የተወለደበትን በረት ሊሳለም ወደ ቤተልሔም ይጎርፋል
በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።
ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ። ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ። ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፣ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 2÷1-6፡፡ የ15 ዓመቷ ብላቴና ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በማህጸንዋ ይዛ በንጉሱ ትዕዛዝ መሰረት ልትቆጥር ወደ ቤተልሔም ከዮሴፍ ጋር ተጓዘች፡፡
ማደሪያ ጠይቀው ቤቶች ሁሉ በእንግዶች ተሞልተዋልና የተገኘው ብቸኛው ማረፊያ የከብቶች ግርግም ነበር፡፡ የዓለሙን ጌታ በማሕጸኑዋ የያዘችውን የዓለሙን እመቤት ቢያውቋት ኖሮ ከእንግዶቻቸው የተወሰኑትን አስወጥተው፣ ያም ባይሆን አሸጋሽገው በቤታቸው ባሳድሯት ነበር፡፡ በዘመኑ እስከ ዓለም ፍጻሜ ይታወስ ዘንድ የታደለ አልነበረምና የሚያስተናግዳቸው አላገኙም፡፡ ምክንያቱም ዓለም ዛሬ በጌታችን ልደት ቀን የተወለደበትን ያንን በረት ሊሳለም ወደ ቤተልሔም ይጎርፋል፡፡ ታላላቅ አብያ መቅደሶች ተገንብተውበታል፡፡ ማደሪያ የከለከሏቸው ሰዎች ግን በስፍራው የሉም፡፡ ከእነርሱ ይልቅ በእስትንፋሳቸው ያሟሟቁት አድግና ላህም "አህያና ላሞቻቸው" ይታወሳሉ።
ከ2018 ዓመታት በፊት የተወለደው የዓለሙ መድኅን፣ የዘመናት ጌታ፣ ዘመን የማይቆጠርለት፣ ሰማይና ምድርን የወሰነ በድንግል ማሕጸን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተወስኖ፣ ሰውን ለማዳን፣ እንደሰው በግዕዘ ሕፃናት በፍጹም ድንግልና ቢወለድ ዘመን ተቆጠረለት፡፡ ከአውግስጦስ ቄሳር ሁሉም በትውልድ ከተማው ተገኝቶ ይቆጠር ወይም ይጻፍ ዘንድ በወጣው ትዕዛዝ መሰረትም ጌታችን እንደ ሰው ተጻፈ፣ ተቆጠረ፡፡ ዛሬም የልባችንን በር ያንኳኳል፤ ገብቼ ልደር ይላል፣ “እርሱና እናቱን በልባችን ለማስተናገድ ምን ያሕል ተዘጋጅተናል?” ልባችን በሌሎች እንግዶች ተይዞብናል? ጌታና እናቱ ወደኛ ሲመጡ ወደ በረቱ ነው የምንመራቸው? በዚያ የብርድ ወራት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን የምታለብሰው ልጅ ብታጣ፣ በጨርቅ ጠቅልላ ያስተኛችው ልጇን አድግና ላሕም ቀርበው በትንፋሻቸው አሞቁት፡፡
እርሱም እንደ ሕፃናት ከእናቱ ጡትን እየለመነ አለቀሰ፡፡ የድንግልና ጡቷንም ይዞ ጠባ፡፡ ይህን መገለጥ፣ ለእረኞች የነገራቸው የእግዚአብሔር መልአክም “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።” ገዳማውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን በበረት ለተወለደው ልባቸውን ሰጥተው ዓለምን ንቀዋታልና፣ ገዳመቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

7 months ago