ኮሎምቢያ ምን ነካት?
#ethiopia | በኮሎምቢያ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ሀገሪቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች።
በዛሬው ዕለት በኮሎምቢያ ምዕራባዊ ክፍል የ7.4 ሬክቴል ስኬል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ80 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል የሆነው በቾኮ ግዛት ሳን ሆዜ ደል ፓልማር አቅራቢያ ነው።
አዲሱ የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት አቤላርዶ ደ ላ እስፕሪዬላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የነፍስ አድን ቡድኖች ወደ አደጋው አካባቢዎች ተሰማርተዋል።
መንግስት ጉዳቱን ለመቆጣጠር እና ተጠቂዎችን ለመታደግ የተቀናጀ የአደጋ መቆጣጠሪያ ማዕከል አቋቁሟል።
የጎረቤት ሀገራት መሪዎችም ለኮሎምቢያ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በተለያዩ ከተሞች ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ተብሏል።
ባለሙያዎች በድጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በካሊ ከተማ ብቻ ከ20 በላይ ህንጻዎች የፈረሱ ሲሆን በፔሬራ እና ኢንቪጋዶ ከተሞችም ከፍተኛ የህንጻ መፍረስ የዜጎች ሞት እና ጉዳት ተመዝግበዋል ሲል ሲ.ኤን.ኤን ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #colombia #earthquake #emergency #magnitude

8 hours ago