Logo
FastMereja
ሜሪ ጆይ የ15 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ተፈራረመ
#fastmereja I የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር ለችግር ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል የ15 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ።

ፕሮጀክቱ 500 ለሚደርሱ ለችግሩ ተጋላጭ ህፃናት፣ሴቶች፣አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ለሚቀጥሉት 2 ዓመት ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደኾነ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ከመንግሥት ተቋማት፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከዳያስፖራ ኮምዩኒቲ ሀብት በማሰባሰብ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ፣ አሳዳጊዎችን አረጋውያን እና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የ15 ሚሊዬን ብር ፕሮጀክት ነው ሜሪጆይ የተፈራረመው።

በዕለቱ ከደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ሥራ የሚውል የመሬት ርክክብም የተደረገ ሲሆን የህፃናት ሁለገብ አገልግሎት የማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል።

የድጋፍ ስምምነቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት በተገኙበት የደብረ ብርሃን ከተማ ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ፣ የከተማው ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ ነው። የሥራ ኃላፊዎቹ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ጋር ተፈራርመዋል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሄዋን ፋውንዴሽን መሥራች ወይዘሮ ሄዋን ቀለመወርቅን ጨምሮ የሜሪ ጆይ የቦርድ አባላት፣ታላላቅ አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ተቀዳሚ ከንቲባው መንግሥት ማህበራዊ ኃላፊነት ከሚወጡ ተቋማት ጎን አብሮ እንደሚቆም ገልፀው በማዕከሉ ግንባታ ላይም ሁሉም ተረባርቦ ድጋፉን ማድረግ አለበት ብለዋል።

በተያያዘ ዜናም፣ ተጋላጭ ህፃናትን ለመደገፍና የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ለማስጀመር ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን የውል ስምምነት በዚያው ዕለት ተፈራርመዋል።

ሔዋን ፋውንዴሽን ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውል ቤት ለሜሪጆይ ያበረከተ ሲሆን ይህም የፋውንዴሽኑ ቀዳሚ ተግባሩ እንደሆነ ወይዘሮ ሔዋን ቀለመወርቅ ተናግረዋል።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.