3 months ago
የአዲስ አበባ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዓለምአቀፍ ዝና እና ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉት ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኙት የተቀናጁ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻሉ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።
ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ (NBC Ethiopia) “አዲሲቱ አዲስ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተጠቆመው፤ ከተማዋ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እያሳየችው ያለው እድገት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ህንጻ መምህር የሆኑት ዳዊት በንቲ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ከተማዋ በተመሰረተችባቸው የቀድሞ ዘመናት በታቀደ ፕላን ያልተመራች በመሆኑ ዘመናዊነትን ለማምጣት ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይህንን ታሪክ እየቀየሩት ይገኛሉ።
በተለይም ዘመናዊ ፓርኮች፣ ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እንዲሁም ለእግረኛ እና ለብስክሌት ተጓዦች ምቹ የሆኑ መንገዶች መገንባታቸው የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ወደ ተሻለ ደረጃ አሸጋግረውታል።
የከተማ እና ቀጣናዊ ፕላኒንግ ተመራማሪው ኢንጂነር እሸትአየሁ ክንፉ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት እየተተገበረ ያለው የከተማ ማደስ ስራ ፍትሃዊነትን ያከለለ እና አዲስ አበባን ከሌሎች የዓለም ታላላቅ ከተሞች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
እነዚህ የተቀናጁ ስራዎች ከተማዋ ለኑሮ ምቹ እና ለቴክኖሎጂ ዝግጁ እንድትሆን ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ተመላክቷል።
የኤንቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ብርሀኑ በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ አዲስ አበባ አሁን ላይ ተጨባጭና ግዙፍ ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ይህንን ለውጥ ከዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች ጋር በማነጻጸር የጥናት ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
#addisababa #urbandevelopment #ethiopiaprogress #moderncity #greendevelopment #cityplanning #newaddis #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments