17 hours ago
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

20 days ago
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሥነ ጽሑፍና በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ የማይረሳ አሻራ ያሳረፉትን ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ለመዘከር የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቤተሰብ አባላት፣ የአካዳሚው አመራሮች፣ ምሁራንና የተለያዩ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ እንደገለጹት፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ከ24 በላይ መጻሕፍትን በመጻፍ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ መሠረት ከጣሉ ሊቃውንት አንዱ ሲሆኑ፣ በዲፕሎማሲ፣ በባንክ ሥርዓት፣ በቴአትር፣ በቀይ መስቀል ማኅበር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘርፎችም የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባልነት እንድትቀላቀል በተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ ከአምባሳደርነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገራቸውን በታማኝነት ማገልገላቸው ተጠቅሷል።
አካዳሚው ታሪካዊ መኖሪያ ቤታቸውን በቅርስነት በመጠበቅ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ እየተጠቀመበት ሲሆን፣ የግል ሰነዶቻቸውን፣ ፎቶግራፎችን፣ መጻሕፍቶችንና ሌሎች ቅርሶችን የያዘ ቋሚ ሙዚየምም ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል።
ሐውልቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእይታ ጥበብ ባለሙያ ሠዓሊ ኢዮብ ኪታባ እና በቡድናቸው የተቀረጸ ሲሆን፣ ለሥራው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የልጅ ልጅ ልጅ ወይዘሮ ገነት ኅሩይ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ የመታሰቢያ ሐውልት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን ታሪካዊ አስተዋጽኦ ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።
#ethiopia #scienceacademy #blatengetahruy #history #heritage #getutemesgen #ጌጡተመስገን

1 month ago
አድናቂም ወዳጅ ይሆናል!
ጊዜው በ90 ዎቹ መጀመሪያ ግድም ነው፡፡ በቢሾፍቱ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ሳለን በሀገራችን ታዋቂ ከሚባሉት የሙዚቃ ባንዶች አንዱ የሜጋ አምፊ ቲያትር ራሚድ ባንድ ነበር።
አንድ ቀን ዝነኛው ራሚድ ባንድ የሙዚቃ ድግሱን ለማቅረብ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ቢሾፍቱ መጥቶ ነበር፡፡ ከባንዱ ጋር ዝግጅታቸውን ሊያቀርቡ ከመጡት ተወዳጅና ታዋቂ አርቲስቶች መካከል፡- ላፎንቴኖች ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ መልካሙ ተበጀ ፣ ጀማል መሀመድ(አቺኩዳ)፣ ፀደንያ ገ/ማርቆስ ፣ ማናልቦሽ ዲቦ፣ ደረጀና ሀብቴ፣ጥላሁን እልፍነህ ፣ ዘውዱ በቀለና ፊሊፕ ማርቲን ይገኙበታል፡፡
የሙዚቃ ዝግጅቱን ለመታደም የከተማችን ነዋሪ በወረፋ ነበር ወደ አዳራሹ የገባው፡፡ እኔም ዝግጅቱን በገጉት ሲጠባበቁ ከነበሩት መካከል አንዱ ነኝ፡፡ አርቲስቶችን ለማስፈረም ሁሉ በኪሴ በቂ ወረቀቶችን ይዤ ነበር የገባሁት፡፡ በወቅቱ ሁሉንም አርቲስቶች የማደንቅ ቢሆንም፣ በተለይ ደግሞ ኮሜዲያን ደረጀንና ሃብቴን ለማየትና ከተቻለም ለማስፈረም በእጅጉ ጓጉቼ ነበር።
በመጨረሻም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ታላቅ የሙዚቃ ድግስ በይፋ ተጀመረ፡፡ እውነት ለመናገር አንድም ቤቱ የቀረ የቢሾፍቱ ነዋሪ ያለ አይመስልም ነበር፡፡ በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ የምናቃቸው ተወዳጅና ዝነኛ ድምጻውያን በየተራ መድረክ ላይ እየወጡ አቀነቀኑ፡፡ ታዳሚው አብሯቸው እየዘፈነ እንደጉድ ጨፈረ፡፡ አዳራሹን በአንድ እግሩ አቆመው፡፡
የመድረክ አጋፋሪው ጥላሁን እልፍነህ፣ በመቀጠል ሥራቸውን የሚያቀርቡት ሁለቱ ተወዳጅ ኮሜዲያን እንደሆኑ ሲያስተዋውቅ፣ ታዳሚው በጩኸትና በፉጨት ደስታውንና ፍቅሩን ገለጸ፡፡ ደረጀና ሃብቴም ወደ መድረኩ ወጥተው በማያልቀው ቀልዳቸውና ለዛቸው አዳራሹን በሳቅ ሞሉት፡፡
ሥራቸውን አቅርበው እንደጨረሱ ከተጠገጠገው ሰው መሃል እንዴት ተፈትልኬ እንደወጣሁ ሳላውቀው፣ ራሴን መድረኩ አጠገብ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አሻቅቤ ወደ ደረጀና ሃብቴ እየተመለከትኩ፣ "ፈርሙልኝ" አልኳቸው - ያዘጋጀሁትን ወረቀት ዘርግቼ፡፡ አንዳቸው ስሜን ጠየቁኝ፡፡ ነገርኳቸው፡፡ ከዚያም ከመድረኩ ጀርባ (ባክ ስቴጅ)ይዘውኝ ገቡ። እዚያ ሌሎችም ታዋቂ አርቲስቶች ነበሩ፡፡ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ሁሉንም አስፈረምኳቸው፡፡
ተልዕኮዬን አጠናቅቄ ከመሄዴ በፊት ግን ኮሜዲያን ሀብቴ ምትኩ ለእነርሱ ከተዘጋጀው ሳንዱች ላይ አንስቶ እንድበላ ጋበዘኝ፡፡ በጣም ነበር ደስ ያለኝ፡፡ በአንዳች በማላውቀው ስሜት ተጥለቅልቄ ነበር፡፡ በቲቪ ብቻ እያየኋቸው የማደንቃቸውና የምወዳቸው ደረጀና ሀብቴ፣ የቅርብ ጓደኞቼ የሆኑ ያህል ተሰምቶኝ ነበር ብል ፈጽሞ አላጋነንኩም፡፡
ከዚያን ጊዜ በኋላ ታዲያ ደረጀና ሃብቴ እንዲሁም ሌሎች አርቲስቶች የፈረሙልኝን ወረቀት ት/ቤት ድረስ በመውሰድ ለጓደኞቼ እያሳየሁ፣ "ደረጃዬን" እንዲያውቁልኝ እጋጋጥ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ "እኔኮ ከደረጄና ሃብቴ ጋር ጓደኛ ነኝ" እያልኩኝ፣ አብሬያቸው ሳንድዊች መብላቴን ሁሉ በማስረጃነት አቀርብ ነበር፡፡
ይሄ ሁሉ የሆነው በታዳጊነት ዕድሜ ላይ ነው - በተማሪነት ዘመን፡፡ ዛሬ ላይ ተወዳጁ ኮሜዲያን ደረጀ የቅርብ ጓደኛዬና ወዳጄ ብቻ ሳይሆን ወንድሜም ጭምር ነው፡፡
ደሬ፤ እንኳን ተወለድክልን !
ረዥም ዕድሜና ጤና እመኝልሃለሁ!
አክባሪህና ወዳጅህ ቴዎድሮስ ታደሰ አየለ

የተስፋ ቀንዲል
#ethiopia | እኒህ እናት ኗሪነታቸው በሸገር ሲቲ በመናገሻ ከተማ ሲሆን ልጃቸው ዘር፤ ቀለም፤ፆታ፤ እድሜ እና የኑሮ ደረጃ በማይለየው ልጃቸው የአእምሮ ህመም ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ከግንቦት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል እያደረጉለት ይገኛሉ፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ፍስሃ ይባላሉ፡፡ እጅግ ጠንካራ፤ ልበሙሉና ለነገው ትውልድ ጥንካሬን ብርታትን የሚያስተጋቡ እናት ናቸው፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ልጃቸው የነበረበትን የቀድሞ ሁኔታ ሲገልፁ ልጄ ፍፁም መናገር አይችልም ነበር አሁን ግን ፈጣሪ ይመስገን በሆስፒታሉ በተደረገለት ህክምናና ክብካቤ መናገር ችሏል ይላሉ፡፡
በእርግጥ እግረ መንገዳችንን ልንገልፅላችሁ የፈለግነው የልጁን የጤና መሻሻል ይሁን እንጅ ዋናቁምነገር ግን ወ/ሮ አስናቀች ፍስሃን ያቀረብንበት ምክንያት ከሌሎች የቤተሰብ አስታማሚዎች ልዩ ሆነው በማግኘታችን ነው፡፡
ወ/ሮ አስናቀች የህክምና ባለሙያም አይደሉም ነገር ግን ተግባራቸው እንደማንኛውም ቤተሰብ ልጃቸው ከህመሙ ተፈውሶ መደበኛ ህይወቱን ሲመራ ማየት ጉጉታቸው ቢሆንም ልጃቸው ሲከታተሉበት የነበረው ሂደት ግን አድናቆትን ስለጫረብን ዛሬ ለእናንተ ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ልጃቸውን በሆስፒታሉ ውስጥ ሲያስታምሙ እንደማንኛውም የቤተሰብ አስታማሚ ጠዋት ቁርሱን፤ ቀን ምሳውን፤ ማታ እራቱን አለፍ ሲልም ንፅህናውን ማስጠበቅ ብቻ አልነበረም ከሚከታተለው ሃኪም ባልተናነሰ የልጃቸውን የመድሃኒት አወሳሰድ፤ አይነት፤ መጠን እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳቱን፤ መድሃኒቱን ሲወስድ የሚታዩ አካላዊና የባህሪ ለውጦችን በሙሉ አጀንዳ አዘጋጅተው የየዕለቱን መዝግበው ይይዛሉ፤፤ ይህንኑ መረጃም ለሚከታተለው የጤና ባለሙያ (ሃኪም) የታዩ ለውጦችን (progress) ቃል በቃል በመዘገቡት መሰረት ያስረዳሉ፡፡
እኒህ እናት በየጊዜው ተኝቶ ለሚታከመው ልጃቸው በሃኪም የሚታዘዙትን መድሃኒቶች የወረቀት ቢን ካርድ አዘጋጅተው ከቢን ካርዱ ላይ የመድሃኒቱን ሳምፕል በመለጠፍ ከስሩ የመድሃኒቱን አይነት (ስም/ብራንድ)፤ መጠን(ዶዝ)፤ የሚወሰድበትን ጊዜ በመመዝገብ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ ታካሚው መድሃኒቱን ሲወስድ የሚያሳያቸውን ለውጦች የጎንዮሽ ጉዳት ጨምሮ ለልጃቸው ሃኪም በሚያስረዱበት እናት መዝገብ(አጀንዳ) ላይ ያሰፍራሉ፡፡ ይህንን ተግባር ለአንድ ጊዜ ወይም ለሁለት ጊዜ ወይም ደግሞ ለሶስት ጊዜ አይደለም እየከወኑት የሚገኙት ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን 2018 ዓ.ም ድረስ እንጅ፡፡
ወ/ሮ አስናቀች እሳቸው የሄዱበትን የህክምና መረጃ አያያዝ የጋን ውስጥ መብራት ሆኖ እንዲቀር አልፈለጉም ፡፡በመሆኑም በአጠገባቸው ለሚገኙ ሌሎች አስታማሚዎችም ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል የሚሉት ወ/ሮ አስናቀች መረጃ በአግባቡ ተሰንዶ መያዞ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነ እረዳለሁ ይላሉ፡፡
ያ መጀመሪያ ላይ ቃል የማይናገረው ብላቴና አልጋ ላይ ሆኖ እናቴ መፅሃፍ ግዥልኝ ይለኛል እኔም ገዝቼ አመጣሁለት እሱም በስርዓቱ አንብቦ የተረዳውን በወረቀት ላይ ያሰፍራል፤ እኔም እከታተለዋለሁ ይሉናል የዛሬዋ እንግዳችን ወ/ሮ አስናቀች፡፡
በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቤተሰብ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ሚኪያስ ታደለ በበኩላቸው የጤና መረጃ ሰነድ አያያዝን አስመልክቶ በሃገራችን በታካሚ ወይም በአስታማሚ ደረጃ ስለሚደረገው ህክምናና ስለህመሙ ሁኔታ መዝግቦ መያዝ የተለመደ እንዳልሆነ አንስተው ነገር ግን ቁርጠኝነት ያላቸውና የችግሩ አሳሳቢነት የገባቸው እንደ ወ/ሮ አስናቀች ያሉ ሰዎች የህክምና መረጃን ሰንደው በመያዝ ግንባር ቀደምና ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው በማለት ያነሳሉ፡፡
ዶ/ር ሚኪያስ አያይዘውም የህክምና መረጃ መያዝ ጠቀሜታው ለታካሚው ብሎም ለቤተሰብ ጭምር ነው፡፡ አንድ ታካሚ ወይም አስታማሚ የሚወስደውን መድሃኒት አይነት፤ የሚያመጣውን ለውጥና የጎንዮሽ ጉዳት ለይቶ ማወቅ የጤንነቱን ሁኔታ እያሻሻለ እንዲሄድ ያግዘዋል ይላሉ፡፡
ምክንያቱን ሲገልፁም በክትትል ወቅት የመድሃኒቶች መደጋገም እንዳይኖር፤ በሃኪሞች መካከል የሚኖረውን መናበብ ለማሻሻል እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ የህክምና ፍሰቱን ወይም ሰንሰለቱን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል በማለት ያነሳሉ፡፡
እንግዲህ እኛም እንደ ወ/ሮ አስናቀች ያሉ ብርቱ፤ ቁርጠኛ እና የህክምና መረጃ ጤና መሆኑን የተረዱ ቤተሰቦችንና ተንከባካቢዎችን ያብዛልን እያልን እንሰናበታለን፡፡
ለአእምሮ ጤናዎ እንተጋለን!
አማኑኤል ሆስፒታል

Sponsored by
Surafel
2 months ago
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏
ልጇን ይዛ ወደ ግብፅ ተሰደደች
የአዳም ተስፋው እውን ሊሆን አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ብስራት በድንግል ማሕጸን አደረ፡፡ የማይቻለውን ቻለችው፣ የማይወሰነውንም ወሰነችው፡፡ ሰማይና ምድርን የፈረጠረውን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በሰማይ ዙፋኑ ሳይጎድል ማኅጸኗን ዓለም አድርጎ ተቀመጠ፡፡ በመጨረሻም በታሕሳስ 29 ቀን በበረት ተወለደ፤ በጨርቅ ተጠቀለለ፣ ሰውና መላዕክት በአንድ ላይ አመሰገኑት፤ ሰብዓ ሰገልም ገበሩለት፡፡ ጌታችን 2 ዓመት ሲሞላው ንጉስ ሔሮድስ ንጉስ መወለዱን ከሰብዓ ሰገል ሲሰማ ሊገድለው ተነሳ። የእግዚአብሔር መልአክም ለዮሴፍ በሕልም ተገልጾ “ተነስተህ እናቱንና ብላቴናውን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ” ብሎ ነገረው፡፡ ይህ የእመቤታችን ስደትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለማሰብም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ወርኀ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ የአበባ ዘመን እየተባለ ይታሰባል፡፡
እመቤታችንም ከዮሴፍ ጋር ልጇን ይዛ ወደ ግብፅ ተሰደደች፡፡ እድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ጋር ወደ ግብፅ በተሰደደችበት ጊዜ ብዙ መከራ ገጥሟታል፡፡ ልጇን ከሞት ለማዳን ብዙ ችግር አይታለች፡፡ የቀን ሐሩር፣ የሌሊት ቊር እየተፈራረቀባት፣ እሾሁ እየወጋት፣ እንቅፋቱ እየመታት፣ መውጫና መግቢያው በማይታወቅ በረሃ ውስጥ ብዙ ተሰቃይታለች፡፡ ሕፃኑን ልጇን ለመግደል ባለ ኃይሉ ይጥር የነበረው ሄሮድስ አራት ወታደሮቹን ከእነጭፍሮቻቸው ሸልሞ እመቤታችንን ከነልጇ ይዘው ከመጡ የበለጠ ሹመትና ሽልማት እንደሚሰጣቸው ነግሮ ላካቸው፡፡ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ ይህንን ሰምቶ ሲነግራቸው ቅድስት ድንግል ማያርም ምርር ብላ አልቅሳለች፡፡ የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ወይም ትርጓሜ እንደሚነግረን በግብፅ በርሃ ሲጓዙም እመቤታችን ወደ ትዕማን ቤት ሄደች፡፡ ይሁንና ያቺ ሴትና አገልጋዩዋ በእመቤታችንና በዮሴፍ ላይ ተዘባበቱ፡፡
በእናቱ እቀፍ የነበረውን ጌታችንንም አገልጋይዋ ኮቲባ ከእናቱ እቅፍ ነጥቃ መሬት ላይ ጣለችው፡፡ ጌታም ትዕማንንና ኮቲባን አጥፍቷቸው በቤቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇና ከዮሴፍ እንዲሁም አብራት ወደ ስደት ከመጣችው ሰሎሜ ጋር ለስድስት ወር ያህል ከተቀመጡ በኋላ ጉዟቸውን ዱር ለዱር አደረጉ፡፡ ይህም እመቤታችን ልጇን እንዳይገሉባት ነበር፡፡
ነገር ግን በስቅለት ዕለት በግራውና በቀኙ የተሰቀሉት ወንበዴዎች ጥጦስና ዳክርስ አገኟቸው፡፡ የጌታን ልብስ ገፈውም ቁመው ሲማከሩ እመቤታችን ልጇን የሚገድሉባት መስሏት አለቀሰች፡፡ ሆኖም ግን ጥጦስ ካደረበት ፍቅርና ርኅራኄ የተነሳ “እነዚህ ሰዎች አሳዘኑኝ! ወደዚህ ቦታ የመጡት ያለ ምክንያት አይሆንምና አንቀማቸው እንተውላቸው” ብሎ ልብሳቸውን መልሶላቸው ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ረዳቸው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደት 42 ወራት አሳልፋለች፡፡
በየዓመቱ ኅዳር 6 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ፣ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በሄሮድስ ምክንያት የደረሰባቸው ስደትና መከራ አልፎ ደብረ ቁስቋም በተባለች ቦታ ያረፉበት ነው፡፡ በማቴዎስ 2÷20 እንደተጻፈው “ሄሮድስም በሞተ ጊዜ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ በግብፅ ሀገር ለዮሴፍ በሕልም ታየው፡፡ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡” አረጋዊው ዮሴፍም ሰሎሜ እያገዘችው የሚያገለግላትን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከተወደደ ልጇ ጋር ይዞ ከስደት ተመልሰዋል፡፡ ገዳማውያን ይሕን የስደቷን ጊዜ በጾምና ጸሎት ያስቡታል፤ በረከትም ያገኙበታል፡፡ ከበረከታቸው እንሳተፍ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

3 months ago
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ቀደምት የኤሪክሰን ስልክ ሲጠቀሙ!
An early Ericsson telephone instrument being used by a former Minister of Foreign Affairs, H.E. Blattengueta Herouy Wolde Selassie.
Ericsson
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #ericsson
#telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

ከሪከርዶችና ከአሸናፊ አትሌቶች ጀርባ ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ስም አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ
በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
እስቲ ሁላችንም ባርኔጣችንን ከፍ አድርገን እናንሳለት፤ምክንያቱም በየጊዜው የሚሠባበሩት ሪከርዶችና ድሎቹ ለአለም የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ለሆነው አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ይሄን እንድናደርግ ያስገድዳሉና።
የቅርቡን ለጊዜው እናቆየውና አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ የሚለው ስም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ድሎች፣ሜዳልያዎችና ሪከርዶች ጀርባ ከፍ ብሎ ሲሠማና ሲውለበለብ ይታያል
♦️2016 ሪዮ ኦሎምፒክ
🥉በ10ሺ ሜትር
በአትሌት ታምራት ቶላ የነሐስ ሜዳልያ
♦️በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በማራቶን
🥇በአትሌት ታምራት ቶላ(ወርቅ)
🥈በአትሌት ትዕግስት አሠፋ(ብር)
♦️በ2009 የአለም ሻምፒዮና በርሊን በማራቶን
🥉አትሌት አሠለፈች መርጊያ(ነሐስ)
♦️በ2017 የአለም ሻምፒዮና በርሊን በማራቶን
🥈አትሌት ታምራት ቶላ (ብር)
♦️በ2022 የአለም ሻምፒዮና አሜሪካ ኦሪገን በማራቶን
🥇አትሌት ታምራት ቶላ (ወርቅ)
♦️በ2023 የአለም ሻምፒዮና ሀንጋሪ ቡዳፔስት በማራቶን
🥇አትሌት አማኒ በሪሶ (ወርቅ)
♦️WR አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ21ኪ.ሜ አዲስ ሪከርድ
♦️አትሌት ትዕግስት አሠፋ ሶስት ጊዜ የአለም ሪከርድ ባለቤት
♦️በቅርቡ ደግሞ አትሌት ፎቴን ተስፋይ ሁለተኛው የማራቶን ምርጥ ሠዓት ሪከርድ ባለቤት
ከእነዚሁ ሁሉ ስኬቶችና ሪከርዶች ጀርባ በውጤት ያሸበረቀ በወርቅ ቀለም ስሙን በደማቁ ያፃፈ የሀገር ኩራት የሆነ ታላቅ ሠው አለ እሱም አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ።
ትናንት በለንደን ሠማይ ስር በማራቶን ታሪክ ሲሠራ የእሱ የስልጠና በረከት ያረፈባቸው አትሌት ትዕግስት አሠፋ አንደኛ ከመውጣት በተከታታይ ዓመት የለንደንን ማራቶን ከማሸነፍ በዘለለ በሴቶች ብቻ (Only Womens) ተይዞ የነበረውን የራሷን ሪከርድ አሻሽላለች።
ሌላኛው የአሠልጣኝ ገመዶ የስልጠና ውጤት የሆነው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በመጀመሪያው የማራቶን ተሳትፎው ሁለተኛ ከመውጣት ባለፈ የሠው ልጅ በዚህ ዘመን ማራቶንን ከ2:00:00 በታች እንደሚገባ በተግባር ካሳየው ዮሚፍ ቀጄልቻ ጀርባም ይሄ የአለማችን የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ገመዶ ደደፎ አለ።
የአሸናፊነትና የሪከርዶች ባለቤት ከሆኑት አትሌቶች ጀርባ ወይም የውጤታማነት ምስጢራቸው የሆነው የአሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ስም ዛሬም እንደ ትላንቱ እንደ ባንዲራ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ይታያል።
👉የስኬታማና የሪከርድ ሠባሪ አትሌቶችን ስም አንስተን ገመዶ ደደፎ የሚለውን ስም አለማንሳት የሀገር ባለውለታውን ውለታ ከመብላቴም ያስቆጥራል።
እንኳን ደስ አለህ!! አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ

📌ከሪከርዶችና ከአሸናፊ አትሌቶች ጀርባ ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ስም አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ
#ethiopia | እስቲ ሁላችንም ባርኔጣችንን ከፍ አድርገን እናንሳለት፤ምክንያቱም በየጊዜው የሚሠባበሩት ሪከርዶችና ድሎቹ ለአለም የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ለሆነው አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ይሄን እንድናደርግ ያስገድዳሉና።

ዛሬም በለንደን ሠማይ ስር በማራቶን ታሪክ ሲሠራ የእሱ የስልጠና በረከት ያረፈባቸው አትሌት ትዕግስት አሠፋ አንደኛ ከመውጣት በተከታታይ ዓመት የለንደንን ማራቶን ከማሸነፍ በዘለለ በሴቶች ብቻ(Only Womens)ተይዞ የነበረውን የራሷን ሪከርድ አሻሽላለች።
ሌላኛው የአሠልጣኝ ገመዶ የስልጠና ውጤት የሆነው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በመጀመሪያው የማራቶን ተሳትፎው ሁለተኛ ከመውጣት ባለፈ የሠው ልጅ በዚህ ዘመን ማራቶንን ከ2:00:00 በታች እንደሚገባ በተግባር ካሳየው ዮሚፍ ቀጄልቻ ጀርባም ይሄ የአለማችን የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ገመዶ ደደፎ አለ።
የአሸናፊነትና የሪከርዶች ባለቤት ከሆኑት አትሌቶች ጀርባ ወይም የውጤታማነት ምስጢራቸው የሆነው የአሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ስም ዛሬም እንደ ትላንቱ እንደ ባንዲራ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ይታያል።
👉የስኬታማና የሪከርድ ሠባሪ አቴሌቶችን ስም አንስተን ገመዶ ደደፎ የሚለውን ስም አለማንሳት የሀገር ባለውለታውን ውለታ ከመብላቴም ያስቆጥራል።
እንኳን ደስ አለህ!! አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

( ከደንቢ ዶሎ እስከ ~ ሚዛን - ተፈሪ )
የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ~ ነጋሶ ጊዳዳ ( ዶ.ር )
ምዕራፍ 1 ( አንድ )
#ethiopia | ብላቴናው ነጋሶ ጊዳዳ ሶለን ደምቢ ዶሎ ሚሲዮናውያን ትምህርት ቤት ( Missionary - School ) ገብተው እየተማሩ ሳለ አንድ ቀን ምሽት ላይ ወላጅ አባታቸው ቄስ ጊዳዳ ሶለን አንዲት አሥደንጋጭ ዜና ይዘው አመጡ።
በወርኃ ሚያዚያ - ( 1955 ዓ.ም ) “ባካችሁ ወደ ቤንች መጥታችሁ እርዱን” የምትል (ቀጭን) ደብዳቤ ደረሰው ሲኖዶሱ የነጋሶ ጊዳዳ ወላጅ አባት ቄስ ጊዳዳ ሶለን ላይ መንፈሳዊ አደራውን ይጥልባቸዋል።
ቄስ ጋዳዳ ፦ እሳቸውም ይኸን ታላቅ ሐዋርያዊ ተልዕኮን ተቀብለው መጥተው ፤በደምቢ ዶሎ ዳሩ የተደላደለ ኑሮ የጀመረውን ቤተሰባቸውን ሰብስበው ወደ ( ቤንች ማጂ ) እንደሚያቀኑ ተናገሩ።
ፀሐፊው ፦ ይኸን ያገኘውት “የጨለማ ሌላኛው ገፅታ” ከተሰኘው የነጋሶ ወላጅ አባት ግለ- ታሪክ ፅሑፍ ነው።
ነጋሶ ፦ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ቤንች- ሚዛን ተፈሪ ምድር ሲሄዱ ገና የ 11 ( አሥራ አንድ ) ዓመት ብላቴና ልጅ ነበሩ።
የሄድነው እናቴ፣ አባቴ፣ ታላቅ እህቴ ራሄል፣ የአክስቴ ልጅ ተስፋዬ ተፈራና ታናሽ ወንድሜ ኤልሳኢ እና እኔ ነጋሶ ነን።
ታላቅ እህታቸው ( ራሄል ጊዳዳ ) ትዳር እስክታገባ ድረስ የቤታቸው የውስጥ ዋና ረዳት ዳሩ ነበረች። ቢሆንም ነጋሶ እንደ ታላቅ ይታዩ ነበር። ውጭ የሚላላኩም ነጋሶ ነበሩ።
ይሄ ደግሞ ነጋሶ በአመዛኙም እዛው ( ጋቸብ ) ከሚገኘው ከቤንች ሕዝብ ጋር እንዲገናኙ ትልቅ እድልን ፈጠረላቸው።
ነጋሶ ፦ እዛ አከባቢ የሚናገሩት ቋንቋ “ቤንችኛ” ይባላል። በእርግጥ ከቤንች ቋንቋ በተጨማሪም እዛ ካፋ ( ካፊቾ )፣ ሸካ ( ሻኪቾ )... እነዚኸ ሁሉ በጊዜው ወደ እኛ ሚሲዮኖን ( Mission ) ጣቢያው ይመጡ ነበር።
ያረፉበት መንደር “ጋቸብ” እንደ ሆነ ነጋሶ ይናገራሉ። ጋቸብ በአከባቢው እየፏለለ እና እያጓራ የሚያልፍ የወንዝ ሥያሜ እንደ ሆነ ብላቴናው ነጋሶ ጊዳዳ ይናገራሉ።
ነጋሶ ፦ ጋቸብ መንደሮች ላይ አልፎ አልፎ ቢሆን ከርቀት ታዲያ ገላጣ ሥፍራ ይታያሉ።
ነጋሶ ፦ ታዲያ በመንደሩ ስናልፍ ጊዜ በመንገድ ይጫወቱ የነበሩ ልጆች ጠጋ ብለን “ወላጆቻችሁ የት ናችሁ” ብለን ጠየቅናቸው። “የሉም ፦ ጫካ ውስጥ ተሸሽገዋል” አሉን። በእግር አለፍን ግን ብዙም ሳንርቅ የጩኸት ድምፅ ሰማን።
ነጋሶ ፦ ጫካ የተደበቁት አባውራዎች እየተሯሯጡ ወጥተው
“ማነው ያለፈው” ይሏቸዋል ? ሕፃናት ልጆቹን።
ሕፃናቱ “አስ ኤሰርጉዌ ቄሱ ባብ ግዚዎ” ትርጓሜው (ሰው አይደለም ቄሱ አባት ነው ) ሲሉ ሕፃናቱም ይመልሳሉ።
እንግዲህ ሰው የሚሏቸው የአሥተዳደር ሰራቸኞችን እና ባለባቶችን ነው። ፍርኃታቸው እስከዚህ ድረስ ነበር።
ነጋሶ ፦ በነሱም መፍረድ አይቻልም። ( ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ) የባርያ ንግድን እስኪያቆሙት ድረስ እንደ ከብት እየታሰሩ ተሽጠዋል። በዚ ምክንያት ቤንች ያልሆኑትን ሰዎች ይፈሩ ነበር። ይላሉ የዛኔው ነጋሶ ጊዳዳ።
ነጋሶ ፦ እናም ሚዛን-ተፈሪ እንደ ሄድኩኝ ከ 3'ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል በላይ የላቸውም። በቃ 3'ኛ (ሶስተኛ) መማርያ ክፍል ገባው። ከዚያ 2 ( ሁለት ) ዓመት አቃጠልኩኝ።
ነጋሶ ፦ ያን ጊዜ ሚሲዮኖቹ Missionaries 1 ( አንድ ) ፍልሥፍና ነበራቸው እስከ 3'ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል ድረስ ካስተማርናቸው ይበቃቸዋል። መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ ይችላሉ ይሉ ነበር።
ነጋሶ ፦ ሚሲዮኖች ( Missionaries ) እኛ እንድንማር አይፈልጉም ነበር። ሥለዚህ እኔ ተመልሼ ፤ ወደ ኦሮሚያ ደምቢ ዶሎ 3'ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል ልማር ዘንድ ገባው።
ነጋሶ ፦ ሚዛን- ተፈሪ የምትኖር የሚሲዬን ጣቢያው ኃላፊ ባለቤት ሚስስ ሃስፐልስ ( Miss Haspels ) ለእኔ በግል ሁሌ ከትምህርት በኃላ በልዩነት (ኦክስፍርድ- እንግሊዘኛ) ( Oxford English ) የሚባል መፅሐፍ ታስተምረኝ ነበር።
ነጋሶ ፦ በዚህ አይነት ሁኔታ መደበኛ የክፍል ትምህርቴን ሳልከታተል 2 ( ሁለት ዓመት ) ካቃጠልኩኝ በኃላ።
ነጋሶ ፦ አንድ ቀን ኳስ ሜዳ ላይ “ከበደ ጨብራሻ” ከሚባል ሰው ጋር ሜዳ ላይ በመጣላቴ ምክንያት አባቴ ቄስ ጊዳዳ ልጆቹን ይኸው ”ሥነ-ምግባር” አያሥተምርም ብለው ክፉኛ የቤተ- ክርስቲያን ሽማግሌዎች ዘንድ ከሰሷቸው።
ነጋሶ ፦ አባቴም ተናደው ከሚዛን- ተፈሪ ወደ ደምቢ ዶሎ መለሱኝ።
“ዳንዲ ፣ የነጋሶ መንገድ” ላይ ( ካነበብኩት ) የተቀነጨበ !
ጌታመሳይ ሙሉጌታ

4 months ago
የፕሮፌሰር አበበ ዘገየ "Sites of Remembering" ዐዲስ መጽሐፍ
* ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
* ከቀኑ 10:30- 12:30
* በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)- ብላቴን ጌታ ኅሩይ አዳራሽ ይመረቃል።
ኹላችሁም ተጋብዛችኋል።
"Sites of Remembering" በፕሮፌሰር አበበ ዘገየ የተጻፈ እጅግ አስተማሪ የሆኾኑ የጽሑፎች ስብስብ ነው። መጽሐፉ የአፍሪካ ጥበብን ለዓለም አቀፍ ሥነ ጥበባዊ አስተሳሰብ ባበረከተው አስተዋጽዖ ምን ያህል አስፈላጊ እንደኾነ ለመመርመር የሚያነሳሱ ቀስቃሽ ጥያቄዎችን ያነሳል።
የባህል እና የዘመናዊነት፣ የአካባቢያዊ ሥር እና የዓለም አቀፍ ውይይት መስተጋብርን በሚያሣዩ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ምሣሌነት ይህንን ጽንሰ ሐሳብ ያፍታታዋል።
1- ሙላቱ አስታጥቄ "ኢትዮ-ጃዝ" በፖል ጊልሮይ "ጥቁር አትላንቲክ" (Black Atlantic) ጽንሰ-ሐሳብ ውስጥ ተቀምጧል። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ስሜት ከምዕራባዊ ጃዝ እና ከአፍሪካ-ዲያስፖራ ዜማዎች ጋር በማዋሐድ የተፈጠረውን የዲያስፖራ ድምፅ ያሳያል።
የሙላቱ አስታጥቄ ሥራ ድብልቅ የባህል መግለጫዎች ኾነው፣ እንደምን ዘረኛ እና ብሔርተኛ ድንበሮችን ሊፈታተኑ እንደሚችሉ፣ እንዲሁም ከአካባቢያዊ ቅርስ እና ከዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ኹኔታዎች ጋር የተጣጣመ የአፍሪካዊ ማንነትን እንዴት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ያሳያል።
2- መጽሐፉ የሠዓሊ ዘሪሁን የትምጌታን የጥበብ ሥራ ይዳስሳል። የዘሪሁን ሥዕሎች የኢትዮጵያን ጥንታዊ መንፈሳዊ ወጎች እና የክርስትና ምስሎችን በመጠቀም ወቅታዊ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እውነታዎችን ይጋፈጣሉ።
3- የሠዓሊ ኤልያስ ስሜ ሥራዎች በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ይቃኛሉ። የኤልያስ "የድብልቅ ሚዲያ" (mixed-media) ሥራዎች የተጣሉ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን በመጠቀም፣ የሥነ-ምኅዳር ቀውስን እና የኅልውና ነጸብራቅን ትንሣኤ የሚሠጡ ቅርጻ ቅርጾችን ይፈጥራሉ።
ይህ መጽሐፍ በዘመናዊ የአፍሪካ ጥበብ ላይ እየተካሔደ ላለው ጥናት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። የጥበብ ታሪክን፣ የጥበብ ቲዎሪን፣ የባህል እና የድኅረ-ቅኝ ግዛት ጥናቶችን በመገዳደር ረገድ እጅግ ውድ ምሁራዊ ዋጋቸው ከፍ ያሉ ሐሳቦችን ይዟል።
በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ላይ ለመገኘት አልጓጉም?
የቅዳሜ 10:30 ቀጠሮዎ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ብላቴን ጌታ ኅሩይ አዳራሽ ይኹን።
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)

ቲማቲም ለመልቀም የተላኩ ሁለት የወንድማማች ልጆች በወንዝ ተወስደዉ ህይወታቸው አለፈ
👉የሟቾች አስክሬን በፍለጋ ላይ ነው
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ቤተሰብ ቲማትም ለቅመዉ እንዲመለሱ ወደ ብላቴ ወንዝ ዳርቻ የተለኩ ሁለት ህፃናት በወንዝ ዉሃ መወሰዳቸዉ ፖሊስ አስታውቋል።
በቁሊቶ ከተማ የ2ኛ ጮሮቆ ቀጠና ነዋሪ የሆኑት የሁለት ህፃናት ቲማቲም ከማሳ ለቅመዉ እንዲያመጡ ተልከዉ ወደ ስፍራዉ መሄዳቸው ተነግሯል።
የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ሁለቱ ታዳጊዎች የወንድማማች ልጆች ሲሆኑ በየ12 ዓመቷ ታዳጊ አዳልጧት ወደ ዉሃዉ ስትገባ የ13 ዓመቷ ታዳጊ ቀድማ የገባችዉን ለማትረፍ ተከትላ ወደ ዉሃዉ ዉስጥ በመግባቷ ሁለቱም በዉሃ ተወስደዉ ህይወታቸዉ ማለፉን ገልጸዋል።
የሁለቱን ታዳጊዎች አስከሬን ለማግኘት ከትላንት ጀምሮ ፍለጋ መቀጠሉ ተገልጿል።በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የዝናብ መጠን እየጣለ በመሆኑ ደራሽ የወንዝ እና የጎርፍ አደጋ የሰዉ ህይወት እንዳይጠፋ ህብረተሰቡ ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲሉ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
seledadotio

5 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

6 months ago
🎭 "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ"
የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን 20ኛ ዓመት መታሰቢያ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ! 🖋️📜
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ ቁንጮ፣ የቃላት ጠቢቡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ 20 ዓመታት ተቆጠሩ።
ይህንን ታላቅ የጥበብ ሰው ለማሰብ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ያዘጋጀው መርሃ-ግብር በታዋቂ ከያንያንና ምሁራን ታጅቦ ተከናውኗል።
✨ ከመርሃ-ግብሩ ዋና ዋና ነጥቦች
📚 ጥልቅ ዳሰሳ፦ አቶ ነብዩ ባዬ የጸጋዬን የቴአትር ድርሰቶች፣ መምህር ወንድወሰን አዳነ የሥነ-ግጥም ሥራዎቹን እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ አጥላው በፋሲል ይትባረክ የተጻፈውን “ምጥቀት በቅኔ አክናፍ” መጽሐፍ ላይ ትንታኔ አቅርበዋል።
🎙️ የከያንያን ድምፅ፦ አንጋፋዎቹ ከያንያን አበበ ባልቻ እና ተፈሪ ዓለሙ የሎሬቱን ነባርና እስካሁን ያልታተሙ ግጥሞች በድንቅ ንባብ አቅርበው ታዳሚውን ወደ ጸጋዬ የቃላት ዓለም ወስደውታል።
🎁 አዲስ የምስራች፦ የሎሬት ጸጋዬ ያልታተሙ ግጥሞች በመጪው ነሐሴ 2018 ዓ.ም ለሚከበረው 90ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያው ታትመው ለንባብ እንደሚበቁ ተገልጿል።
📅 የፊታችን ቅዳሜ ግብዣ (የካቲት 21/2018)፦
ጥበብ አያልቅባትም! የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በዶ/ር ኢንጂኒየር ብርሃኑ ግዛው “ወርቃማው የፔዞ ቡሩሌያዊው በገና” የተሰኘ የምርምር እና የበገና ደርዳሪዎች ዝግጅት ስለሚቀርብ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
"ጸጋዬን በምን ያስታውሱታል?"
የሎሬቱ የትኛው ስራ (ግጥም ወይስ ቴአትር) በልብዎ ታትሞ ቀርቷል? ለጥበብ ሰው ያለዎትን ክብር በኮሜንት ይግለጹ። 👇
#tsegayegebremedhin #ethiopianliterature #poetry #art #ethiopia #memorial #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ማንነት?
#ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ የስነዳ ሥራ ታሪካቸው መዝገበ አእምሮ ላይ የሚሰነድላቸው ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይጠቀሳሉ።ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክና ባህል ዙሪያ በርካታ መፅሐፍትን በመድረስ ትልቅ አሻራ አኑረዋል።ከ30 በላይ መፅሀፍትን የደረሱት እኒህ ሰው የሀይማኖት ሰባኪ፣ ፀሀፊ እና ዲስኩር አቅራቢ በመሆን ለአገራቸው አገልግሎት ሰጥተዋል። የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን የመሠረቱት ዲያቆን ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ፣ የኢቢሲ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሹመዋል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ታሪክ ሰንደውታል።
#ቅድመ ነገር
በነገረ ሀይማኖት፣ በሥነጽሑፍ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በጥናትና ምርምሮች ከምልዓት በተጠጋ መሰጠት ያገለገሉ ሰው ናቸው፣ ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የተወለዱት ደሴ ከተማ ነው። በወላጅ አባታቸው የንግድ ሥራና እንቅስቃሴ ምክንያት፣ ነፍስ በማያውቁበት እድሜ የመላ ቤተሰቡ ቋሚ መኖሪያ ወደ ባህርዳር ከተማ ተዛወረ። በመሆኑም አብዛኛውን ለሕይወት ስንቅ ሆኖ የቆያቸውን የእውቀት መሠረት ያገኙት በዚሁ በባህርዳር ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጼ ሰርጸ ድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መለስተኛ ደረጃን በፋሲል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚህ መደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ወላጅ እናታቸው ለትምህርትና ንባብ የሰጡት ትኩረት የንባብ ልምዳቸውን በእጅጉ እንደቃኘው በተለያየ ጊዜ በሰጧቸው ቃለመጠይቆች ደጋግመው ያወሳሉ።
#የሥነጽሑፍ ፍቅር
በልጅነት እድሜ ከዘመናዊ ትምህርት ጎን ለጎን፣ ባደጉበት ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርትን በሚገባ ቀስመዋል። ይህም አገልግሎታቸው ከፍ ብሎ ቤተክርስትያንን በዲቁና እንዲያገለግሉ የክህነት መዓረግ አስገኝቷቸዋል። ከዚያም ባሻገር ወደ አካባቢው ከሚያቀኑ በእውቀትና በመንፈሳዊ ጽናት የታወቁ አባቶች መምህራን ብዙ ትምህርትን የመቅሰም እድል ነበራቸው፣ ተጠቅመዉበታልም።
ይህ ሁሉ ተዳምሮ በልጅነት እድሜ የተለያዩ ሥነጽሑፋዊ ሥራዎችን እንዲጽፉ፣ አልፎም በትምህርት ቤት በጠዋት የተማሪዎች ሰልፍ ሰዓት መድረክ ላይ ወጥተው እንዲያቀርቡ አስችሏቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉም በሰልፍ ሰዓት ለተማሪዎች ዜና ያቀርቡ ነበር። በንባብ የተገነባ መሠረት ላይ የተጣለ ማንነታቸውም ለሥነጽሑፍ በተለየ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል።
#ከአዲስ አበባ እስከ ኬንያ
ከባህር ዳር አዲስ አበባ ያቀኑት በ1982 ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ እንደገቡም ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። በዚያም ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአቅራቢያ በሚገኘው በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጡ ነበር።
የአንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ታድያ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የተናጠችው ኢትዮጵያ፣ ወጣት ተማሪዎቿ ወደ ብላቴ እንዲሄዱ ተወሰነባት። ዲያቆን ዳንኤልም በዚህ መሠረት ወደብላቴ የውትድርና ማሠልጠኛ ከሄዱ ተማሪዎች መካከል ሆኑ። ይህ ከተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ወጣቶችን በአንድ እንዲሰባሰቡ እድል የፈጠረው አጋጣሚ፣ ለዳንኤል የተለያዩ ባህሎችን፣ የሀገር መልኮችን እንዲያዩ እድል የፈጠረላቸው ነበር።
የብላቴ ሥልጠና ተጠናቅቆ ምረቃ ሳይደርስ ግን ደርግ ወርዶ ኢሕአዴግ ገባ። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም አብዛኞቹ ወደ ኬንያ ሄዱ። ዳንኤልም በኬንያ የተወሰኑ ወራት ቆይተው፣ ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን አደላድሎ ከያዘ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወጣቶች ሁሉ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተባለና ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ። በአንድ ዓመት ውስጥም የሦስት መንፈቅ ትምህርት ተከታትለው ዲፕሎማቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀብለው አጠናቀቁ።
#መምህርነት
ከዚህ በኋላ በተመረቁ ተማሪዎች ምደባ መሠረት ሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር (በቀድሞ አጠራር) ደረሳቸው። ምንም እንኳ አዲስ አበባ ላይ ሥራ ያገኙና ምደባውን መተው የሚችሉ ቢሆንም፥ “እንዲሁ በነጻ የተማርኹትን ያህልም ቢሆን ማገልገል አለብኝ” በማለት ምድባውን ተቀብለው፣ እንደውም ‘ቢቻል ሰው ሊሄድ የማይመርጥበት ራቅ ያለ ስፍራ መድቡኝ’ አሉ። በጊዜው ግን አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት የደረሳቸው በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅሩ ነበርና በዚያ የአማርኛ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ።
በዚያም የመምህራን እጥረት ስለነበር፣ ከአማርኛ ባለፈ ታሪክ እና አካባቢ ሳይንስ (ጂኦግራፊ) ያስተምሩ ነበር። ከዚያ ጎን ለጎን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠትና በማስተማር የአካባቢውን ማኅበረሰብ አገልግለዋል።
የማገልገል ጽኑ ፍላጎት እና ባመኑበት ‘ለብቻም ቢሆን የመቆም’ ጽናት ውስጥ ሆነው፣ የመምህርነት አገልግሎታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባ ተመለሱ።
ቀጥለውም ዲፕሎማ በተመረቁበት ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል። ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊትም ሆነ በኋላ፥ በማኅበረ ቅዱሳን በመደበኛ አገልግሎት ሠርተዋል። ሐሳብ አመንጭቶ መጽሐፍ ከመጻፍ በላይ የማሳተምና ማሰራጨት ክብደቱን በመረዳት የመጽሐፍ ህትመት ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ‘አግዮስ’ የተባለውን የራሳቸውን የመጽሐፍ ማሳተሚያና ማሰራጫ ከፍተው በዘርፉ ሠርተዋል።
ከዚህም ባሻገር የምክር አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በ2010 ዓ.ም የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።
#የመጽሐፍ ሥራዎች
መሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሠላሳ ሦስት በላይ መጻሕፍትን ለአንባብያን አድርሰዋል። እነዚህም እንደ ‘ብቻዬን እቆማለሁ’፣ ‘ጠጠሮቹ እና ሌሎችም’፣ ‘የሰርቆ አደሮች ስብሰባ’ ከሚሉና ከመሳሰሉ ከተወሰኑ የወግ ስብስብ መጽሐፎች ባለፈ፣ ዳጎስ ያሉ በጥናትና ጥልቅ ንባብ ላይ የተመሠረቱ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ናቸው።
ዳንኤል እስከ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መሥራች ናቸው። ከዚህም ባሻገር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መሥራቾች መካከል ይገኙበታል። በዚህ ማኅበር ውስጥ የሚታተሙ መጽሔት፣ ጋዜጣና መጻሕፍት ዝግጅት ክፍል ላይም ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔትም ላይ በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ በቅርብ በፋና ሚድያ ኮርፖሬት የቦርድ አባል ብሎም ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ለሀገር ይጠቅማል ብለው ባመኑበት መስክ እና ተቋም የቦርድ አባልና ሊቀመንበር ሆነዋል፣ ሠርተዋል።
‘የዳንኤል ክብረት ዕይታዎች’ የሚለው መጦመሪያ ድረገጻቸው ላይ የሚያሰፍሯቸው ጽሑፎች ብሎም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት የሚያቀርቧቸውና የሚሰጧቸው ማኅበራዊ ኂሶች ብዙ ትኩረት የሚስቡና ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ፣ ናቸው። በቃል ብቻ ሳይሆን በመጽሐፎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚሆኑ የሆኑ ሥራዎቻቸውም ጥቂት አይደሉም።
ብዙ የደከምኩባቸው የሚሏቸው ሁለት መጻሕፍት አሉ። አንደኛው ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘው በአቡነ ተክለሃይማኖት የሕይወት ታሪክ ዙሪያ የሠሩት ሲሆን ሌላው ‘አራቱ ኃያላን’ የተሰኘ መጽሐፍ ነው። በቅርብና መጨረሻ ላይ ለንባብ ካቀረቡት ዳጎስ ያለ መጠን ያለው ‘የትርክት እዳና በረከት’ መጽሐፋቸው በፊትም፣ ‘እጨጌ እንባቆም ከየመን እስከ ደብረሊባኖስ’፣ ‘ራዕየ ዮሐንስ’፣ ‘ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ’ የተሰኙ የመጽሐፍ ሥራዎቻቸው ከብዙ በጥቂት የሚጠቀሱ ናቸው።
#ቤተሰብ
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ከትዳር አጋራቸው ወይዘሮ ጽላት ጌታቸው ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል። በዚያም ሦስት ወንዶች (አቤሜሌክ ዳንኤል፣ ባሮክ ዳንኤል እና ባህራን ዳንኤል) እና አንዲት ሴት ልጅ (አንኪዮን ዳንኤል) አባት ለመሆን በቅተዋል።
ሙሓዘ ጥበባት የሚለውን ማዕረግ፣ ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘውን መጽሐፍ ባስመረቁበት ወቅት ‘ስም ከግብር አብሮ ይሄዳልና...’ ሲሉ፣ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ የሰጧቸው ስያሜ ነው። ሙሓዘ ጥበባት ማለት ‘የጥበብ መፍሰሻ’ ማለት ነው።
#ምስክርነት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመገናኛ ብዙኃን አመራርና አሠራር ጥሩ እውቀትና ልምድ አለው፡፡ አዳዲስ አሠራሮች እንዲጎለብቱ ሃሳብ በማፍለቅና እንዲሳካ ጥረት የማድረግ ብቃት አለው፡፡ አሁንም የጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነትና የሚዲያው ኤዲቶሪያል አቅም እንዲጎለብት እንዲሁም ተቋማዊ አቅሙ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነፃነት ተስፋዬ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ
##########
ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በይዘት ደረጃ ካየነው በባህል ኪነጥበበ እና በታሪክ ዙሪያ የኢትዮጵያን መልክ በፅሑፎቹ እና በንግግሮቹ ለማሳየት ከፍተኛ አበርክቶ ሰጥቷል። ፅሑፎቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቶች የተሠሩባቸው አሁንም ይበልጥ ሊጠኑ የሚገባቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። ዲያቆን ዳንኤል በፅሑፎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፍልስፍናዎችን፣ ጥበባትን፣ ታሪክን፣ ሀይማኖትን፣ ባህልን፣ ሥነ ጽሁፍን ፍንትው አድርጎ በማሳየት የራሱን አሻራ ያኖረ ነው። አበርክቶውም ትልቅ ነው።
እርሱ በፅሑፍ ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ሰው በመሆኑ ትውልድ በማነፅ፣ ሥነ-ምግባርን በማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያን በመመርመርና በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ኂስ በጥበብ በመስጠት፣ ያነበባቸውን መፅሀፎች ወይም ያካበተውን ዕውቀት ጥበባዊ ስልት በተላበሰ ምጡቅ መንገድ በማቅረብ ይታወቃል።
የራሱን አሳታሚ ድርጅትና የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን በመመሥረትና በመምራት ለእውቀት እና እውቅና መስፋፋት ዋና ሚና ተጫውቷል።
በመንግሥት ኃላፊነቱም ቀድሞ ሲከውን የነበረውን ተግባር በላቀ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ እንደመሆኑ መጠንም ተቋማትን በመመሥረትና በማጠናከር ሚናው ትልቅ እንደሆነ እረዳለሁ።
ዲያቆን ዳንኤል ከ30 በላይ መፅሀፍትን እንደማሳተሙ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዴት ይሆን? የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። እርሱ ግን ምናልባት በሰላሳ አመት የጽሁፍ ታሪኩ ከሰላሳ በላይ መጻሕፍትን እና እጅግ ብዙ መጣጥፎችን በሙበርከት ፕሮሊፊክ እና ዐቢይ ሥፍራ የሚደጠው ደራሲ እና የሃሳብ መሪ መሆኑን አስመስክሯል።ለሁሉም እንደሁኔታው ጊዜ በመመደብ ለሁላችን አርዓያ ነው።
ተመራማሪው ዳንኤል፣ ከመዛግብት ተነስቶ የሚፅፋቸውን ታሪኮች አይቻለሁ። በመካከለኛው ዘመን በአገራችን የተደረጉ ብዙ ክስተቶችን ለታሪክ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንዲሆን አድርጎ ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሰነደ ነው። ይህ ቀላል አይደለም።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሳስታውስ ብላቴን ጌታ ህሩይን ያስታውሰኛል። እርሳቸው በአንድ በኩል የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ይዘው በአንድ በኩል ይፅፋሉ። ምርምሮችንም ያደርጉ ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ድንቅ የፈጠራ ክህሎቱን በመጠቀም የሚያቀርባቸው ሥራዎች ከንባብ እና ነገሮች በጥልቀት ተረድቶ የሚያቀርባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያን የማሳየት አቅም አላቸው ብዬ አምናለሁ። አበርክቶው እና ጽኑ ሰብዕናው በአጭሩ ተተርኮ የሚያበቃ አይደለም።
ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ የባህልና ኪነ ጥበብ ሚኒስትር ዴኤታ
######
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የማውቀው ከ20 ዓመት በፊት ነው ። የዐውደ ምሕረቱ ፈርጥ ፣የቤተክርስቲያን አጽራር መከታ ከወንድሞች ጋር ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ሲያገለግልና ለብዙዎቻችን መንፈሳዊ መሠረት ጣይ በነበረ ጊዜ አውቀዋለሁ። በሚጽፋቸው መንፈሳዊና ትዝብት አዘል ማኅበረሰባዊ ጽሑፎች ያልተማረ ,ያልተገሰጸ በነፍሱ ሀሴት ያላደረገ በዙሪያው የነበረ ማንም አልነበረም። በተለይ በማኀበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በሚያዘጋጅበት ወቅት የከተባቸው ጽሑፎች ዘመን የተሻገሩ እስካሁን ለብዙዎች መንፈሳዊ ሙላት የኾኑ ጥዑም ዘለላዎች ናቸው።
የጻፋቸው መጽሐፍት እንዲሁም በብሎጉ በዕይታ ያስቀመጣቸው ትዝብቶቹ በቤተክህነቱም በቤተመንግሥቱም ቅቡልነታቸው የበዛ ነበር።
የቀረቡት ኹሉ ግለሰባዊ ማንነቱን ሊገነዘቡለት የማይከብዳቸው ዳንኤል በዐውደ ምሕረትም ሆነ በመድረክ ራሱን ሳያካብድ ለአገርና ለቤተክርስቲያን በጥልቀት በሚያውቀው የታሪክ አረዳዱ እያገለገለ የሚገኝ ምስጉን ወንድም ነው።
ኢዮብ ስዩም

ዝምተኛው የብሌን ሰቆቃ እና የአባት ፍቅር ሰንሰለት
በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ፣ የጊዜን መቁጠር በሰከንድ ሳይሆን በትንፋሽ እያሰላች የምትኖር አንዲት ብላቴና አለች—ብሌን። የብሌን ዓለም እንደ እኩዮቿ ሰፊ ሜዳና ኳስ ሳይሆን፣ አራት ግድግዳዎችና የአልጋው ጠርዝ ብቻ ነው።
ደራሲያን እንደሚሉት፡ "አንዳንድ ህመሞች በቃላት ሊገለጹ የማይችሉ ግጥሞች ናቸው፤ ግጥምነታቸውም በቃላት እጦት ውስጥ በሚፈሰው የእንባ ዜማ ይገለጻል።" ብሌን መናገር አትችልም፤ ነገር ግን አይኖቿ "እባካችሁ ህመሜ ይብቃኝ" የሚል የሺህ ገጾች መጽሐፍ ያነባሉ።
የአሸናፊ ጽናት፦ የመንገዱ ጽዳትና የልቡ ስንጥቅ
አባቷ አቶ አሸናፊ፣ በየቀኑ የከተማዋን መንገዶች እየጠረገ የሌሎችን ቆሻሻ ያስወግዳል። በሚገርም ግጥጥሞሽ ግን፣ በገዛ ልቡ ውስጥ ያለውን የሐዘን ቆሻሻ የሚያጥብለት አላገኘም።
መቆምም ሆነ መቀመጥ የማትችለው ብሌን፡ ልክ እንደ ሸምበቆ ወዝዋዥ ህይወቷ በአባቷ እጆች ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ነው።
የ"ራበኝ" ጥሪ በዝምታ፡ አንድ ህፃን "ርቦኛል" ብሎ ማልቀስ መቻሉ ጸጋ መሆኑን የምንረዳው ብሌንን ስናይ ነው። እሷ ግን ረሃቧን የምትገልጸው በአይኖቿ ቅፅበታዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው።
የዶክተሮች ብይን እና የተስፋው ጭላንጭል
የዘውዲቱ ሆስፒታል ቦርድ የፈረደው "የመዳን ተስፋ አላት" የሚለው ቃል፣ ለአሸናፊ እንደ አዲስ የልደት ምስክር ወረቀት ነው። ሆኖም ይህ ተስፋ 3 ሚሊየን ብር (20,000 ዶላር) በሚባል ትልቅ ግንብ ታጥሯል።
"ድህነት የህክምና እጦት ብቻ አይደለም፤ ድህነት ተስፋ እያለህ አቅም ማጣት ነው" ይላል ደራሲው።
ለብሌን ምን ማድረግ እንችላለን?
ብሌን ዛሬ አቅም ያላት እኛ ስንረዳት ብቻ ነው። አባቷ በመንገድ ጽዳት ስራው ያላጠራቀመውን ይህን 3 ሚሊየን ብር፣ እኛ በትንሽ ጠብታዎቻችን ባህር ልናደርገው እንችላለን።
የባንክ አካውንት፦ 1000056783214 (አሸናፊ አሰፋ / Ashenafi Assefa)
ስልክ፦ +251913554594
የእኛ ድርሻ፦
የገንዘብ ድጋፍ፡ ያለንን ጥቂት ሳንቲም በመለገስ የብሌን ህይወት ላይ አሻራ ማሳረፍ።
መልዕክቱን ማጋራት (Share)፦ መረጃው ለሚመለከተው ደግ ሰው እንዲደርስ ድልድይ መሆን።
ጸሎት፡ ፈጣሪ ለብላቴናዋ ምህረቱን እንዲልክ መለመን።
የመጨረሻ ቃል፡ ዛሬ ብሌን እንድትቆም የምናደርገው እገዛ፣ ነገ እሷ ቆማ እንድናያት የሚያስችል የታሪክ ኢንቨስትመንት ነው።

7 months ago
ያልተፈታ ቅኔ
……………
(ጋሻው ደበበ )
…………….
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
ደንቢያ -ተላከኝ
ፊት በር -ታዘዘኝ
አርማጭሆ -ግድም
ቋራም -‹እሺ› በለኝ
ለልሂቃን-ንገር ከሀሳብ አድነኝ፡፡
‹‹በዚህች ብላቴና -ቅኔ የታሰረ
ብዕሩን እንደ እንዝርት -ጧት ማታ እያሾረ
ይሄ ጉብል ወጣት -ከመንገድሽ ቢቀር
ደርሶ ላያስችልሽ -ላትጨክኝ ነገር
…ቅጣቱ ምንድነው? ››
ብሎ ለመጠየቅ -ጎርጎራስ አንሶ ነው?
አረ በአባ ታጠቅ -በቋራው አንበሳ!
የቡርቧክስ አዝማሪ-መሰንቆህን አንሳ!
ጎረቤት ጨከነ -ዝ…ም አለኝ በለሳ
ልክ እንደአያቶችሽ -እንደነገስታቱ፤
አገርሽን ፍለጋ
በ ‹ጎ› የሚጀምር - ቦታ ያገኙ ዘንድ
በራዕይ ተመርተው- አሀዱ እንዳሉቱ፤
የቅኔሽን መፍቻ-አንድ ቃል ንገሪኝ-እስኪ ባርባራቱ፡፡
‹‹ቃል ማለት- ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ገና ከከተራው -ከጥምቀቱ ቀድሞ
ሺ ጥቁር- እንግዳሽ -ውበትሽን ታድሞ
በምጥን ፈገግታ -በአርምሞ ታዝበሽ
በኩራት እርምጃ-የሄድሽው አቋርጠሸ
ዱካሽ ባረፈበት -ቅኔም ታስቀምጫለሽ ?
በውበትሽ ከንፎ-በፍቅርሽ እፍፍፍ ብሎ-
በአንቺ ያበደን ሰው፤
በቅኔ ሰንሰለት -ጠፍንጎ መፈተን
ምንኛ ቅጣት ነው?
አረ በአባ ታጠቅ ! ጃን ተከል ተላከኝ
ደንቢያ ወገራ
ቅዳሜ ገበያ
ማራኪ ‹እሺ› በለኝ
ቅኔዋን ትፍታና -ከልቧ-ታኑረኝ፡፡
‹‹ያቺ-ነገር እርሙ
ያች -ፀበል ሀኪሙ
ያች - አርብ ሮብ -ብርቁ
ያቺ -የሰንበት ፈርጥ
የአባይ ዳር ቄጤማ
የአዲስ አለም- ቀንበጥ››
ተብሎ -የተዘመረው
የቅኔሽ መግቢያ ነው?
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ -ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ -ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ከጥምቀተ ባህሩ-ማልጄ እሄዳለሁ
በቅዱሱ መሬት- ታቦት እሸኛለሁ
የጥንካሬና የክብርሽን ምስጢር -ተገንዝቤዋለሁ!
ፀበሉን አስረጭኝ-እጠመቀዋለሁ፡፡
የልብሽ መገኛ-ፍቅር መዳረሻው
የሽር ጉድ ወጉ-የአብሮነት ምምሻው
አንቺነትሽን ማወቅ -ከሆነ ነገሩ
እምቢ! ጎንደር ልቅር-አልወጣም ካገሩ!
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ያልተፈታ ቅኔ እያብሰለሰልኩኝ -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ፍቻ…!!
……………
(ጋሻው ደበበ )
…………….
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
ደንቢያ -ተላከኝ
ፊት በር -ታዘዘኝ
አርማጭሆ -ግድም
ቋራም -‹እሺ› በለኝ
ለልሂቃን-ንገር ከሀሳብ አድነኝ፡፡
‹‹በዚህች ብላቴና -ቅኔ የታሰረ
ብዕሩን እንደ እንዝርት -ጧት ማታ እያሾረ
ይሄ ጉብል ወጣት -ከመንገድሽ ቢቀር
ደርሶ ላያስችልሽ -ላትጨክኝ ነገር
…ቅጣቱ ምንድነው? ››
ብሎ ለመጠየቅ -ጎርጎራስ አንሶ ነው?
አረ በአባ ታጠቅ -በቋራው አንበሳ!
የቡርቧክስ አዝማሪ-መሰንቆህን አንሳ!
ጎረቤት ጨከነ -ዝ…ም አለኝ በለሳ
ልክ እንደአያቶችሽ -እንደነገስታቱ፤
አገርሽን ፍለጋ
በ ‹ጎ› የሚጀምር - ቦታ ያገኙ ዘንድ
በራዕይ ተመርተው- አሀዱ እንዳሉቱ፤
የቅኔሽን መፍቻ-አንድ ቃል ንገሪኝ-እስኪ ባርባራቱ፡፡
‹‹ቃል ማለት- ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ገና ከከተራው -ከጥምቀቱ ቀድሞ
ሺ ጥቁር- እንግዳሽ -ውበትሽን ታድሞ
በምጥን ፈገግታ -በአርምሞ ታዝበሽ
በኩራት እርምጃ-የሄድሽው አቋርጠሸ
ዱካሽ ባረፈበት -ቅኔም ታስቀምጫለሽ ?
በውበትሽ ከንፎ-በፍቅርሽ እፍፍፍ ብሎ-
በአንቺ ያበደን ሰው፤
በቅኔ ሰንሰለት -ጠፍንጎ መፈተን
ምንኛ ቅጣት ነው?
አረ በአባ ታጠቅ ! ጃን ተከል ተላከኝ
ደንቢያ ወገራ
ቅዳሜ ገበያ
ማራኪ ‹እሺ› በለኝ
ቅኔዋን ትፍታና -ከልቧ-ታኑረኝ፡፡
‹‹ያቺ-ነገር እርሙ
ያች -ፀበል ሀኪሙ
ያች - አርብ ሮብ -ብርቁ
ያቺ -የሰንበት ፈርጥ
የአባይ ዳር ቄጤማ
የአዲስ አለም- ቀንበጥ››
ተብሎ -የተዘመረው
የቅኔሽ መግቢያ ነው?
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ -ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ -ልበ-መልካም ፤
ወርቅና ሰምሽን -ለይቼ ሳላውቀው -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ከጥምቀተ ባህሩ-ማልጄ እሄዳለሁ
በቅዱሱ መሬት- ታቦት እሸኛለሁ
የጥንካሬና የክብርሽን ምስጢር -ተገንዝቤዋለሁ!
ፀበሉን አስረጭኝ-እጠመቀዋለሁ፡፡
የልብሽ መገኛ-ፍቅር መዳረሻው
የሽር ጉድ ወጉ-የአብሮነት ምምሻው
አንቺነትሽን ማወቅ -ከሆነ ነገሩ
እምቢ! ጎንደር ልቅር-አልወጣም ካገሩ!
አረ ምን ፊት ብቻ!
ደሞ የምን ፍትፍት!
የእምነትሽ ጥግ ነው-ልብ የሚከተክት
አንጀት የሚያባዝት፡፡
‹‹ቃል ማለት ምንድነው?
የዕምነት ማጥበቂያ- ኪዳን ካላሰረው?››
ብለሽ የጠየቅሽኝ…
አንቺ -ውስጠ-ወይራ
አንቺ-ሆደ -ቅኔ
አንቺ ልበ-መልካም ፤
ያልተፈታ ቅኔ እያብሰለሰልኩኝ -ካገርሽ አልወጣም፡፡
ፍቻ…!!
Sponsored by
Surafel
7 months ago
ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች ... ቅድስት አርሴማ
ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ንጉሡ መልኳ ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ።
እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ቆይተው ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሲያገኙ ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። እናታችን ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች። ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና እንዲያመጡለትም አዘዘ። ደናግላኑ ይህን እንደሰሙ ከቅድስት አርሴማና ከገዳሙ እመምኔት ቅድስት አጋታ ጋር ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። አካባቢውን የሚገዛው ንጉሥ ድርጣድስ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው።
እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ይህችን ውብ ሴትማ ለራስ ነው እንጂ ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይገባም በማለት ከደናግሉም ጋራ ካሠራት በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን ሊያታልላት ይጥር ጀመር።
ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገችው እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች ናትና፤ ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ። እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ በደናግሉ ሁሉ ፊትም አሠራትና በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው።
ቅድስት አርሴማ ግን ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት “አይዟችሁ!” እያለችም ታጽናናቸው ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት። በመጀመሪያ ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣቸው፤ እርሷም እንዲህ ሳለች ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየት ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ዕለትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል።
በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡
እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በዚህ ቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

የመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብር
የመጽሐፍቱ ርዕስ፡
ሎዛ ዘፀአት (2014 ዓ.ም)
የሎዛ ድርሳናት (2017 ዓ.ም) - (የመጀመሪያው ተከታይ ክፍል)
ደራሲ፡ ጋዜጠኛ እና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ
የመጽሐፍቱ ጭብጥ፡ በኢትዮጵያ ሚሊኒየም ዋዜማ ላይ የተመሰረተ፣ ከአፍሪካ እስከ አውሮፓ የሚዘልቅ የስደት ታሪክን፣ ፍቅርን፣ ባህልን እና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ልቦለድ።
የመርሐ ግብሩ ዝርዝር፡
ቀን፡ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)
ቦታ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጄንሲ (ወመዘክር)፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አዳራሽ።
የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ፡ ጋዜጠኛና ደራሲ ታምሩ ከፈለኝ
ልዩ ተጋባዥ እንግዶች፡
ዝግጅቱ ላይ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎች የሚታደሙ ሲሆን፣ የሚከተሉት እንግዶች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡
ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ
ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል
ደራሲት የዝና ወርቁ

የተወለደበትን በረት ሊሳለም ወደ ቤተልሔም ይጎርፋል
በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።
ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ። ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ። ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፣ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 2÷1-6፡፡ የ15 ዓመቷ ብላቴና ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በማህጸንዋ ይዛ በንጉሱ ትዕዛዝ መሰረት ልትቆጥር ወደ ቤተልሔም ከዮሴፍ ጋር ተጓዘች፡፡
ማደሪያ ጠይቀው ቤቶች ሁሉ በእንግዶች ተሞልተዋልና የተገኘው ብቸኛው ማረፊያ የከብቶች ግርግም ነበር፡፡ የዓለሙን ጌታ በማሕጸኑዋ የያዘችውን የዓለሙን እመቤት ቢያውቋት ኖሮ ከእንግዶቻቸው የተወሰኑትን አስወጥተው፣ ያም ባይሆን አሸጋሽገው በቤታቸው ባሳድሯት ነበር፡፡ በዘመኑ እስከ ዓለም ፍጻሜ ይታወስ ዘንድ የታደለ አልነበረምና የሚያስተናግዳቸው አላገኙም፡፡ ምክንያቱም ዓለም ዛሬ በጌታችን ልደት ቀን የተወለደበትን ያንን በረት ሊሳለም ወደ ቤተልሔም ይጎርፋል፡፡ ታላላቅ አብያ መቅደሶች ተገንብተውበታል፡፡ ማደሪያ የከለከሏቸው ሰዎች ግን በስፍራው የሉም፡፡ ከእነርሱ ይልቅ በእስትንፋሳቸው ያሟሟቁት አድግና ላህም "አህያና ላሞቻቸው" ይታወሳሉ።
ከ2018 ዓመታት በፊት የተወለደው የዓለሙ መድኅን፣ የዘመናት ጌታ፣ ዘመን የማይቆጠርለት፣ ሰማይና ምድርን የወሰነ በድንግል ማሕጸን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተወስኖ፣ ሰውን ለማዳን፣ እንደሰው በግዕዘ ሕፃናት በፍጹም ድንግልና ቢወለድ ዘመን ተቆጠረለት፡፡ ከአውግስጦስ ቄሳር ሁሉም በትውልድ ከተማው ተገኝቶ ይቆጠር ወይም ይጻፍ ዘንድ በወጣው ትዕዛዝ መሰረትም ጌታችን እንደ ሰው ተጻፈ፣ ተቆጠረ፡፡ ዛሬም የልባችንን በር ያንኳኳል፤ ገብቼ ልደር ይላል፣ “እርሱና እናቱን በልባችን ለማስተናገድ ምን ያሕል ተዘጋጅተናል?” ልባችን በሌሎች እንግዶች ተይዞብናል? ጌታና እናቱ ወደኛ ሲመጡ ወደ በረቱ ነው የምንመራቸው? በዚያ የብርድ ወራት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን የምታለብሰው ልጅ ብታጣ፣ በጨርቅ ጠቅልላ ያስተኛችው ልጇን አድግና ላሕም ቀርበው በትንፋሻቸው አሞቁት፡፡
እርሱም እንደ ሕፃናት ከእናቱ ጡትን እየለመነ አለቀሰ፡፡ የድንግልና ጡቷንም ይዞ ጠባ፡፡ ይህን መገለጥ፣ ለእረኞች የነገራቸው የእግዚአብሔር መልአክም “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።” ገዳማውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን በበረት ለተወለደው ልባቸውን ሰጥተው ዓለምን ንቀዋታልና፣ ገዳመቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

'የካርታው መሸላለም የኔ አቋም አይደል''መከላከያ ሰራዊት'' መከላከያ ሰራዊት ስለ አሰብ ካርታ መልስ ሰጠ ‹‹አሰብ የተጠቃለለበት ካርታ የመከላከያ አቋም አይደለም›› ጀነራሉ
በትናንትናው ዕለት የብላቴ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸው ምልምል ወታደሮች ሲያስመርቅ አዲስ ነገር ታይቷል፡፡ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ለወራት ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ምልምል ወታደሮችን ነው በትናንትናው እለት ያስመረቀው።
በምረቃው ላይ በተደረገ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ አሰብን ወደ ኢትየዮጵያ ያካለለ ካርታ ለተሸላሚው ሲበረከት ታይቷል፤ ምስሉ በመከላከያ ይፋዊ ገፅ ላይ ሰፍሯል፤ ይህን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የመከላከያ ሰራዊት የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን፣ ‹‹ምስሉ የተቋሙ ወይም የሰራዊቱ አይደለም፤ ኢትዮጵያ በአሰብም ይሁን በሌላ የባህር በር ጥያቄ ያላት ቢሆንም፤ የተሰራጨው ምስል ግን መውጣት አልነበረበትም›› ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ምላሽ መስጠታቸውን አንዳፍታ ሚዲያ ተመልክቷል፡፡
ጉዳዩ እንደሚታረም የገለጹም ሲሆን፤ ምስሉ ከመከላከያ ሰራዊት ይፋዊ ገጽ ላይ መነሳቱን ተረጋግጧል።

አረጋዊው ጻድቁ ዮሴፍ በትዳር ዓለም 40 ዓመት ኖሮ 83 ዓመት ሲሆነው እመቤታችንን ለመጠበቅ ከአረጋውያን ሽማግሌዎች መካከል ዕጣ ወጥቶለት ተመረጠ፡፡
እመቤታችንን ከቤተ መቅደስ ሊወስድ ሲል መልአኩ ተገልጦለት “ብላቴናዋን ተረከብና ወስደህ ጠብቃት” ብሎት ወደቤቱ ወስዷታል፡፡
ጻድቁ ትውልዱ ከዳዊት ወገን ሲሆን ሀገሩ ናዝሬት ነው፡፡ በተወለደ ጊዜ መልአክ መጥቶ ለወላጆቹ “የተመረጠና ታማኝ አገልጋይ ይሆናል” ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ አናጺም ነጋዴም የነበረ ሲሆን ሦስት ሴቶችና ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በፍጹም ተዋህዶ መለኮትን እንደምትወልድ፣ የአምላክ እናት እንደምትሆን አላወቀም ነበር፡፡
አረጋዊው ዮሴፍ ይህ እጅግ ድንቅ ምሥጢር ግልጽ የሆነለት ጌታችንን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወልዳ በበረት ስታስተኛው ነው፡፡ መላእክት እንደ ቅጠል ረግፈው ሲያመሰግኑት፣ እንስሳት እስትንፋሳቸውን ሲገብሩለት፣ ሰብዓ ሰገል ለአምላክነቱ እጅ መንሻ ሲሰጡት ሲመለከት ያን ጊዜ ነው አምላክን መውለዷን ያወቀው፡፡
ቅዱስ ማቴዎስም በወንጌሉ 1÷24 “የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም” ተብሎ የተነገረው ይህን ትልቅ እውነት ነው፡፡ ሄሮድስ ጌታችንን ያገኘ መስሎት 144 ሺህ የቤቴልሔም ሕፃናትን በሰይፍ ሲፈጅ መልአኩ ተገልጦለት “እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ” ብሎ በነገረው መሠረት አረጋዊው ዮሴፍ ታማኝ አገልጋይ በመሆን ለ42 ወራት ከእመቤታችንና ከጌታችን ጋር በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት ኖሯል፡፡ ይህም ጻድቅና አረጋዊ እመቤታችንና የተወደደ ልጇን መድኃኔዓለምን በእጆቹ ሥራ ይመግባቸው ነበር፡፡
ሁለቱንም ከሄሮድስ ለማዳን ብዙ ሰማዕትንት የተቀበለ ነው፡፡ ጌታችንንም ተሸክሞ ሲሰደድ ይመረኮዛት የነበረችው የምርኩዝ በትሩ የተባረከች ሆና ለምልማለች፡፡ ጌታችን በዚህች የአረጋዊው ዮሴፍ በትር ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ዛሬም ድረስ በግብፅ ደብረ ቁስቋም ትገኛለች፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ ሊያርፍ ሲል ጌታችን ተገልጦለት “ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?” ቢለው “በሞትኩ ጊዜ ሥጋዬን በምድር አታስቀርብኝ” አለው፡፡ ጌታችንም በክብር እንዲያርፍ አድርጎት ሥጋውን ብሔረ ብፁዓን አስገብቶለታል፡፡
ቅዱሳንና ገዳማውያን ለትልቅ መንፈሳዊ ሕይወት በእግዚአብሔር ይመረጣሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተካፋይ እንሆናለን፡፡

8 months ago
አባቱ የሦርያ ሊቀ ካህናት ነው። ከእርሱ በቀር ልጅ አልነበረውም።
የሥሩግ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ቅዱስ ያዕቆብ ወይም ከ366 – 438 ዓ.ም የኖረው አባት ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ። ኤፍራጥስ በተባለች መንደር በ451ዓ.ም ተወለደ። ያዕቆብ ማለት አኃዚ፣ አዕቃጺ ማለት ወይም ሰኮና የሚይዝ ማለት ነው፡፡ በ3 ዓመቱ እናቱ ይዛው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሄደች። በዕርገት ቊርባን ጊዜ ከእናቱ ተለይቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ። ሊቀ ጳጳሱ ጸጋ እግዚአብሔር እንደጠራቸው ዐውቆ በጽዋው 3 ጊዜ ከደሙ አጠጣው። ብላቴናው ያዕቆብም በሕዝቡ ፊት ”3 ነገሮች ያስፈሩኛል“ በማለት ማልቀስ ጀመረ። ጳጳሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት፡፡ እርሱም ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ፣ ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ፣ በእኔ ላይ ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው፡፡ ሕዝቡና ካህናቱ ይህንን ሲሰሙ “እግዚአብሔር በሕፃኑ አድሮ ገሠጸን ” በማለት ማልቀስ ጀመሩ። ቅዱስ ያዕቆብ የተማረው በኤዴሳ ነው።
ኤዴሳ የዛሬዋ ቱርክ ከተማ ነበረች። የዛሬን አያድርገውና ጥንተ ክርስትና የተሰበከባት የክርስትና ማዕከል ነበረች። ኤዴሳ በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ደግሞ ”ሮሐ“ በሚል ስያሜ ትታወቃለች። ዛሬ ግን ኡርፋ በመባል ትጠራለች። ቅዱስ ያዕቆብ በሰባት ዓመቱ የብሉያትና ሐዲሳት መጻሕፍትን አጥንቷል። በአስራ ሁለት ዓመቱ ድርሰት መድረስ ችሏል። አንድ ቀን አምስት ያህል ጳጳሳት መጥተው ቅዱስ ያዕቆብን “ከፊታችን ቆመህ እኛ እየሰማህን አዲስ ድርሰት ድረስልን” አሉት። ቅዱስ ያዕቆብም ትሕትና ልማዱ ስለሆነ “አባቶቼ በእናንተ ፊት እንኳን እንግዳ ድርሰት መድረስ ያጠናሁትን ቀለም አከናውኖ መናገር አይቻለኝም” አላቸው። “እንግዲያውስ በቤተ ክርስቲያን ያለውን ሥዕል አርባዕቱ እንሰሳ ተርጉምልን” አሉት። ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤል በኮባር ወንዝ እንዳያቸው ሆነው አንገታቸውን ዘንበል ዘንበል አድርገው ተሥለዋል።
ቅዱስ ያዕቆብም ይህንንስ ይሁን ብሎ “ሁለት ክንፋቸው ወደ ታች ማድረጋቸው ደኃራዊነቱን ይመረምሩታል፤ ያጡታል። ሁለት ክንፋቸው ወደ ላይ ማድረጋቸው ቀዳማዊነቱን ይመረምሩታል፤ ያጡታል፡፡ ሁለቱን ክንፋቸውን ወዲያና ወዲህ ማድረጋቸው ጽንፍ እስከ ጽንፍ ምልዓቱን፣ ስፋቱን ይመረምራሉ፤ ያጡታል። የማይመረመር ስለሆነ ስለዚህ ዕፁብ ዕፁብ ዕፁብ ይላሉ። ብሎ ተርጉሞላቸዋል። ለረጅም ዓመታት አነስተኛ የሆነችውን የሥሩግ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስን በመጎብኘት ያገለግል ነበር። በ519 ዓ.ም በባትናም ኤጲስ ቆጶስነት ተሹሞ ሁለት ዓመት ከመንፈቅ አገልግሎ ዐርፏል። ዕረፍቱም ሰኔ 27 ነው። ገድል ተጽፎለታል፣ ጽላት ተቀርጾለታል። በሦርያ ቋንቋ በመቶዎች የሚቆጠሩ በግጥም መልክ የተዘጋጁ ድርሳናትን፣ በመጻፍ “ዕንዚራ መንፈስ ቅዱስ“ የመንፈስ ቅዱስ ዋሽንት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
በስሙ የሚታወቅ ቅዳሴም ደርሷል። በሀገራችን በቅዱሳን መላእክት በዓላትና በነገረ ምጽአት መታሰቢያ ዕለት ቅዳሴው ይቀደሳል። ስለ ነገረ ድኅነት በስፋት አስተምሯል። ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በግጥም መልክ የተዘጋጀ ድርሰት ደርሷል። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ የመለኮትና የሰውን ፍጹም ተዋሕዶ በማስተማሩ “የተዋሕዶ ጠበቃ “ተብሏል። የንስጥሮስንና በ451 ዓ.ም የተካሔደውን የኬልቄዶን ጉባኤ የምንታዌ ትምህርትም አውግዟል፡፡
ይህን የቅዱሳን የሃይማኖት መሠረት የያዙ ገዳማውያንም በእምነት ጽናት፣ በጾምና በጸሎት ትጋት ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍ በዓቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ቆይተው ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሲያገኙ ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። እናታችን ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች። ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና እንዲያመጡለትም አዘዘ።
ደናግልኑ ይህን እንደሰሙ ከቅድስት አርሴማና ከገዳሙ እመምኔት ቅድስት አጋታ ጋር ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። አካባቢው ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ነበርና ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው። እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ይህችን ውብ ሴትማ ለራስ ነው እንጂ ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይገባም ለራሱ ፈልጎ እዚያው አኖራት።
ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን በብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች፣ ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ። እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ እርሷንም በደናግሉ ሁሉ ፊት አሠራትና በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው።
እርሷ ግን “አይዟችሁ!” እያለች ታጽናናቸው ነበር። ይልቁንም ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት። በመጀመሪያ ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣቸው፤ እርሷም እንዲህ ሳለች ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየት ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። ታኅሣስ 6 ቀንም የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ነው።
ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡
በቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

ጠጅ ቀጂው የ15 አውሮፕላን ባለቤት ሆኖ ማየት እንዴት ይገርማል?!
በአክሊሉ ተስፋዬ
#ethiopia | ከሳምንት በአንዷ ቀን በዕለተ ረቡዕ የምትመጣውን አውሮፕላን ለማየት ሳይሆን ድምጿን ለመስማት ይጓጓ ነበር፤
እንኳን አውሮፕላን መኪና አይቶ አያውቅም ነበርና በአንድ ወቅት ትንሿን ከተማቸውን ለመጎብኘት የመጣችውን ላይንድ ክሩዘር ለማየት ሶስት ኪሎ ሜትር ሮጦ ነበር፤
ካፒቴይን ሰለሞን ግዛው!
ረቡዕ ረቡዕ ድምጿን ብቻ የሚሰማትን አውሮፕላን በአይን ለማየት ይናፍቅ የነበረው ብላቴና ዛሬ አድጎ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የግል አቪዬሽኑ አውራ አቢሲኒያ አቪዬሽንን መስርቶ የ15 አውሮፕላኖች ባለቤት ሆኗል።
ወዳጄ ዛሬ የምታልፍበት እና የሚታይህ ነገ ለየቅል ቢሆንብህን አንድ ነገር አስተውል ራዕይህን ትክ ብለህ መመልከትህን ቀጥል። እግዚአብሔር ያነሳል! ያከብራል! ሰውም ያደርጋል!
ከየት እንዳነሳው ከቶ ያልዘነጋው ይህ ጀግና ሰው አዘውትሮ የሚላትን አንድ ንግግር በብዕሬ ተንፍሼ ልጨርስ " ዛሬ የመጨረሻ ቀኔ ቢሆን እግዚአብሔርን አክብሬ መሞት ነው የምፈልገው ይላል።"
(ትልቅ ራዕይ ለሰነቀ አንድ ወዳጃችሁ አጋሩለት!)

የሌሊት ወፍ
#ethiopia | "የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡
የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡
ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡
ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡
ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡
የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡
ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ
የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡"
(ብላቴን ጌታ ኅሩይ)
#muktarovich

9 months ago
ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም.
የግርማዊ ቀዳማዊ የዘውድ በዓል ሲዘከር።
"በክብር የነገሡት፤ በግርማ የታጀቡት"
► #በአበው ሥርዓት በግርማ ነግሠዋል፤ በአበው ሕግ ተገዝተዋል፤ ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ በሕያው አምላክ ፊት ቃል ኪዳን ገብተዋል፤ ቃል ኪዳናቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ታትረዋል።
#ከአበው የተቀበሏት፤ በዓምላክ ፈቃድ ዙፋን ተቀምጠው የሚመሯት፤ በበትረ መንግሥታቸው መንገዷን የሚጠርጉላት ሀገራቸው ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ሠርተዋል።
#ተናግረው ይሰማሉ፤ መክረው ይመልሳሉ፤ ገስጸው ያስተካክላሉ፤ ዘምተው ያሸንፋሉ፤ አስበው ያደርጋሉ፤ ጀምረው አምላካቸውን ይዘው ይፈጽማሉ።
#አበው ስለ ጠበቋት ሀገራቸው በጽናት ቆመዋል፤ ከአበው ስለተቀበሏት የከበረችው ሠንደቅ ዓላማቸው በጀግንነት ተፋልመዋል፤ ነጻነቷን እንዳታጣ ከጠላቶቿ ጋር ተጋጥመዋል፤ ዓለም ሁሉ ፊቱን ባዞረባቸው ጊዜ እውነትን፣ ቃል ኪዳንን እና ተስፋን ይዘው ብቻቸውን ቆመዋል።
#ሃሰተኞች በሚፈርዱበት፣ ሀሰተኞች በሚመሰክሩበት፣ ሀሰተኞች የፍርዱን ውሳኔ በሚያጸኑበት፣ የፍርድ ሚዛን ሁሉ ወደ ቅኝ ገዢዎች በምታዘነብልበት በዚያ ጊዜ በተስፋ ቆመዋል፤ ከእውነት ጋር ቆመው የእውነት፣ በእውነት፣ ስለ እውነት ለሀገራቸው ነጻነት ታግለዋል።
#እውነትን ይዘው ሀሰተኞችን በፍርድ ዓደባባይ አሸንፈዋል፤ ቅኝ ገዢዎችም በጦር ሜዳ ድል መትተዋል፤ በድል አድራጊነትም በግርማ እና በከፍታ በዓደባባይ ታይተዋል፤ በዙፋን ላይ እንደ ጫካ አንበሳ በአስፈሪ ክብር ተቀምጠዋል ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን ሰብስበዋል፤ መለያየትን አውግዘው አንድነትን አምጥተዋል፤ የአንድነቱን መሠረት አጥብቀዋል፤ የተረሱትን አስታውሰዋል፤ አንገታቸውን የደፉትን ቀና እንዲሉ አድርገዋል፤ የተገፉትን ደግፈዋል፤ ስለ ራሳቸው በራሳቸው የማይመክሩትን ስለ ራሳቸው እንዲመክሩ፣ መፍትሔም እንዲያበጁ አድርገዋል።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን በአንድነት ሰብስበው አቅማቸውን አደርጅተዋል፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲናገሩ መንገዱን አሳይተዋል፤ ስለ እነርሱ ከእነርሱ በላይ እንደሌለ አሳይተዋቸዋል፤ በቅኝ ገዢዎች ምክንያት የጨለመችባቸውን የነጻነት ጀንበር እንዲመለከቱ አድርገዋል፤ በነጻነት ጀንበር በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ አድርገዋል ጃንሆይ።
#እኒህ አያሌ ታሪክ የሚነገርላቸው፤ አፍሪካውያን የአንድነታችን አባት የሚሏቸው ንጉሠ ነገሥት ዘውድ የጫኑት፣ በከበረው ዙፋን ላይ የተቀመጡት፣ በትረ መንግሥቱን የጨበጡት፤ ቅብዓ መንግሥቱን የተቀቡት፤ የአበውን አደራ ይሸከሙ ዘንድ እጃቸውን ከፍ አድርገው ቃል ኪዳን የገቡት በዛሬዋ ቀን ነበር፤ ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም።
#የነገሡበት ቀን በሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ዓመተ ምኅረት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ደብርም ክብረ በዓሉ የሚከበረው በሃያ ሦስት ነው። ሃያ ሦስት የተገጣጠመላቸው ባለ ግርማው ንጉሥ።
#ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሕይዎቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለ ንግሥናቸው ሲጽፉ መስከረም 17/1909 ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ ሲነግሡ እኔም ለአልጋ ወራሽነቱ እና ለእንደራሴነቱ ስለተመረጥሁ በባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቴ የመንግሥቱን ሥራ እየሠራሁ 14 ዓመታት ቆየሁ።
#ንግሥት ዘውዲቱ መጋቢት 24/1922 ዓ.ም ስላረፉ በማግሥቱ የንጉሠ ነገሥቱ ዐዋጅ ተነግሮ በዙፋኑ ተቀመጥሁ።
#ወደ ፊት ያለው ወራቱ ክረምት ስለነበረ የዘውድ በዓላችን ሰባት ወራት እንዲቆይ አደረግን። በኢትዮጵያ ያሉ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ፣ ባላባቶችም ሁሉ፣ በየገዳማቱ ያሉ አባቶች፣ የየአድባራቱ አለቆች፣ መጥተው የደስታችን ተካፋዮች እንዲኾኑ የጥሪ ደብዳቤ ተላከላቸው። ለዘውድ በዓሉም ዝግጅት ተደረገ ብለዋል።
#ልብሠ መንግሥቱ፣ ዘውዱ እና ሉሉ፣ በትረ መንግሥቱ እና ሰይፉ፣ ቀለበቱ ይህንም የመሰለው ሁሉ በተለየ በወርቅ እና በአልማዝ እየኾነ ተሠራ። ለመሳፍንቱ፣ ለመኳንንቱ፣ ለጦር አበጋዞች ሁሉ እንደየ ክብራቸው የክብር ልብስ ተዘጋጀላቸው።
#በዘውድ በዓሉ ዋዜማ በጅሮንዱ የንጉሠ ነገሥቱን ልብሰ መንግሥት እና ዘውዱን፣ ሉሉን፣ በትረ መንግሥቱን፣ ሰይፉን፣ የአልማዝ ቀለበቱን፣ የእቴጌይቱንም ልበሰ መንግሥት እና ዘውድ፣ የአልማዝ ቀለበት በሠረገላ አስገብቶ በታላቅ ሰልፍ ወስዶ በመናገሻው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጳጳሳቱ አስረክቦ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸለይበት አደረ ይላሉ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ በሌሊት ወደ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አቀኑ። ጸሎቱም ማካሄዱን ቀጠለ።
#ጃንሆይ ሲጽፉ ሥርዓተ ንግሡ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡ ቄርሎስ ገበታው የወርቅ የኾነ ወንጌል ይዘው ቀርበው የመሐላ ቃል እንድንፈጽም አደረጉ ብለዋል።
#ብላቴ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተሰኘው መጽሐፋቸው ሲጽፉ የዘውዱ ዋና በዓል ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም እሑድ ነበር። ቅዳሜ ማታ የመናገሻ ጊዮርጊስ ካህናት እና ከየአድባራቱ ተመርጠው የመጡ መዘምራን ከማታው ጀምረው ማኅሌት ቆመው አደሩ።
#እኩሌቶቹ መወድስ ሲቆሙ እኩሌቶቹ ክስተት አርያም ያደርሱ ነበር እና ማኅሌቱ ደምቆ አደረ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱም በሌሊት በመሳፍንቱ እና በመኳንንቱ ታጅበው ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው ለዚህ ማዕረግ ላበቃቸው ከዚህ ዕለት ላደረሳቸው አምላክ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ወደ ማረፊያ ድንኳን ሄደው ጸሎተ ሕሊና ሲያደርሱ አደሩ።
#ጠዋት ሲነጋ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ሙሉ የማዕረግ ልብሳቸውን ከኒሻን ጋር ለብሰው የራስ ሉል እና የራስ ወርቅ ደፍተው በአዳራሹ ውስጥ በተሰናዳላቸው ስፍራ በየማዕረጋቸው ተቀመጡ። ጳጳሳት እና መምህራን ለሥርዓቱ ተዘጋጁ።
#ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ንግሥ ወደሚፈጸምበት ገቡ። በመንበሩ አጠገብ ተሳልመው ጸሎት አደረሱ። ጸሎታቸው እንደጨረሱ በተሰናዳው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
#በዚህም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡነ ቄርሎስ ፊታቸውን ወደ መሳፍንቱ እና ወደ መኳንንቱ አዙረው እንዲህ አሉ።
"እናንት የኢትዮጵያ መሳፍንት እና መኳንንት፣ የጦር አለቆች ወታደሮች እና ሠራዊቶች፣ በቤተ ክህነትም ያላችሁ ሊቃውንት እና አለቆች መምህራን እና ቀሳውስት ሁሉ ንጉሠ ነገሥታችን ግርማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሰሎሞን እና ከንግሥተ ሳባ ከተወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ሳይቋረጥ ከመጣው መኾኑን ታውቃላችሁ።
#አሁን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ቸርነት ዘውድ ጭኖ እንዲነግሥ ልቀባው ነው እና በሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሥራው ሁሉ ሀገርም በማሠልጠን ሃይማኖትም በማጽናት በዘመኑም ኢትዮጵያ በዕውቀት እና በትምህርት በጥበብም ከፍ ከፍ እንድትል በመትጋት ከወሰን እስከ ወንሰን የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲዘረጋ በማድረግ ይህንንም በመሰለው በመልካም ሥራው ሁሉ እንድትገዙለት እና እንድትረዱት አደራ እላችኋለሁ" አሉ።
#ሕዝቡም በዕልልታ አጀባቸው።
#ከዚያም ልብሰ መንግሥቱን አለበሷቸው፤ ቤተ መንግሥቱን አስጨበጧቸው፤ ሉሉንም ሰጧቸው፤ የአልማዙን ቀለበቱንም አጠለቁላቸው፤ የንግሥና ወግ እና ማዕረግ የኾነው ሰይፉን እና ጦሩንም ሰጧቸው፤ ቅብዓ መንግሥቱንም ቀቧቸው፤ ዘውዱንም ባርከው ደፉላቸው፤ በዚህም ጊዜ እልልታው አስተገባ፤ ታላቅ ደስታም ኾነ።
#ንጉሡም በግርማ ኾነው ከዙፋናቸው ላይ ተቀመጡ። የእተጌዋም በሥርዓቱ መሠረት ተፈጸመ። የአልጋ ወራሹም ከዙፋኑ ግርጌ ኾነው ቃል ኪዳን አሠሩ። እልልታውና ጭብጨው ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ። ንጉሡና እና ንግሥቷ ከፍ ባለ ሥፍራ ኾነው በታዩ ጊዜ እልልታው ቀለጠ።
#በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ሥርዓት በተጠናቀቀ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌይቱ በስድስት ፈረሶች በሚሳብ በወርቅ ሠረገላ ተቀምጠው፣ ከፊትም ከኋላም በመሳፍንት እና በመኳንንት ታጅበው፣ በሠራዊት ሰልፍ መካከል አልፈው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ተመለሱ።
#መሳፍንት እና መኳንንት የመንግሥታት መልእክተኞችም በየማዕረጋቸው በሠረገላ እና በአውቶሞቢል ኾነው አጀቡ። እምቢልታውና መለከቱ ሲንካለል፣ ነጋሪቱ እየተጎሰመ ገብር ገብር ሲል እጅግ ደስ ያሰኝ ነበር።
#በመንገድ ዳር ኾኖ ለማየት የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰላምታ እየሰጠና እጅ እየነሳ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ አጨበጨበ። ከቤተ መንግሥት በደረሱ ጊዜም ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ ለመሰናበቻ በተሰናዳው ሥፍራ ቆመው ሲያዩት ሕዝቡ ሁሉ እንደገና እያጨበጨበ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ እየመረቀ ተሰናበተ። የዘውዱ በዓል ግብርም ተገባ ተብሎ ተመዝግቧል።
#አምባሳደር ዘወዴ ረታ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት በተሰኘው መጽሐፋቸው ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ በወርቅ ሰረገላ ኾነው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ሲያመሩ ከሕዝቡ የጎረፈላቸው የደስታ መግለጫ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው እየተባለ ይነገራል ብለው ጽፈዋል።
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እስከ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ድረስ በተደረገው የአንድ ሰዓት የእርጋታ ጉዞ ላይ እምቢልታው እና መለከቱ ሲነፋ፣ ነጋሪቱ ሲጎሸም፣ ካህናቱ ሲዘምሩ፣ ወታደሩ ሲሸልል፣ ከዚህ ሁሉ ጋር የሴቶች እልዕልታ እና የወንዱ ጭብጨባ ሲያስተጋባ፣ የአዲስ አበባን የጥቅምት ፀሐይ እጅግ ያጋላው ይመስል ነበር።
#በዋዜማው ቅዳሜ ከማታው በአራት ሰዓት የተጀመረው ጸሎተ ቅዳሴ እና የንግሥ በዓል ሥርዓት የተፈጸመው በማግሥቱ እሑድ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲኾን ነው።
#ለአሥራ አራት ሰዓታት ያለማቋረጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ ያሳዩትን ጥንካሬ እና የመንፈስ ጽናት ያላደነቀ አልነበረም።
#በተለይም በበዓሉ ተካፋይ ለመኾን ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአሜሪካ የመጡት የአሥራ አንድ ሀገራት እንደራሴዎች ከዚህ ቀደም በየትኛውም ዓለም ያላዩትን ይህን እጅግ ረጅም እና ከፍተኛ የኾነ ሥነ ሥርዓት ሲመለከቱ ኢትዮጵያ ያላት ጥንታዊ ባሕል ምን ያህል የሚደንቅ እና የሚከበር መኾኑን መገንዘብ የሚያስችላቸው ነው ብለው ጽፈዋል።
#ዘውድ በጫኑበት ዕለት በእርስዎ መሪነት ኢትዮጵያ ዘመናችን ያፈለቀውን ሥልጣኔ አግኝታ በዓለም ላይ የክብር ቦታ እንድትይዝ የሚያደርጉት ጥረት የተባረከ ይኹን ተብለው እንደተመረቁ ሁሉ ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ በነጻነት የተቀበሏት ሀገራቸውን ታላቅ እና ገናና ትኾን ዘንድ አቅማቸው የፈቀደውን ሳይሰስቱ ሰጥተዋል።
#የኢትዮጵያን ክብር እና ጥቅም አስከብረዋል፤ ገናናቷን በአፍሪካ እና በቀረው ዓለም ደጋግመው አስመስክረዋል። የአፍሪካውያንን የአንድነት መሠረት ጥለው አልፈዋል።
#ኢትዮጵያን ስላገለገሉ እናመሰግንዎታለን፤ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ስለታተሩ እናከብረዋታል።
✍️በታርቆ ክንዴ(አሚኮ)
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm

10 months ago
ኢትዮጽያን በታላቅ ክብር ያስጠራውና የቻይና መንግስት በቀይ ምንጣፍ የተቀበለችው ሠዓሊ
"ሰዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም የባህል ዲፕሎማሲው ጠንካራ ምሳሌ ነው"አምባሳደር ተፈራ ደርበው
(ይትባረክ ዋለልኝ)
ሠዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም በልጅነቱ እ ኤ አ በ1986 ዓ.ም የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ህፃናት ሠዓሊዎች አንድ የሥዕል ውድድር አዘጋጅቶ ነበር:: በዚህ የሥዕል ውድድር ላይ ብላቴናው ፍቅሩ ተወዳደረ:: ዉድድሩንም አሸናፊ ሆኖ ተሸለመ:: በልጅነቱ በሙያው የሸለመችው ቻይና ከ 39 ዓመት በኃላም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያው የላቀ ደረጃ የደረሰውን ይህን የተከበረውን ይህን የሥነጥበብ ባለሙያ ዳግም ሞሽራና አክብራ በክብር ተቀብላና ከፍ አድርጋ ሞሽራ አስትናግዳዋለች::
ባለፈው ሳምንት እ ኤ አ መስከረም 27 ቀን 2025 ዓ.ም “Cross World: Fikru in China” በሚል ርዕስ በቻይና Kaifeng Art Bonding in Hebei Province. ላይ የታዋቂው ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም 64 የስነጥበብ ስራዎች ለእይታ በቅተዋል።
በዚህ “Cross World: Fikru in China” በሚል ርዕስ በልዩ ዝግጅት በድምቀት የተዘጋጀውን የስዕል ዓውደ ርዕይ በይፋ የከፈቱት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና የመንግስት ከፍተኛ ሓላፊ የሆኑት ኮማንደር ሁዢን/ ZHU Jinxi/ እና በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው ሲሆኑ በርካታ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና የመንግስት ከፍተኛ ሓላፊዎች በዚህ የስዕል ዓውደ ርዕይ ላይ ተገኝተዋል።
ይህን ዓለም የሚያደንቀውና የሚያከብረውንኢትዮጵያዊ ሠዓሊ የቻይና መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ስራዎቹ በቻይና ትልቁ የስነጥበብ ሙዚየም ውስጥ እንዲታዩ ያደረጉ ሲሆን ይህን ታላቅ የስነጥበበ ባለሙያምን የቻይና መንግስት ከፍተኛ ሐላፊዎች በላቀ ክብር በቀይ ምንጣፍ ተቀብለውታል።
"Cross World “ የስዕል ዓውደ ርዕይ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው እንደተናገሩት"የስዕል ዓውደ ርዕይ እንደ ደማቅ የባህል ድልድይ ከመሆኑም በላይ በሁለቱ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል የጋራ መግባባትን ይፈጥራል።በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለውን የባሕል ግንኙነት በማጠናከር ለአለም አቀፍ ብዝሐ ባሕል ከፍ ያለ አድናቆትን በመስጠት የባህል ዲፕሎማሲው ጠንካራ ምሳሌ ነው።እንዲሁም ይህ ዓውደ ርዕይ ስነጥበብ ባህሎችን እንዴት አንድ እንደሚያደርግ እና አለም አቀፍ ወዳጅነትን የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረዋል።"
ሰዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም ሶስት አስርት አመታት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ታላላቅ ስራዎችን የሰራ ተወዳጅ ሰዓሊ ነው።በስነጥበብ ስራዎቹ ዓለም የሚያደንቀውና የሚያከብረው በስነጥበብ ባለሙያ ብቻ ሳይሆን በስነጥበ ስራዎቻቸው በአለም ላይ ስማቸው ከፍ ብሎ ከሚጠሩት ታላላቅ ሰዓሊያን መካከልም አንዱ ነው።በዓለም ዓቀፍ የስነጥበብ ደረጃ የላቀ ቦታ ያለው ሰዓሊ ነው።
ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ተመርቋል።ፍቅሩ በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ባያጠናቅቅም በኢትዮጵያ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ስራዎቹን አሳይቶአል።በፓሪስ አስር አመታትን በጥበብ ስራ አሳልፏል።ሰዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም በዓለም ላይ በስነጥበብ ስራዎቻቸው ከሚታወቀው እንደ ቻጋል፣ሚሮ ጂአሮሜትቲ፣ፒካሶ ሶላጅስ እና ሌሎችም ካሉ ታዋቂ አርቲስቶች ጋር በመሆን የማሳየት እድል አግኝቷል።
ይህ ዐውደ ርዕይ በኢትዮጵያዊው አርቲስት ፍቅሩ ሥዕሎች የተሣተበት የአፍሪካን ህይወት ህያውነት እና መንፈስ ከጥልቅ ባህላዊ ትረካዎች ጋር በማዋሃድ የአፍሪካ እና የእስያ ወጎችን የሚያገናኝ ልዩ ውይይት የፈጠረ ሲሆን የባህል ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በሁለቱ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች - ኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል የጋራ መማማርን እና መግባባትና በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ትርጉም አለው።
በመጨረሻም አስገራሚው የቻይናና የፍቅሩ ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ ይህ ነው:: ሠዓሊ ፍቅሩ ገብረማርያም በልጅነቱ እ ኤ አ በ1986 ዓ.ም የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ህፃናት ሠዓሊዎች አንድ የሥዕል ውድድር አዘጋጅቶ ነበር::
በዚህ የሥዕል ውድድር ላይ ብላቴናው ፍቅሩ ተወዳደረ:: ዉድድሩንም አሸናፊ ሆኖ ተሸለመ:: በልጅነቱ በሙያው የሸለመችው ቻይና ከ 39 ዓመት በኃላም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያው የላቀ ደረጃ የደረሰውን ይህን የተከበረውን ይህን የሥነጥበብ ባለሙያ ዳግም ሞሽራና አክብራ በክብር ተቀብላና ከፍ አድርጋ ሞሽራ አስትናግዳዋለች::

እግር ኳስ ተስፋ ያቀበለው የመርሲሳይዱ ክለብ ድምቀት
#ethiopia | ይህ ክታብ በፍቅር ሀይል ትንፋሽ ስለተቀጠለለት አንድ ብላቴና ያትታል። ተአምር ሰው ቢሆን የእርሱን ስጋ ይላበስ ነበር፡፡ ጉዳዩ ባለታሪኩ በእናቱ ማህጸን ባለመኖር ሳለ ጀምሮ የሚመዘዝ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ስለ እሱ በሀኪሞች የተተነበየ ነገር ነበር፡፡ አይኖቹ ከማየት ጆሮዎቹ ከመስማት እግሮቹ ከእርምጃ ውጪ እንደሚሆኑ በሀኪሞች ተነግሯል፡፡ ከተወለደ በኋላ ግን የተባለው ሳይሆን ቀረ፡፡ የህይወቱ ተዓምራዊነት ከዚያን ጊዜ ይጀምር ነበር፡፡
ምድሪቱን ከማወቁ ቀድሞ ከWolf-Hirschhorn syndrome ጋር ተዋውቋል፡፡ ጉዳዩ የዘረመል ችግር ነው። ይህ ደግሞ በዝግታ እንዲያድግ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ ከውልደቱ ጀምሮ የሀኪም ቤቶች ቋሚ ደንበኛ ነው፡፡ ተደጋጋሚ ቀዶ ጥገናዎችን አድርጓል፡፡ ልቡም በዚህ መንገድ አልፋለች፡፡
በእርሱ ምክንያት ተስፋ የተቀጠለላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ በህይወት ማዕበል ለሚዳፉ ሁሉ የ "አላለቀም" የ "ይቀጥላል" ህያው ምስክር ነው፡፡ ሰው በሞት ካልተረታ "አበቃ" ብሎ ነገር ያለመኖሩ ማሳያም ጭምር፡፡ ፍቅር ድንበር የለሽ መሆኑን ለዓለምና መላዋ አስመስክሯል፡፡ የመርሲሳየዱ ክለብ ሊቨርፑል ታማኝ ወዳጅ አይዛክ ኬርኒ፡፡
እግር ኳስ የሰው ዘርን በአንድ ያነጋገረ ዓለምን አቀፍ ቋንቋ ነው። ጠቀሜታውም ከተራ ስፖርትነት የዘለለ ነው። ብዙዎች ህይወታቸው ተመስርቶበታል። በምክንያትነቱ እልፎች እንጀራቸው ተጋግሮበታል። ለበርካቶች የማይናቅ ታላቅ ጉዳይ ነው።
እግር ኳስ የድል ደስታን ከመስጠትም ባሻገር ነው፡፡ ህመምን የሚሽር ተስፋን የሚያበቅል ሀያል መድኃኒት ነው፡፡ በስድስት ዓመቱ አይዛክ ልብ ውስጥም የታየው ይሄው ነው፡፡ አይዛክ የሊቨርፑል ጥልቅ ፍቅር አለበት፡፡ ይሄ ፍቅሩ ታድያ ሁሉንም እንዲችል አቅም ሆኖታል፡፡ እሱ በእድሜ ትንሹ የአንፊልድ ኮከብ ነው።
አይዛክ ካራቴም ተምሯል፡፡ የአሻንጉሊት ጊታሩን ይዞ የክለቡን መዝሙሮች በደስታ ይዘፍናል፡፡ ይህ ታድያ በጥልቅ ስሜት የታጀበ አዘፋፈን ነው፡፡ ማንም የማይነጥቀው አይነት ደስታን ይደሰታል፡፡
ስለሱ የተሰራጨው ቪዲዮ ዓለም ስለ ፍቅር ሌላ መልክ እንዲያይ እድል ሰጥቷል፡፡ እውነትም እግር ኳስ የተአምራዊ ኃይል ባለቤት ነው አስብሏል፡፡ አይዛክ የወደደው ክለብ ሊቨርፑል ቤተሰባዊነት የሚታይበት ነው፡፡ የአይዛክን ፍቅር በመረዳት ሞሀመድ ሳላህን እና ቨርጂል ቫን ዳይክን የማግኘት እድል ተፈጥሮለታል፡፡ በዚህ ጊዜ የነበረው የአይዛክ ደስታ ከንግግር አቅም በላይ ነበር፡፡ የህይወት ፈተናን የሚያስረሳ ጥርስን በፈገግታ የሚሞላ ሀይል አለው፡፡
ወላጆቹ በልጃቸው ሰበብ አድገዋል፡፡ የአይዛክ ፍቅር ለቤተሰቡ ትልቅ መንፈሳዊ ብርታት ሆነ። እናቱ ሜሊሳ አይዛክ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ችግር ላለባቸው ተስፋ መሆኑን ትመሰክራለች፡፡ ከራሱ አልፎ ለሌሉች ወላጆች ተስፋ መሰነቅ ሰበብ ሆነ፡፡ እነዚህ ወላጆች ለችግሩ ድጋፍ መጠጊያ ጥጋት ፍለጋ ባዝነን ነበር ይላሉ። የአይዛክ ህልሙን መኖር ነገሮችን ቀያየረ። ይህም ለአይዛክ ወላጆች ተጨማሪ ደስታ ነው ብላለች፡፡
አይዛክ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮችን አፍርቷል፡፡ እግር ኳስ በትንሹ በእርሱ ፍቅር በኩል ብዙዎችን አክሟል፡፡ ስለ ህመሙም ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ውጤቱ አስደሳች ነበር፡፡ ይህም ከማንኛውም ዘመቻ በላይ የሆነ ተፅዕኖ አሳይቷል።
በዳግማዊት ግርማ

ቅድስት አርሴማ የልባችሁን መልካም መሻት ትሙላላችሁ🙏
ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት ነበር
ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ንጉሡ መልኳ ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ቆይተው በሮሜ አንድ ባለ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ንጽሕት ቅድስት አርሴማ ሲያገኙ ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት።
እናታችን ቅድስት ቅድስት አርሴማ ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ የሆነ መልከ መልካም ነበረች። ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ በልቡ በእጅጉ ፈቀዳትና እንዲያመጡለትም አዘዘ። ይህን እንደሰሙ እኒያ ደናግልና ቅድስት አርሴማ የገዳሙም እመምኔት የሆነችው ቅድስት አጋታ ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። በዚያም ሳሉ ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ግዛቱ ነበርና ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው።
እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ይህችን ውብ ሴትማ ለራስ ነው እንጂ ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይገባም ለራሱ ፈልጎ እዚያው አኖራት። ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ ቅድስት እናታችን ቅድስት አርሴማን ብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች፣ ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች።
ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ በልጥ አጸናቻት። ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ።
እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ እርሷንም በደናግሉ ሁሉ ፊት አሠራትና በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን “አይዟችሁ!” እያለች ታጽናናቸው ነበር። ይልቁንም ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ እጅግ በብዙ መከራ አሠቃያት። በመጀመሪያ ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣቸው፤ እርሷም እንዲህ ሳለች ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየትን ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሠላሳ ዘጠኝ ሴቶች ደናግል ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ።
ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው።
በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ ገዳማውያኑም ይህን ቃል ኪዳኗን አስበው አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Comments