Logo
FastMereja
ዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ ይፋዊ የምረቃ እና የምስረታ ስነ-ስርዓቱን አካሄደ
#fastmereja I በመዋቢያ እና የውበት ጥበብ (Aesthetics) ዘርፍ ላይ ያተኮረው የዴልታ ኤስፒኤምዩ አካዳሚ (DELTA SPMU ACADEMY) ይፋዊ የምረቃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ ተካሄደ።

የዴልታ ኤስቴቲክስ ትሬይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤደን ካሳሁን በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ ተቋሙ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች በተለይም ከዋና ከተማው ውጪ በየክልሎቹና በየገጠራማው አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ተደራሽ የሚሆን ተግባራዊ እና ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎችን ለመስጠት ራዕይ ሰንቆ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለጸው፣ ተቋሙ በውበት ጥበብ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ እና ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል ያለመ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በማብራሪያቸው “ስራን ለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ስራን ለመፍጠር፣ ገቢን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ነጻነትን ለመቀናጀት፣ ክህሎትን ለመማር ብቻ ሳይሆን ህይወትን ለመለወጥ” በሚል መርህ ተቋሙ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመው፣ ዴልታ አካዳሚ ፍጹም ባይሆንም ስህተቶችን እየታረመ እና የአሰራር መንገዶችን እያሻሻለ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንነት ለመስራት ቃል መግባቱን አስረድተዋል።

የዴልታ ኤስቴቲክስ ትምህርቱን 80 ፐርሰንት በኦንላይን ሲሆን 20 ፐርሰንት በተግባር ይሰጣል ተብሏል።

በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ ተቋሙ ለወደፊት ተማሪዎቹ፣ ለደጋፊዎቹ እና ለሽርክና አጋሮቹ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ የምስረታ ታሪክ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አዲስ የስራ እድል እና የክህሎት በር የሚከፍት መሆኑም ተመልክቷል። በፕሮግራሙ ላይ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የሜሪጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፏል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.