1 month ago
«ፍቅር እስከ መቃብር» — የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታላቅ ሥራ የሆነውን «ፍቅር እስከ መቃብር» በሥዕል የሚያስቃኘው የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ የሥዕል አውደ-ርዕይ በFendikaHyatt ተከፍቷል።
የአዲስ ዓለማየሁ የሥነ-ጽሑፍ ድንቅ ሥራ በነጋለኝ ሉሌ ሥዕሎች አማካኝነት በአዲስ የጥበብ ትርጓሜ ቀርቧል። የፍቅር፣ የቤተሰብ እና የመንፈሳዊነት ታሪኮችን በምስል የሚያስቃኘው አውደ-ርዕዩ፣ ሥነ-ጽሑፍን ከሥዕል ጥበብ ጋር የሚያገናኝ ልዩ የጥበብ ልምድ ይሰጣል።
የአውደ-ርዕዩ ጋለሪ በማስታወቂያው መሠረት 24/7 ክፍት ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍ ቅርስ በሥዕል መልክ ለመመልከት የሚፈልጉ የጥበብ አፍቃሪዎች እንዲጎበኙት ጥሪ ቀርቧል።
«ፍቅር እስከ መቃብር» — በቃላት የተጻፈው ታሪክ፣ በቀለም እንደገና ሲነገር።
ርዕስ፦ ፍቅር እስከ መቃብር በስዕል
በአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ
ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም - መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም (August 26, 2026 – September 21, 2026)
የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ ግል ታሪክ (Biography)
በ1958 ዓ.ም በጎጃም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለዱ። የእድሜያቸው ትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በፍኖተ ሰላም ከተማ፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በደብረ ማርቆስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በሥነ ጥበብ ዲዛይን ትምህርት ቤት (Balle Design School) በ1983 ዓ.ም በስዕል ጥናት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
በተለያዩ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች ከ30 ዓመት ያላነሰ በሙያቸው አገልግለዋል። ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የተለያዩ የሥነ ጥበብ ሥራዎችን በመሥራት አሳልፈዋል።
1983 ዓ.ም፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በጋራ የስዕል ኤግዚቢሽን አሳይተዋል።
1991 እና 1999 ዓ.ም፦ በባህር ዳር ከተማ በቡድን ሥራዎችን አሳይተዋል።
2008 እና 2010 ዓ.ም፦ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ያዘጋጇቸውን የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ የስዕል ሥራዎች አቅርበዋል።
2009 ዓ.ም፦ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በጋራ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በላቀቋቸው የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ገጸ ባሕርያት የስዕል ሥራዎቻቸው የዕድሜ ልክና የምርጥ የሥነ-ጥበብ ተሸላሚ ሆነዋል።
«ፍቅር እስከ መቃብር» — የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት መነሻ ምክንያት እንደተናገሩት "የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ የገጸ-ባሕርያት ስዕሎችን እንድስል ያነሳሳኝ ምክንያት ዘመን ተሻጋሪ የሆነው የፍቅር እስከ መቃብር ትረካ በወጋየሁ ንጋቱ ድምፅ በሬዲዮ ሲነበብና ሲተረክ መስማቴ፣ እንዲሁም በቤተሰቦቼ ሲነገረኝ በነበረው በነበረው የጎጃም ማኅበረሰብ አኗኗርና ሥርዓት እየተደመምኩ ያደግኩበት ታሪኮች ስዕሎቹን ለመሳል መነሻዎች ናቸው።
የሳልኳቸው የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ገጸ ባሕርያት ሥራዎች ማኅበራዊ ሕይወትን የተለያዩ ውጣ ውረዶችን የሚጋፈጡ ሰዎችን የሕይወት ጉዞና ፅናት በተምሳሌትነት ይገልጻሉ። ስለዚህም የሥዕሎቹ ዋና ዓላማ ስሜቴንና ፍላጎቴን ከመግለጽ በተጨማሪ በሰው ልጅ መካከል ያለውን የጋራ መግባባትና ስምምነት ማጎልበት ነው።
ነሐሴ 20 ቀን የተከፈተ ሲሆን መስከረም 11 ቀን 2019ዓ.ም የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት የአውደ-ርዕዩ ጋለሪ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ይጠናቀቃል።
ኢሜይል፦ Fendikagalleryartproposalgmail.com
የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ
+251 91 874 8346
ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል
+251 911 547 577
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ፍቅርእስከመቃብር #ነጋለኝሉሌ #negalegnlulie #fikereskemekaber #ethiopianart #ethiopianliterature #fendika #artexhibition #addisababa

Comments