ቲማቲም ለመልቀም የተላኩ ሁለት የወንድማማች ልጆች በወንዝ ተወስደዉ ህይወታቸው አለፈ
👉የሟቾች አስክሬን በፍለጋ ላይ ነው
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ቤተሰብ ቲማትም ለቅመዉ እንዲመለሱ ወደ ብላቴ ወንዝ ዳርቻ የተለኩ ሁለት ህፃናት በወንዝ ዉሃ መወሰዳቸዉ ፖሊስ አስታውቋል።
በቁሊቶ ከተማ የ2ኛ ጮሮቆ ቀጠና ነዋሪ የሆኑት የሁለት ህፃናት ቲማቲም ከማሳ ለቅመዉ እንዲያመጡ ተልከዉ ወደ ስፍራዉ መሄዳቸው ተነግሯል።
የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ሁለቱ ታዳጊዎች የወንድማማች ልጆች ሲሆኑ በየ12 ዓመቷ ታዳጊ አዳልጧት ወደ ዉሃዉ ስትገባ የ13 ዓመቷ ታዳጊ ቀድማ የገባችዉን ለማትረፍ ተከትላ ወደ ዉሃዉ ዉስጥ በመግባቷ ሁለቱም በዉሃ ተወስደዉ ህይወታቸዉ ማለፉን ገልጸዋል።
የሁለቱን ታዳጊዎች አስከሬን ለማግኘት ከትላንት ጀምሮ ፍለጋ መቀጠሉ ተገልጿል።በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የዝናብ መጠን እየጣለ በመሆኑ ደራሽ የወንዝ እና የጎርፍ አደጋ የሰዉ ህይወት እንዳይጠፋ ህብረተሰቡ ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲሉ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
seledadotio

4 months ago