2 months ago
ዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ ይፋዊ የምረቃ እና የምስረታ ስነ-ስርዓቱን አካሄደ
#fastmereja I በመዋቢያ እና የውበት ጥበብ (Aesthetics) ዘርፍ ላይ ያተኮረው የዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ (DELTA SPMU ACADEMY) ይፋዊ የምረቃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ ተካሄደ።
የዴልታ ኤስቴቲክስ ትሬይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤደን ካሳሁን በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ ተቋሙ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች በተለይም ከዋና ከተማው ውጪ በየክልሎቹና በየገጠራማው አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ተደራሽ የሚሆን ተግባራዊ እና ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎችን ለመስጠት ራዕይ ሰንቆ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለጸው፣ ተቋሙ በውበት ጥበብ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ እና ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል ያለመ ነው።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በማብራሪያቸው “ስራን ለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ስራን ለመፍጠር፣ ገቢን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ነጻነትን ለመቀናጀት፣ ክህሎትን ለመማር ብቻ ሳይሆን ህይወትን ለመለወጥ” በሚል መርህ ተቋሙ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመው፣ ዴልታ አካዳሚ ፍጹም ባይሆንም ስህተቶችን እየታረመ እና የአሰራር መንገዶችን እያሻሻለ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንነት ለመስራት ቃል መግባቱን አስረድተዋል።
የዴልታ ኤስቴቲክስ ትምህርቱን 80 ፐርሰንት በኦንላይን ሲሆን 20 ፐርሰንት በተግባር ይሰጣል ተብሏል።
በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ ተቋሙ ለወደፊት ተማሪዎቹ፣ ለደጋፊዎቹ እና ለሽርክና አጋሮቹ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ የምስረታ ታሪክ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አዲስ የስራ እድል እና የክህሎት በር የሚከፍት መሆኑም ተመልክቷል። በፕሮግራሙ ላይ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የሜሪጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፏል።

ቀኝ አዝማች በኩረ ምዕመናን ትዛዙ ኮሬ የኢትዮጵያን ባህል፣ ቱሪዝምና በጎ አድራጎት በማስፋፋት የሚታወቁ ታዋቂ ኢንተርፕረነር፣ የባህል አምባሳደር እና ሀገር በቀል ሽማግሌ ናቸው። በተለይም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን እና ግዙፍ የባህል ምግብ ቤቶች አንዱ የሆነውን ዮድ አቢሲኒያ (Yod Abyssinia) ባህላዊ ምግብ ቤት በመመስረታቸው በሰፊው ይታወቃሉ።
ስለ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ዋና ዋና መረጃዎች
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና ባለቤት በ1996 ዓ.ም.
(እ.ኤ.አ. በ2003) ዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ ምግብ ቤትን መስርተዋል።
ምግብ ቤቱ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች፣ ሙዚቃዎች እና ውዝዋዜዎች ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ዜጎች በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
እንደ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ያሉ በርካታ የዓለም መሪዎችን እና የውጭ አገር ዲፕሎማቶችን በምግብ ቤታቸው አስተናግደዋል።
❸ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
ለተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት እና ችግረኛ ወገኖች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃሉ።
በበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸው ምክንያት በ2016 ዓ.ም የፊላንትሮፒ (የበጎ አድራጎት) ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።
በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰላምን ለማስፈንና እርቅ ለማውረድ እንደ ትልቅ የሀገር ሽማግሌ ሆነው ያገለግላሉ።
በጎ ተግባራት እና ማህበራዊ ሀላፊነት በመወጣት አርዓያነት ያለዉን ተግባራት በመስራት ይታወቃል።
የዓመቱን 360 ቀናት ለኢትዮጵያ ሀገራቸዉ እንዲሁም 4 ቀናት ለበጎ አድራጎት ተግባራት ሲውል ፤ 365 ኛውን ቀን ደግሞ ዕድገት እንደሚያስተዋዉቅ የሚያምኑት የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ናቸዉ።
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ እንዲሁም ድርጅታቸዉ 'ዮድ አቢሲኒያ'ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር፣ ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ፣ ለቶራ የህፃናት ማሳደጊያ ፣ ለሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ ለየወደቁትን እናንሳ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ለሌሎችም በማገዝና በመርዳት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በጎ ስምና አርዓያነትን በተግባር ለማሳየት ችሏል።ወደፊትም ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
❹እዉቅናና ሽልማት
➢የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና
ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደዉ የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና በቅርስ ባህል እና ቱሪዝም ዘርፍ ዮድ አቢሲኒያ፡የባሕል ምግብ አዳራሽ ተሸልሟል።
የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦችን ፤ ውዝዋዜዎችን እና ባህላዊ እሴቶችን ለቱሪስቶች እና ማህበረሰቡ የሚያቀርብ ተቋም ሲሆን የኢትዮጵያን እሴቶችን በማስተዋወቅ ረገድ ያስቀመጠው ደማቅ አሻራ ከፍ ያለ ነዉ።
ዮድ አቢሲኒያ ባህል ባንድ
ለቱሪስቶች የአገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎች ዉዝዋዜን በማሳየት ቱባ ባህላችንን ሳይበረዝና ሳይከለስ ያሳያል።
➢ የቱሪዝም አዋርድ
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሐምሌ 6/2016ዓ.ም በአድዋ መታሰብያ ሙዚየም ባካሄደው የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ምስረታና 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለከተማችን የቱሪዝም ልማትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቱሪዝም ተቋማትና አካላት የቱሪዝም አዋርድ ከተሰጡት መካከል አንዱ ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ ነዉ።
የቱሪዝም ተቋማቱ በሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት ባላቸው የቱሪዝም ፈጠራ ስራ እንዲሁም የቱሪስት አያያዝና የመሳሰሉት መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ ከዘርፉ 1ኛ በመዉጣት ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ፣የቱሪዝም አዋርድ ተሸልሟል።
➢"የ8ኛዉ የአርአያ ሰው ሽልማት"
ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት"የአርአያ ሰው ሽልማት" በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡
ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ አንዱ ነዉ።
ዓለም አቀፍ እውቅና
የኢትዮጵያን ባህልና ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቃቸው “የባህልና ቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ክብር ተሰጥቷቸዋል።
በቅርቡ (እ.ኤ.አ በ2025) በአሜሪካ ሲያትል በተካሄደው የ42ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል (ESFNA) ላይ ለሀገራቸው ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ልዩ የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
❺ዋና ዋና ቅርንጫፎችና አድራሻዎች
ዮድ አቢሲኒያ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቁልፍ ቦታዎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ ይገኛል፦
ቦሌ ቅርንጫፍ (ዋናው)፦ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ፣ ከብራስ ሆስፒታል ከፍ ብሎ የሚገኝ የነበረ ሲሆን አሁን ቀድሞ ከነበረበት በ100 ሜትር ገባ ብሎ ኬኬር ህንፃ አጠገብ ይገኛል።ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርብ በመሆኑ ለቱሪስቶች ተመራጭ ነው።
ፒያሳ (ቴዎድሮስ አደባባይ) ቅርንጫፍ፦ በቅርቡ በዲል ፕላዛ ፊት ለፊት የተከፈተ አዲስና ዘመናዊ የባህል አዳራሽ፣ የስፖርት ባር (Sport Bar) እና የባዛር ማዕከል ነው።
ዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል፦ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ማዕድን ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል ነው።
❻የ"ዮድ" መሪ ቃል በተግባር
የድርጅቱ መሪ ቃል የሃገራችን ኢትዮጵያን ”ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ” የሚል ነው ባለፉት 22 ዓመታት የኢትዮጵያን ባህልና መስተንግዶን ጨምሮ ሲያስተዋውቅ ኖሯል ፡፡ ለዚህም አስተዋፅኦው ”የኢትዮጵያ የባህልና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ዕውቅና ከመንግስት ተሰጥቶታል ፡፡
“ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ” በሚል መርህ ከመላው ዓለም ወደ ሃገራችን ለመጡ እንግዶች የባህል ምግብና መጠጦች መስተንግዶ በመስጠት ፣ የብሔር ብሄረሰቦችን ሙዚቃዎችና ውዝዋዜዎች በማቅረብ ፣ የሀገራችንን የታሪክ የባህልና የቱሪዝም ሃብቶችና ቅርሶቻችንን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በመገንባት ብዙ በመስራት ”የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል እውቅናን ለማግኘት ችሏል፡፡
"ዮድ"
ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ
በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ እሱ ኃያልና
ጽኑዕ የሆነ ነው ማለት በሌላ መልኩ"ዮድ" ማለት በጉራጌ ቋንቋ "መመስከር ወይም መናገር" ማለት ነዉ።
ከ1996ዓ.ምማለትምላለፉት 22 ዓመታት በተለያዩ ወቅቶች ወደ ሀገራችን የመጡ በርካታ የሀገራት መሪዎችን ፣ ዲፕሎማቶችን ፣ የዓለም ታላላቅ ሰዎችን፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ አትሌቶች ፣ አርቲስቶች የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎችም በሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችንና ኢትዮጵያዊያን እንግዶችን ተቀብሎ በፍቅርና በአክብሮት ሲያስተናግድ የቆየው ዮድ አቢሲኒያ በቀጣይም በሀገራችን ለሚከናወኑ ታላላቅ ሁነቶች ሙሉ አገልግሎት ለመስጠት ከወትሮው በተለዬ አኳኋን መዘጋጀቱ ተስተዉሏል።በ500 ብር ካፒታል እና በአነስተኛ የስራ ጅምር በጥረት የተገነባ ካምፓኒ በበርካታ ፈተናዎች ዉስጥ አልፎ ዛሬ በርካታ ቁጥር ላላቸዉ ወገኖቻችን የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ኩባንያ ለመሆን በቅቷል።
"የሃገራችን ኢትዮጵያን ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ”ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ
ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ

3 months ago
ሜሪ ጆይን ለማገዝ የእግር ጉዞ ተደረገ
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "ኩላሊት ጤና፣ ህይወት ተስፋ" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የገቢ ማሰባሰቢያ የሩጫ መርሀ ግብር አዘጋጀ።
እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም መነሻውን ካዛንችስ ዑራዔል በአዲሱ መንገድ ወደ ወሎ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው የተጀመረ ሲሆን ከ7000 በላይ ሰዎችም ተሳትፈዋል።
በዕለቱ' የኩላሊት ጤና ጉዳይ ያገባኛል ከሜሪጆይ ጋር እቆማለሁ' ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ህብረ-ዝማሬዎችን እየዘመሩ ለሩጫው ትልቅ ድምቀት ሰጥተውት ነበር።
በሩጫ ወይም በአጭር የእግር ጉዞው ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎች እንደነገሩን እንዲህ ዓይነት መርሀ- ግብሮች ህብረተሰቡን የማሰባሰብ አቅም ያላቸው በመሆኑ በኩላሊት ጤና ጉዳይ ላይ በቀላሉ ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
ወይዘሮ ጠይባ ሀሠን የስደተኞችና ተመለሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሩጫ መርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጡ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
ወይዘሮ ቆንጂች ደበላ የአዲስ አበባ የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣የኢትዮጵያ የሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር አፎሚያ አበበ፣ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ፣ እና የሜሪ ጆይ የቦርድ አባላት በሩጫ መርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት መገኘታቸው ታውቋል።
የመከላከያ የማርሽ ቡድን አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ከተዘመረ በኃላ ከፊት ሆነው የእግር ጉዞውን ያስጀመሩ ሲሆን ተሳታፊዎችም እነርሱን በመከተል ነበር የእግር ጉዞውን ያደረጉት።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ የኢትዮሪልስቴት አልሚዎች ማህበር፣የዋሪት፣ የዳሸን ባንክ፣ የህብረት ባንክ ሌሎችም ተቋማት ድጋፍ በማድረግ ለመርሀ ግብሩ መሳካት የበኩላቸውን አድርገዋል።
በሩጫ መርሀ ግብሩ ላይ የታደሙት ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ፣ ከ10,000 ሰዎች በላይ ቲሸርት ገዝተው ድጋፍ ያደረጉ መሆኑን ገልፀው 7000 ሰዎች በሩጫው ላይ መሳተፋቸው ለሜሪ ጆይ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።
በተመሳሳይ መልኩ ሌላ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሩጫ መርሀ -ግብር በሀዋሣ ከተማ እንደሚደረግ ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለውን ስለ ኩላሊት የማስተማር ዘመቻ ከፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በ1986 ዓ.ም. በህግ የተቋቋመ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ከ3 አሰርት ዓመታት በላይ በተለያዩ ክልሎች የተቀናጀ የልማት እና ሰብዓዊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በመንግስት፤ የግሉ ዘርፍ እና በማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ የጤና አገልግሎቱን ለማጠናከር እና ማህበረሰቡን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሆስፒታል ግንባታ ስራዎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እያጠናከረ የሚገኝ ሲሆን በተለይም ለኩላሊት ጤና ችግሮች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የኩላሊት እጥበት ህክምና ማዕከላት በሃዋሳ፤ በአዲስ አበባ እና አርባ ምንጭ ከተሞች አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ በቅርቡ አገልግሎቱን በደብረ ብርሃን ከተማ ለመጀመር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህንን አገልግሎት በሌሎች ከተሞች ለማስፋፋት እና ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የዚህን መርሀ ግብር የሚድያ ማስተባበር ሥራ ያከናወነው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን (ዕዝራ እጅጉ ) እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

አርቲስት ነፃነት አንበርብር የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል አምባሳደር ሆነች
#ethiopia | ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ሰብአዊ ተግባር ይበልጥ ለማሳደግ ታዋቂዋን ተዋናይት ነፃነት አንበርብርን የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧታል።
ላለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት በጤና፣ በትምህርት እና በተለያዩ ማህበራዊ ድጋፎች ላይ በስፋት ሲሳተፍ የቆየው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ አርቲስቷን አምባሳደር አድርጎ የሾመው ተቋሙ በኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለህዝብ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በማለም ነው።
ማዕከሉ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የኩላሊት ህሙማን የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ የሚለውን መሪ ቃል በመጠቀም የሚንቀሳቀሰው ሜሪ ጆይ፣ ይህ አዲስ አጋርነት የኩላሊት እጥበት አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና ግንዛቤ ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
#ሜሪጆይ #ጤና #ነፃነትአንበርብር #ኩላሊትእጥበት #ሰብአዊነት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
"የእኔም ልጆች ናቸው"
— የ50 ሺህ ሕፃናትን ተስፋ የምናለመልምበት ጥሪ
#"Ethiopia | ትምህርት ሚኒስቴር የዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደገለጸው፣ በሀገራችን ከ7 እስከ 9 ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው። ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ታላቅ የሰብዓዊነት ንቅናቄ ጀምሯል።
የጥሪው ዓላማ፦
"የእኔም ልጆች ናቸው
ይህ ንቅናቄ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ትምህርት የራቃቸውን 50,000 ሕፃናት ወጪ በመሸፈን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ያለመ ነው።
የእነዚህ ሕፃናት "የቆምኩለት ወላጅ" በመሆን የሚከተለውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ፦
በሀገር ውስጥ፦
በአንድ ልጅ በወር 1,000 ብር (በዓመት 12,000 ብር)።
ከሀገር ውጭ፦
በአንድ ልጅ በወር 10 ዶላር።
📺 ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት
ይህንን በጎ ዓላማ ለማሳካት ታዋቂዎቹ ባለሙያዎች አዜብ ወርቁ እና መዓዛ ወርቁ ከሜሪ ጆይ መሥራች እማዋይሽ ዘውዱ ጋር በመሆን ዛሬ ማታ ልዩ ዝግጅት ያቀርባሉ።
ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም.
ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ።
የመገናኛ ዘዴ፦ በአባይ ቴሌቪዥን (Abay TV) የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት።
አንድ ልጅ ከትምህርት ገበታው እንዳይቀርና የተሻለ ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከጎናቸው እንቁም። ይህንን መልእክት ላልሰሙት በማድረስ (Share በማድረግ) የበኩላችሁን እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
አንድ ልጅ ማስተማር — ትውልድን መታደግ ነው!
#የእኔምልጆችናቸው #ሜሪጆይኢትዮጵያ #ትምህርትለሕፃናት #አዜብወርቁ #መዓዛወርቁ #ኢትዮጵያ #maryjoyethiopia #educationforall #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
5 months ago
ሜሪ ጆይ በአዲስ አበባ አዲስ የኩላሊት እጥበት ማዕከል አስመረቀ! ✨
#ethiopia | ከተመሠረተ 32 ዓመታትን ያስቆጠረውና በሰብዓዊ አገልግሎቱ የሚታወቀው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ አበባ አስኮ አካባቢ የሚገኘውን ዘመናዊ የኩላሊት እጥበት ሕክምና ማዕከል የካቲት 20/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
የማዕከሉ ዋና ዋና ገጽታዎች፦
አገልግሎት፦
ማዕከሉ በ10 አልጋዎች ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ ሕክምናውን ለዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ያለመ ነው።
ተገኝተው ያስመረቁ፦
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ተቋማትና በጎ አድራጊዎች።
ስፋት፦
ሜሪ ጆይ ቀደም ሲል በሀዋሳ ማዕከል የከፈተ ሲሆን፣ በቀጣይም በአርባ ምንጭ፣ በደብረ ብርሃን እና በሆሳዕና ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቱን ጨርሷል።
🤝 የወገን ደራሽነትና የክብር አባልነት፦
የማዕከሉ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፣ ለማዕከሉ መሳካት አስተዋፅኦ ያበረከቱትን አመስግነው፤ በዕለቱም በርካታ ግለሰቦችና ተቋማት የማዕከሉ "የክብር አባል" በመሆን ፊርማቸውን አኑረዋል።
ከክብር አባላቱ መካከል፦
ካዲስኮ (Kadisco)
ዶ/ር መቅደስ ዳባ (የጤና ጥበቃ ሚኒስትር)
ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን (የስደትና ተመላሾች አገልግሎት ኮሚሽን ዳይሬክተር)
አዋጭ ብድርና ቁጠባ
የቶቶት ምግብ ቤት ባለቤት አቶ ጠንክር ቴኒ እና ሌሎችም...
የእርስዎ ሚና፦
የኩላሊት ሕመም ብዙዎችን ለከፍተኛ ወጪና ስቃይ የሚዳርግ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ ማዕከላት እንዲጠናከሩ ሁላችንም ከሜሪ ጆይ ጎን ልንቆም ይገባል።
#ሜሪጆይ #የኩላሊትእጥበት #ጤናኢትዮጵያ #ሲስተርዘቢደርዘውዴ #አዲስአበባ #maryjoyethiopia #dialysis #healthcare #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
ሜሪ ጆይ የ15 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ተፈራረመ
#fastmereja I የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር ለችግር ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል የ15 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ።
ፕሮጀክቱ 500 ለሚደርሱ ለችግሩ ተጋላጭ ህፃናት፣ሴቶች፣አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ለሚቀጥሉት 2 ዓመት ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደኾነ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ከመንግሥት ተቋማት፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከዳያስፖራ ኮምዩኒቲ ሀብት በማሰባሰብ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ፣ አሳዳጊዎችን አረጋውያን እና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የ15 ሚሊዬን ብር ፕሮጀክት ነው ሜሪጆይ የተፈራረመው።
በዕለቱ ከደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ሥራ የሚውል የመሬት ርክክብም የተደረገ ሲሆን የህፃናት ሁለገብ አገልግሎት የማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል።
የድጋፍ ስምምነቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት በተገኙበት የደብረ ብርሃን ከተማ ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ፣ የከተማው ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ ነው። የሥራ ኃላፊዎቹ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ጋር ተፈራርመዋል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሄዋን ፋውንዴሽን መሥራች ወይዘሮ ሄዋን ቀለመወርቅን ጨምሮ የሜሪ ጆይ የቦርድ አባላት፣ታላላቅ አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ተቀዳሚ ከንቲባው መንግሥት ማህበራዊ ኃላፊነት ከሚወጡ ተቋማት ጎን አብሮ እንደሚቆም ገልፀው በማዕከሉ ግንባታ ላይም ሁሉም ተረባርቦ ድጋፉን ማድረግ አለበት ብለዋል።
በተያያዘ ዜናም፣ ተጋላጭ ህፃናትን ለመደገፍና የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ለማስጀመር ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን የውል ስምምነት በዚያው ዕለት ተፈራርመዋል።
ሔዋን ፋውንዴሽን ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውል ቤት ለሜሪጆይ ያበረከተ ሲሆን ይህም የፋውንዴሽኑ ቀዳሚ ተግባሩ እንደሆነ ወይዘሮ ሔዋን ቀለመወርቅ ተናግረዋል።

11 months ago
ለምስክርነት የቆየች ህይወት
#ethiopia | በዮድ አቢሲኒያ ባለቤት የተዘጋጀው "ለምስክርነት የቆየች ህይወት" መጽሐፍ ለአንባቢያን ልትበቃ ነው።
የአቶ ትዕዛዙ ከልጅነት እስከዛሬ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ እና ታሪካቸው የያዘ መፅሐፍ ነው።
“ለምስክርነት የቆየች ህይወት" በሚል ርዕስ የተሰናዳው ይህ መፅሐፍ የህትመትና ሌሎችም ወጪዎች ጨምሮ ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።
"ለምስክርነት የቆየች ህይወት" መጽሐፍ ለመጀመርያ ጊዜ 5ሺ ቅጅ መታተሙ የተገለጸ ሲሆን የዚህ መጽሐፍ ሽያጭ ሙሉ ገቢው ለተመረጡ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይውላል ተብሏል።
ድርጅቶቹም መቄዶንያ ፣ ሜሪጆይ ፣ ቶራ የህፃናት ማሳደጊያ ፣ ሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ የወደቁትን እናንሳ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ናቸው።
መጽሐፉ የፊታችን መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ/ም ይመረቃል ተብሏል።
በቀኝ አዝማች ትዕዛዙ ህይወት ዙርያ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት የተጻፈው ወጣቶች፣ እየታተሩ ያሉ ሰዎች የትኛውም ችግር በሚያጋጥማቸው እንዴት መቋቋም ይችላሉ ችግር እንዴት ማለፍ ይችላሉ የሚለውን የማስተማር ነው ብለዋል።
ዮድ አቢሲኒያ በየአመቱ የሚያከብረው የዘንድሮው"መስቀረንዳ በቃያንዳ" ፕሮግራም እንዲህ አይነት የበጎ አድራጎት ስራ የሚከናወንበት ይሆናል ብሏል።
ቀደም ሲል እንደምናደርገው የዓመቱን 360 ቀናት ለኢትዮጵያ ሀገሬ 4 ቀናት ለበጎ አድራጎት ተግባራት ሲውል ፤ 365 ኛውን ቀን ደግሞ ዕድገት ያስተዋውቃል።
በመሆኑም ከቋሚ ደንበኞቻችን ፣ ከአጋሮቻችንና ከባለድርሻዎቻችን ጋር ከዚህ የተዘጋጀው 15ኛው የጉራጌ መስቀል በዓል እና የደንበኞች ቀን የፊታችን እሁድ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል ነው የተባለው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Comments