6 months ago
ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ 32 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
#ethiopia | ኦፕሬሽኑ በስጋ ቤቶች እና በግንባታ እቃዎች መሸጫዎች ላይ አነጣጥሯል
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ትላንት ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን፤ ህጋዊ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
የኦፕሬሽኑ ዝርዝር:
መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በተደረገው በዚህ ዘመቻ፤ 19 ስጋ ቤቶች እና 6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሸ ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
እርምጃው:
በቁጥጥር ስር የዋሉት የንግድ ድርጅቱ ባለቤቶችና ሽያጭ ያከናወኑ ሰራተኞች ሲሆኑ፤ የመንግስትን ግብር ለመሰወር እና አዋጅን በመተላለፍ ወንጀል ተጠርጥረው ለፍርድ ይቀርባሉ።
ማስጠንቀቂያ:
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኦፕሬሽን ተግባር በቀጣይ ቀናትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ህብረተሰቡ ግብይት ሲፈጽም ደረሰኝ እንዲጠይቅ እና ጥቆማ ለመስጠት በ 7075 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።
ህግን ማክበር ለራስ ሰላም ነው!
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
#addisababa #revenuesbureau #taxcompliance #operation #legalaction #mercato #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
11 የኮንስትራክሽን ግብአት ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
* "ያለ ደረሰኝ የሚደረግ ግብይት በህግ ያስጠይቃል!"
#ethiopia | የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ድንገተኛ የኦፕሬሽን ስራ፤ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ የተገኙ 11 የኮንስትራክሽን ግብአት አከፋፋዮች እና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ገለጸ።
የኦፕሬሽኑ ዝርዝር፡-
📅 ጊዜ፡ አርብ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 ቦታ፡ መርካቶ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች
🏗 ዘርፍ፡ የኮንስትራክሽን ግብአት አከፋፋይ ድርጅቶች
ቢሮው እንዳስታወቀው፤ 10 የንግድ ድርጅቶች ህጋዊ የደረሰኝ አጠቃቀም ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው፤ 11 የንግድ ስራ ባለቤቶች እና ሰራተኞች ተጠርጥረው ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል።
#addisababa #revenuesbureau #taxlaw #construction #mercato #businessnews #reportcorruption

እጅ ከፍንጅ! ጉቦ ሲቀበል የነበረው የኦዲት ባለሙያ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | "ሰነድህ ትክክል አይደለም" እያሉ የግብር ከፋዩን መብት በመርገጥ ጉቦ የጠየቁ አካላት በሕግ ወጥመድ ገብተዋል።
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኦዲት ባለሙያ እና አስተባባሪ፤ አንድ ግብር ከፋይ ያቀረበውን የ3 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ የወጪ ሰነድ "አንቀበልም" በማለት ለአንድ ወር ሲያመላልሱት ቆይተዋል።
ነገሩ ወዲህ ነው...
እነዚህ አካላት ትክክለኛውን ሰነድ ወደ ጎን በመተው ጉቦ እንዲሰጣቸው ግብር ከፋዩን ወጥረው ይይዛሉ። ግብር ከፋዩ ግን በድርጊቱ ባለመተባበር በቢሮው 7075 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ ይሰጣሉ።
በተደረገው ክትትልም፦
ባለሙያው 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ጉቦ ሲቀበል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ይዞታል። የኦዲት አስተባባሪዋም ከኃላፊነት ተነስተው ጉዳዩ እየተመረመረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ መልዕክት:
ሌብነትን ዝም አንበል! ግብር ከፋዩ እንዳደረገው በ 7075 በመደወል የበኩላችንን እንወጣ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
#addisababa #revenuesbureau #anticorruption #7075 #justice #bole

Comments