29 days ago
ከዓለም ታላላቅ ከተሞች አዲስ አበባ 2ኛ ወጣች
#addisababa #climateresilience #greenlegacy #corridordevelopment #ethiopiaprogress
5 months ago
የአዲስ አበባ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዓለምአቀፍ ዝና እና ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉት ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኙት የተቀናጁ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻሉ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።
ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ (NBC Ethiopia) “አዲሲቱ አዲስ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተጠቆመው፤ ከተማዋ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እያሳየችው ያለው እድገት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ህንጻ መምህር የሆኑት ዳዊት በንቲ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ከተማዋ በተመሰረተችባቸው የቀድሞ ዘመናት በታቀደ ፕላን ያልተመራች በመሆኑ ዘመናዊነትን ለማምጣት ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይህንን ታሪክ እየቀየሩት ይገኛሉ።
በተለይም ዘመናዊ ፓርኮች፣ ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እንዲሁም ለእግረኛ እና ለብስክሌት ተጓዦች ምቹ የሆኑ መንገዶች መገንባታቸው የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ወደ ተሻለ ደረጃ አሸጋግረውታል።
የከተማ እና ቀጣናዊ ፕላኒንግ ተመራማሪው ኢንጂነር እሸትአየሁ ክንፉ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት እየተተገበረ ያለው የከተማ ማደስ ስራ ፍትሃዊነትን ያከለለ እና አዲስ አበባን ከሌሎች የዓለም ታላላቅ ከተሞች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
እነዚህ የተቀናጁ ስራዎች ከተማዋ ለኑሮ ምቹ እና ለቴክኖሎጂ ዝግጁ እንድትሆን ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ተመላክቷል።
የኤንቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ብርሀኑ በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ አዲስ አበባ አሁን ላይ ተጨባጭና ግዙፍ ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ይህንን ለውጥ ከዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች ጋር በማነጻጸር የጥናት ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
#addisababa #urbandevelopment #ethiopiaprogress #moderncity #greendevelopment #cityplanning #newaddis #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
ሩጫ ለልማት
ከኢትዮ ሪል እስቴት ጋር ለተሻለ ነገ እንሩጥ! 🏃♂️✨
ኢትዮጵያ የፈጣን ዕድገት ጉዞ ላይ ናት!
በዚህ ጉዞ ውስጥ የሪል እስቴት ልማት የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት፣ የከተማ መዋቅርን በማሻሻልና የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ትልቅ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል።
የ“ኢትዮ ሪል እስቴት ልማት ሩጫ” ፋይዳ፦
የአንድነት ምልክት፦
ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ባለሙያዎችና የቢዝነስ ማህበረሰቡ በአንድነት ለተሻለ ነገ የሚሮጡበት መድረክ ነው።
የልማት አጋርነት፦
ከአርኪ ኤቨንትስ እና ከእፎይ ለቤቴ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ሩጫ፣ ልማት የሁላችንም የጋራ ጉዞ መሆኑን ያበስራል።
ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፦
የዘርፉን እንቅስቃሴ በማነቃቃት ለሀገር ግንባታ የሚኖረውን አስተዋፅኦ ማጉላት።
ከኢትዮ ሪል እስቴት ጋር እንሮጥ — ለተሻለ ነገ፣ ለተገነባ ሕይወት!
#ethiorealestaterun #runfordevelopment #ethiopiaprogress #arkievents #effoylebete #urbandevelopment #healthyliving #addisababa #realestateethiopia #ልማት #ሩጫ #ሪልእስቴት #ኢትዮጵያ #ለተሻለነገ

9 months ago
🌳 ቴፒን በጋራ እናልማ
የ"ትንሿ ኢትዮጵያ" ዳግም ውልደትና የልማት ጥሪ
#ethiopia | የታሪክ ድርሳናት እንደሚነግሩን ቴፒ ከተማ በ1911 ዓ.ም የተቆረቆረች፣ የኢትዮጵያ የዘመናዊነት አውራ ጎዳና ቀዳሚ ተጠቃሚ የነበረች ታሪካዊ የንግድ ማዕከል ናት። ገና በ1960ዎቹ የአውሮፕላን ትራንስፖርት፣ በ1966 የጤና ጣቢያና የጠጠር መንገድ የነበራት ቴፒ፤ ዛሬም ያንን ገናና ታሪኳን አድሳ ወደ ከፍታ ለመመለስ ቆርጣ ተነስታለች።
ቴፒ፦ የብዝሃነትና የተፈጥሮ ዕንቁ
አረንጓዴ ካባ የደረበችው ቴፒ፣ "ትንሿ ኢትዮጵያ" ተብላ ትጠራለች። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ የቡናና የቅመማ ቅመም ምርቷን ለዓለም ገበያ የምታቀርብ የኢኮኖሚ ምሰሶ ናት።
🚧 የልማት እንቅፋትና አዲስ ተስፋ
ከተማዋ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ምርት የምታቀርብ ብትሆንም፣ የዘመናዊ መንገድ መሠረተ ልማት እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኖባት ቆይቷል። ይህንን ችግር ለመፍታት፦
ከሚዛን፣ ከማሻ-ጎሬ እና ከሽሽንዳ የሚመጡ ዋና ዋና መንገዶች በፍጥነት እየተገነቡ ይገኛሉ።
ነገር ግን፦
የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሁላችንንም እገዛ ይሻሉ።
🤝 የ"ህብረት" ጥሪ ለቴፒ ልጆችና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!
የቴፒ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነባራዊ እድገትና ቀደምት ስልጣኔ ባገናዘበ መልኩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በራስ አቅም ለመገንባት ፕሮጀክት ነድፎ ወደ ተግባር ገብቷል።
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ የቴፒ ተወላጆች፣ ወዳጆችና የልማት አጋሮች በሙሉ፦ "ዘንድሮ የምትሞሸረውን ቴፒን በጋራ እናስውብ!" ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
💰 የልማት ተሳትፎዎን በሚከተለው የባንክ አካውንት ያድርጉ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000731791558
የአካውንቱ ስም፦ ቴፒ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ አስፓልት ግንባታ
💡 መፈክራችን፦ "በኅብረት ሁሉን እንችላለን!!"
የከተማችን መልማት የሀገራችን ብልፅግና መሠረት ነው። ዛሬ ለቴፒ የምናደርገው ድጋፍ ለነገው ትውልድ የምናስቀምጠው ትልቅ አሻራ ነው።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር፤
በመምህር ኃይማኖት ተስፋዬ እና
በናትናኤል ዳኜ በኩል የተላለፈ መልዕክት
#tepi #ethiopia #development #communityservice #infrastructure #coffeeland #unityindiversity #ethiopiaprogress #tepicity

Sponsored by
Surafel
Comments