Logo
Getu Temesgen
ታዋቂው ዩቲዩበር ​ስፒድ (IShowSpeed) በአዲስ አበባ ከፍተኛ ትኩረት አገኘ!

​ከ263,000 በላይ ሰዎች ጉብኝቱን በቀጥታ እየተከታተሉት ነው! 🇪🇹🎥
#ethiopia | ​ታዋቂው አሜሪካዊ ዩቲዩበር IShowSpeed (አይ ሾው ስፒድ) በአዲስ አበባ እያደረገ ያለው ጉብኝት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን ስቧል። በዩቲዩብ ቻናሉ እያስተላለፈ የሚገኘውን የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) በዚህ ደቂቃ ከ263 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ተመልካቾች እየተከታተሉት ይገኛሉ።

​የ21 ዓመቱ ወጣት ዩቲዩበር በአጠቃላይ 20 የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክ እና መልካም ገጽታ ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራ ይገኛል።

​ተደራሽነት፡ ስፒድ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ማስተዋወቂያ እንደሚሆን ታምኖበታል።

​አሁን በመስቀል አደባባይ አየተጠበቀ ነው።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.