5 months ago
የገቢዎች ቢሮ ድንገተኛ ኦፕሬሽን
ያለ ደረሰኝ የሱፍ ልብስ ሲሸጡ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ! ⚖️
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከል ባደረገው የተቀናጀ ድንገተኛ ኦፕሬሽን፣ በሱፍ ልብስ ንግድ ላይ የተሰማሩና ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 7 ግለሰቦችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
📌 የኦፕሬሽኑ ዝርዝር፦
የተያዙት፦ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነ ኦፕሬሽን በ5 የንግድ ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ 7 ተጠርጣሪዎች (ባለቤቶችና ሰራተኞች) እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
የተፈጸመው ጥፋት፦ በመንግስት የተጣለባቸውን የደረሰኝ አጠቃቀም ግዴታ በመጣስ፣ የመንግስትን ግብር ለመሰወር ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።
ቀጣይ እርምጃ፦ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በፖሊስ ተይዞ ለፍርድ የሚቀረቡ ሲሆን፣ ቢሮው ኦፕሬሽኑን በሌሎች ዘርፎችም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
📊 የቢሮው የሁለት ወራት አፈጻጸም፦
ቢሮው ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ በጎማ፣ በኤሌክትሮኒክስ፣ በስጋ ቤትና በኮንስትራክሽን ዕቃዎች ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በወሰደው እርምጃ 67 ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ ይዞ ለሕግ ማቅረቡን አስታውሷል።
💡 ለህብረተሰቡ የቀረበ ጥሪ፦
የንግዱ ማህበረሰብ ማንኛውንም ግብይት በደረሰኝ ብቻ እንዲፈጽም ቢሮው አሳስቧል።
ህብረተሰቡ መሰል የደረሰኝ አለመቁረጥ ወንጀሎችን ሲመለከት በ 7075 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም እንዲያጋልጥ ጥሪ ተላልፏል።
#addisababarevenues #taxcompliance #ethiopia #economicintegrity #lawenforcement #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ 32 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
#ethiopia | ኦፕሬሽኑ በስጋ ቤቶች እና በግንባታ እቃዎች መሸጫዎች ላይ አነጣጥሯል
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ትላንት ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን፤ ህጋዊ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
የኦፕሬሽኑ ዝርዝር:
መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በተደረገው በዚህ ዘመቻ፤ 19 ስጋ ቤቶች እና 6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሸ ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
እርምጃው:
በቁጥጥር ስር የዋሉት የንግድ ድርጅቱ ባለቤቶችና ሽያጭ ያከናወኑ ሰራተኞች ሲሆኑ፤ የመንግስትን ግብር ለመሰወር እና አዋጅን በመተላለፍ ወንጀል ተጠርጥረው ለፍርድ ይቀርባሉ።
ማስጠንቀቂያ:
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኦፕሬሽን ተግባር በቀጣይ ቀናትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ህብረተሰቡ ግብይት ሲፈጽም ደረሰኝ እንዲጠይቅ እና ጥቆማ ለመስጠት በ 7075 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።
ህግን ማክበር ለራስ ሰላም ነው!
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
#addisababa #revenuesbureau #taxcompliance #operation #legalaction #mercato #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
ማስጠንቀቂያ ለነጋዴዎች!
ልዩ መለያ (QR-Code) የሌለው ደረሰኝ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ዋጋ አይኖረውም!
#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከግሉ ዘርፍና ከመንግሥት አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እንደተገለጸው፤ ልዩ መለያ ወይም QR-Code የሌላቸው ነባር ደረሰኞች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከሥራ ውጭ ይሆናሉ።
🔍 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የQR-Code አስፈላጊነት፦ ማንኛውም ነጋዴ የሚያሳትመው ደረሰኝ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ልዩ መለያ (QR-Code) ሊኖረው ይገባል። ይህ አሰራር የታክስ ስሌትን ትክክለኛ ለማድረግና ሕገ-ወጥ ደረሰኞችን ለመቆጣጠር የታለመ ነው።
የጊዜ ገደብ፦ ነባር (ልዩ መለያ የሌላቸው) ደረሰኞች የሚያገለግሉት እስከ መጪው ሳምንት መጀመሪያ ድረስ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
ውይይቱ፦ ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው ምክር ቤቱ የኢንቨስትመንት መልካም አስተዳደርንና የተቋማትን ቅልጥፍና ለማሻሻል ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ ላይ ነው።
💡 ለነጋዴዎች የተላለፈ መልዕክት
ነጋዴዎች ያሏቸውን ነባር ደረሰኞች በአዲሱና ልዩ መለያ ባለው ደረሰኝ በአስቸኳይ እንዲተኩ ተሳስቧል። ይህንን ሳያደርጉ ቀርተው በነባሩ ደረሰኝ ግብይት መፈጸም በሕግ ሊያስጠይቅ እንደሚችል ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #addisababa #taxnews #businessalert #qrcode #taxcompliance #economy #tradenews #update

8 months ago
በግብር ህጉ መሰረት ኪሳራን ስንት ግዜ ማሸጋገር ይፈቀዳል ❓
(Loss carry forward)
#ethiopia | ግብር ከፋይ ሁልግዜ ትርፍ ሊያተርፍ አይችልም አንዳንድ ግዜ ኪሳራም ያጋጥመዋል ፡፡ እዚህ ጋር በጥንቃቄ መታየት ያለበት ነገር ቢኖር የግብር ህግ የኪሳራ ትርጉም የተለየ መሆኑን ነው ፡፡
በግብር ህጉ የኪሳራ ትርጉም ❓
በገቢ ግብር አዋጁ አንቀጽ 26(1) መሰረት ለግብር ዓመቱ ተቀናሽ የሚደረገው ወጪ ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከበለጠ በብልጫ የታየው የገንዘብ መጠን ግብር ከፋዩ የደረሰበት ኪሳራ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ኪሳራን ለማስላት ከግምት የምናስገባው ሁሉንም ነጋዴው ያወጣውን ወጪ ሳይሆን በግብር ህጉ መሰረት የተፈቀዱ ወጪዎች ብቻ ናቸው ፡፡
ግብር ከፋይ በአንድ ግብር አመት ኪሳራ ካጋጠመው ይህንኑ ኪሳራ ከሚቀጠለው የግብር አመት ከሚገኝ ገቢ ላይ እንደወጪ በመያዝ ሊቀንስ ይችላል ፡፡ የዚህ አመት ኪሳራ የሚቀጥለው አመት ተቀናሽ ይሆናል ማለት ነው ፡፡
በአንድ አመት ያጋጠመ ኪሳራ እየተሸጋገረ ለተከታታይ ለአምስት አመታት ከሚገኝ ገቢ ላይ እየተቀነሰ ሊሄድ ይችላል ፡፡ ይህም ማለት ኪሳራው ተቀንሶ እስከሚያልቅ ድረስ ግብር ከፋዩ የገቢ ግብር አይከፍልም፡፡
ኪሳራ የሚየሳይ ግብር ከፋይ ቀደም ብሎ ሂሳቡን በገለልተኛ ❗የውጪ ኦዲተር ❗በማስመርመር ይህንኑ ሰነድ ለግብር ባለስጣኑ ማቅረብ አለበት ፡፡ ይህም ማለት በራሱ የሂሳብ ባለሙያ ተሰርቶ የሚቀርብ የሂሳብ መዝግብ ለኪሳራ ማሸጋገር ተቀባይነት የለውም፡፡
በአንቀጽ 26(4) እንደተቀመጠው ግብር ከፋዩ በግብር እድሜው( በምስረታ እና ስራ በሚያቆምበት ሰአት) ኪሳራውን ሊያሸጋገር የሚችለው ለሁለት ግዜያት ወይንም ተከታታይ አስር አመታት ብቻ ነው ፡፡
አንድ ነጋዴ ከሁለት ግዜ በላይ ሊከስር እንደሚችል ይገመታል ነገር ግን የግብር ህጉ እያለ ያለው ስንት ግዜም ብትከስር እኔ የማይልህ የሁለት ግዜ ብቻ ነው እያለ ነው ፡፡ በነገራችን ላይ ሁለት ግዜ ኪሳራ ማለት ለተከታታይ አስር አመታት ግብር ከፋዩ ግብር አይከፍልም ማለት ነው ፡፡
ከተፈቀደው ግዜ ውጪ የሚመጣን ኪሳራ በተመለከተ ኪሳራ ያሳየበት መዝገብ ውድቅ እየተደረገ የግብር ከፋዩ ግብር በግምት እንዲከፍል ይገደዳል ፡፡
#taxawareness #taxeducation #taxcompliance
በህግ ባለሙያ ዮሴፍ አለሙ (LLB,LLM) የተዘጋጀ
ከጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Comments