5 months ago
በአዲስ አበባ የግንባታ ዘርፍ የሠራተኞችን ደኅንነት የሚያስከብር አዲስ መመሪያ ሊተገበር ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄዱ የሕንፃ ግንባታዎች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችንና የሕይወት መጥፋትን ለመቀነስ፣ የግንባታ ባለቤቶች (አስገንቢዎች) የሠራተኞችን ደኅንነት የሚከታተል ባለሙያ እንዲቀጥሩ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዳስታወቀው፣ ይህ መመሪያ ማንኛውም አስገንቢ ልክ እንደ አማካሪና ኮንትራክተር ሁሉ በዘርፉ የሠለጠነ የደኅንነት ባለሙያ እንዲመድብ ያስገድዳል። 17 ነጥቦችን የያዘው ይህ ሰነድ፣ የግንባታ አካባቢዎች በደኅንነት መረብ እንዲሸፈኑ እንዲሁም ሠራተኞች እንደ ራስ ቆብ (Helmet)፣ የደኅንነት ጫማ፣ ጓንትና አንጸባራቂ ልብሶችን በግዴታ እንዲጠቀሙ የሚያዝ ነው።
ባለሥልጣኑ ለዚሁ ተግባር እንዲውል በ2018 በጀት ዓመት 2,000 ባለሙያዎችን ለማሠልጠን አቅዶ፣ እስካሁን ከ800 በላይ የሚሆኑትን ማሠልጠኑ ተመላክቷል።
ይህ ጥብቅ መመሪያ አስፈላጊ የሆነው ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ በግንባታ ቦታዎች ላይ በሚከሰቱ ጥንቃቄ የጎደላቸው አደጋዎች የ142 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል ያለው ስፑትኒክ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #addisababa #constructionsafety #ethiopianews #safetyfirst #urbandevelopment #buildingregulation #ethiopia

Comments