1 month ago
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የዛጎል ኩባንያ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ
#ethiopia | የኪነ ጥበብ ባለሙያው አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የዛጎል (ZAGOL) የብራንድ አምባሳደር ሆኖ መመረጡን ኩባንያው አስታወቀ።
ዛጎል ሲስተምስ ትሬዲንግ አርቲስቱን የቆየ የስራ ልምዱንና ህዝባዊ ተደማጭነቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቋሙ ውክልና እንዲሰጠው መምረጡን ገልጿል።
በተደረገው ስምምነት መሰረትም አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የድርጅቱን የጉዞ እና የትኬት ሽያጭ አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ ያከናውናል።
ዛጎል በተለይም የአየር መንገድ በረራ ትኬት መቁረጥን፣ የሆቴል አልጋ ማስያዝንና ሌሎች ተያያዥ የጉዞ አገልግሎቶችን በዘመናዊ የዲጂታል አማራጮች ለማቅረብ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።
በቴአትርና በፊልም ሙያ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገለው አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ የመጀመሪያ የሙያ ሽልማቱን ያገኘው በ1988 ዓ.ም እንደነበር አስታውሶ እስከ አሁንም በሙያው ማህበረሰቡን በማገልገል ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
አርቲስቱ ለተሰጠው የብራንድ አምባሳደርነት ማዕረግ ፈጣሪውንና ቤተሰቦቹን አመስግኗል።
ከሙያ ስራው በተጨባጭ ከሚያከናውናቸው ህብረተሰባዊ አገልግሎቶች መካከልም ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች ኢትዮጵያ እና ከብሬክስ ህፃናት መደገፊያ ማህበር ጋር የሚሰራቸው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ይጠቀሳሉ።
አንጋፋው ባለሙያ ባለፉት ረጅም ዓመታት ያካበተውን ልምድና ዝህብራዊ ተቀባይነት በመጠቀም የዛጎልን አገልግሎቶች ለህዝብ ተዳራሽ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።
#alemayehutadesse #zagol #zagolsystems #ethiopianart #travelethiopia #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments