"የመንገድ ትዝብት" ~ ሰለሞን ኦሊ
#ethiopia | ዛሬ ጠዋት ኮዬ ወደ ጎሮ የሚወስደዉ መንገድ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ አንድ ከባድ የመንገድ ሥራ ማሽን በሚኒባስ ታክሲ ላይ ወድቆ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት አሳዛኝ አደጋ ተከስቷል::
ይህን ዓይነት አደጋ በ“ሾፌሩ ስህተት”፣ “የማሽኑ ብልሽት” ወይም “የመንገድ ሁኔታ” ብቻ መግለጽ በቂ አይደለም። የሚጠየቀው ጥያቄ፦
1. የመንገድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የአደጋ ግምገማ ያስፈልጋል
ማንኛውም የመንገድ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው:-
👉የሥራ ቦታው ምን ያህል የትራፊክ እንቅስቃሴ አለው?
👉ሠራተኞች ከተሽከርካሪ ጋር የመጋጨት አደጋ አለ?
👉ከባድ ማሽኖች ከሕዝብ ትራፊክ ጋር የሚገናኙት የት ነው?
👉የማሽን ክፍል ወደ ሕዝብ መንገድ ሊወድቅ ይችላል?
👉የመንገዱ አንድ ክፍል ቢዘጋ ትራፊኩ እንዴት ይመራል?
👉እግረኞች እንዴት ይጠበቃሉ?
👉አምቡላንስ ወይም የእሳት አደጋ መኪና እንዴት ይደርሳል?
ይህ የአደጋ ግምገማ ከሥራ በፊት ብቻ ሳይሆን የሥራው ሁኔታ ሲቀየር በየጊዜው መዘመን አለበት።
2. የጊዜያዊ ትራፊክ አስተዳደር ዕቅድ ያስፈልጋል
የመንገድ ሥራ በሚካሄድበት ጊዜ ትራፊክ እንዴት እንደሚቀጥል ከመጀመሪያው መወሰን አለበት።
የዕቅዱ አካላት:-
👉የሥራ ቦታ አቀማመጥ
👉የመንገድ መዘጋት
👉የመኪና መስመር መቀነስ
👉የትራፊክ ማዞሪያ
👉ጊዜያዊ ምልክቶች
👉የፍጥነት ቁጥጥር
👉የእግረኛ መንገድ
👉የከባድ ማሽን መግቢያና መውጫ
👉የአደጋ ጊዜ መድረሻ
👉 የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች
👉የአደጋ ምላሽ ሥርዓት
3. የሥራ ቦታ ከሕዝብ ትራፊክ መለየት
በመንገድ ሥራ ቦታ ላይ ኮኖችን መትከል ብቻ በቂ አይደለም።
እንደ ሁኔታው:-አጥር፣መከላከ፣የትራፊክ ምልክቶች፣የጊዜያዊ መንገድ መስመሮ፣አንጸባራቂ ምልክቶች፣የማታ መብራቶች እና የአደጋ መከላከያ ባሪየሮ መጠቀም ይገባል።
የሥራ ቦታው ለአሽከርካሪው ግልጽ፣ ቀድሞ ሊታይ የሚችል እና የማያሳስት መሆን አለበት።
4. የፍጥነት ቁጥጥር
በመንገድ ሥራ ቦታ የፍጥነት ቁጥጥር በጣም ወሳኝ ነው።
ምልክት ብቻ መትከል አይበቃም። አሽከርካሪው በቂ ርቀት ቀድሞ እንዲያውቅ፣ ፍጥነቱን እንዲቀንስ እና በሥራ ቦታው በደህንነት እንዲያልፍ የተቀናጀ ሥርዓት ያስፈልጋል።
5. ከባድ ማሽኖች ለብቻቸው የእንቅስቃሴ ዕቅድ ሊኖራቸው ይገባል
ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ቡልዶዘር ወይም ሌላ ከባድ ማሽን ከሥራ ቦታ ወደ ሌላ ሲጓጓዝ ወይም ወደ ሥራ ቦታ ሲገባ የራሱ የእንቅስቃሴ ዕቅድ ሊኖረው ይገባል።
በተለይ፦
መጫን 👉መቆለፍ 👉ማሰር 👉 መፈተሽ 👉መጓጓዝ 👉ወደ ሥራ ቦታ መግባት እያንዳንዱ ደረጃ በቁጥጥር ሥር መሆን አለበት።
ኤክስካቫተር በሚጓጓዝበት ጊዜ ተንቀሳቃሽ ክፍሎቹ በትክክል መቆለፍ፣ በተገቢው የማሰሪያ መሳሪያ መጠበቅ እና ከመነሳቱ በፊት ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት።
Hydraulic ስርዓት ብቻ ላይ መተማመን በቂ አይደለም።
6. የጭነት ማሰሪያ በራሱ የደህንነት ስርዓት ነው
የከባድ ማሽን ክፍል በመንገድ ላይ ከተለቀ ወይም ከወደቀ ውጤቱ ከባድ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ የማሰሪያ ሰንሰለቶችና ሌሎች መሳሪያዎች፦
👉የጭነቱን ክብደት ሊቋቋሙ የሚችሉ
👉በተገቢ ቦታ የተያያዙ
👉 የማይበላሹ
👉የማይለቀቁ
👉በጉዞ ወቅት እንደገና የሚፈተሹ
መሆን አለባቸው።
7. እግረኞችን መርሳት የለብንም
የመንገድ ሥራ ዕቅድ መኪናን ብቻ ማስተናገድ የለበትም።
እግረኞች፣ ብስክሌተኞች፣ ሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች በዕቅዱ ውስጥ መካተት አለባቸው።
የእግረኛ መንገድ ከተዘጋ ደህንነቱ የተጠበቀ ጊዜያዊ መንገድ መሰጠት አለበት።
8. በሥራ ቦታ የማሽንና የሰው እንቅስቃሴ መለየት
በኤክስካቫተር ዙሪያ የሚንቀሳቀስ ሰው ለአደጋ በጣም ተጋላጭ ነው።
በሚያስፈልግበት ጊዜ ማሽኑን የሚመራ የመሬት ላይ አስተባባሪ መመደብ እና ማሽኑ የሚሰራበትን የአደጋ ክልል መለየት ያስፈልጋል።
9. የአደጋ ጊዜ ዕቅድ
አደጋ ከተከሰተ በኋላ ምን እናድርግ? የሚለው ጥያቄ ከአደጋው በፊት መመለስ አለበት።
የአደጋ ጊዜ ዕቅድ፦
ማስጠንቀቅ 👉 ትራፊክ ማቆም/መቆጣጠር 👉 አደጋውን መለየት → የሕክምና እርዳታ 👉 የእሳት አደጋ/ማዳን 👉ፖሊስ👉መንገዱን መልሶ ማስኬድየሚል ግልጽ ሂደት ሊኖረው ይገባል።
10. የሥራ ቦታ በየጊዜው መመርመር
የTraffic Management Plan አንድ ጊዜ ተዘጋጅቶ በፋይል ውስጥ የሚቀመጥ ሰነድ ብቻ መሆን የለበትም።
“ዕቅዱ አሁንም የሥራ ቦታውን ደህንነት ያረጋግጣል?” ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።
11. ኃላፊነት በአንድ ሰው ላይ ብቻ አይጣልም
እንዲህ ያለ አደጋ ሲከሰት በአንድ ሾፌር ወይም ኦፕሬተር ላይ ብቻ ጥፋተኝነትን መጫን የስርዓቱን ችግር ሊደብቅ ይችላል። መመርመር ያለበት፦
ባለማሽኑ👉ኮንትራክተር 👉 የማጓጓዣ አካል 👉ሾፌር 👉የሥራ ቦታ አስተዳደር
12. የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪም ሚና አለው
ኢንሹራንስ ማለት አደጋ ከተከሰተ በኋላ ገንዘብ መክፈል ብቻ አይደለም።
‘’የመንገድ ሥራ የሚለካው በተሰራው ኪሎሜትር ብቻ ሳይሆን፣ ሥራው በምን ያህል ደህንነት እንደተከናወነ ጭምር መሆን አለበት።’’
ሰሎሞን ኦሊ
የኢንሹራንስና ሪስክ ማኔጅመንት አማካሪና ባለሙያ ተፃፈ #roadsafety #roadworksafety #trafficmanagement #riskmanagement #constructionsafety #ethiopia #insurance #publicsafety #roadinfrastructure

1 month ago