ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች ... ቅድስት አርሴማ
ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ንጉሡ መልኳ ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ።
እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ቆይተው ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሲያገኙ ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። እናታችን ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች። ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና እንዲያመጡለትም አዘዘ። ደናግላኑ ይህን እንደሰሙ ከቅድስት አርሴማና ከገዳሙ እመምኔት ቅድስት አጋታ ጋር ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። አካባቢውን የሚገዛው ንጉሥ ድርጣድስ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው።
እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ይህችን ውብ ሴትማ ለራስ ነው እንጂ ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይገባም በማለት ከደናግሉም ጋራ ካሠራት በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን ሊያታልላት ይጥር ጀመር።
ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገችው እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች ናትና፤ ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ። እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ በደናግሉ ሁሉ ፊትም አሠራትና በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው።
ቅድስት አርሴማ ግን ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት “አይዟችሁ!” እያለችም ታጽናናቸው ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት። በመጀመሪያ ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣቸው፤ እርሷም እንዲህ ሳለች ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየት ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ዕለትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል።
በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡
እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በዚህ ቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

7 months ago