የተስፋ ቀንዲል
#ethiopia | እኒህ እናት ኗሪነታቸው በሸገር ሲቲ በመናገሻ ከተማ ሲሆን ልጃቸው ዘር፤ ቀለም፤ፆታ፤ እድሜ እና የኑሮ ደረጃ በማይለየው ልጃቸው የአእምሮ ህመም ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ከግንቦት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል እያደረጉለት ይገኛሉ፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ፍስሃ ይባላሉ፡፡ እጅግ ጠንካራ፤ ልበሙሉና ለነገው ትውልድ ጥንካሬን ብርታትን የሚያስተጋቡ እናት ናቸው፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ልጃቸው የነበረበትን የቀድሞ ሁኔታ ሲገልፁ ልጄ ፍፁም መናገር አይችልም ነበር አሁን ግን ፈጣሪ ይመስገን በሆስፒታሉ በተደረገለት ህክምናና ክብካቤ መናገር ችሏል ይላሉ፡፡
በእርግጥ እግረ መንገዳችንን ልንገልፅላችሁ የፈለግነው የልጁን የጤና መሻሻል ይሁን እንጅ ዋናቁምነገር ግን ወ/ሮ አስናቀች ፍስሃን ያቀረብንበት ምክንያት ከሌሎች የቤተሰብ አስታማሚዎች ልዩ ሆነው በማግኘታችን ነው፡፡
ወ/ሮ አስናቀች የህክምና ባለሙያም አይደሉም ነገር ግን ተግባራቸው እንደማንኛውም ቤተሰብ ልጃቸው ከህመሙ ተፈውሶ መደበኛ ህይወቱን ሲመራ ማየት ጉጉታቸው ቢሆንም ልጃቸው ሲከታተሉበት የነበረው ሂደት ግን አድናቆትን ስለጫረብን ዛሬ ለእናንተ ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡
ወ/ሮ አስናቀች ልጃቸውን በሆስፒታሉ ውስጥ ሲያስታምሙ እንደማንኛውም የቤተሰብ አስታማሚ ጠዋት ቁርሱን፤ ቀን ምሳውን፤ ማታ እራቱን አለፍ ሲልም ንፅህናውን ማስጠበቅ ብቻ አልነበረም ከሚከታተለው ሃኪም ባልተናነሰ የልጃቸውን የመድሃኒት አወሳሰድ፤ አይነት፤ መጠን እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳቱን፤ መድሃኒቱን ሲወስድ የሚታዩ አካላዊና የባህሪ ለውጦችን በሙሉ አጀንዳ አዘጋጅተው የየዕለቱን መዝግበው ይይዛሉ፤፤ ይህንኑ መረጃም ለሚከታተለው የጤና ባለሙያ (ሃኪም) የታዩ ለውጦችን (progress) ቃል በቃል በመዘገቡት መሰረት ያስረዳሉ፡፡
እኒህ እናት በየጊዜው ተኝቶ ለሚታከመው ልጃቸው በሃኪም የሚታዘዙትን መድሃኒቶች የወረቀት ቢን ካርድ አዘጋጅተው ከቢን ካርዱ ላይ የመድሃኒቱን ሳምፕል በመለጠፍ ከስሩ የመድሃኒቱን አይነት (ስም/ብራንድ)፤ መጠን(ዶዝ)፤ የሚወሰድበትን ጊዜ በመመዝገብ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ ታካሚው መድሃኒቱን ሲወስድ የሚያሳያቸውን ለውጦች የጎንዮሽ ጉዳት ጨምሮ ለልጃቸው ሃኪም በሚያስረዱበት እናት መዝገብ(አጀንዳ) ላይ ያሰፍራሉ፡፡ ይህንን ተግባር ለአንድ ጊዜ ወይም ለሁለት ጊዜ ወይም ደግሞ ለሶስት ጊዜ አይደለም እየከወኑት የሚገኙት ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን 2018 ዓ.ም ድረስ እንጅ፡፡
ወ/ሮ አስናቀች እሳቸው የሄዱበትን የህክምና መረጃ አያያዝ የጋን ውስጥ መብራት ሆኖ እንዲቀር አልፈለጉም ፡፡በመሆኑም በአጠገባቸው ለሚገኙ ሌሎች አስታማሚዎችም ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል የሚሉት ወ/ሮ አስናቀች መረጃ በአግባቡ ተሰንዶ መያዞ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነ እረዳለሁ ይላሉ፡፡
ያ መጀመሪያ ላይ ቃል የማይናገረው ብላቴና አልጋ ላይ ሆኖ እናቴ መፅሃፍ ግዥልኝ ይለኛል እኔም ገዝቼ አመጣሁለት እሱም በስርዓቱ አንብቦ የተረዳውን በወረቀት ላይ ያሰፍራል፤ እኔም እከታተለዋለሁ ይሉናል የዛሬዋ እንግዳችን ወ/ሮ አስናቀች፡፡
በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቤተሰብ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ሚኪያስ ታደለ በበኩላቸው የጤና መረጃ ሰነድ አያያዝን አስመልክቶ በሃገራችን በታካሚ ወይም በአስታማሚ ደረጃ ስለሚደረገው ህክምናና ስለህመሙ ሁኔታ መዝግቦ መያዝ የተለመደ እንዳልሆነ አንስተው ነገር ግን ቁርጠኝነት ያላቸውና የችግሩ አሳሳቢነት የገባቸው እንደ ወ/ሮ አስናቀች ያሉ ሰዎች የህክምና መረጃን ሰንደው በመያዝ ግንባር ቀደምና ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው በማለት ያነሳሉ፡፡
ዶ/ር ሚኪያስ አያይዘውም የህክምና መረጃ መያዝ ጠቀሜታው ለታካሚው ብሎም ለቤተሰብ ጭምር ነው፡፡ አንድ ታካሚ ወይም አስታማሚ የሚወስደውን መድሃኒት አይነት፤ የሚያመጣውን ለውጥና የጎንዮሽ ጉዳት ለይቶ ማወቅ የጤንነቱን ሁኔታ እያሻሻለ እንዲሄድ ያግዘዋል ይላሉ፡፡
ምክንያቱን ሲገልፁም በክትትል ወቅት የመድሃኒቶች መደጋገም እንዳይኖር፤ በሃኪሞች መካከል የሚኖረውን መናበብ ለማሻሻል እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ የህክምና ፍሰቱን ወይም ሰንሰለቱን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል በማለት ያነሳሉ፡፡
እንግዲህ እኛም እንደ ወ/ሮ አስናቀች ያሉ ብርቱ፤ ቁርጠኛ እና የህክምና መረጃ ጤና መሆኑን የተረዱ ቤተሰቦችንና ተንከባካቢዎችን ያብዛልን እያልን እንሰናበታለን፡፡
ለአእምሮ ጤናዎ እንተጋለን!
አማኑኤል ሆስፒታል

1 month ago