪፖርት
#fastmereja | የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ባወጣው የጠዋት የምርጫ ሂደት ሪፖርት መሠረት፣ 7ኛው አገራዊ ምርጫ በአብዛኞቹ ክልሎች በሰላማዊ እና በተደራጀ ሁኔታ መጀመሩ ተገልጿል። ይሁን እንጂ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ስጋት፣ የተኩስ ድምፅ እና የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት መከሰቱ ተመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በምርጫው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ 14,160 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን ሲከታተል ቆይቷል። የፌዴሬሽኑ ግኝቶች የሚያሳዩት ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
📌 የምርጫው አጀማመር እና ተሳትፎ፦ ምርጫው በ10 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ሳይገጥመው በሰላም ተጀምሯል። በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ተሳትፎ ከጠዋቱ ጀምሮ ከፍተኛ እንደነበር ታዛቢዎች ገልጸዋል።
📌 የአማራ ክልል ሁኔታ፦ በደብረ ታቦር፣ ደብረ ጎንደር እና አዊ ዞኖች የተኩስ ድምፅ መሰማቱ የተዘገበ ሲሆን፣ በክልሉ የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት መኖሩም ተነግሯል።
📌 የጣቢያ መክፈቻ መዘግየት፦ በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ እና አዲስ አበባ አንዳንድ ጣቢያዎች በሰዓቱ ባለመከፈታቸው የጥቂት ደቂቃዎች መዘግየት ታይቷል።
📌 የታዛቢዎች ስምሪት፦ ፌዴሬሽኑ 14,160 ታዛቢዎችን በማሰማራት የሴቶችን ደህንነትና የምርጫ ሂደቱን ቢከታተልም፣ በሎጂስቲክስ እና በተደራሽነት ችግር ምክንያት 22,788 የምርጫ ጣቢያዎች ያለ ታዛቢ ቀርተዋል።
📌 ምክረ ሃሳብ፦ ፌዴሬሽኑ በአማራ ክልል የፀጥታ ክትትል እንዲጠናከር፣ የጎደሉ የምርጫ ቁሳቁሶች በፍጥነት እንዲሟሉ እና ለሚቀጥሉት ሰዓታት ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ አቅርቧል።
ይህ ሪፖርት በኦሮሚያ እና በአዲስ አበባ ሴቶች ፌዴሬሽን የተሰበሰበውን መረጃ ጨምሮ እንደ ሀገር አቀፍ የፌዴሬሽኑ መረጃ ተቀናጅቶ የቀረበ ነው።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የቅድመ ምርጫ ትዝብትና የሴቶች ተሳትፎ ሪፖርት ይፋ አደረገ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ዙሪያ ሲያከናውን የቆየውን ሰፊ የቅድመ ምርጫ ትዝብትና የሴቶች ተሳትፎ የዳሰሰበትን አጠቃላይ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ እንደገለጸው፣ በምርጫው ሂደት የሴቶች መራጭነት ተሳትፎ ከፍተኛ ታሪካዊ ውጤት የታየበት ቢሆንም፣ በዕጩነት የመቅረብ እና የመወዳደር ምጣኔያቸው ግን አሁንም ሰፊ ክፍተት ያለበትና ትኩረት የሚሻ መሆኑን አመልክቷል።
በዚሁ ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት፣ በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገቡት 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 አጠቃላይ መራጮች ውስጥ 26 ሚሊዮን 667 ሺህ 132 ማለትም 49.3 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ታውቋል ።
ይህ ከፍተኛ የመራጭነት ቁጥር የታየ ቢሆንም፣ በዕጩነት ደረጃ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረቡት ሴቶች ግን 23.1 በመቶ ብቻ ሲሆኑ፣ ለአጠቃላይ ብሔራዊ ምክር ቤት ደግሞ የሴቶች ዕጩዎች ድርሻ 25.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ አኃዝ በሴቶች መራጭነትና ዕጩነት መካከል የ23.5 በመቶ ሰፊ የአሳታፊነት ልዩነት ወይም ክፍተት መኖሩን በግልጽ እንደሚያሳይ በሪፖርቱ ተመልክቷል።
የሴቶች ፌዴሬሽን የዜጎችን ንቃተ ህሊና ለማሳደግና መራጮችን ለማስተማር ሰፊ የቴክኖሎጂና የሚዲያ ዘመቻዎችን ማካሄዱን በዝርዝር አስረድቷል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ ስምምነት 255 ሚሊዮን የፅሁፍ መልዕክቶች በነፃ የተላኩ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ6 ቋንቋዎች የተዘጋጁ መልዕክቶች 42 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሴቶችና 87 ሚሊዮን ለሚሆኑ አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች መድረስ መቻላቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በኤፍ ኤም ሬዲዮና በቴሌግራም ቦት አማካኝነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የምርጫ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ባልተደጋገመ ስሌት ከ90 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ዘመቻውን መድረስ መቻሉ ተረጋግጧል።
ሂደቱን በታዛቢነት ከመከታተል አንፃርም ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉንና 5 ሺህ 432 ታዛቢዎችን ለማሰማራት አቅዶ እንደነበር አስታውቋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ 267 የረጅም ጊዜ ታዛቢ አሰልጣኞች በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ እነዚህ አሰልጣኞች በተራቸው 5 ሺህ 165 የሚሆኑ የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን በየደረጃው ማሰልጠን መቻላቸው በስራ አፈፃፀሙ ላይ ተገልጿል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ለቀጣይ ምርጫዎች መሻሻል የሚረዱ በርካታ የውሳኔ ሐሳቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች አቅርቧል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱን ይበልጥ እንዲያሻሽልና የታዛቢዎችን የገንዘብና የዕቃዎች አቅርቦት በወቅቱ እንዲያደርስ የጠየቀው ፌዴሬሽኑ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቢያንስ 30 በመቶ የሴቶች ዕጩ ተሳትፎን የሚያረጋግጥ ውስጣዊ ደንብ እንዲያወጡና የሴቶችን በራስ የመተማመን አቅም የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በፅኑ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

የ7ኛው ምርጫ የቅድመ ምርጫ ትዝብት ሪፖርት ይፋ ሆነ፤ በሴት መራጮችና ዕጩዎች መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩ ተጠቆመ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎን አስመልክቶ ያዘጋጀውን የቅድመ ምርጫ ትዝብት ሪፖርት ዛሬ ይፋ አደረገ። ፌዴሬሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በምርጫው ከተመዘገቡት አጠቃላይ መራጮች ውስጥ 49.3 በመቶው ሴቶች ቢሆኑም፣ በዕጩነት የቀረቡት ግን 25.8 በመቶ ብቻ መሆናቸውን በመጥቀስ በውሳኔ ሰጪነት ረገድ አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩን አስታውቋል። የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ገነት ስዩም እንደገለጹት፣ ይህንን ክፍተት ለመሙላት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያንስ 30 በመቶ የሴት ዕጩዎች ተሳትፎን የሚያረጋግጥ አስገዳጅ የውስጥ ደንብ ሊያወጡ ይገባል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎና የቅድመ ምርጫ ሂደቱን ለመታዘብ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። ፌዴሬሽኑ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ባካሄደው ሰፊ የኤስኤምኤስ (SMS) የንቅናቄ ዘመቻ 255 ሚሊዮን መልዕክቶችን በ6 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ በፋና ሬዲዮ በኩልም ከ32 ሚሊዮን በላይ መደበኛ አድማጮች ጋር መድረሱን በሪፖርቱ አመልክቷል። በተጨማሪም በቴሌግራም፣ በፌስቡክ እና በቲክቶክ ማህበራዊ ገጾች አማካኝነት የዲጂታል ሚዲያ ቅስቀሳዎች ተካሂደዋል። በምርጫ ሂደቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖር ለማስቻልም 267 የረጅም ጊዜ ታዛቢ አሰልጣኞችን በማሰማራት፣ ለ5,165 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎች ደረጃ በደረጃ ስልጠና ተሰጥቷል።
በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ያለውን የሴቶች ውክልና አስመልክቶ የወጣው የቁጥር መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የሴት ዕጩዎች ድርሻ 71.4 በመቶ በመድረስ ከፍተኛውን ቦታ ሲይዝ፣ በአንጻሩ በሲዳማ ክልል 40 በመቶ ሴት መራጮች ቢመዘገቡም የሴት ዕጩዎች ድርሻ ግን 8.2 በመቶ ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ሁኔታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ፓርቲዎች በቂ የሴት ዕጩዎችን በማቅረብ ረገድ ያጋጠማቸውን ድክመት እንደሚያሳይ ሪፖርቱ ይገልጻል።
በቅድመ ምርጫ ሂደቱ ወቅት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የታዩ የጸጥታ ስጋቶች ለመራጮችና ለዕጩዎች ዋነኛ ፈተና ሆነው ማለፋቸው ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም የሃሰት መረጃዎች ስርጭት፣ የኢንተርኔት ተደራሽነት ውስንነት፣ የባጀት እጥረትና መዘግየት በታዛቢዎች ስልጠናና ስምሪት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ በሪፖርቱ ተቀስሷል። ፌዴሬሽኑ ያጋጠሙ ችግሮችን መነሻ በማድረግ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሚመለከታቸው አካላት የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት እንዲሻሻልና ለታዛቢዎች የሚሆን በቂ በጀት በወቅቱ እንዲለቀቅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል።

ጥቂት ስለ ግጥምና ገጣምያን!
ደረጀ በላይነህ
ገጣሚና ሐያሲ
#ethiopia | ግጥም እንደ ቋንቋ ጥንታዊና ሁለንታዊና መግባቢያ ስለሆነ፣ጥንታውያኑ ተጠቅመውበታል፤ዘመናውያኑ ደግሞ ኮትኩተውታል ይላሉ-ፕሮፌሰር ሎረነስ ፐሪኔ።
ግጥም ከሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ተወዳጅና አክሊል የሚባለውም እንደ ጥንቅሽ እየተላጠ ተበልቶ ትዝታው ስለማይጠፋ፣የዋሽንቱ ዜማ ከልብ ስለማይገሠሥ ነው።
ዜማዊነቱ ለአይረሴነቱ ሰበብ ሲሆን፣ እምቅነቱ፣ምናባዊነቱ፣ተውኔታዊነት፣ቁጥብነት ወዘተ መለያ ባህርያቱ ናቸው።
ሌላው ብርቅ ከሚያሰኙት አንዱ ደግሞ አተያዩና ፍካሬው ነው። እንደ አልማዝ የተለያዩ ነጸብራቆች ስላሉት የዚያ ብርቅርቅታና ቀለም የገጣሚውን ምናብ ይለካዋል።
ግጥም ይፈላሰፋል፤ግን ፍልስፍና አይደለም። ገጠመኝን አሳምሮ፣በምናብ ወልውሎ ያመጣል እንጂ!
Its primary concern is not with beauty,not philosophical truth,not eith percuation,but with experience. ይላሉ።
ፊትን በመስታወት እንደማየት ይመስላል፤ ጥሬ ምስል አይደለም። ብዙ ቀለም በርካታ ቅርጾች አሉት። ምናልባትም በተሰባበረ መስተዋት እንደማየት ሊሆን ይችላል።.
በቅርጹም ወይ ተራኪ፣ተውኔታዊ፣አሊያም ሌሪክ ይሆንና እንደገና በየፈርጁ ይሸነሸናል።...በተለይ ስሜት ንክር፣ሙዚቃዊ የሆነው ሌሪክ የስሜት ዳንሶች ይዞ በሙሾ ሊያላዝን፣በፍቅር እስክስታ ሊመታ፣በትዝታ ቆርፍዶ እንባው በረዶ ሊሆን ይችላል።...እንጉርጉሮ ቢሆን፣ ጸሎትና ምሕላ፣ሽለላና ቀረርቶም እንደዚሁ።
ቃላት ለግጥም አንዱ መታበያው፣የቁመናው ጌጥ፣የመጋረጃው ዘርፍ ነው።...በተለይ ዘይቤያዊ ቃላት ደመና ላይ ሰቅለው ቼ! በለው የሚሉበት የከፍታው ጉልላት ነው።
ቃላቱንም እማሬያዊና ፍካሬያዊ ብለን ብንለያቸው፣በአብዛኛው ከዘወትራዊው ይልቅ በተምሳሌታዊና አምሳያዊ ትዕምርቶች በወደድነው ሥፍራ ብንዶላቸው ጣማቸው ይጨምራል።
ወይም ስሜት የነሸጠውን ያየንበት ትዝብት ውል ሲልብን፣እንደ መንግሥቱ ለማ፦
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ እንደክዋክብት
"ሳማት ሳማት"አሉት"ዕቀፍ ዕቀፋት"
አላወላወለም፤ወጣቱ ታዘዘ፤
ወገቧን አንገቷን፤በእጅና እጁ ያዘ፤
ከንፈሩ በረአድ ወዳፏ ተጠጋ።
-ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የበረዶ አለንጋ፤
ጆሮግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
በጠራው ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን ፤ዋ ተማሪነት፣
ዋ ትዕዛዝ መፈጸም፣ዋ ምክር መስማት።
እንግዲህ ተራኪው ግጥም እንዲህ ያለ መልዕክት፣ሲያስላልፍ ሥዕሉ ደምቋል። ጣቶቿ አለንጋ፤ጡቶቿ ሹል፣ሲል የልጅቷ ዕድሜ ከውስጥ ፤ቁመናው ከላይ ይታዩናል። ከዚህም አልፎ ደግሞ የምንበረብረው ሳጥን አለ። ከንፈሩ ለምን ቀዘቀዘ?...ፈርቷል። የፈራው ለምንድነው?...ልጅቷ እንዳትቆጣ!...ያኔ በዘመኑ ዐውድ ልጃገረ በእጅ መንካት ሽጉጥ ያስመዝዛል። ግን ተማሪ ጓደኞቹ አሳሳቱትና ጥፊ ቀመሰ።ቅምሻ ብቻ አይደለም ተናጋ። ሲናጋ ድምፅ አለው።
እዚህ ጋ ምሰላ ይመጣል- ድምፅ፣እላይ አጎጠጎጤ- ምስል፤ዐይኖችዋ መጉላት-ዕይታ።
ግጥም እንዲህና እንዲያ ነው። ሙዚቃው ያግባባል፤ሐሳቡ ሆድ ይገባል።
ግጥም የየዘመኑን ዳና ያስቀራል ስንል፥ ፖለቲካው፣ሥነ ልቦናው፣ፍልስፍናው ባሕሉ ወዘተ ቀለሙ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የረሃብ ይሆን ጥጋብ፤የጸብ ይሁን ፍቅር የትውልዱን ትዝብት፣ የነውጡን ንፋስ ፈትል ሰማይ ላይ ረጭቶ፣ የትካዜው ፉጨት፣የሳቁን ዜማ፣የትዝታውን ጥላ፤ ሻካራና እሾሁን፣ ሕመምና ጥዝጣዜውን፣ሳቅና ፍካቱን፣...
የአማርኛ ግጥሞች ዕድሜ ብዙ ሩቅ አይደለም።በዚያ ላይ አዳዲስ ፈርጆችን ይዞ አላስደነቀም። ከፖለቲካው ሥርዐትና ርዕዮት ጋር የቀየረው ቅርጽ የለም።ርዕዮቶችን በአንቀልባ እያዘሉ ከማውረድ የተለየ ሚናም አልነበረው። እንደ ፈረንጆቹ፣ወይም እንደላቲኖቹ፣ካልሆነም እንደመካከለኛ ምሥራቋ እሰራኤል የቤት ዐመታት ላይ የመጣው ለውጥ አልተመዘገበም።
ዘውጉን ሳይለቅ የቁመና ለውጥ ያመጣው ባለፉት አርባ ዐመታት ይመስለኛል። ያም ከፖለቲካዊና አገዛዛዊ ሸምቀቆ ጋር ተያይዞ የመጣ መጉበጥ ይመስላል።
አጫጭር ግጥሞች መብዛታቸውም፣የመታከት፣ብዙ ለመተንተን ሰሚ በማጣት የተፈጠረ መሰልቸት ይመስላል፤ዝም ብሎ ለመተንፈስ ብቻ። ቢጨንቀውና ሰሚ ቢያጣ መሬት ቆፍሮ ለመሬት እንዳወራው ሰው ዓይነት።
በዚሁ ተመሳሳይ ዘመን ሌላም ነገር ታይቷል። በግጥሙ መዝጊያ ላይ አንድ መገረሚያ ማምጣት። ትንሽ ቆይቶም፣
የአዳራሽ ግጥሞች በሙዚቃ እየታጀቡ መቅረብ መጀመራቸው ዘለግ ያሉና መድረክ ላይ የሚያቆዩትን አመጣ። እነዚህ የተንዛዙ ግጥሞችን ወደ ኅትመት ሰፈር ሲመጡ ዘልዛላ ሆኑ።
የመጀመሪያ መጻሕፍታቸው ያማሩላቸው ገጣምያን ሳይቀሩ ግጥሞቻቸው ለዛቸውንና እምቅነታቸውን ነጠቋቸው።
ከዚህ ዘመን ገጣምያን አንዷ ሜሮን ጌትነት ነበረች። ሜሮን ነገሮችን የምታይበትና የምትፈትልበት መንገድ ግሩም ነው። "ዙረት" በሚለው የግጥም መጽሐፏ አንገት በሚያስነቀንቁ፣ልብ በሚንጡ ግጥሞቿ አስመሰከረች።
መድረኮች ላይ ስትወጣ ግን፣እንደነምሥራቅ፣እንደነ ዶክተር በድሉ፣አረዘመቻቸው። ከነርዝመቱ ለዛውን ጠብቆ የሚሄደው አሳየኸኝ ረጋሳ ይመስለኛል። ትዕግሥት ማሞም አንዳች የማይረግብ ገሞራ አላት።
በግጥም ኅትመት ዓለም ብዙዎቹ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውና ቀጣዮቹ እኩል አይደምቁም። ስስነትና እርግበት ይታይባቸዋል። በዚህ ፈተና ያልወደቀው ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ ነው፤የእነ ደበበ ሰይፉን ደጅ እያንኳኳ ይመስላል።እነ አበረ አያሌው ገና አልተፈተኑም። ትዕግሥት ዓለምነህም ወደፊት በመጀመሪያ ግጥሟ ልክ ከመጣች፣ተዐምር ነው።ቋንቋ፣አተያይዋና Allusion አጠቃቀሟ ድንቅ ነው።
ወደ ሜሮን አዲሱ መጽሐፍ ልምጣ ። ስሜት የሚያሞቁት ከበሮ ድብደባዎች፣በቀጭን የሚመጡት ሳቆቿ ፣አንገት የሚያወዛውዙት ግርምቶች፣በአጫጭር ግጥሞቿ የምታደርጋቸው ተዐምራት የቀነሱ ይመስላል።
ቆንጆ ግጥሞች አሏት?...አዎ። ግን እንደድሮ አይደሉም። አዳዲስ ውበቶችና የቃላት ውበት ጨምራለች።
ግጥሞቿ፣ይስበኩን አይባልም። poetry does not teach:but it inspires.ይላሉ የዘርፉ ሰዎች።...ለነገሩ በዚህ የሚያምኑት ሊቃውንት በርካታ ናቸው።
እስቲ ከሜሮን ልምዘዝ፦
መተላለፍ 2
ሐቀኛ ነጋዴ በአመድ ገበያ ላይ ዱቄት ይዟል ማልዶ፣
የታይታ ሀብታም ሰው በሥጋ ወረፋ ይሰለፋል ማዶ።
ዘመን ሰውነትን ሸቀጥ አርጎ አውጥቶ ዐየን እንደዋዛ፣
የወረቀት ገንዘብ ወርቅ ሕልም እየገዛ።
ይህ ግጥሟ ሐሳቡ ብቻ ሳይሆን የቤት መምቻው ድምፅ ደማቅ ነው። ይህን ያደረጉት አናባቢዎቿ ናቸው። ሐሳቡም ግዙፍና የነፋሱን ዘመን በእፍኝ የሰፈረ ነው። ወርቅ ሕልም ፣በወረቀት እየሸጠ፤ዕንቁ በእሪያዎች ፊት እየተጣለ።
ልበ...
የአንተም ልብ ድንጋይ...
የእኔም ልብ ድንጋይ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ)
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።
ግጥም ሙዚቃ፣ ሥዕልም የተካተቱበት የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ሰለሆነ፣ነፍስ ያፍነከንካል ፤ትርዒት ያሳያል።
ጋሽ ጸጋዬ በዘይቤዎቹ መዐዛ፣ በምሰላዎቹ ምትሐት ቀልብ ሲስብ፣ ገብረክርስቶስ በሜሎዲዎቹ ብብት ይኮረኩራል። ደበበ ሐሳብ እንደሽንኩርት እየላጠ ያስደምማል። ሁሉም በየራሳቸው ድንኳን የሚሰጡን ጣ'ም አለ።
ላምቦርን("ዶ/ር)ስለዚህ ሲጽፉ፦ Since every one likes pictures and most find pleasure in music,the common indifference to poetry must be due to a failure to realize that poetry is really both.

3 months ago
ከቤተ-መንግሥት ወደ ስብከት መድረክ
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሽግግር እንቆቅልሽ
የአንድ አገር መሪ ከስልጣን ሲወርድ የሚመርጠው መንገድ የራሱን የነበረውን ማንነት የወደፊት እጣ ፈንታውን እና የህዝቡን የታሪክ ትውስታ ይወሰናል። በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ በማስገባት የመጀመሪያው መሪ በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ያ ውሳኔ በወቅቱ ለነበረው ህዝባዊ አመፅና ውጥረት የተወሰነ መተንፈሻ የሰጠ በጎ እርምጃ ተደርጎ ቢወሰድም ከስልጣን በኋላ የመረጡት የሕይወት መስመር ግን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄና ትዝብትን እያስከተለ ይገኛል።
በተለይም በቅርብ ጊዜያት በመድረኮች ላይ እንደ ወንጌል ሰባኪና የሃይማኖት መምህር ሆነው መታየታቸው ፖለቲካው በፈጠረው ቁስል ላይ የወንጌል ፈውስ ወይስ የታሪክ ሽሽት? የሚል ጠንከር ያለ ክርክር አስነስቷል።
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩባቸው ዓመታት (ከ2005 እስከ 2010 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የዜጎች መፈናቀልና የብዙ ወጣቶች ህይወት የጠፋባቸው ከባድ ዓመታት ነበሩ። ምንም እንኳን ውሳኔዎች በጋራና በፓርቲ (ኢህአዴግ) መዋቅር ይሰጡ የነበረ ቢሆንም እርሳቸው የአገሪቱ የመጨረሻው የሥልጣን ማማና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው መጠን በዚያ ዘመን ለደረሰው መከራና የደም መፋሰስ ቀጥተኛ የታሪክና የሞራል ተጠያቂነት አለባቸው።
ህዝብ በበደልና በደምና በደመ ነፍስ የታለፉ ቁስሎችን በቀላሉ አይረሳም። በጥይት የተመቱ ወጣቶች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች፣ የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ትውስታ ዛሬም ትኩስ ነው። ስለሆነም ያንን ሁሉ መከራ ያስተናገደ ህዝብ በወቅቱ የነበረው መሪ በአንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ በመድረክ ላይ ሲሰብክ ሲያይ መገረሙ መጠራጠሩና መቆጣቱ ሰብአዊና አመክንዮአዊ ምላሽ ነው።
በክርስትና እምነት (በተለይም አቶ ኃይለማርያም በሚከተሉት የሃዋርያት እምነት መሠረት) ማንኛውም ሰው በማንኛውም ጊዜ ንስሐ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የመመለስና የማገልገል መብት አለው። ይሁን እንጂ የወንጌል መሠረታዊ አስተምህሮ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ብቻ ሳይሆን ከበደሉት ሰውና ማህበረሰብ ጋር መታረቅንም ይጨምራል።
"እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ ከዚያም መጥተህ መባህን አቅርብ።" (ማቴዎስ 5:23-24)
የአቶ ኃይለማርያም ወደ ወንጌል አገልግሎት መግባት ትልቅ ጥያቄ የሚነሳበት እዚህ ጋ ነው። በመሪነታቸው ዘመን ለተፈጠሩት ስህተቶች፣ ለጠፋው ሕይወትና ለፈሰሰው ደም የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ፣ በግልጽና በስም ጠርተው ይቅርታ ጠይቀዋል ወይ? ጥፋቱን አምኖ ንስሐ መግባት፣ የተበደሉትን መካስና ይቅርታ መለመን የወንጌል ስብከት መነሻ እንጂ መድረሻ ሊሆን አይገባም ነበር?
እነዚህ ጥያቄዎች ሳይመለሱ በቀጥታ ወደ መድረክ ወጥቶ መስበክ ለብዙዎች ታሪኬ ተረስቶልኛል ከሚል ግምት ወይም የህዝብን ቁስል ካለማክበር የመነጨ ሊያስመስለው ይችላል።
በሌላ በኩል የአቶ ኃይለማርያምን ወገን የሚከላከሉ ሰዎች እርሳቸውም ቢሆኑ የራሳቸው የህሊና ጉዞ እንዳላቸው ይከራከራሉ። ስልጣን በገዛ ፈቃድ መልቀቅ ራሱ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ የመጸጸትና ለውጥ የመሻት መግለጫ እንደነበር የሃይማኖት አገልግሎታቸውም የዚሁ የውስጥ ለውጥና ሰላምን የመፈለግ ጉዞ አካል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
በተጨማሪምከፖለቲካው ዓለም ሙሉ በሙሉ ርቀው በግል ሕይወታቸውና እምነታቸው ላይ ማተኮራቸው መብታቸው እንደሆነ ይነገራል።
ነገር ግን ግለሰቡ ተራ ዜጋ ሳይሆኑ የአገር መሪ ነበሩ።
የአገር መሪ የህዝብ ሃብት ነው ታሪኩም፣ ውሳኔውም፣ ከስልጣን በኋላ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ሁሉ በህዝብ መነጽር መቃኘቱ አይቀሬ ነው።
የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የወንጌል ሰባኪነት ጉዞ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አሁንም የተደበላለቀ ስሜት ይፈጥራል። በአንድ በኩል የሰው ልጅ መለወጥና ወደ እምነቱ መመለስ የሚደገፍ ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ያለ ይፋዊ ይቅርታና የፖለቲካ ተጠያቂነት ወደ መንፈሳዊ መድረክ መሻገር የህዝብን ቁስል የሚነካ ሆኖ ተገኝቷል።
እውነተኛ የወንጌል አገልግሎት የሚጀምረው ከእውነትና ከፍትህ ነው። አቶ ኃይለማርያም ካለፈው ታሪካቸው ጋር በግልጽ ተጋፍጠው ለደረሰው ጥፋት የድርሻቸውን ሃላፊነት ወስደው ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታን እስካላወረዱ ድረስ ስብከታቸው ምንም ያህል ጥራዝ ቢኖረው በብዙሃኑ ዘንድ ካለፈው ታሪክ የመሸሻ ጥላ ተደርጎ መታሰቡ አይቀሬ ነው።
ታሪክ አይረሳም የህዝብ እምባም ዝም ብሎ አይታለፍም።
Via Henock Megerssa

ከ88 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አለመሆናቸውን አንድ ሪፖርት አመለከተ
በኢትዮጵያ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ትዝብት ካደረጉባቸው ጣቢያዎች መካከል 88 በመቶ የሚሆኑት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አለመሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ ባካሄደው ጉብኝት ማረጋገጡን አስታውቋል።
ሕብረቱ በ4 ሺህ 396 የምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው ቅኝት የደረሰበትን ድምዳሜ ሪፖርት አድርጓል፡፡ በሪፖርቱ፡- ምዝገባው ከተከናወነባቸው ስፍራዎች መካከል በሕግ ከተፈቀደው ውጭ በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በሃይማኖታዊ ተቋማት እና በመጠጥ ቤቶች የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ማረጋገጡን ገልጾአል።
የሕብረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ኃይለማርያም ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ የምዝገባ ጣቢያዎች በተገቢው ስፍራ ቢቋቋሙም፣ ሕጉን ባልተከተለ መልኩ የተመሰረቱ ውስን ጣቢያዎች መኖራቸውን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ ጣቢያዎቹ ለአካል ጉዳተኞችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በሚመች መልኩ አለመዘጋጀታቸውን በጥናት ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
የምዝገባ ሂደቱ በአብዛኛው መልካም መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ 87 በመቶዎቹ ጣቢያዎች የመራጮችን ማንነት በአግባቡ በመለየት ቢመዘግቡም፣ ቀሪዎቹ 13 በመቶዎቹ ግን መመሪያውን ሳይከተሉ መመዝገባቸውን አስረድተዋል። በተጨማሪም በጥቂት ስፍራዎች ላይ ሰዎች በአካል ሳይገኙ ምዝገባ መከናወኑን ህብረቱ በትዝብቱ ማረጋገጡን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል አሐዱ የሕግ ጥሰት በተፈጸመባቸው ጣቢያዎች ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ሰብሳቢዋ በሰጡት ምላሽ ቦርዱ የሕግ ጥሰት ተገኝቶባቸዋል ባላቸው በ5 ክልሎች በሚገኙ 23 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የእግድ እርምጃ መውሰዱን መግለጻቸው ይታወሳል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የመራጮች ምዝገባ ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ሂደቱም ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ተራዝሞ ቆይቷል። ቦርዱ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፤ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን አስታውቋል።
አሐዱ ሬዲዮ

4 months ago
"ነዳጅ ሳያነደን ምን እናድርግ?"
- የረዳት ፕ/ር ነቢዩ ባዬ የጠዋት ትዝብት 🤔
#ethiopia | አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው ረዳት ፕ/ር ነቢዩ ባዬ፣ በዛሬው የጠዋት ጉዞው የታዘበውንና ሁላችንንም ሊሞግት የሚገባውን ቁምነገር እንዲህ አጋርቶናል።
የትዝብቱ ዋና ነጥቦች፦
ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ባስተዋላቸው መኪኖች ውስጥ ወደ 70 በመቶ የሚሆኑት አሽከርካሪዎች ብቻቸውን የሚጓዙ ናቸው።
በመንገድ ዳር በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች፣ እናቶችና አረጋውያን በሰልፍ እየተሰቃዩ ባለበት ሁኔታ፣ ቢያንስ አራት ሰው ማሳፈር የሚችሉ መኪኖች ባዶ መሄዳቸው ለምን ይሆን?
መረዳዳት በባህላቸው የለም የምንላቸው ሀገራት እንኳን "የመኪና ክለብ" (Car Club) መስርተው ተሽከርካሪን የመጋራት ልምድ ሲኖራቸው፣ እኛ ለምን ከወገናችን ራቅን?
ረዳት ፕ/ር ነቢዩ ራሱን በመውቀስ "ቢያንስ ከምኖርበት የጋራ መኖሪያ ተሽከርካሪ የሚቸገሩ ጓደኞቼን አፈላልጌ በጋራ ለመገልገል እሞክራለሁ" ይላል።
ይህ ተግባር የነዳጅ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ፣ የመወዳጀት ዕድልን ያስፋፋል፤ ለፈጣሪም ተወዳጅ ተግባር ነው።
#getu #nebiyubaye #carpoolingaddis #socialresponsibility #ethiopiatransport #addisababalife #kindnessmatters #ethiosociety #መኪናመጋራት #ነብዩባዬ #ትዝብት #አዲስአበባ #ሰብአዊነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

በዝርፊያ ወቅት ገንዘብ ያጣው ሌባ ያስቀመጠው አስገራሚ መልዕክት
#ethiopia | በህንድ ማድያ ፕራዴሽ ግዛት ውስጥ በአንድ የመንግስት ባለስልጣን መኖሪያ ቤት የተፈጸመ አንድ ለየት ያለ የሌባ ድርጊት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ለዝርፊያ ወደ ባለስልጣኑ መኖሪያ ቤት የገባው ግለሰብ፣ በቤቱ ውስጥ ሊሰርቀው የሚችል በቂ ገንዘብም ሆነ ውድ ንብረት በማጣቱ ከፍተኛ ብስጭት አድሮበታል። ሌባው በባዶ እጁ ከመውጣት ይልቅ፣ ለቤቱ ባለቤት ያለውን ንዴት የሚገልጽ አጭር መልዕክት ትቶ ወጥቷል።
ሌባው በወረቀት ላይ አስፍሮት የሄደው መልዕክት፦ "ገንዘብ ከሌለህ ለምን ቁልፍ ትቆልፋለህ?" የሚል ነበር።
ይህ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተከሰተ ድርጊት ቢሆንም፣ የሌባው ድፍረት እና የትዝብት መልዕክት አሁንም ድረስ በአስገራሚነቱ ይጠቀሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ፊደልፖስት #indianews #madhyapradesh #unusualnews #crimestories #strangeencounter #funnynews

5 months ago
📱 የሶሻል ሚዲያ ጉድ፦ የፊልተር መላቀቅ 150 ሺህ ተከታዮችን አሳጣ!
በኦንላይን አለም የምናየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም ለሚለው ንግግር ማረጋገጫ የሚሆን አንድ አስገራሚ ክስተት በቻይና ተከስቷል።
ምን ተፈጠረ?
አንዲት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏት ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ "Influencer" በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) ላይ ሳለች፣ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ትጠቀምበት የነበረው የውበት ማሳመሪያ ፊልተር (Beauty Filter) በድንገት ይላቀቃል።
ውጤቱ፦
ለ4 ሰከንድ ብቻ በቆየው በዚህ ክስተት፣ እውነተኛ መልኳ በማያ ገጹ ላይ የታየው ተመልካቾች በድንጋጤ ተሞልተዋል።
ከእውነተኛ ማንነቷ መጋለጥ በኋላ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ150,000 በላይ ተከታዮቿ "Unfollow" በማድረግ ፊታቸውን አዙረውባታል።
ትዝብት፦
ይህ ክስተት በዲጂታል አለም ያለውን የውሸት ውበት እና የማንነት ቀውስ በድጋሚ መነጋገሪያ አድርጎታል። ብዙዎች "በፊልተር የታጀበ ውበት እምነትን ያጠፋል" በሚል አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
📌 የእናንተስ አስተያየት ምንድነው? በሶሻል ሚዲያ የምናያቸውን ሰዎች ውበት ምን ያህል እናምናለን?
seledadotio

የኤልያስ መልካ የነፍስ ስቃይ ፦ በአልጋ ህመም ላይ የተፃፈው "ወይ ልምጣ ወይ ምጣ..."
ይህን ግጥም በዜማ የዘፈነችው መሰሉ ፋንታሁን ዘፈኑ በሞት አፋፋ ላይ ያለ ሰው ትዝብት እና ጩኸት መሆኑን ባለመረዳት እንደ ሌላ ባህላዊ ዘፈን ክሊፑን በእስክስታ ሰርታዋለች።
ኤልያስ አልጋ ላይ በህመም ሳለ እያለ የፃፈውን ይሄ ግጥም የሚጀምረው "አገሩና ደጄ ሩቅ እየመሰለኝ፣ እንደ ወፍ እንግዳ እያብሰለሰሉኝ" በሚል ጥልቅ ህመም ነው። በዚህ በዙሪያው ያለው ዓለም ለእሱ እውነት መሆኑ ቀርቶ እንደ ህልም ወይም እንደ ሩቅ ምስል መታየት አንደጀመረ መረዳት እንችላለን።
"ደጄ ሩቅ መሰለኝ" የሚለው ሐረግ፣ ኤልያስ ከቤቱ፣ ከማህበረሰቡ እና ከሚወደው ሙያ ጋር የነበረው ትስስር መበጠሱን ያሳያል። "እንደ ወፍ እንግዳ" መሆኑ የብቸኝነት ስቃዩን ያሳያል።
አንድ ታማሚ የጤነኞችን ዓለም ሲመለከት ራሱን እንደ ባዕድ ይቆጥራል። ይህ ስሜት በአእምሮ ውስጥ ከፍተኛ የባዶነት እና የትርጉም ማጣት ስሜት ይፈጥራል።
"ወይ ልምጣ ወይ ምጣ... ከሆንክ የኔ እጣ፣ በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ?" እነዚህ ስንኞች እጅግ አስለቃሽ የሚሆኑት፣ በውስጣቸው የያዙት የተስፋ መቁረጥ ጥልቀት ነው። ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቀጥተኛ ሙከራ ባያደርግም፣ ሞት መጥቶ ቢወስደው ግን በደስታ እንደሚቀበለው ይገልጻል። "ወይ ልምጣ ወይ ምጣ" የሚለው ቃል "ስቃዩ ካልቆመ ህይወቴ ይቁም" የሚል የነፍስ ጩኸት ነው።
"በምን ጥፋቴ ነው?" የሚለው ጥያቄ ደግሞ ታማሚው ለደረሰበት ስቃይ ምክንያት ፍለጋ ሲባዝን የሚፈጠር የጥፋተኝነት ስሜት ነው። ሳይኪያትሪስቶች እንደሚሉት፣ ሰዎች ለስቃያቸው ምክንያት ካላገኙ አእምሮአቸው በከፍተኛ ጭንቀት ይወጠራል። ኤልያስ በህመሙ ውስጥ ፍትህን እየፈለገ ነበር፣ ነገር ግን ያገኘው ዝምታን ብቻ ነው።
ኤልያስ በሚያሳዝን ድምፅ "አለ ጋደም ጋደም ሰው ሁሉ ሊተኛ... እኔ ቁጭ ብያለሁ ያንተ በሽተኛ" ሲል በእንቅልፍ ማጣት እና እየተሰቃየ መሆኑን እንረዳለን። ኤልያስ የሚገልጸው ሁኔታ "ሰው ሁሉ ሲተኛ እኔ አልተኛሁም" የሚል ነው። ሌሊት ለታማሚ ሰው ረጅም እና አስፈሪ ነው። በዙሪያው ያሉት ሰዎች ሲተኙ፣ እሱ ከህመሙ ጋር ፊት ለፊት ይጋጠማል።
ሌላው ሰው እረፍት ሲያደርግ፣ ኤልያስ ግን "ያንተ በሽተኛ" በማለት ስቃዩን ከአምላኩ ጋር ብቻውን እየተጋፈጠ ነው። ይህ የሌሊት ንቅቃት ለአእምሮ ጤና እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ ምክንያቱም በዚያ ሰዓት አፍራሽ ሀሳቦች በከፍተኛ ሁኔታ ይገነፍላሉ።
ውዱ የሙዚቃ ሰው "ዘመዶቼም ጠሉኝ እኔም ጠላኋቸው... ያጣ ሰው አያገኝ እየመሰላቸው" ሲል የደረሰበትን ማህበራዊ መገለል ይገልጻል። በሳይንስ እንደሚታወቀው፣ ለታማሚ ሰው ፈጣን ማገገሚያው ማህበራዊ ድጋፍ ነው። ኤልያስ ግን ዘመዶቹ "ተስፋ እንደቆረጡበት" ተረድቷል።
"ያጣ ሰው አያገኝ እየመሰላቸው" የሚለው መስመር ሰዎች በታማሚው ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ይገልጻል። ይህ ሲሆን ታማሚው በምላሹ "እኔም ጠላኋቸው" የሚል መከላከያ ይፈጥራል። ይህ ግን የጥላቻ ሳይሆን የከፍተኛ ጉዳት ውጤት ነው። አንድ ሰው በህመም አልጋ ላይ ሆኖ የቅርብ ሰዎቹን "ጠላኋቸው" ሲል፣ በውስጡ ያለውን የመንፈስ ስብራት ማሰብ ይከብዳል።
"እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር... በል በርታ ልቤ ጨከን በል፣ ሲመጣ ይመጣል እውነቱን ተቀበል" የሚለው የዘፈኑ የግጥም ክፍል ላይ ሞትን "እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር" ማለቱ ከህይወት ጋር ያለውን ትግል አቁሞ ለፍጻሜው መዘጋጀቱን ያሳያል።
ሆኖም በውስጡ "በል በርታ" በማለት ራሱን ለማጠንከር የሚሞክርበት መስመር ደግሞ የሰው ልጅ የመኖር ፍላጎት እስከ መጨረሻው እንደማይጠፋ ያሳያል። ይህ በመሞት ፍላጎት እና በመኖር ተስፋ መካከል የሚደረግ የነፍስ መወዛወዝ ነው።
ኤልያስ የሞተው በህመም ብቻ አይደለም፤ ስቃዩን ማንም ሊረዳለት ባለመቻሉ በሚፈጠር የነፍስ ብቸኝነት ጭምር ነው።

6 months ago
የክብር ቀብር፦ በታምራት ደስታ "ከአንቺ አይበልጥም" ውስጥ በፍቅር ሰንሰለት የታሰረው የነፍስ ጩኸት
ለዚህ ዘፈን መነሻ ነው የተባለ ታሪክ ነው። ከሆነ አመት በፊት አንዲህ ሆነ። በአዲስ አበባ የሰው ድምፅ በሚበዛባቸው ምግብ ቤቶች መካከል አንድ የምግብና መጠጥ ቤት ባለቤት የሆነ ሰው፣ ሕይወቱንና ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ክብሩንም ለሚስቱ አሳልፎ ሰጥቷል። ሚስቱ በሰው ፊት ስትጎነተል፣ ከሌሎች ጋር ስትላፋና እንዲያውም "እንሶላ ትጋፈፋለች" ተብሎ በሚወራበት ሁኔታ ውስጥ፣ እሱ ግን ምርጫው ሆዱ እያረረ ዝምታ ሆነ።
አንድ ቀን ሆድ ሲከፋው ተጣላት ። ግን ፍቅሯ አገረሸብኝ ብሎ በሽማግሌ ቢመልሳትም፣ ድርጊቷ አልታረመም። በመጨረሻም ይህ ሰው "ካንቺ አይበልጥም ክብሬ" ብሎ ራሱን ለውርደት አሳልፎ ሰጠ።
ይህ ዝምታ ግን የትዕግስት ሳይሆን፣ የማንነት መፈራረስ ምልክት ነው። ታምራት ደስታ በዜማው እንዳቀነቀነው፣ ይህ ሰው ክብሩን እንደ አሮጌ ልብስ አውልቆ ጥሏል። ለምን? ምክንያቱም ከብቸኝነት ይልቅ ውርደት ይቀልለዋልና። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ፍርሃት "ብቻን መቅረት" ነው። ይህ ባል ሚስቱን ለብቻው ሳይሆን ከህዝብ ጋር ይጋራታል።
እሷ በሰው ፊት ክብሩን ስትገፈው፣ እሱ ግን ውስጡ እያረረ "ይሁን" ይላል። ይህ ውሳኔ ከፍቅር የሚመነጭ ሳይሆን፣ ራስን ካለመቀበል የሚመጣ የባርነት ጽዋ ነው። ራሱን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ቁስ (Object) እየቆጠረ፣ የሰዎችን ትዝብትና ንቃትን ዋጥ አድርጎ ለመኖር መወሰኑ፣ የሰብአዊነቱ ማብቂያ ደወል ነው።
ፈላስፎች "ገሃነም ማለት ሌሎች ሰዎች ናቸው" ይላሉ። ለዚህ ባል ግን፣ ገሃነም የሚስቱ መሄድ እንጂ የሰዎች ትዝብት አይደለም። በሰው ፊት ስትላፋ፣ ሌላው ሲዳብሳት እያየ "ክብሬን ተውት" አለ።
ለእሱ ገሃነም የሚጀምረው እሷ የቤትዋን በር ዘግታ ስትወጣ ነው። የሰዎች አይን እንደ ሾህ ቢወጋውም፣ የእሷ አለመኖር ግን እንደ ሞት ይከብደዋል። "ካንቺ አይበልጥም" የሚለው ቃል፣ የፍቅር መገለጫ ሳይሆን የነፍስ ባርነት መግለጫ ነው። ነፃነት የሌለው ፍቅር ደግሞ ፍቅር ሳይሆን እስራት ነው።
እዚህ ጋር ፍቅረኛው ወህኒ ቤት ሆናለች፣ እሱ ደግሞ በገዛ ፈቃዱ ቁልፉን የዋጠ ዘበኛ ነው።
የናይጄሪያው ደራሲ ቺኑዋ አቼቤ በታላቅ ስራው Things Fall Apart ላይ፣ ወንድ ልጅ ክብሩ ሲነካ የሚሰማውን መርዶ ይገልጻል። በዚህ ግጥም ውስጥ ግን "ነገሮች አልተበተኑም" ። ይልቁንም በውርደት ውስጥ ተለጥፈው እንዲቆዩ ተደርጓል።
ባለታሪኩ የባህልን አጥር ሰብሮ፣ የወንድነትን ካባ አውልቆ፣ በባዶነቱ ፊት ቆሟል። "የት አባቱ ክብሬ" ሲል፣ የዘመናት ባህልንና የቤተሰብን ስም አቃጥሎ አመዱን ለንፋስ ሰጥቶታል።
አቼቤ እንደሚለው ባህል ሲፈርስ ህዝብ ይበተናል፤ እዚህ ግን ግለሰቡ ሲፈርስ ክብሩ ይበተናል። ይህ ሰው የቆመው በባዶ መሬት ላይ ሳይሆን፣ በራሱ ማንነት ፍርስራሽ ላይ ነው።
ግጥሙ "የማየውና የምሰማው ክብሬን ይነካኛል" በማለት ይጀምራል። ይህ ማለት ሰውየው ድንዛዜ ውስጥ አይደለም፤ ህመሙ ይሰማዋል። የሚስቱ እጅ በሌላ ሰው ትከሻ ላይ ሲያርፍ፣ ልቡ እንደ መስታወት እንደሚሰበር ያውቃል። ነገር ግን ሰባሪዋን ሴት ከመጥላት ይልቅ፣ የተሰበረውን ማንነቱን ይዞ ሊለምናት ይመርጣል።
ይህ አስለቃሽ እውነት ነው—አንድ ሰው ራሱን ማክበር ሲያቅተው፣ የሚሰጠው ፍቅር ሁሉ የውርደት ውጤት ይሆናል። ሕመሙን እያወቀው ወደ ሕመሙ መሮጥ፣ የሥነ-ልቦና ራስን የማጥፋት ተግባር ነው።
እያንዳንዱ ስንኝ የልብ ትርታ ሳይሆን የቁስል አቃቂር ነው።
ይህ ባል የቆሰለ ትዳሩን በውርደት ተሸክሞ በየቀኑ ወደ ምግብ ቤቱ ይሄዳል። ሚስቱ ስታዋርደው ድንጋዩ ይንከባለላል፤ እሱ ግን ደግሞ "ካንቺ አይበልጥም" እያለ ድንጋዩን ለመጫን ይሮጣል።
ይህ ትርጉም አልባ ህይወት በኢትዮጵያዊው ይሉኝታ ውስጥ ሲያልፍ፣ ታሪኩን እጅግ መራራ ያደርገዋል። የዚህ ሰው ድንጋይ የሚወደው ሰው ክህደት ነው። በየቀኑ የሚደገም ውርደት፣ በየቀኑ የሚታደስ መሸነፍ።
"ፈጣሪዬ አቅሜን ያውቃል ላልችል አልሰጠኝም" የሚለው ስንኝ፣ የግጥሙ እጅግ ልብ ሰባሪ ክፍል ነው። እዚህ ጋር ግለሰቡ መለኮታዊ ኃይልን ለውርደቱ ምስክር ያደርገዋል።
እግዚአብሔር የሰጠው አቅም "ክፋትን የመቋቋም" ሳይሆን "ውርደትን የመቻል" ይመስል ይናገራል። ይህ የሀይማኖታዊ እይታ ስህተት ሳይሆን፣ የግለሰቡ ተስፋ መቁረጥ የመጨረሻ ደረጃ ነው። መሸከም የማይገባውን ቀንበር፣ የፈጣሪ ፈቃድ አድርጎ መውሰዱ የሞራል ሞቱን ያፋጥነዋል።
ፈጣሪ ነፃነትን ሰጥቶት ሳለ፣ እሱ ግን ባርነትን የፈጣሪ ስጦታ አድርጎ መቁጠሩ የነፍስ ጨለማ ነው።
በናይጄሪያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ የሚታወቀው ወሌ ሶይንካ፣ "በአምባገነን ፊት ዝም የሚል ሰው በቁሙ የሞተ ነው" ይላል። እዚህ ጋር አምባገነኑ ፖለቲከኛ ሳይሆን "ፍቅር" ነው። ይህ ባል በፍቅር ስም የሚፈጸምበትን ግፍ ዝም ብሎ ሲቀበል፣ በቁሙ እየሞተ ያለ በድን ሆኗል።
"ሄደሽብኝ ከምሰቃይ ችላለሁ ቢያመኝም" የሚለው ቃል፣ በብቸኝነት ጨለማ ውስጥ ከመኖር፣ በውርደት ብርሃን ውስጥ መቃጠልን እንደሚመርጥ ያሳያል። ሞት አንድ ጊዜ ነው፤ ውርደት ግን በየቀኑ የሚሞቱት ሞት ነው። እሱ ግን የዘላለም ሞትን መርጧል።
ግጥሙ "ክብሬን አይል ያፈቀረ የተሸነፈ ሰው" ሲል የሽንፈትን አዋጅ ያውጃል። ፍቅር ድል መሆን ነበረበት፤ እዚህ ግን ፍቅር መሸነፍ ሆኗል። "የተሸነፈ ሰው" ለራሱ የሚሆን ትርፍ የለውም።
ለራሱ የማይራራ ሰው፣ ለክብሩ አይቆምም። ይህ ስንኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንባ ያፈስሳል። ምክንያቱም ብዙዎች በዝምታ የሚሰቃዩበትን፣ ለፍቅር ሲሉ ማንነታቸውን ያጡበትን ድበቅ ህይወት ይገልጻልና። ሽንፈቱ ከሚስቱ ጋር ሳይሆን ከገዛ ራሱ ህሊና ጋር ነው። ራሱን ድል ያደረገ ሰው ብቻ ነው ለክብሩ የሚሞተው፤ እሱ ግን በራሱ ተሸንፏል።
ታሪኩ በአዲስ አበባ ምግብ ቤት ውስጥ መከሰቱ፣ ማህበራዊ ትዝብቱን ያጠነክረዋል። ሰዎች "እንዴ ባሏን እንኳን አትፈራም?" ብለው ሲጠይቁ፣ መልሱ "ባሏ ራሱን አይፈራም" የሚል ነው። ራሱን የማያከብር ሰው፣ ሌላው እንዲያከብረው ሊጠይቅ አይችልም።
የሚስቱ ድፍረት የመነጨው ከእሱ ደካማነት ሳይሆን፣ እሷን ለማጣት ካለው ከፍተኛ ስጋት ነው። ይህ ስጋት ደግሞ እንደ ካንሰር ውስጡን እየበላው፣ የውጭውን ስሙን አርክሶታል።
"ካንቺ አይበልጥም ክብሬ ክብሬ" የሚለው መደምደሚያ፣ የአንድን ሰው ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ያሳያል። ግጥሙ ሲያልቅ የሚቀረው ዜማ ሳይሆን፣ የክብር የቀብር ስነ-ስርዓት ነው።
በሞት የተለየን ታምራት ደስታ ይህንን ሲዘፍን፣ የአንድን ግለሰብ ታሪክ ሳይሆን፣ የብዙዎችን ስውር ስቃይ ነው ያወጣው። "ክብሬ" የሚለው ቃል ደጋግሞ ሲነሳ፣ ትርጉሙ እየጠፋ ይሄድና "ባዶነት" ብቻ ሆኖ ይረፋል።
ይህ ነው እንግዲህ ፍቅር ከክብር በላይ ሲሆን የሚመጣው አሳዛኝ ፍጻሜ። የሰው ልጅ ያለ ፍቅር ሊኖር ይችላል፣ ያለ ክብር ግን መኖር አይችልም—ቢኖርም ጥላ ሆኖ ነው።
ፍቅር መስዋዕትነትን ይጠይቃል ይባላል፣ ነገር ግን መስዋዕቱ የሰውየው ክብር ሲሆን፣ መለኮታዊነቱ ቀርቶ ሰይጣናዊ እስራት ይሆናል።
ክብር አንዴ ከተቀበረ ትንሳኤ የለውም። ታሪኩም ሆነ ዜማው የሚያስተምሩን መራራ እውነት ቢኖር፡- ለሌላው ክብር ስንል የገዛ ክብራችንን የምንቀብር ከሆነ፣ የምንኖረው ሕይወት የራሳችን ሳይሆን የገዳያችን ነው የሚል ነው።

🩺 አዲስ የሕክምና ግኝት
"ለስኳር ሕመምተኞች አዲስ የምሥራች" 🌟
#ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሚያጠቃው ለስኳር በሽታ (Diabetes) አዲስና የተሻለ የሕክምና ዘዴ ለማግኘት የሚያስችል ትልቅ ሳይንሳዊ ግኝት ይፋ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
🔍 የግኝቱ ዋና ፍሬ ነገር፦
ሳይንቲስቶች በኦክስጅን እጥረት እና በደም ውስጥ ባለው የስኳር መጠን መቀነስ መካከል ያለውን ቀጥተኛ ዝምድና አረጋግጠዋል። የሰውነታችን ሕዋሳት የኦክስጅን መጠን ሲቀንስ ስኳርን በከፍተኛ ፍጥነት የማቃጠልና ከደም ውስጥ የማስወገድ ተፈጥሯዊ ባህሪ እንዳላቸው ጥናቱ አሳይቷል።
💡 ለምን አስደሳች ሆነ?
ተፈጥሯዊ መፍትሔ፦ ይህ ግኝት በተለይ ተራራማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ለምን ዝቅተኛ እንደሚሆን ለዘመናት ለነበረው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።
አዲስ የሕክምና መንገድ፦ ተመራማሪዎች ሕዋሳቱ የኦክስጅን እጥረት ያለባቸው እንዲመስላቸው የሚያደርጉ (ነገር ግን ጉዳት የማያደርሱ) የሕክምና ዘዴዎችን በመቀየስ ላይ ናቸው።
ከመርፌ ነፃ የሆነ ሕይወት፦ ግኝቱ ወደ መድኃኒትነት ሲቀየር፣ ሕመምተኞችን በየቀኑ ከሚወሰዱ ከባድ መድኃኒቶችና መርፌዎች ሊገላግላቸው እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
🇪🇹 ለኢትዮጵያ ያለው ትርጉም፦
ይህ ግኝት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ከፍተኛ ተራራማና ደጋማ ቦታዎች ለሚኖሩ ማኅበረሰቦች ልዩ ትርጉም አለው። የሀገራችን ተፈጥሯዊ ከፍታ ለአትሌቲክስ ስኬታችን ብቻ ሳይሆን ለስኳር በሽታ መከላከልና ሕክምና ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ በሳይንሳዊ መንገድ የሚያረጋግጥ ነው።
የእርስዎ አስተያየት፦
የሀገራችን ደጋማ አካባቢዎች ለጤና ያላቸውን ፋይዳ በተመለከተ ምን የተለየ ትዝብት አላችሁ? አዲሱ ግኝትስ ምን ተስፋ ሰጣችሁ?
#healthnews #diabetescure #sciencebreakthrough #ethiopia #medicaldiscovery #highlandhealth #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

ቤት አልባው ባለቤት፦ የነገ ጭንቀት የዛሬን ፀሐይ ሲጋርድ
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚታየው እልህ አስጨራሽ ሩጫ አንድ ግብ አለው— "ነገ የተሻለ ቦታ መገኘት"። በዚህ ሩጫ ውስጥ ግን ብዙዎቻችን "ዛሬን" እንደ ትርፍ አንጀት ቆርጠን ጥለናታል። በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ አንድ ሰው ታሪክ የዚህ እውነት ህያውና ረመጥ የሆነ ምስክር ነው።
ይህ ሰው የራሱ መጠለያ ቤት ባለመኖሩ ዘወትር ይሰበሳጭ፣ የኑሮው ትርጉም አልባነትም በኪራይ ቤት መኖሩ ይመስለው ነበር። በትርፍ ሰዓቱ እየሰራ፣ ያማረውን ሳይበላ፣ ወቅቱ የጠየቀውን ሳይለብስ፣ የልጆቹን ሳቅ ሳያደምጥ ሳንቲም በአንቲም አጠራቅሞ ያቺን የናፈቃትን ቤት ገዛ። ነገር ግን እጣ ፈንታ ሌላ ስውር እጅ ነበራት። አዲሱ ቤቱ በገባ በወሩ፣ እንጨት ወድቆበት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የደከመበትን ቤት ሳይኖርበት፣ በላቡ ያመጣውን ውጤት ሳይጠቀምበት፣ የገዛው እንጨቱ መቃብሩ ሆኖ አለፈ።
ይህ ታሪክ የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የከንቱነት ጉዞ ማሳያ ነው።
"የማይጠግበው የሰው ልጅ ስልጣኔ"
የታሪክ ምሁራን የሰውን ልጅ ጉዞ ሲመረምሩ አንድ የሚገርም ተቃርኖ (Paradox) ያገኛሉ።
የሰው ልጅ ኑሮውን ለማቅለል የፈለሰፋቸው ነገሮች ሁሉ መልሰው የጭንቀቱ ምንጭ ሲሆኑ ይታያሉ። የታሪክ ተመራማሪው ዩቫል ኖህ ሀራሪ "Sapiens" በሚለው መጽሐፉ እንደገለጸው፣ የሰው ልጅ ግብርናን የጀመረው ለነገ የሚሆን ምግብ አከማችቶ በሰላም ለመኖር ነበር። ነገር ግን ግብርናው ለበለጠ ስራ፣ ለንብረት ጥበቃ ስጋትና ለጦርነት ዳረገው።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ አውድ፦ በአጼዎች ዘመን የነበሩ መኳንንት "ፎቅ" ለመስራትና ርስት ለማስፋፋት እድሜያቸውን በጦርነት ሲያሳልፉ፣ በመጨረሻ ግን ያከማቹት መሬት ሳይሆን የገዛ አፈራቸው በላያቸው ላይ ሲመለስ ታይቷል።
ታሪክ የሚነግረን "ነገን" ለመገንባት ዛሬን የጨረሱ ሰዎች፣ ታሪክ ሲፃፍ ስማቸው ቢኖርም ነፍሳቸው ግን በሰላም አልኖረችም።
የስነ-ልቦና ጥናትና ምርምር፦ "የደስታ ወጥመድ" (Hedonic Adaptation)
በስነ-ልቦና ሳይንስ ውስጥ "Hedonic Adaptation" የሚባል ጽንሰ-ሃሳብ አለ። ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው የሰው ልጅ አንድን ትልቅ ስኬት (ቤት፣ መኪና፣ ሀብት) ሲያገኝ የሚሰማው ከፍተኛ ደስታ በአማካይ ከ 3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠፋል። ከዚያ በኋላ ግለሰቡ ወደ ቀድሞው የጭንቀትና የጎደለኝ ስሜት ይመለሳል።
የምርምር ውጤት፦ እ.ኤ.አ በ 1978 የተደረገው ታዋቂው የሎተሪ አሸናፊዎች ጥናት እንደሚያሳየው፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያሸነፉ ሰዎች ከአንድ ዓመት በኋላ ያላቸው የደስታ መጠን፣ ምንም ካላሸነፉ ተራ ሰዎች ጋር እኩል ሆኖ ተገኝቷል።
ትርጉሙ፦ ያ በአዲስ አበባ ቤቱን ለመግዛት ሲጥር የነበረው ሰው፣ ቤቱን ከገዛ በኋላም ጭንቀቱ እንደማይለቀው ሳይንሱ ያረጋግጣል። ምክንያቱም ደስታን በቁስ ላይ "ነገ" በሚባል የቀጠሮ ቀን ላይ ሰቅሎት ነበር። ዛሬ ባለው ጥቂት ነገር ማረፍ ያልቻለ አእምሮ፣ ነገ ቢሊዮን ብር ቢኖረውም "ሀብቴን ማን ይወስድብኛል?" በሚል ስጋት መጠቃቱ አይቀሬ ነው።
ከድንበር ባሻገር ያለ እውነተኛ ሰቆቃ፦ የቪቻይ ታሪክ
ይህ የሰው ልጅ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በታይላንድ ይኖር የነበረውና በሪል ስቴት ንግድ እጅግ ስኬታማ የነበረው ቪቻይ ስሪቫዳናፕራባ ታሪክም ተመሳሳይ የልብ ስብርባሪ አለው። ቪቻይ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት አከማችቶ፣ የእግር ኳስ ክለብ ገዝቶ፣ በዓለም ዙሪያ ታዋቂ ሆነ።
በፈረንጆቹ ጥቅምት 2018 ላይ በገዛው ስታዲየም ውስጥ ጨዋታውን ተመልክቶ፣ በገዛው የግል ሄሊኮፕተር ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲነሳ፣ ያቺ በሚሊዮን ዶላር የገዛት ሄሊኮፕተር ስታዲየሙ አጥር ላይ ተከስክሳ በእሳት ነደደች።
ያን ሁሉ ሰፊ መሬትና ሰማይ ጠቅላይ ህንፃ የገዛው ሰው፣ መጨረሻው በገዛው ብረት ውስጥ አመድ ሆኖ መቅረት ሆነ። የገነባው ሀብት፣ የገዛው ቅንጦት መጨረሻው መጥፊያው ሆነ። ይህ የሚያስተምረን የምንለፋለት ነገር ሁሉ የጥፋታችንም በር ሊሆን እንደሚችል ነው።
"የህይወት ግጥምና ምሬት"
ደራሲያን ህይወትን ልክ እንደ ሸክላ ሰሪ ውጤት ያዩታል። ሸክላው ተሰርቶ ሳያልቅ ሊሰበር ይችላል። ኢትዮጵያውያን ደራሲያን በስራዎቻቸው ውስጥ በተደጋጋሚ የሚያነሱት ጭብጥ የሰው ልጅን ምኞትና የሞትን ቀጠሮ አልባነት ነው።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በአንድ ግጥሙ "ሰው መሆን" ያለውን ከባድ ሸክም ሲገልጽ፣ የሰው ልጅ ለምድር ባይሆንም ለምድር እንደሚጨነቅ ያሳያል።
የደራሲያን ትዝብት፦ "ሰው ለራሱ ቤት ሲሰራ፣ ለሞቱ ጉድጓድ እየቆፈረ እንደሆነ ይዘነጋል"። ያ የቤት ባለቤት የገደለው እንጨት፣ እሱ ራሱ የቤቱ ጣራ እንዲሆን የመረጠውና የገዛው ነው። ይህ የሚያሳየው ብዙዎቻችን ተጨንቀን የምናመጣው ሀብት፣ ዝና ወይም ስልጣን በውስጡ የጥፋታችንን ዘር ሊይዝ እንደሚችል ነው።
"የእለት እንጀራ" ፍልስፍና
እንደ ሃይማኖትም ሆነ እንደ ስነ-ልቦና፣ ትልቁ ጥበብ "የእለት እንጀራችንን ስጠን" ብሎ መኖር ነው። "የአመት እንጀራችንን አከማችልን" አንልም። ምክንያቱም የአመት እንጀራ አመትን ሙሉ የመጨነቅ ዋስትና እንጂ የአመቱን ህይወት የመኖር ዋስትና አይሰጥም።
ሀብትና ሰላም፦
ብዙዎቻችን ተጨንቀን የምናመጣው ነገር ምን አልባት መጥፌያችን ሊሆን ይችላል።
ሀብት መጥቶ ጤና ሊታጣ ይችላል።
ዝና መጥቶ ጭንቀት ሊነግስ ይችላል።
ብር ተገኝቶ ሰላማዊ እንቅልፍ ሊጠፋ ይችላል።
የዛሬን ፀሐይ አትጋርዱ
የተሻለ መመኘትና መስራት ክፋት የለውም። ነገር ግን "ዛሬን" ለነገ መረገጫ ማድረግ ማስተዋልን ይጠይቃል። ዛሬ ያለህን ጤና፣ ዛሬ አጠገብህ ያሉትን ቤተሰቦችህ፣ ዛሬ የምትበላትን የዕለት እንጀራ በደስታ ተቀበል።
ምን አልባት የዛሬው "ምንም የለኝም" የምትልበት ሁኔታህ፣ ነገ ላይ ሆነህ ደግመህ ለማግኘት የምትጸልይበት ብርቅዬ ቀን ሊሆን ይችላል። ዛሬ የምትረግጠው መሬት፣ ዛሬ የምትተነፍሰው አየርና ዛሬ የምትጠጣው ውሃ ከነገው ትልቅ ህንፃ በላይ ዋጋ አላቸው።
የመጨረሻው እውነት፦ የገነባኸው ቤት ሳይሆን፣ የኖርክበት ሰላማዊ ቅጽበት ነው ትክክለኛ ቤትህ። ያ በአዲስ አበባ እንጨት ወድቆበት የሞተው ሰው፣ ለቤቱ ሲል ራሱን ባይቀጣና ዛሬውን ባይበድል ኖሮ ቢያንስ ያለፉትን አመታት በደስታ ይኖር ነበር።
ዛሬን ኑር፤ ምክንያቱም ነገ ለማን እንደምትሆን አታውቅም!

የአርታዒው መግቢያ
#ethiopia | በእንባ የቀጠነ፣በደም ድርሳን የተጎነጎነ ታሪክ ያላት ሀገራችን፣ስሟ የተፈተለው በጀግንነት ቢሆንም፤ ፍሬዋን በፍሰሐ ሳታይ የከሰመባት ሽሕር ትመስላለች።
ይሁን እንጂ በዚህች ባለዝንጉርጉር ዳና ምድር፣በታሪክ ደመራ ነበልባል መሐል የሚስፈነጠሩት ትንታጎች ቀለማቸውና ቅርጻቸው ይለያይ እንጂ የየራሳቸውን ሥዕል አትመው ማለፋቸው አይቀሬ ነው።
ስለዚህ አንዳንዶቹ ሀገሩን በፍካትና ብርሃን ሲያጥለቀልቁት፣ሌሎች ዙሪያውን ጭጋግ አጉርሰው፣ ጠባሳ አልብሰው ያልፋሉ።
መቼም ጠባሳና አሻራ ለየቅል ናቸውና ሠናዮቹ ደመ-ግቡ ዐለም ፈጥረው፣ሳቅ ፈትፍተው ሲታወሱ፣እኩዮቹ በሕመማቸው ጥዝጣዜ በጠባሳቸው ሐፍረት የሀገር ቀሚስ ገልበው፣ገመና አስጥተው በታሪክ ሰልፍ ይተምማሉ።
ይሁንና የትውልድ አሻራ የሚዘልቀው ወይም ሕመም የሚከርመው በሀገር መሪነት መንበር፣በገዢነት ዙፋን ላይ በተቀመጡት ብቻ አይደለም።
እንደ ዝንጀሮ ጎረምሳ እግር የሚለካኩትና ትከሻ የሚጋፉትም ጭምር እንጂ!
ከመንግሥት መቀመጫ በተቃዋሚ ጎራ ሆነው የዘመን ወጀብ በሚያወላግዳት ሀገር የማይረሳ ዜማ የሚያሰሙ፣ወይም በሚያምም ሙሾ አንጀት አገላብጠው የሚገርፉ፤ልብ የሚሰብሩ ይኖራሉ።
የታሪክ ገጾች በተገለጡ ቁጥር የሚጎፈንን ስሜት፣እንደ እንደሽንኩርት የሚላጥ ሰቀቀን አስቀምጠው የሚያልፉ ብዙ ናቸው።
በትልቋ ሀገር አሜሪካ በዘመነ ሊንከን አሜሪካ በእርስ በርስ ጦርነት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎቿን ስታጣ፣እጁን ደም የነካው የሊንከን ጀኔራል ዩሊሰስ ግራንት ብቻ አልነበረም። ግራንት ሀገር እንዳትናድ ሲከላከልና እሳቱን ሊያጠፋ ሲባትት፣ሮበርት ኢ. ሊ ደግሞ የሀገሪቱን ካስማ በመናድና የሀገር አንድነትን በሚያናጋ ሰልፍ ቆሞ ነበር። የተቀደሰና የተረገመ የታሪክ ዳንዳ ማለት ይህ ነው።
አንዱ እየሳቀ እሳቱን እንዳበባ ሲያሽሞነሙን፣ሌላኛው አበባው እሳት እንዳይሆን ውሃ ያጠጣ ነበር። ታሪክ ቀለሙ ብዙ፣አድማሱ ሰፊ፣ዘመኑ እልፍ ነው። ቁስሉ ጠዝጣዥ፣ሕመሙ ድርብ ነው።
የኢትዮጵያም ታሪክ ከዐለም ታሪክ ዘውግ አይወጣም። ግን ደግሞ በደም የቀላ፣በስሜት የፈላና የተንተከተከ ነው፣በትግል የሾረ ነው። የነፃነታችን ከበሮም ቢሆን የድል ብስራት ብቻ አልነበረም፤ ከጀርባው አያሌ ሰቀቀን የሸሸገ፣በደም የተነከረ ሐውልት አቁሟል። መሪዎቻችን የተዋከቡ፣ መረጋጋት ባጣ ትንፋሽ ተሟግተውና ተዋግተው ሀገር ያቆዩ ፣ግን ኑሯቸው የባይተዋር ነበር። ተቀናቃኞቻቸውም እልፍ ናቸው።
ቴዎድሮስ ጥይት ቅመው እስኪወድቁ አላረፉም። ዮሐንስ አንገታቸው እስኪቀላ እላይ ታች ሲሉ ባትተዋል። የዮሐንስ ቀኝ እጅ የነበሩት አፍሪካዊው ጀኔራል አሉላ ጦርነቱ ብቻ ሳይሆን የራሳቸው ሰዎች ባላንጣ ሆነው ጥይት ተኩሰውባቸዋል።
ከዶጋሊ፣ጉራዕና .ጉንደት ይልቅ የወገናቸው ሾተል አፏጭቶባቸዋል። ተፈሪ መኮንን ከኢያሱ ጋር ያደረጉት የሰገሌ ጦርነት ብቻ አይደለም ምጣቸው። መሳፍንቱና መኳንንቱ የየራሳቸውን ጎጆ ከሀገር በላይ አልቀው ፈተና ሆነውባቸዋል።
እነዚህ ሁሉ የታሪካችን አንቀልባ ላይ የታዘሉ፣የቃሬዛ ማኅተሞች ናቸው። መልካቸው ዝንጉርጉር፣ሕመማቸው ጥልቅ ትዝታቸው የማይደበዝዝና በየትውልዱ ልብ የዘለቀ ነው።
ኢትዮጵያም እንደሌሎቹ ሀገራት፣ምናልባትም በባሰ የሬት ገንዳ የተጠመቁ የታሪክ ሕመሞች አሏት። ከልጆቿም በየዘመኑ እንባዋን ለማበስ ሌት ተቀን የባተሉ፣በአጣብቂኝ ወራቷ በፍቅር የጋረዷትና በደም መሥዋዕትነት የታደጓት የመኖራቸውን ያህል፤ እንባዋን እንደ ማር ጣፍጧቸው የጠጡ አሏት። የእናት ሆድ ዝንጉርጉር እንዲሉ ልጆቿ በየዘመኑ ሺህ መልክ አውጥተው፣እልፍ ዱካ አስቀምጠው አልፈዋል።
ጋዜጠኛ በቀለዐመነ ባሳተመው በዚህ መጽሐፍ፣በተለያዩ ጊዜያት የሠራቸው ቃለ ምልልሶ ተካትተዋል። በእነዚህም ውስጥ ሐሳባቸውን የተናገሩ፣ሕመማቸውን ያወጉ፣ቂማቸውን የሰለቁ፣ቁጭታቸውን የተነፈሱ ኢትዮጵያውያንን ዜማና ስሜት፣ሕልምና ተስፋ በተለያየ ስልት ቀርቧል። እነዚህን ሐሳቦችና ሕልሞች በአንክሮ ለማጤን ሞክሬያለሁ።
የእነዚህን የአንድ ዘመን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ምሕዳር ሰዎች አቋምና ቁመና በመዘንኩት ልክ፣ በሀገር ወዳድነት የተመሰጡትን፣በቁጭት ፍም ላይ ተቀምጠው የነደዱትን፣ቂማቸውን ቆርፍዶ የለወዘውንና ልባቸው ውስጥ የነደደው እሳት ጢስ ያጠገበው ልባቸውን አይቸበታለሁ።
በአንዳንዶቹ የሀገር ፍቅር ስሜትና የአንድነት ተስፋ ስደመም፣በምሬት ከስለው ጥቀርሻ በበላቸው አዝኛለሁ።
እውነት ነው፤ሀገር ከሰፈር በላይ፣ሀገር ከጤና፣ሀገር ከግል ክብርም በላይ እንደሆነች ያነበብኳቸው ብዙ የታሪክ ገጾች ኢትዮጵያዊ መልካችንን ውበት አሳይተውኝ አላለፉም። በአሁኑ ሜዳም እነዚያን አባቶች የመሰሉ፣በአንድ ልብ የበቀሉ ያህል ጥዑም መዐዛ ያዘሉ እንዳሉ አይቼ አፌን ሳቅ ሞልቶታል።
ከእነዚህ የቀደሙናኢትዮጵያ የአሁን ቅርጿን እንድታገኝ የሕክምና ቀጠሯቸውን ትተው ለሙግት የበረሩት ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ሀገር ከሕይወት በላይ ናት"በሚል የልቤን ደጅ ደብድበውታል። ሀገር ነፍስ ይከፈላታል"ያሉና ስለሀገራቸው ክብር ሽጉጣቸውን ጠጥተው ያንቀላፉትን ኮሎኔልና ጀኔራሎች አስታውሻለሁ። ቃል ከራስ በላይ መሆኑን ያሳዩትን የታሪካችን ጉልላቶች እነፊታውራሪ ገበየሁን፣ከንጉሡ ተጣልተው፣"በሀገር አይኮረፍም" ብለው በአረጋዊ እድሜያቸው ዳግም በጥይት አረር ነድደው የሞቱትን አባነፍሶ ባልቻ ከፊቴ ውል ብለዋል።
ዛሬ ግን ራስን ማስቀደም ከሀገር ክብርና ልዕልና ይልቅ የጎላ ይመስላል።ትውልድ የሚቀጣበት ምራንጣ አንጠልጥሎ መሄድ ወግ ሆኗል። ያኔ ሰው ስለሀገሩ የሞተውን ያህል፣ዛሬ ሰው ለራሱ ሀገሩን የሚገድልበት ሰይፍ የታጠቀ ይመስላል።
ብዙ ጊዜ ንዳዱን በሩቁ፣ሌሎች የደከሙበትን እሸት ቀርቦ ወደ መጋጡ ያደላል።
እዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት ባለታሪኮች ሀገሪቱ ዛሬ ላለችበት ሁኔታ በመልካምም ሆነ በክፉ አሻራ ያላቸው፣ጠባሳ ያስቀመጡ፣ወይም አበባ ያሳቀፉ፣ወይም እሾህ ነስንሰው እሸቷን የነጠቁ የታሪክ ቃንዛዎች ናቸው።
ሁሉም ግን የሆኑትን፣ ምናልባትም ያልሆኑትን ይናገራሉ። የተናገሩትን ሁሉ አንሰማም፤የሰማነውን ሁሉም አናምንም፤እንፈትሻለን። ዝም ያሉትን እናመሳክራለን እንጂ አንቆፍርም።ምክንያቱም ታሪክ በሌላ ክንፉ ይዟቸው የሚመጣ መልኮች አሉትና ።
እጅግ የወደድኳቸውና የአንድ ዘመን ከእነዚህ ባለታሪኮች የኢትዮጵያን ትውልዶች መልክና ቀለም ያሳዩኝ፣እነጀነራል ደምሴ ቡልቶ፣ጀነራል መርዕድ ንጉሤ፣ውስጥ የነበረውን ታማኝነትና ሀገር ወዳድነትና ሓላፊነት ከእንጀራ በላይ መሆኑን በነፍሳቸው ያወሩልኝ ፤ጊዜ በተለወጠ ቁጥር፣ለእንጀራ ተማርኮ እጅ ያለመስጠትን ያስተማሩኝ ዘውድ ያልጫኑ የታሪክ ንጉሦችም አሉ። ሳላውቅ በወሬ ፈርጃቸው ግን ደግሞ ሀገራዊ ሕልማቸውና የወገን አቅራቢ ሐሳባቸው የማረከኝ ፖለቲከኞችም አልጠፉም። በፊትም የማላምናቸው አሁንም ያንኑ ሐሳባቸውን ደርተው አነባበሮ የጋገሩ የየዘመኑን እንኩሮዎች ታዝቤበታለሁ።
ይሁንና ከሁሉ በላይ የዘመኑን ማኅበረ-ፖለቲካዊ መልክ፣ከያ ትውልድ ተሻግሮ ዛሬም በየአምባው የሚጮኸውን ጅራፍ ድምፅና ቁስሉን በሚገባ ለማየት ጥሩ ስብስብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ሥልጣን ላይ ሆነው ሲከንፉ ፋታ ያጡ ሰዎች ወንበራቸው ተንሸራትቶ፣ሰው ሆነው ሲቀመጡ ሕይወትን ያስተዋሉበትን ትዝብትና የፖለቲካችንን ቁመና መዝኜበታለሁ፤ተምሬበታለሁም።
ስለትናንት ብቻ ሳይሆን ስለነገም የሚገለጡ መዛግብት ሆነው ለቀጣዩ ጉዟችን ፍንጭ ይሰጡናል የሚል እምነት ያኖሩም አሉ። የተደመምንባቸውን በታሪክ ገጾች ከማንገሥ ባሻገር የምንወርሰው ሀብት፣የሳቱትና የአደባባይ ሕጸጻቸውን ጉያቸው ሥር የወሸቁትንም የምንታዘብበት ነው።

ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ማንነት?
#ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ የስነዳ ሥራ ታሪካቸው መዝገበ አእምሮ ላይ የሚሰነድላቸው ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይጠቀሳሉ።ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክና ባህል ዙሪያ በርካታ መፅሐፍትን በመድረስ ትልቅ አሻራ አኑረዋል።ከ30 በላይ መፅሀፍትን የደረሱት እኒህ ሰው የሀይማኖት ሰባኪ፣ ፀሀፊ እና ዲስኩር አቅራቢ በመሆን ለአገራቸው አገልግሎት ሰጥተዋል። የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን የመሠረቱት ዲያቆን ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ፣ የኢቢሲ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሹመዋል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ታሪክ ሰንደውታል።
#ቅድመ ነገር
በነገረ ሀይማኖት፣ በሥነጽሑፍ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በጥናትና ምርምሮች ከምልዓት በተጠጋ መሰጠት ያገለገሉ ሰው ናቸው፣ ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የተወለዱት ደሴ ከተማ ነው። በወላጅ አባታቸው የንግድ ሥራና እንቅስቃሴ ምክንያት፣ ነፍስ በማያውቁበት እድሜ የመላ ቤተሰቡ ቋሚ መኖሪያ ወደ ባህርዳር ከተማ ተዛወረ። በመሆኑም አብዛኛውን ለሕይወት ስንቅ ሆኖ የቆያቸውን የእውቀት መሠረት ያገኙት በዚሁ በባህርዳር ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጼ ሰርጸ ድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መለስተኛ ደረጃን በፋሲል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚህ መደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ወላጅ እናታቸው ለትምህርትና ንባብ የሰጡት ትኩረት የንባብ ልምዳቸውን በእጅጉ እንደቃኘው በተለያየ ጊዜ በሰጧቸው ቃለመጠይቆች ደጋግመው ያወሳሉ።
#የሥነጽሑፍ ፍቅር
በልጅነት እድሜ ከዘመናዊ ትምህርት ጎን ለጎን፣ ባደጉበት ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርትን በሚገባ ቀስመዋል። ይህም አገልግሎታቸው ከፍ ብሎ ቤተክርስትያንን በዲቁና እንዲያገለግሉ የክህነት መዓረግ አስገኝቷቸዋል። ከዚያም ባሻገር ወደ አካባቢው ከሚያቀኑ በእውቀትና በመንፈሳዊ ጽናት የታወቁ አባቶች መምህራን ብዙ ትምህርትን የመቅሰም እድል ነበራቸው፣ ተጠቅመዉበታልም።
ይህ ሁሉ ተዳምሮ በልጅነት እድሜ የተለያዩ ሥነጽሑፋዊ ሥራዎችን እንዲጽፉ፣ አልፎም በትምህርት ቤት በጠዋት የተማሪዎች ሰልፍ ሰዓት መድረክ ላይ ወጥተው እንዲያቀርቡ አስችሏቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉም በሰልፍ ሰዓት ለተማሪዎች ዜና ያቀርቡ ነበር። በንባብ የተገነባ መሠረት ላይ የተጣለ ማንነታቸውም ለሥነጽሑፍ በተለየ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል።
#ከአዲስ አበባ እስከ ኬንያ
ከባህር ዳር አዲስ አበባ ያቀኑት በ1982 ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ እንደገቡም ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። በዚያም ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአቅራቢያ በሚገኘው በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጡ ነበር።
የአንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ታድያ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የተናጠችው ኢትዮጵያ፣ ወጣት ተማሪዎቿ ወደ ብላቴ እንዲሄዱ ተወሰነባት። ዲያቆን ዳንኤልም በዚህ መሠረት ወደብላቴ የውትድርና ማሠልጠኛ ከሄዱ ተማሪዎች መካከል ሆኑ። ይህ ከተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ወጣቶችን በአንድ እንዲሰባሰቡ እድል የፈጠረው አጋጣሚ፣ ለዳንኤል የተለያዩ ባህሎችን፣ የሀገር መልኮችን እንዲያዩ እድል የፈጠረላቸው ነበር።
የብላቴ ሥልጠና ተጠናቅቆ ምረቃ ሳይደርስ ግን ደርግ ወርዶ ኢሕአዴግ ገባ። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም አብዛኞቹ ወደ ኬንያ ሄዱ። ዳንኤልም በኬንያ የተወሰኑ ወራት ቆይተው፣ ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን አደላድሎ ከያዘ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወጣቶች ሁሉ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተባለና ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ። በአንድ ዓመት ውስጥም የሦስት መንፈቅ ትምህርት ተከታትለው ዲፕሎማቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀብለው አጠናቀቁ።
#መምህርነት
ከዚህ በኋላ በተመረቁ ተማሪዎች ምደባ መሠረት ሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር (በቀድሞ አጠራር) ደረሳቸው። ምንም እንኳ አዲስ አበባ ላይ ሥራ ያገኙና ምደባውን መተው የሚችሉ ቢሆንም፥ “እንዲሁ በነጻ የተማርኹትን ያህልም ቢሆን ማገልገል አለብኝ” በማለት ምድባውን ተቀብለው፣ እንደውም ‘ቢቻል ሰው ሊሄድ የማይመርጥበት ራቅ ያለ ስፍራ መድቡኝ’ አሉ። በጊዜው ግን አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት የደረሳቸው በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅሩ ነበርና በዚያ የአማርኛ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ።
በዚያም የመምህራን እጥረት ስለነበር፣ ከአማርኛ ባለፈ ታሪክ እና አካባቢ ሳይንስ (ጂኦግራፊ) ያስተምሩ ነበር። ከዚያ ጎን ለጎን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠትና በማስተማር የአካባቢውን ማኅበረሰብ አገልግለዋል።
የማገልገል ጽኑ ፍላጎት እና ባመኑበት ‘ለብቻም ቢሆን የመቆም’ ጽናት ውስጥ ሆነው፣ የመምህርነት አገልግሎታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባ ተመለሱ።
ቀጥለውም ዲፕሎማ በተመረቁበት ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል። ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊትም ሆነ በኋላ፥ በማኅበረ ቅዱሳን በመደበኛ አገልግሎት ሠርተዋል። ሐሳብ አመንጭቶ መጽሐፍ ከመጻፍ በላይ የማሳተምና ማሰራጨት ክብደቱን በመረዳት የመጽሐፍ ህትመት ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ‘አግዮስ’ የተባለውን የራሳቸውን የመጽሐፍ ማሳተሚያና ማሰራጫ ከፍተው በዘርፉ ሠርተዋል።
ከዚህም ባሻገር የምክር አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በ2010 ዓ.ም የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።
#የመጽሐፍ ሥራዎች
መሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሠላሳ ሦስት በላይ መጻሕፍትን ለአንባብያን አድርሰዋል። እነዚህም እንደ ‘ብቻዬን እቆማለሁ’፣ ‘ጠጠሮቹ እና ሌሎችም’፣ ‘የሰርቆ አደሮች ስብሰባ’ ከሚሉና ከመሳሰሉ ከተወሰኑ የወግ ስብስብ መጽሐፎች ባለፈ፣ ዳጎስ ያሉ በጥናትና ጥልቅ ንባብ ላይ የተመሠረቱ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ናቸው።
ዳንኤል እስከ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መሥራች ናቸው። ከዚህም ባሻገር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መሥራቾች መካከል ይገኙበታል። በዚህ ማኅበር ውስጥ የሚታተሙ መጽሔት፣ ጋዜጣና መጻሕፍት ዝግጅት ክፍል ላይም ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔትም ላይ በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ በቅርብ በፋና ሚድያ ኮርፖሬት የቦርድ አባል ብሎም ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ለሀገር ይጠቅማል ብለው ባመኑበት መስክ እና ተቋም የቦርድ አባልና ሊቀመንበር ሆነዋል፣ ሠርተዋል።
‘የዳንኤል ክብረት ዕይታዎች’ የሚለው መጦመሪያ ድረገጻቸው ላይ የሚያሰፍሯቸው ጽሑፎች ብሎም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት የሚያቀርቧቸውና የሚሰጧቸው ማኅበራዊ ኂሶች ብዙ ትኩረት የሚስቡና ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ፣ ናቸው። በቃል ብቻ ሳይሆን በመጽሐፎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚሆኑ የሆኑ ሥራዎቻቸውም ጥቂት አይደሉም።
ብዙ የደከምኩባቸው የሚሏቸው ሁለት መጻሕፍት አሉ። አንደኛው ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘው በአቡነ ተክለሃይማኖት የሕይወት ታሪክ ዙሪያ የሠሩት ሲሆን ሌላው ‘አራቱ ኃያላን’ የተሰኘ መጽሐፍ ነው። በቅርብና መጨረሻ ላይ ለንባብ ካቀረቡት ዳጎስ ያለ መጠን ያለው ‘የትርክት እዳና በረከት’ መጽሐፋቸው በፊትም፣ ‘እጨጌ እንባቆም ከየመን እስከ ደብረሊባኖስ’፣ ‘ራዕየ ዮሐንስ’፣ ‘ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ’ የተሰኙ የመጽሐፍ ሥራዎቻቸው ከብዙ በጥቂት የሚጠቀሱ ናቸው።
#ቤተሰብ
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ከትዳር አጋራቸው ወይዘሮ ጽላት ጌታቸው ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል። በዚያም ሦስት ወንዶች (አቤሜሌክ ዳንኤል፣ ባሮክ ዳንኤል እና ባህራን ዳንኤል) እና አንዲት ሴት ልጅ (አንኪዮን ዳንኤል) አባት ለመሆን በቅተዋል።
ሙሓዘ ጥበባት የሚለውን ማዕረግ፣ ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘውን መጽሐፍ ባስመረቁበት ወቅት ‘ስም ከግብር አብሮ ይሄዳልና...’ ሲሉ፣ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ የሰጧቸው ስያሜ ነው። ሙሓዘ ጥበባት ማለት ‘የጥበብ መፍሰሻ’ ማለት ነው።
#ምስክርነት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመገናኛ ብዙኃን አመራርና አሠራር ጥሩ እውቀትና ልምድ አለው፡፡ አዳዲስ አሠራሮች እንዲጎለብቱ ሃሳብ በማፍለቅና እንዲሳካ ጥረት የማድረግ ብቃት አለው፡፡ አሁንም የጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነትና የሚዲያው ኤዲቶሪያል አቅም እንዲጎለብት እንዲሁም ተቋማዊ አቅሙ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነፃነት ተስፋዬ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ
##########
ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በይዘት ደረጃ ካየነው በባህል ኪነጥበበ እና በታሪክ ዙሪያ የኢትዮጵያን መልክ በፅሑፎቹ እና በንግግሮቹ ለማሳየት ከፍተኛ አበርክቶ ሰጥቷል። ፅሑፎቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቶች የተሠሩባቸው አሁንም ይበልጥ ሊጠኑ የሚገባቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። ዲያቆን ዳንኤል በፅሑፎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፍልስፍናዎችን፣ ጥበባትን፣ ታሪክን፣ ሀይማኖትን፣ ባህልን፣ ሥነ ጽሁፍን ፍንትው አድርጎ በማሳየት የራሱን አሻራ ያኖረ ነው። አበርክቶውም ትልቅ ነው።
እርሱ በፅሑፍ ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ሰው በመሆኑ ትውልድ በማነፅ፣ ሥነ-ምግባርን በማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያን በመመርመርና በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ኂስ በጥበብ በመስጠት፣ ያነበባቸውን መፅሀፎች ወይም ያካበተውን ዕውቀት ጥበባዊ ስልት በተላበሰ ምጡቅ መንገድ በማቅረብ ይታወቃል።
የራሱን አሳታሚ ድርጅትና የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን በመመሥረትና በመምራት ለእውቀት እና እውቅና መስፋፋት ዋና ሚና ተጫውቷል።
በመንግሥት ኃላፊነቱም ቀድሞ ሲከውን የነበረውን ተግባር በላቀ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ እንደመሆኑ መጠንም ተቋማትን በመመሥረትና በማጠናከር ሚናው ትልቅ እንደሆነ እረዳለሁ።
ዲያቆን ዳንኤል ከ30 በላይ መፅሀፍትን እንደማሳተሙ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዴት ይሆን? የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። እርሱ ግን ምናልባት በሰላሳ አመት የጽሁፍ ታሪኩ ከሰላሳ በላይ መጻሕፍትን እና እጅግ ብዙ መጣጥፎችን በሙበርከት ፕሮሊፊክ እና ዐቢይ ሥፍራ የሚደጠው ደራሲ እና የሃሳብ መሪ መሆኑን አስመስክሯል።ለሁሉም እንደሁኔታው ጊዜ በመመደብ ለሁላችን አርዓያ ነው።
ተመራማሪው ዳንኤል፣ ከመዛግብት ተነስቶ የሚፅፋቸውን ታሪኮች አይቻለሁ። በመካከለኛው ዘመን በአገራችን የተደረጉ ብዙ ክስተቶችን ለታሪክ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንዲሆን አድርጎ ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሰነደ ነው። ይህ ቀላል አይደለም።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሳስታውስ ብላቴን ጌታ ህሩይን ያስታውሰኛል። እርሳቸው በአንድ በኩል የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ይዘው በአንድ በኩል ይፅፋሉ። ምርምሮችንም ያደርጉ ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ድንቅ የፈጠራ ክህሎቱን በመጠቀም የሚያቀርባቸው ሥራዎች ከንባብ እና ነገሮች በጥልቀት ተረድቶ የሚያቀርባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያን የማሳየት አቅም አላቸው ብዬ አምናለሁ። አበርክቶው እና ጽኑ ሰብዕናው በአጭሩ ተተርኮ የሚያበቃ አይደለም።
ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ የባህልና ኪነ ጥበብ ሚኒስትር ዴኤታ
######
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የማውቀው ከ20 ዓመት በፊት ነው ። የዐውደ ምሕረቱ ፈርጥ ፣የቤተክርስቲያን አጽራር መከታ ከወንድሞች ጋር ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ሲያገለግልና ለብዙዎቻችን መንፈሳዊ መሠረት ጣይ በነበረ ጊዜ አውቀዋለሁ። በሚጽፋቸው መንፈሳዊና ትዝብት አዘል ማኅበረሰባዊ ጽሑፎች ያልተማረ ,ያልተገሰጸ በነፍሱ ሀሴት ያላደረገ በዙሪያው የነበረ ማንም አልነበረም። በተለይ በማኀበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በሚያዘጋጅበት ወቅት የከተባቸው ጽሑፎች ዘመን የተሻገሩ እስካሁን ለብዙዎች መንፈሳዊ ሙላት የኾኑ ጥዑም ዘለላዎች ናቸው።
የጻፋቸው መጽሐፍት እንዲሁም በብሎጉ በዕይታ ያስቀመጣቸው ትዝብቶቹ በቤተክህነቱም በቤተመንግሥቱም ቅቡልነታቸው የበዛ ነበር።
የቀረቡት ኹሉ ግለሰባዊ ማንነቱን ሊገነዘቡለት የማይከብዳቸው ዳንኤል በዐውደ ምሕረትም ሆነ በመድረክ ራሱን ሳያካብድ ለአገርና ለቤተክርስቲያን በጥልቀት በሚያውቀው የታሪክ አረዳዱ እያገለገለ የሚገኝ ምስጉን ወንድም ነው።
ኢዮብ ስዩም

ፎቶ መነሻ ልቀቁልኝ በሚል በታይላንድ ታዋቂው የቱሪስት መዳረሻ ላይ በቱሪስቶች መካከል የተከሰተ ፀብ
ሰሞኑን በታይላንድ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘውና "ዋት ሮንግ ኩን" ተብሎ በሚጠራው ዝነኛ የቱሪስት መስህብ ስፍራ፣ በሁለት ጥንዶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ድብድብ ተከስቷል።
ሁኔታው ምን ነበር?
ስፍራው በውበቱና ፎቶ ለመነሳት በሚመች ድባቡ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ሁለቱ ጥንዶች በፎቶ መነሻ ቦታ ምክንያት በቃላት መጣላት ይጀምራሉ።
ጭቅጭቁ እየተባባሰ ሄዶ አራቱም ቱሪስቶች በቦታው በነበሩ ሌሎች ጎብኚዎች ፊት እርስ በርስ ወደ መደባደብ ተሸጋግረዋል።
ይህ ድርጊት በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ዘንድ መደነቅንና ትዝብትን ፈጥሯል።
የነጭ ቤተ መቅደሱ (White Temple) ሰላማዊ ድባብም በዚህ ድንገተኛ ግጭት ለጥቂት ደቂቃዎች ተረብሾ ውሏል።

7 months ago
በአፍጋኒስታን፦ የጨለማው ቀለበት እና የነፍስ ጩኸት
በካቡል ዳርቻ፣ በተራራው ግርጌ በሚገኝ አንድ ምስኪን ድንኳን ውስጥ፣ አየሩ የሞት ሽታን አርግዟል። የ55 ዓመቱ ሳሚኡላህ በድንኳኑ መጋረጃ ስንጥቅ በኩል ወደ ውጭ የሚወርደውን በረዶ ይመለከታሉ። በረዶው ውበት ሳይሆን ለእሳቸው የሬሳ ከፈን ነው። በእጃቸው የያዙት የደረቀ ዳቦ ድንጋይ ሆኗል፤ በብርጭቆው ውስጥ ያለው ሻይ ደግሞ እንደ ነፍሳቸው በረድ ብሏል።
“ታውቂያለሽ ረሃና?” አሉ ሳሚኡላህ ለባለቤታቸው። ድምፃቸው ከጥልቅ ጉድጓድ እንደሚመጣ ማሚቶ ይርገበገባል። “በኢራን ስደት ላይ ሳለን ‘አገሬ ስገባ እፎይ እላለሁ’ እል ነበር። ዛሬ ግን አገሬ ሆዷን ዘግታብኛለች። ሞት እዚህ ግቢ ውስጥ እንደ ቤተሰብ አባል እየተዘዋወረ ነው፤ እኛ ግን መሞት እንኳ አቅቶናል።”
የስደት እና የውርደት ጉዞ
ከሃያ ዓመታት የስደት ሕይወት በኋላ፣ ሳሚኡላህና ቤተሰቦቻቸው በአንድ ሌሊት ነበር ከኢራን የተባረሩት። ፖሊሶች የቤታቸውን በር ሰብረው ሲገቡ፣ ዩሱፍ የሃያ ዓመቱ ልጃቸው፣ ለዓመታት ያጠራቀመውን ጥቂት ገንዘብ እንኳ እንዲወስድ አልተፈቀደለትም። “ተነሱ! እናንተ ባዕድ ናችሁ!” የሚለው ጩኸት ዛሬም በጆሮው ያንባርቃል።
አፍጋኒስታን ሲደርሱ የጠበቃቸው ግን የእናት አገር እቅፍ ሳይሆን፣ በረሃብ የደረቀ ምድር ነበር። ዓለም አቀፍ እርዳታዎች ተቋርጠዋል፣ ሥራ የለም፣ ተስፋም የለም። ዛሬ ሳሚኡላህ የሦስት ወር የልጅ ልጃቸውን ማርያምን በደረታቸው ላይ አቅፈዋል። ሕፃኗ መለቅሶ እንኳ አቁማለች፤ አይኖቿ ብቻ በክብደት ይከፈታሉ፣ ይዘጋሉ። ይህ የረሃብ የመጨረሻው ምዕራፍ እንደሆነ ሳሚኡላህ ያውቃሉ።
የዝምታው ግድግዳ (የሴቶች መከራ)
በድንኳኑ ጥግ የ16 ዓመቷ ፋጢማ ተቀምጣለች። ፋጢማ ትምህርት ትወድ ነበር፤ በስደት ሳለች በፋርስ ቋንቋ ግጥም ትጽፍ ነበር። ዛሬ ግን መጽሐፎቿን ለምድጃ ማቀጣጠያነት ተጠቅማባቸዋለች። በአፍጋኒስታን ሴት መሆን ማለት በቁም መቀበር ማለት ሆኗል።
“አባዬ፣” አለች ፋጢማ። ድምጿ እንደ መስታወት ስብርባሪ ይቆርጣል። “ረሃቡን እችለዋለሁ። ግን በድንኳን ውስጥ ታስሬ፣ ሳልማር፣ ሳልሠራ፣ ሳልናገር የምሞትበትን ቀን መጠበቁ ግን ነፍሴን ገደላት። በረዶው ውጭ ብቻ ሳይሆን እኛ ሴቶች ልብ ውስጥም ጭምር ነው።”
እናቷ ቢቢ ረሃና የልጇን ፀጉር እያሻሸች በዕንባ ታጅባ እንዲህ አለች፦ “ልጄ ሆይ፣ ሴት ልጅ በዚህች ምድር ላይ እንደ ጧፍ ናት። ራሷ እየቀለጠች ለሌላው ብርሃን ትሰጣለች። ዛሬ እየቀለጥን ያለነው ግን ብርሃን ለመስጠት ሳይሆን በረሃብ ጭልጭል ብለን ለመጥፋት ነው።”
የዓለም ቸልተኝነት እና የፖለቲካ ቁማር
ከድንኳኑ ጥቂት ርቀት ላይ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መጋዘኖች አሉ። እዚያ ውስጥ ምግብ አለ። ነገር ግን በፖለቲካው ውጥረት ምክንያት፣ ያ ምግብ ወደ ሳሚኡላህ ድንኳን አይደርስም። የዓለም መሪዎች በአየር ማቀዝቀዣ ባላቸው አዳራሾች ውስጥ ስለ ‘ሰብአዊ መብት’ ይከራከራሉ። እዚህ ግን ‘መብት’ ማለት አንዲት ደረቅ እንጀራ ሆናለች።
17 ሚሊዮን አፍጋኒስታውያን በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ነው። ዓለም ግን እንደ ድራማ በትዝብት ይመለከታቸዋል። የሳሚኡላህ ታሪክ የስምንት ነፍሳት ብቻ ሳይሆን፣ የጠቅላላ አገር የቁም ስቅል ነው። በየቀኑ አዳዲስ ተባራሪዎች ከፓኪስታንና ከኢራን ወደ ድንበሩ ይጎርፋሉ፤ ሁሉም የሚያገኙት ግን ባዶነትን ብቻ ነው።
ያልተጠበቀው የንጋት ጨረር
ሌሊቱ ሊነጋ ጥቂት ሲቀረው፣ ሕፃኗ ማርያም ትንፋ` መቆራረጥ ጀመረ። ሳሚኡላህ በድንጋጤ ተነሱ። “አምላኬ ሆይ! እኔን ውሰደኝ፣ እሷን ግን ተዋት!” እያሉ ሲጮሁ፣ ከድንኳኑ ውጭ አንድ ድምፅ ተሰማ።
አንድ ወጣት አፍጋኒስታናዊ፣ እርሱም እንደነሱ ተፈናቃይ የሆነ፣ በእጁ ጥቂት ወተትና ዱቄት ይዞ መጣ። “አጎቴ፣” አላቸው ወጣቱ በብርድ እየተንቀጠቀጠ። “ይህን ለሕፃኗ ውሰዱ። ዛሬ ከተማ ውስጥ አንድ ደግ ሰው የሰጠኝ ነው። እኛ ካልተረዳዳን ማንም አይረዳንም።”
ያቺ ትንሽ ወተት ለሳሚኡላህ ቤተሰብ ከመንግሥት እርዳታ በላይ ትርጉም ነበራት። ቢቢ ረሃና ወተቱን አሙቃ ለሕፃኗ ስታጠጣ፣ ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ አይኖቿን ከፍታ እናቷን አየች። በዚያች ሰከንድ፣ በዚያች ጠባብ ድንኳን ውስጥ፣ ተስፋ እንደገና ተወለደ።
የመጨረሻው ጥሪ
ይህ በአፍጋኒስታን ምድር ላይ የሚፈጸም እውነተኛ ሰቆቃ ነው። ሳሚኡላህ ዛሬም በዚያ ድንኳን ውስጥ አለ። ነገ የሚበሉት ይኑር አይኑር አይታወቅም። ነገር ግን ይህ ታሪክ ለዓለም ሕሊና የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
“እኛን አትዘንጉን!” ይላል የሳሚኡላህ አይን። “እኛ ቁጥር አይደለንም፤ እኛም እንደ እናንተ የምንርብ፣ የምንጠማ፣ የምንፈራና የምንወድ ሰዎች ነን።”
አፍጋኒስታን ዛሬም በበረዶ ተሸፍናለች። በዚያ በረዶ ስር ግን የሚሊዮኖች ጩኸት ተቀብሯል። ያ ጩኸት እንዲሰማ፣ የዓለም የቸልተኝነት ግድግዳ መፈራረስ አለበት።

ግራንድ ፕሮጀክት የሌለው ግራንድ ካባ
የአማራ ክልል ባለስልጣናት የሃሳብ ስንፈት እና
የሽልማት ድግስ ትዝብት
በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል የሚስተዋለው የባለስልጣናት እንቅስቃሴ በልማት ስኬት ሳይሆን እርስ በርስ በሚሰጣጡ "የካባ ሽልማቶች" ተውጧል።
ክልሉ በከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የመሠረተ ልማት መጓተት ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ሹማምንቱ በየመድረኩ በሚከናነቡት ካባ ብዛት መፎካከራቸው ብዙዎችን እያስገረመ ይገኛል።
1. የታቀደ "ግራንድ ፕሮጀክት" የሌለው ክልል
ለባለስልጣናቱ የሃሳብ ስንፈት ትልቁ ማሳያ በሃገሪቱ ቀጣይ ሊተገበሩ ከታቀዱ ግዙፍ (Grand) ፕሮጀክቶች መካከል አንዱም በክልሉ ውስጥ አለመኖሩ ነው።
የፌዴራል መንግስቱ በሌሎች አካባቢዎች ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የኃይል ማመንጫዎችንና የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን ሲያቅድ የአማራ ክልል መሪዎች ግን ክልላቸውን ወደ ብሔራዊ የልማት ካርታ የሚያስገባ አሳማኝ የልማት ፕሮጀክቶች ይዘው መቅረብ አልቻሉም።
ይህ ክፍተት የሚያሳየው ባለስልጣናቱ በቢሮዎቻቸው ተቀምጠው ስልታዊ ዕቅድ ከማውጣት ይልቅ በየአደባባዩ ለካሜራ እይታ የሚሆኑ የሽልማት ድግሶችን ማስቀደማቸውን እንደሆነ ይነገራል።
2. የካባ ፖለቲካ እና የሃሳብ ድርቀት
በክልሉ በሚዘጋጁ ፕሮግራሞች ላይ ከሚመጣ ባለስልጣን ጋር "ካባ መለዋወጥ" እንደ ትልቅ ስራ ተቆጥሯል ይህ ሁኔታ "የሃሳብ ስንፈት" ማሳያ እንደሆነ የሚገልጹ ተንታኞች፣ ባለስልጣናቱ አዲስ የሥራ ፈጠራ ሲሳናቸው በባህላዊ ሽልማቶች ሽፋን ስራ እየሰሩ ለማስመስል እንደሚሞክሩ ይገልጻሉ።
ካባውና እውነታው
አምስትና ስድስት ካባ ደርቦ መታየት ክብር ቢመስልም ከካባው ስር ያለው "ባዶ የልማት መዝገብ" ግን የክልሉን የልማት ጉዞ አዝጋሚ አድርጎታል።
3. "የጥምቀት ጥድፊያ"
እና የጎንደር የኮሪደር ስራ
የባለስልጣናቱ የአቅም ማነስ ሌላኛው ማሳያ የከተሞች ወቅታዊ ጥገና ነው ለምሳሌ የታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥምቀት በመጣ ቁጥር ብቻ መንገድ ለመስራትና የኮሪደር መብራቶችን ለመትከል ሲጣደፍ ይታያል።
ጥድፊያው በዓሉ ሊደርስ ጥቂት ቀናት ሲቀሩ የሚደረገው ሩጫ መብራቶች እንኳን ሳይደርሱና ስራው ጥራቱን ሳይጠብቅ እንዲከናወን ያደርገዋል።
የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከአንገታቸው በላይ የሚከመር ካባን ሳይሆን በመሬት ላይ የሚታይ የልማት አሻራን እንዲያስቀድሙ ይጠበቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክልሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ "ግራንድ ሃሳብ" ማመንጨት ካልተቻለ በየሳምንቱ የሚደረብ ካባ የክልሉን ድህነትና የባለስልጣናቱን ድክመት ከመሸፈን ይልቅ ይበልጥ አጉልቶ ያሳያል።
ሹማምንቱ ከልብስ ስፌትና ከካባ ግብዣ ወጥተው ወደ እውነተኛው የልማትና የፖሊሲ ስራ እንዲመለሱ የብዙዎች ምኞት ነው።

8 months ago
"ሰግጥና ፈምስ፤" cracking the algorithm code!
በፍቃዱ ዘኃይሉ !
ትላንትና ማታ፣ በአርትስ ቲቪ የቲክቶክ ክሪኤቲቭ አዋርድ ሲተላለፍ፥ በኢቲቪ ደሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር መንግሥት ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ እየተላለፈ ነበር። ዩቱዩብ ላይ የአርትስ ቲቪው 63 ሺ የቀጥታ ተመልካች ሲያገኝ፣ የኢቲቪው 700 ብቻ ነበረው። ይኼን ስጽፍ ያኛው 600 ሺሕ ተመልካች አልፎ፣ ይኼንኛው 6 ሺ ላይ ቆሟል። ይኼንን የተጋነነ ልዩነት ከፈጠሩት ምክንያቶች ዋነኛው አዶናይ እና ዩቲናስ የተባሉት የትልቁ ሽልማት እጩዎች ደጋፊዎች ባደረጉት ፉክክር ነው። ውድድሩ ከዕጩዎቹ በላይ የደጋፊዎቻቸው ነበር።
የስግጥና ሰሙ!
ሰገጤ የሚለው ቃል፣ ከዐሥር ዓመት በፊት እዚሁ ፌስቡክ ላይ ነበር "የፈመሰው።" ያኔ ራሳቸውን አራዳ ብለው የሰየሙ ፌስቡከሮች ሌሎችን የሚያጣጥሉበት ቃል ነበር። ዘንግታችሁት ይሆናል እንጂ ሸገር ነፃ አውጪ ግንባር (ሸነግ) የሚባል የቀልድ ንቅናቄ ተፈጥሮ ነበር። ሸነጎች ሌሎቹን ነፃ አውጪዎች በሙሉ ሰገጤ እያሉ ይጠሯቸው ነበር።
ሶሻል ሚዲያ እብደት ይወዳል። ቲክቶክ ደግሞ የባሰበት ነው። እናም ቲክቶክ ላይ "የሚፈምሱ" ሰዎች ከተለመደው ስርዓት እና ሁኔታ ወጣ ብሎ ትንሽ "ቀዌ" ነገር የሠሩ ናቸው፤ በድብቅ የሚደረጉ እና የሚታወቁ፣ ነገር ግን በአደባባይ የማይወሩ እና የሚያሳፍሩ፣ የሚያናድዱ እና የሚያስቆጡ ነገሮችን ማድረግና ማለት ነው። ብዙ ዝግጅት አድርገው ጥሩ የሠሩ ሰዎችም ተመልካች ያገኛሉ። ነገር ግን፣ የነዚህኞቹ ተከታይ የማፍራት ሒደት ትንሽ ሔዶ እንደሐውልት ቆሞ ይቀራል።
በዚህ መሐል ነው አዶናይ ነጥሮ የወጣው። "ሰግጥና ፈምስ" የሚለው ቃሉ መታወቂያ ሰንደቅ አላማው ሆኗል። መጀመሪያ እሱም ሲናገር ይህንን ያለ ይሉኝታ፣ ያለ ሐፍረት፣ ራስን መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ የሰውን ትኩረት ስለመሳብ ነው ያወራው። ምክንያቱም "መፈመስ" ረብጣ ያመጣል። እሱ ራሱ መጀመሪያ መሰገጥን እንደአማራጭ መፍትሔ ነበር ያቀረበው። ነገር ግን ልክ ያኔ በ2010 በጋራ ስናብድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋግመው ከሚጠቀሟት ቃል "መደመር" ጋር ሕዝቡ ፍቅር ሲይዘው፣ እርሳቸውም ከተራ ቃልነት ወደ "ፖለቲካዊ ፍልስፍናነት" እንዳዘዋወሯት፥ አዶናይም እንደዋዛ የተናገራትን "ሰግጥና ፈምስ" የሚለውን ወደ "ማነቃቂያ ንግግርነት" ሳያስፎግር ቀየራት።
አዶናይ እንዴት ሰገጠ?
ሰገጠ የሚለው ቃል አሁን አንድምታው ተቀይሯል። ያለይሉኝታ ማድረግ ያለብህን አድርገህ የተመልካች ትኩረት ግዛ እንደማለት ነው። አዶናይ የመጀመሪያ ሰሞን ሴቶችን የሚያንቆለጳጵሱና የሚያወድሱ ንግግሮችን በመናገር ነበር የቲክቶክን ቀልብ የሳበው። በኋላ ላይ "ገንዘብ ተቸግሬ ጎዳና ልወጣ ነው" ብሎ አወራና በጎ ፈቃደኞች ገንዘብ አዋጥተው ታደጉት። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ "ሴጋ" (ግለ ወሲብ) ብዙ ጊዜ እንደሚፈፅም አወራ። በነዚህ ጊዜዎች ውስጥ እየተቀለደበትም፣ እየታዘነለትም፣ እየተተቸም የቲክቶክን የቀልብ እርካብ እየወጣ ነበር። በስተመጨረሻ ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ፣ ተከታዮቹን በማስተባበር እርዳታ እና ትኩረት የሚሹ ሰዎችን በካሜራ ፊት መርዳት ጀመረ። ቁንፅል ሃይማኖተኝነት እና ከታዋቂ ሰዎች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባትም አንዱ የመሰገጥ ፍልስፍና ነው። ሁሉም ለሱ ትኩረት አስገኘለት። ሕይወቱ በአደባባይ ነው። በተቻለው መጠን አነጋጋሪ እና ብዙዎች የሚወዱትን ወይም የሚያወሩለትን ነገር በየቀኑ ያደርጋል። በዚህም በየቀኑ መቶ ሺሕ ተከታዮችን ማፍራት ጀመረ።
በተቃራኒው፣ በትወና ጥበብ ይዘቶችን የምትፈጥረው ዩቲናስ ቆማለች። እሷም ከቀደምት ቲክቶከሮች አንዷ ናት፤ ላይቭ እየገባች ትኩረት የሚያስገኙ ነገሮችን ያደረገችበት "ኤፕሶዶች" አሏት። ሆኖም፣ የምትሠራቸው ሥራዎች ቁጣ ወይም ትዝብት ያስከተሉ ከመሰላት ትሰበሰባለች። ለምትሠራቸው አጫጭር ትወናዎች ብዙ ወጪ ታወጣለች፣ ብዙ ዝግጅት ታደርጋለች፣ ወዘተ። እያደር እየበሰለች እና እያደገች ነው የመጣችው። ነገር ግን የግል ሕይወቷን እምብዛም አናውቅም፣ አታሳየንም። የምንስቅባት፣ እንድንናደድባት፣ ወይም እንድንተቻት የሚያደርጉ ሥራዎችን አትሠራም (በአሁኑ ቋንቋ አትሰግጥም) ስለዚህ የመጀመሪያዋ ሚሊዮን ተከታይ አፍሪ ብትሆንም፣ ሌሎች ከኋላዋ እየመጡ አልፈዋታል።
አዶናይ እና ዩቲናስ ለመኪናው ሽልማት እጩ ከሆኑ በኋላ በግል ምንም ኃይለ ቃል አልተለዋወጡም። ጦርነቱ የነበረው በደጋፊዎቻቸው እና አድናቂዎቻቸው ነበር። በዚህ መሐል አዶናይ እዚህም እዚያም እየሔደ አጀንዳ መሆኑን አጧጧፈው። ዩቲናስ ግን ከውዝግብ ራሷን ለማራቅ ጣረች። በዚህ ምክንያት የሱ ደጋፊ በረከተ። ይህም ለአዶናይ ቢያንስ የሽልማቱን መንበር አቆናጥጦታል።
የስግጥና ወርቁ!
ስግጥና ተብሎ እየተሸጠ ያለው ነገር በሁለት ቃላት ይገለጻል፤ ማስቆጣት (outrage) እና ተጋላጭነት (vulnerability)። የአዶናይ እያንዳንዱ እርምጃ እነዚህ ሁለቱ ናቸው። ዮኒማኛ ከሃይማኖት ሃይማኖት የሚንዛለለው፣ ጂጂ ኪያ ከልጇ ጋር ወንድ ስለመቀማማት የምታወራው ከነዚህ ሁለቱን ለማግኘት ነው። ሶሻል ሚዲያ፣ በተለይም ቲክቶክ እነዚህን - ሌሎችን ማበሳጨት ወይም ራስን ማጋለጥ - ከሰጣችሁት ዝናችሁን ሰማይ ይሰቅለዋል። ከዛ በኋላ ዝናችሁን እንዴት እንደምትጠቀሙበት እናንተው ትወስናላችሁ። አዶናይ እየቆመረ ያለው "there is no such thing as bad publicity" (መጥፎ ዝና የሚባል ነገር የለም) በሚል ፈሊጥ ይመስላል። ዝናውን ለበጎ አድራጎት እያዋለው ለማሳየት ይሞክራል። ነገር ግን ይህ አካሔድ ዘላቂ አይመስለኝም። ተከታዮቹ ተጨማሪ የሚያስቆጣ ነገር፣ ተጨማሪ ራስን አጋልጦ ማቅረብ፣ ተጨማሪ ከሌሎች ጋር የሚደረግ እሰጥ አገባ ይፈልጋሉ። እነዚህን ነገሮች በሙሉ ተምኔታዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ ካልቻለ ተመልካቾቹ ወደ አዲሱ ትርዒት ይዞራሉ፤ ይህንን ማድረግ ከቻለ ደግሞ የግልና የተረጋጋ ሕይወት የሚባለውን ነገር መሰናበት አለበት። አልጎሪዝሙ የሚፈልጋችሁ፣ ስትጋለጡ ወይም ስትባልጉ ብቻ ነው።

9 months ago
ዮም
ንሴብሖ ፍቅሬ
አሰናኝ፡፦ ጥላሁን ክፍሌ እርገጤ
#ethiopia | በተለያዩ ጊዜያት፣ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት፣ ከተለያዩ ቤተሰቦች የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ይወለዳሉ፡፡ በስልጣኔና በአመለካከት የበለጸጉት ሀገራትም ኦቲዝምን እንደአንድ የተፈጥሮ ጸጋ በመቀበል በኦቲዝም ጥላ ሥር ለመኖር ዓለማችንን የተቀላቀሉትን ህጻናት እንደየፍላጎታቸው ተንከባክበው በማሳደግ፣ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ለሚኖሩባት ዓለም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ይሠራሉ፡፡
በእርግጥ ከዓለማችን ሀገሮች ብዛት አንጻር በዚህ መልኩ የሚተጉት ጥቂት ናቸው፡፡ ቀላል ቁጥር የማይዘው የዓለማችን በተለይም የሀገራችን ማህበረሰብ ኦቲዝምን ድጋፍና እንክብካቤ የሚሻ እክል አድርጎ ከመቁጠር ይልቅ፣ “ርግማን” እንደሆነ አምኖ ይህንኑ የሚያስተጋባ ነው፡፡
የበኩር ልጃችን ዮም ንሴብሖ፣ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ እያደረግናቸው ያሉትን ወሰን አልባ ጥረቶች በመጽሐፍ ሰንዶ ለአንባቢያን ለማድረስ መነሳቱን ከተፈጠሩት ምክንያቶች አንዱም ኦቲዝምን በሚመለከት ያለን መረዳት ለማረቅ መሻት ነው፡፡
በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን የተዛባ አረዳድ በማስተካከል ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖር የሚረዳ ተጠቃሽ መጽሐፍ' ካበረከተው ከዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ጋር በዮም ምክንያት በተደጋጋሚ የመገናኘት አጋጣሚ ነበረኝ።
ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ዶክተር ዮናስ፣ “የሕይወት ተሞክሮህ በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለአንባቢ ቢቀርብ ብዙ ነገር ሊያስተምርይችላል" በሚል የሰነዘረው አስተያየት ልቤን ሰቅዞ ይዞት፣ ለረጅም ጊዜ ሳስብበት ቆየሁ:: የዶክተር ዮናስ ሃሳብ በልቤ ውስጥ ብቻ አልቀረም:: ከወዳጄ እና አብሮ አድጌ ጥላሁን ክፍሌ ጋር በመሆን ይህንን በእጃችሁ ላይ የሚገኘው መጽሐፍ እንዲወለድ ሆነ፡፡ በእርግጥም ምጡ ቀላል አልነበረም!
ከጥላሁን ጋር መጽሐፉን ለማዘጋጀት በምንተጋበት ጊዜ፣ እጅግ የሚወዳቸውና የሚሳሳላቸው እናቱ ወ/ሮ ጥሩወርቅ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ፡፡ በዚህ ሁኔታ የመጽሐፉን ዝግጅት ማስቀጠል፣ ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ እናቱን ለሚያስታምመው ጥላሁን ከባድ ነበርና፣ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቋረጥ ሆነ:: ሆኖም የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና፣ ለአምስት ወራት ያህል በሕክምና ሲረዱ የቆዩት እናቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ፡፡ ጥላሁን ክፍሌን የሚያውቅ ማንም ሰው እናቱን ያውቃል፧ ሁለቱን የሚያውቅ ደግሞ በመካከላቸው ያለውን የተለየ ፍቅር ያውቃል:: ያን ጊዜ፣ ጥላሁን የቀድሞው ጥንካሬ እና ሞራል ኖሮት ይህን ሥራ እንጨርሰዋለን
ምክንያት አለው ብዬ ራሴን አሳመንኩ። እንዴት ይበረታ ይሆን? እያልኩ ብጨነቅም ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና አጽናኝ መላእኩን ልኮ እኒያን ጥቋቁር የሐዘን ቀናት በጸጋው አሳለፋቸው:: ብርቱው ባለተሰጥኦ ጥላሁንም በሚያስደንቅ ትጋትና ብርታት መጽሐፉን አጠናቆ እነሆኝ አለኝ፡
ባሳለፍኩት የሕይወት መንገድ ያጋጠሙኝን የደስታም ሆነ የሐዘን፣ የከፍታም ሆነ የዝቅታ፣ የስኬትም ሆነ የመፈተን ውጣ ውረዶችን በዚህ መጽሐፍ ለማጋራት ሞክሬአለሁ፡፡ በተለይም ልጃችን ዮም ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ መሆኑን ካወቅንበት ዕለት ጀምሮ እኔና ቤተሰቤ መፍትሔና ፈውስ ፍለጋ፣ የወጣን የወረድንባቸው ጎዳናዎች፣ ያንኳኳናቸው ደጆች፣ የገፋናቸው የመከፋትና የመፈተን ወራት እና ለዐይን ጥቅሻ ዕድሜ እንኳን ከጎናችን ባልተለየንና ይልቁንም ከፊታችን ይቀድም በነበረው እግዚአብሔር የቻልናቸውን ስኬቶች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታነባላችሁ፡፡
ከሕይወት ልምዴ ከተወሰደ ቀጥተኛ ተሞክሮ በተጨማሪ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከንባብ እና በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ካላቸው ወላጆችም ጋርበነበረኝ ማኅበራዊ ግንኙነቶች የተረዳኋቸውን ግንዛቤዎች በመጽሐፉ ለማካተት ሞክሪያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኦቲዝምን በተመለከተ ህብረተሰባችን ያለው ግንዛቤ በአብዛኛው የተዛባ ነው፡፡ ይህም ወላጆች/አሳዳጊዎች ሊሻሻል በሚችለው በዚህ የአእምሮ ዕድገት እክል የተጠቁ ልጆቻቸውን ለማገዝ የሚችሉትን እንዳያደርጉ፣ በዚህም የእነሱና የልጆቻቸው ስቃይ ቀጣይና ማብቂያ የሌለው እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይህ መጽሐፍ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆች ላላቸው ወላጆች እና በኦቲዝም ሳቢያ የሚፈጠሩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም ለመላው ማኅበረሰባችን የተሻለ ግንዛቤን በማስጨበጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡
መጽሀፉ በአራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ ዮም ከመወለዱ በፊት የነበረኝን ህይወት በመጠኑም ቢሆን የሚያስቃኝ ነው:: ሁለተኛው ምዕራፍ የመጽሃፉ ዋና አስኳል ሲሆን ይህም ዮም ከተወለደ ጀምሮ ይህ መጽሀፍ እስኪዘጋጅ ድረስ የተኖረውን ዋና ዋና የህይወት ክፍል ይዳስሳል:: ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ልጆቻቸው በኦቲዝም የተጠቁ እና በእኔ ማህበራዊ ህይወት ዙሪያ የነበሩ ወላጆች ቅንጫቢ ታሪኮች ስብስብ ነው:: በመጨረሻው ምዕራፍ ከእኔ የህይወት ልምድ እና ትዝብት በተጨማሪ በኦቲዝም ዙሪያ ከተለያዩ ምንጮች የቃረምኳቸው ጠቃሚ እውነታዎች ተገልፀዋል:: በእኔ እና በልጄ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ለበጎ አላማና ተግባር የተዘጋጀውን ይህን መፅሃፍ በአክብሮት ታነቡልኝ ዘንድ የምጋብዛችሁ በፍፁም ትህትና ዝቅ ብዬ ነው፡፡
መልካም ንባብ!
ንሴብሖ ፍቅሬ ወንድማገኝ
***
አቶ ንሴብሖ ፍቅሪ ከባለቤቱ ጋር በመሆን የኦቲዝም ተግዳሮት ያለበትን ልጃቸውን በመንከባከብ ያለፉበትንና እያደረጉ ያለውን ልምድ ለህብረተሰቡ ለማካፈል ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀቱ እጅግ እመሰግነዋለሁ።
ጥንዶቹ ባጋጠማቸው ተግዳሮት ተስፋ ላይቆርጡ ስለሁኔታውና መወለድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች በራሳቸው ጥረት ተረድተው አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ በፍጹም ፍቅር እያደረጉ መገኘታቸው የሚደነቅ ነው።
ይህ ልምዳቸውም በመጽሐፍ መታተሙ፣ ተመሳሳይ ተግዳሮት በቤተሰባቸው ውስጥ ኖሮ ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ለተጋቡና፣ ምናልባትም የማይገቡ እርምጃዎችን ለሚተገብሩ ቤተሰቦች ተገቢውን መንገድ በማመላከት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።
በህብረተሰቡ ውስጥ ከሚወለዱ እንድ መቶ ህፃናት አንዱ ወይም ሁለቱ የኦቲዝም ተግዳሮት የሆነ የነርቭ እና የእድገት ልዩነት ሊያጋጥማቸው ይችላል ፤ ነገሩ እጣ ነው። እጣው በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛችንም ቤት ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ሁላችንም በተጨባጭ ልምድ ከካበተው ንሴብሖና ቤተሰቡ በመማር ስለጉዳዩ እውቀት እንዲኖረን እመክራለሁ። ለዚህም የዚህ መጽሐፍ አስተዋጽኦ የጎላ ነው።
ዶ/ር ምኒልክ ደስታ
የአዋቂዎችና ህፃናት አእምሮ ሐኪም
***
ልጆቻቸው የኦቲዝም ችግር ያለባቸው በርካታ ወላጆች ፣ የሰዎችን አላዋቂ አንደበትና መገለል በመፍራት የልጆቻቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ችግርና ስቃይ በሚደብቁበት ወቅት፣ ንሴብሖ የኦቲዝም ተጠቂ የሆነውን ልጁን ችግርና የቤተሰቡን ውጣ ውረድ በመጽሐፍ መተረኩ የሚያስመሰግነው ነው።
እርግጥ ነው ንሴብሖ በልጁ ዮም ምክንያት በብዙ መረበሸ፤ እንቅልፍ ማጣት፤ ማህበራዊ መገለል ተከብቦ ያሳለፈውን ህይወት እና የከፈለው ዋጋ ቀላል አልነበረም፤ ይህም ሆኖ "የዮም መፃኢ እድል ፈንታ ምን ይሆን?'' የሚለው ከባድ የሃሳብ ሸክም አሁንም ከትከሻው አልወረደም።
ይህ ግለ ታሪክ በዚህ ችግር ውሰጥ የምናልፍ ቤተሰቦችን ችግሮች ገልጦና አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ፣ መጽሐፉን ልዩ የሚያደረገው ዋናው ነገር እንደተለመደው ስለ ችግሩ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎች ሳይሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ በሆነ አባት መቅረቡ ነው።
መልዕክቱ የኦቲዝምን ችግር እየተጋፈጡ ላሉ ቤተሰቦች አስተማሪና ጉልበትን የሚሰጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ተጋብተው መውለድ ለሚያቅዱ ጥንዶች፣ ለእምነትና ለትምህርት ተቋማት፣ በኦቲዝም ላይ ለሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ ጥልቅ ግንዛቤን በማስጨበጥ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው።
ይህንን መጽሐፍ ሳነብ ፣ በፈተና ውስጥም ሆነን በጎ ማሰብና ፣ ከችግራችን በላይ በሆነ ጠንካራ ማንነት መታነጽ እንደሚቻል አይቻለሁና ሁሉም እንዲያነበው እመኛለሁ።
ዶ/ር ፍርድአወቀ ማሞ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
***
ለብዙዎቻችን ፈተና (መከራ) ሁልጊዜ የኃጢአት ውጤት ይመስለናል። አንድ ሰው ጤናን፣ ሀብትን፣ ልጅንና የመሳሰሉትን ሲያጣ እግዚአብሔር በኃጢአቱ እየቀጣው ነው ብለን እንደመድማለን፡፡
አቶ ንሴብሖ ፍቅሬና ባለቤቱ ወይዘሮ ሳምራዊት ድንቁ ፈተናን በመጋፈጥ የጽናት ተምሳሌት ሆነውናል… አቶ ንሴብሖ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆችን ለሚያሳድጉ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ጉልበትን የሚሰጥ፣ ጥበብን የሚያመላክት ሥራን መሥራቱ ደስ ያሰኛል።
ይኸውም ያላዋቂዎችን ትችት በመፍራት በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ያሉ ወገኖችን ከማግለል ይልቅ ማቀፍና መንከባከብ፣ ሰብአዊና ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን በመጽሐፍ ሰንዶ በማቅረቡ ሊመሰገን ይገባል።
በብዙ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ንሴብሖ አሁንም አምላኩን አመስጋኝ መሆኑ ሌላው በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ይህንን መጽሐፍም ማንበብ ለሁሉም፣ በሁሉ መንገድ አቅም ይሰጣል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
***
ንሴብሖ ፍቅሬ
ስልክ
+251911212012
ኢ-ሜይል
yomnesebehogmail.com

የሀገሩን ጥሪ አልቀበልም ያለው የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች መነጋገሪያ ርዕስን ከፍቷል
#ethopia | ፌዴሪኮ ኪዬዛ የሀገሩን ጣልያን ብሄራዊ ቡድን ጥሪ አልቀበልም ማለቱን የአዙሪዎቹ አለቃ ጂናሪዮ ጋቱሶ በይፋ አሳውቋል።
ኮቬርሲያኖ በሚገኘው እና ብሄራዊ ቡድኑ በሚሰበሰብበት ቦታ ላይ መግለጫ የሰጠው የአዙሪዎቹ አለቃ እና የቀድሞ አስደናቂ ታጋይ አማካኝ መስመር ተጫዋች የሆነው ጂናሪዮ ጋቱሶ በስብስቁ ውስጥ ለምን ለፌዴሪኮ ኪዬዛ ጥሪ አልቀረበም ለሚለው ጥያቄ ጥሪው ደርሶታል ፤ በግል ጉዳዮች ምክንያት መካተት እንደማይፈልግ ነው የነገረን ሲሉ ተደምጠዋል።
ጣልያን ባለችበት ምድብ ኖርዌይ ምድቡን እየመራች እንደምትገኝ ይታወቃል። እስካሁን ከእንግሊዝ ውጪ ለ2026ቱ የአለም ዋንጫ ቲኬት መቁረጧን ያረጋገጠች ሀገር የለችም። ታዲያ የ4 ጊዜ የአለም ዋንጫ እንዲሁም የ2 ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ሀገር ጣልያን በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ላይ መሳተፏን ለማረጋገጥ ከሞልዶቫ እና ኖርዌይ ጋር ተጠባቂ ጨዋታዎቿን ታደርጋለች።
ለነዚህ ተጠባቂ ጨዋታዎች ደግሞ ቁልፍ የሚባሉ ተጫዋቾች ያስፈልጋሉ ፤ ኪዬዛም አንዱ ነው ፤ ሀገሩ በዚህ ወሳኝ ሰአት ስትፈልገው በግል ምክንያቶች በሚል ጥሪውን ያልተቀበለበት መንገድ በብዙዎች ተጫዋቹ ትዝብት ውስጥ እንዲገቃ አድርጎታል።
አሰልጣኝ ጋቱሶ ታክቲካል ወይም physical assessment ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጥቀስ ተጫዋቹ በራሱ ፍላጎት ጥሪውን እንዳልተቀበለ ተናግሯል ፤ እንግዲህ ተጫዋቾች የሚሉትን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለንም ሲልም አያይዞ ሀሳቡን ሰጥቷል።
ጣልያን በአለም ዋንጫ መሳተፏን የምታረጋግጥ ከሆነ ኪዬዛ ጥሪ ይቀርብለታል የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነወ። በርካታ የእግርኳስ ቤተሰቦች በክለቡ ደረጃ እንኳን የመሰለፍ እድልን ከስንት አንድ ጊዜ የሚያገኝ ተጫዋች የትኛውም የግል ምክንያት ቢኖረው ጥሪውን የመቀበል ግዴታ ነበረበት የሚል ሀሳብ እንዲያነሱ እያስገደዳቸው ይገኛል። ሀገሩ ስትፈልገው ካልተገኘ ፤ ሀገሩ ለአለም ዋንጫ ስታልፍ ጥሪ ሊደርሰው እንደማይገባ ሀሳቦችን እያሰፈሩ ይገኛሉ ሲል መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Comments