እግር ኳስ ተስፋ ያቀበለው የመርሲሳይዱ ክለብ ድምቀት
#ethiopia | ይህ ክታብ በፍቅር ሀይል ትንፋሽ ስለተቀጠለለት አንድ ብላቴና ያትታል። ተአምር ሰው ቢሆን የእርሱን ስጋ ይላበስ ነበር፡፡ ጉዳዩ ባለታሪኩ በእናቱ ማህጸን ባለመኖር ሳለ ጀምሮ የሚመዘዝ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ስለ እሱ በሀኪሞች የተተነበየ ነገር ነበር፡፡ አይኖቹ ከማየት ጆሮዎቹ ከመስማት እግሮቹ ከእርምጃ ውጪ እንደሚሆኑ በሀኪሞች ተነግሯል፡፡ ከተወለደ በኋላ ግን የተባለው ሳይሆን ቀረ፡፡ የህይወቱ ተዓምራዊነት ከዚያን ጊዜ ይጀምር ነበር፡፡
ምድሪቱን ከማወቁ ቀድሞ ከWolf-Hirschhorn syndrome ጋር ተዋውቋል፡፡ ጉዳዩ የዘረመል ችግር ነው። ይህ ደግሞ በዝግታ እንዲያድግ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ ከውልደቱ ጀምሮ የሀኪም ቤቶች ቋሚ ደንበኛ ነው፡፡ ተደጋጋሚ ቀዶ ጥገናዎችን አድርጓል፡፡ ልቡም በዚህ መንገድ አልፋለች፡፡
በእርሱ ምክንያት ተስፋ የተቀጠለላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ በህይወት ማዕበል ለሚዳፉ ሁሉ የ "አላለቀም" የ "ይቀጥላል" ህያው ምስክር ነው፡፡ ሰው በሞት ካልተረታ "አበቃ" ብሎ ነገር ያለመኖሩ ማሳያም ጭምር፡፡ ፍቅር ድንበር የለሽ መሆኑን ለዓለምና መላዋ አስመስክሯል፡፡ የመርሲሳየዱ ክለብ ሊቨርፑል ታማኝ ወዳጅ አይዛክ ኬርኒ፡፡
እግር ኳስ የሰው ዘርን በአንድ ያነጋገረ ዓለምን አቀፍ ቋንቋ ነው። ጠቀሜታውም ከተራ ስፖርትነት የዘለለ ነው። ብዙዎች ህይወታቸው ተመስርቶበታል። በምክንያትነቱ እልፎች እንጀራቸው ተጋግሮበታል። ለበርካቶች የማይናቅ ታላቅ ጉዳይ ነው።
እግር ኳስ የድል ደስታን ከመስጠትም ባሻገር ነው፡፡ ህመምን የሚሽር ተስፋን የሚያበቅል ሀያል መድኃኒት ነው፡፡ በስድስት ዓመቱ አይዛክ ልብ ውስጥም የታየው ይሄው ነው፡፡ አይዛክ የሊቨርፑል ጥልቅ ፍቅር አለበት፡፡ ይሄ ፍቅሩ ታድያ ሁሉንም እንዲችል አቅም ሆኖታል፡፡ እሱ በእድሜ ትንሹ የአንፊልድ ኮከብ ነው።
አይዛክ ካራቴም ተምሯል፡፡ የአሻንጉሊት ጊታሩን ይዞ የክለቡን መዝሙሮች በደስታ ይዘፍናል፡፡ ይህ ታድያ በጥልቅ ስሜት የታጀበ አዘፋፈን ነው፡፡ ማንም የማይነጥቀው አይነት ደስታን ይደሰታል፡፡
ስለሱ የተሰራጨው ቪዲዮ ዓለም ስለ ፍቅር ሌላ መልክ እንዲያይ እድል ሰጥቷል፡፡ እውነትም እግር ኳስ የተአምራዊ ኃይል ባለቤት ነው አስብሏል፡፡ አይዛክ የወደደው ክለብ ሊቨርፑል ቤተሰባዊነት የሚታይበት ነው፡፡ የአይዛክን ፍቅር በመረዳት ሞሀመድ ሳላህን እና ቨርጂል ቫን ዳይክን የማግኘት እድል ተፈጥሮለታል፡፡ በዚህ ጊዜ የነበረው የአይዛክ ደስታ ከንግግር አቅም በላይ ነበር፡፡ የህይወት ፈተናን የሚያስረሳ ጥርስን በፈገግታ የሚሞላ ሀይል አለው፡፡
ወላጆቹ በልጃቸው ሰበብ አድገዋል፡፡ የአይዛክ ፍቅር ለቤተሰቡ ትልቅ መንፈሳዊ ብርታት ሆነ። እናቱ ሜሊሳ አይዛክ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ችግር ላለባቸው ተስፋ መሆኑን ትመሰክራለች፡፡ ከራሱ አልፎ ለሌሉች ወላጆች ተስፋ መሰነቅ ሰበብ ሆነ፡፡ እነዚህ ወላጆች ለችግሩ ድጋፍ መጠጊያ ጥጋት ፍለጋ ባዝነን ነበር ይላሉ። የአይዛክ ህልሙን መኖር ነገሮችን ቀያየረ። ይህም ለአይዛክ ወላጆች ተጨማሪ ደስታ ነው ብላለች፡፡
አይዛክ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮችን አፍርቷል፡፡ እግር ኳስ በትንሹ በእርሱ ፍቅር በኩል ብዙዎችን አክሟል፡፡ ስለ ህመሙም ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ውጤቱ አስደሳች ነበር፡፡ ይህም ከማንኛውም ዘመቻ በላይ የሆነ ተፅዕኖ አሳይቷል።
በዳግማዊት ግርማ

1 year ago