9 months ago
🛑 "በጎነትን አናሰናክል!"
- በሽንሺቾ ከተማ ለአቅመ ደካሞች የተዘጋጀው የገና ድጋፍ አደጋ ላይ ወደቀ!
ከወ/ሮ ብርቱኳን ፀጋዬ (ቡዬ) መታሰቢያ ፋውንዴሽን የተሰጠ መግለጫ
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ "ቡዬ ፋውንዴሽን" (Buye Memorial Foundation) ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር፤ በሽንሺቾ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የገና ስጦታ እና ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ እንደነበረ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ፋውንዴሽኑ፡-
✅ ከ100 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሰንጋ በሬ ገዝቷል።
✅ ከ250 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ጥሪ አድርጓል።
✅ ለዝግጅቱ የሚሆኑ ሌሎች ወጪዎችን አውጥቶ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ነገር ግን የሽንሺቾ ከተማ አስተዳደር ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን በጎ ተግባር "በአዳራሽ መሰብሰብ አትችሉም" በማለት ከልክሏል! የሚገርመው ደግሞ አስተባባሪ ኮሚቴዎቹ "ከፈለጋችሁ ስጋውን በፌስታል/ፕላስቲክ እያዞራችሁ ስጡ" የሚል ምላሽ መሰጠቱ ነው።
በመሆኑም ከፋውንዴሽኑ መስራቾች፣ ደጋፊዎች እና ከማህበረሰቡ ለከተማው አስተዳደር የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርባለን፡-
1️⃣ ክብር የት ሄደ?
ሰፊና ምቹ የሆነ የከተማው ምክር ቤት አዳራሽ እያለ፣ እነዚህን አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች በክብር ጋብዞ ማስተናገድ ሲቻል፣ ለምን በፌስታል እንዲዞር ተፈለገ?
2️⃣ ሞራላዊ ተጠያቂነትስ?
በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀን የድጋፍ መርሐ-ግብር ማስተጓጎል የሞራል ተጠያቂነት የለውም ወይ?
3️⃣ ተስፋን ማጨለም አይሆንም ወይ?
ከ250 በላይ ወገኖች ተስፋ አድርገው እና በጉጉት እየጠበቁ፣ ይህን መርሐ ግብር ማሰናከል ምን የሚሉት አሰራር ነው?
4️⃣ ጥሪ ለሚመለከታቸው አካላት!
የከምባታ ዞን ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሺንሽቾ ከተማ ማህበራዊ እና ዋስትና እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት፤ ይህን በጎ ስራ በማስተጓጎል እና ቦታ በመከልከል ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በአስቸኳይ አይተው ማብራሪያ እንዲሰጡንና ለተቸገሩ ወገኖቻችን ፍትህ እንዲሰጥ እንጠይቃለን!
በጎ ስራን እናበረታታ ወይስ እናዳክም?
BUYE MEMORIAL FOUNDATION
(ወ/ሮ ብርቱኳን ፀጋዬ (ቡዬ) መታሰቢያ ፋውንዴሽን) #shinshicho #justice #charity #kembata #ethiopia #buyefoundation #genna -KWWMN የልማት ቲቢ
ታሕሣሥ 27፣ 2018
***
ይህንን ዘገባ ያጠናቀርነው የ"ቡዬ መታሰቢያ ፋውንዴሽን" (Buye Memorial Foundation) ያወጣውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ነው። ጉዳዩን በተመለከተ ሚዛናዊ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ለጊዜው ልናገኛቸው አልቻልንም።
ሆኖም፣ የሚሰጡት ምላሽ ወይም ማብራሪያ ካለ ለማስተናገድ እና ለህዝብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን።

Comments