24 days ago
ከተመካከርን የማንሻገረው አረንቋና የማንፈታው የችግር ቋጠሮ አይኖርም - የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች
*******************
ታዋቂና አንጋፋ የኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አሁን ላይ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ውስብስብ ችግሮች በራሳቸው መንገድና አገር በቀል እሴቶች የመፍታት ጥበባቸውን ለዓለም በተግባር የሚያሳዩበት ታሪካዊና ወሳኝ አጋጣሚ መሆኑን ገለጹ።
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረጉት እነዚህ ባለሙያዎች፤ ምክክሩ ላለፉት ዓመታት በርካታ መሰናክሎችን አልፎ አሁን ለተጨባጭ ጉባኤ በመብቃቱ መላው ሕዝብ ዕድለኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ታላቅ ሂደት በስኬት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ቀድሞ የነበራትን ታሪካዊ ክብር ይበልጥ አጎናጽፎ ወደፊት እንድትራመድ ብርቱ መሠረት እንደሚጥልላት አስገንዝበዋል።
አንጋፋው ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ባደረገው ቆይታ፣ ሀገራችን ችግሮችን በሽማግሌዎች የመፍታት የዳበረ እሴት ያላት መሆኑን ጠቅሶ፣ አሁን ይህንን ለዓለም ጭምር አርአያ በሚሆን መልኩ የምንተገብርበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲል ተናግሯል።
ይህ የምክክር ጉዞ ላለፉት ዓመታት በርካታ መሰናክሎችን ቢያሳልፍም፣ ሁሉንም ተቋቁሞ ለመጨረሻው ታሪካዊ ጉባኤ በመብቃቱ ሁላችንም እጅግ ዕድለኞች ነን ሲል አስረድቷል።
ይህ ታሪካዊ ጉባኤ በስኬት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን ክብር ይበልጥ አጎናጽፎ ወደፊት እንድትራመድ ትልቅ በር እንደሚከፍትላት ያነሳው አርቲስቱ፤ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነትና በኅብረት መቆም እንደሚገባው አሳስቧል።
ታዋቂው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ጥላሁን ጉግሳ በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያጋጠሟትን አገር በቀል ችግሮች በራሷ መንገድ ስትፈታ የኖረች ኩሩ አገር መሆኗን ጠቅሶ፤ አሁን የተጀመረው አገራዊ ምክክር እነዚህን ታሪካዊና ባህላዊ የችግር አፈታት እሴቶች ዳግም ለማነቃቃትና በዘመናዊ መንገድ ለመተግበር የተከፈተ ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቁሟል።
ምክክር ማለት እርስ በርስ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር መሆኑን የጠቀሰው አርቲስት ጥላሁን፤ "ከተመካከርን የማንፈነቅለው ቋጥኝ፣ የማንሻገረው አረንቋና የማንፈታው የችግር ቋጠሮ አይኖርም" ሲል የምክክርን አስደናቂ ኃይል አብራርቷል።
ታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ ድምፃዊ ዘለቀ ገሠሠ፣ የኢትዮጵያ ውስብስብ ችግሮች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት በምክክርና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን እንደሚያምን ተናግሯል።
በሀገሪቱ ለረጅም ዘመናት የቆዩ ችግሮች በጦርነትና በተኩስ ቢሞከሩም መፍትሔ እንዳልተገኘላቸው ጠቅሶ፣ አሁን የመጣውን ታሪካዊ የምክክር ዕድል በመጠቀም ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
ታዋቂው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ደበሽ ተመስገን በበኩሉ፣ በኢትዮጵያ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር የሀገሪቱን ውስብስብ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚከፈትበት ታላቅ ሂደት መሆኑን ተናግሯል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት እንዲህ ዓይነት ታላቅ አጋጣሚ መፈጠሩ በራሱ ትልቅ የታሪክ ክስተት መሆኑንም አብራርቷል።
በየተመኙሽ አያሌው
#ebc #nationaldialogue #ethiopianartists #peaceandunity #homegrownsolutions

4 months ago
የትንሳኤ ስጦታ
ዳሽን ቢራ ለ5 አንጋፋ አርቲስቶች ቤት ገንብቶ አስረከበ
#ethiopia | ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ላለፉት ዓመታት ጥበብን ሲያገለግሉ ለቆዩ 5 አንጋፋ አርቲስቶች አዲስ የገነባላቸውን መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
የአርቲስቶቹ የነበሩ የጭቃ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰው በዘመናዊ መልክ የተገነቡ ሲሆን፣ ሙሉ የቤት ቁሳቁስም ተሟልቶላቸዋል።
ተ/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማትያስ ጌታቸው እንደገለጹት፣ ፋብሪካው ላለፉት 25 ዓመታት ለማህበራዊ ኃላፊነት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል።
የኮከብ መልቲ ሚዲያና ማስታወቂያ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል፣ ዳሽን ቢራ ላደረገው ፈጣን ምላሽ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ፋብሪካው "የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች በጎ አድራጎት ማህበር የክብር አምባሳደር" ሆኖ እንዲሾም መወሰኑን ገልጸዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች እንዲሁም የዳሽን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ቤቶቹ ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።
"ጥበብን ማክበር - ታሪክን ማክበር ነው!" 🙏
#getu #dashinbeer #ethiopianartists #philanthropyethiopia #eastergift #addisababa #ethiopia #artcommunity #buildinglives #ዳሽንቢራ #ኪነጥበብ #ትንሳኤ #በጎአድራጎት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments