እጅ ከፍንጅ! ጉቦ ሲቀበል የነበረው የኦዲት ባለሙያ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | "ሰነድህ ትክክል አይደለም" እያሉ የግብር ከፋዩን መብት በመርገጥ ጉቦ የጠየቁ አካላት በሕግ ወጥመድ ገብተዋል።
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኦዲት ባለሙያ እና አስተባባሪ፤ አንድ ግብር ከፋይ ያቀረበውን የ3 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ የወጪ ሰነድ "አንቀበልም" በማለት ለአንድ ወር ሲያመላልሱት ቆይተዋል።
ነገሩ ወዲህ ነው...
እነዚህ አካላት ትክክለኛውን ሰነድ ወደ ጎን በመተው ጉቦ እንዲሰጣቸው ግብር ከፋዩን ወጥረው ይይዛሉ። ግብር ከፋዩ ግን በድርጊቱ ባለመተባበር በቢሮው 7075 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ ይሰጣሉ።
በተደረገው ክትትልም፦
ባለሙያው 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ጉቦ ሲቀበል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ይዞታል። የኦዲት አስተባባሪዋም ከኃላፊነት ተነስተው ጉዳዩ እየተመረመረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ መልዕክት:
ሌብነትን ዝም አንበል! ግብር ከፋዩ እንዳደረገው በ 7075 በመደወል የበኩላችንን እንወጣ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
#addisababa #revenuesbureau #anticorruption #7075 #justice #bole

5 months ago