2 months ago
"78 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዲጂታል ይደረጋሉ"
- አቶ እንድሪስ አብዱ
#ethiopia | ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የባህል፣ የኪነ-ጥበብ እና የእንቁ እሴቶች ሀብቶች በአግባቡ በማልማት ለሀገር ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትስስር የሚውሉበትን አዲስ የሦስት ዓመት የልማት እና ኢንቨስትመንት አቅጣጫ መዘርጋቱን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንድሪስ አብዱ እንደገለጹት፣ ይፋ የሆነው የሦስት ዓመት የልማት እና ኢንቨስትመንት ዕቅድ የሀገሪቱን ባህልና ኪነ-ጥበብ ወደ ተሻለ ደረጃ ከማሸጋገር ባለፈ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባትና የአሰራር ስርዓቶችን ለማዘመን ያለመ ብለዋል።
በዚሁ መሠረት ሚኒስቴሩ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ሀገራዊ ጥናቶች መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ተሸሽገው የቆዩ የባህል እሴቶችን፣ የባህላዊ እርቅና ሽምግልና ስርዓቶችን እንዲሁም በርካታ የቋንቋ ሀብቶችን ለህዝብ ለህዝብ ትስስርና ለሀገር ገጽታ ግንባታ የማዋል ሰፊ ስራዎች ተቀይሰዋል።
በተለይም ሀገሪቱ በ2030 ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ራዕይ ስኬት ባህልና ቋንቋ ወሳኝ መሆናቸውን በመገንዘብ፣ እስካሁን ዲጂታላይዝ ከተደረጉ 30 የሀገሪቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ በቀጣይ የስትራቴጂ ዓመታት ሁሉንም 78 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዲጂታል የማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከዚህ ጎን ለጎን ቤተ-መጻሕፍትንና የጥበብ ክበባትን በማስፋፋት አዲስ የሚያነብ ትውልድ የመፍጠር፣ ሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህላዊ ህክምናዎችን ለኢኮኖሚ ጥቅም የማዋል እንዲሁም የኢትዮጵያን ሀብት የኪነ-ጥበብ ባህል በአፍሪካና በአለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ ዲፕሎማሲን የማጠናከር ተግባራት ዋና ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopianculture #ethiopianart #creativeeconomyethiopia #digitalethiopia #digitalethiopia2030 #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments