4 hours ago
"ልቤ ተሰብሯል" ሻኪራ
#ethiopia | በኮሎምቢያ እንደምልክት የምትታየው ዝነኛዋ አርቲስት ሻኪራ በሀገሯ በተከሰተው አደጋ ልቧ ተሰብሯል።
ሻኪራ በዛሬው እለት በሀገሯ ኮሎምቢያ የተከሰተውን የ7.4 ሬክቴል ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከትሎ የዜጎች ህይወት ማለፉን እጅጉን እንዳሳዘናት ገልጻለች።
ዝነኛዋ አርቲስት በስፓኒሽ ቋንቋ ባስተላለፈችው መልዕክት ይህንን የመሬት መንቀጥቀጥ ዜና ከሰማሁበት ሰአት ጀምሮ ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ሃሳቤ በሙሉ ከእናንተ ጋር ነው ብላለች።
በአደጋው ምክንያት በጭንቅ ውስጥ ሆናችሁ እያሳለፋችሁ የምትገኙ ዜጎች ሁላችሁም ከጎናችሁ ነኝም ነው ያለችው።
በእነዚህ መሰል ጊዜያት እኛ ኮሎምቢያውያን አንድ መሆንንና እርስ በእርስ መደጋገፍን እናውቃለን።
ሙሉ ብርታቴና ፍቅሬ ለሀገሬ ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ልጥፋ ላይ አጋርታለች።
በአደጋው ለተጎዱ ዜጎች በተቻለ ፍጥነት መርዳት እንድንችል የሚሰጡ መመሪያዎችን እንከታተል ስትል ጥሪ አቅርባለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #colombia #shakira #earthquake #emergency #magnitude

6 hours ago
በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪዲዮ በምዕራብ ኮሎምቢያ 7.4 በMagnitude የተለካ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰበት ቅጽበት የአንድ ቤተክርስቲያን የፊት ለፊት ገጽታ በ ከፊል ሲናድ ያሳያል።
በ ሀገሪቱ በደረሰው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 20 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
የ ነብስ አድን ስራዎች ለማገዝ ወታደሮች እየተሰማሩ ይገኛሉ ሲል CNN ዘግቧል::
Seledadotio

7 hours ago
ኮሎምቢያ ምን ነካት?
#ethiopia | በኮሎምቢያ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ሀገሪቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች።
በዛሬው ዕለት በኮሎምቢያ ምዕራባዊ ክፍል የ7.4 ሬክቴል ስኬል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ80 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል የሆነው በቾኮ ግዛት ሳን ሆዜ ደል ፓልማር አቅራቢያ ነው።
አዲሱ የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት አቤላርዶ ደ ላ እስፕሪዬላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የነፍስ አድን ቡድኖች ወደ አደጋው አካባቢዎች ተሰማርተዋል።
መንግስት ጉዳቱን ለመቆጣጠር እና ተጠቂዎችን ለመታደግ የተቀናጀ የአደጋ መቆጣጠሪያ ማዕከል አቋቁሟል።
የጎረቤት ሀገራት መሪዎችም ለኮሎምቢያ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በተለያዩ ከተሞች ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ተብሏል።
ባለሙያዎች በድጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በካሊ ከተማ ብቻ ከ20 በላይ ህንጻዎች የፈረሱ ሲሆን በፔሬራ እና ኢንቪጋዶ ከተሞችም ከፍተኛ የህንጻ መፍረስ የዜጎች ሞት እና ጉዳት ተመዝግበዋል ሲል ሲ.ኤን.ኤን ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #colombia #earthquake #emergency #magnitude

Comments