Logo
Getu Temesgen
“በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ግንባታ በእጅጉ ተደንቂያለሁ”
#ethiopia | በኢትዮጵያ ያለውን የመሰረተ ልማት ግንባታና የሕንጻ ጥበብ በመመልከት በጣም መደነቁን ታዋቂው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ገለጸ።

የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ለ30 ቀናት በአፍሪካ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ በሰጠው ቃለ መጠይቅ፤ በኢትዮጵያ ያየው የመሰረተ ልማት ግንባታ እጅግ አስገራሚ መሆኑን ገልጿል።

በጉዞው ካያቸው ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያ የሕንጻ ጥበብ ምርጡ መሆኑን ጠቅሶ፤ የሕንጻዎቹ ጥበብ የወደፊቱን ጊዜ ቀድሞ የተነበየና የራሱ የሆነ አፍሪካዊ ወይም ኢትዮጵያዊ ቅኝት እንዳለው አስረድቷል።

አዲስ አበባ ከተማን ያደመቁት ዘመናዊ ሕንጻዎችና ግዙፍ የዲጂታል ስክሪኖች ከተማዋን ልዩ እንዳደረጓት የገለጸው አይሾው ስፒድ፤ የሕንጻዎቹ አወቃቀር ከሌላው ዓለም የተለየና የሀገሪቱን ማንነት የሚገልጽ መሆኑን ተናግሯል።

ይህ ልዩ የሕንጻ ጥበብና ፈጣን የመሰረተ ልማት ዕድገት ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም በንግግሩ አመልክቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #epa #ኢትዮጵያ #አይሾው_ስፒድ #መሰረተ_ልማት #ሕንጻ_ጥበብ #አዲስ_አበባ #ishowspeed

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.