3 months ago
ቅዱስ ሲኖዶስ ውዝግብ ያስነሳውን መጽሐፍ አገደ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው የአምስተኛ ቀን ውሎው "ዋልድባ አብረንታት ገዳምን ይወቁ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በየትኛውም አህጉረ ስብከት እንዳይሰራጭ አገደ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ) ለ EOTCTV በሰጡት ማብራሪያ መጽሐፉ በእምነት አስተምህሮ ላይ ጉድለት ያለበትና ለክፍፍል የሚዳርግ ነው ተብሏል።
ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ የቀረበው መጽሐፍ በቤተክርስቲያኗ የሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ፤ "እመቤታችን ከሰማይ እንደወረደች አድርጎ የሚያሳይ፣ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ቁጥር የሚያፋልስና ለመነኩሴ የማይገባ ስድብና ትችት የበዛበት" መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት መጽሐፉ እንዲወገዝ በሊቃውንቱ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ምልዓተ ጉባኤው ተመልክቶታል።
ይሁን እንጂ ሲኖዶሱ መጽሐፉን ከማገድ ባለፈ፣ የሊቃውንት ጉባኤ የጽሑፉን ባለቤትነትና ጸሐፊውን ለይቶ ባለማቅረቡ ጉዳዩ በድጋሚ ተጣርቶ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብ መርቷል። እስከዚያው ድረስ ግን የገዳሙ አባቶች በሰላምና በፍቅር እንዲቆዩና መጽሐፉም ከሥርጭት ውጪ እንዲሆን ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

5 months ago
የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚያቃልል ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማኅበራዊ ሚዲያ ያሰራጩት ግለሰቦች በአንድ አመት ተቀጡ
#ethiopia | በ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ወቅት የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእምነቱን ሥርዓት የሚያቃልል ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።
የቁጫ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት፣ ቁጫ ወረዳ ያጋራ ቀበሌ ውስጥ የተፈጸመውን ድርጊት ተከትሎ ነው። ሕዝቅኤል ማጃ እና መርዶክዮስ ማጃ የተባሉ ተከሳሾች በቲክቶክ (TikTok) አማካኝነት የሃይማኖትን ሰላምና የእምነት ተከታዮችን ስሜት የሚነካ ምስል ማሰራጨታቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ በ1997 የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 492(ለ) መሠረት ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።
የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ፤ ቤተክርስቲያን የይቅርታና የሰላም ተምሳሌት ብትሆንም፣ እንዲህ ያሉ ፀያፍ ድርጊቶች በሕግ አግባብ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራች መሆኑን ገልጿል። ይህ የፍርድ ውሳኔም መሰል ድርጊቶችን ለሚፈጽሙ አካላት ትልቅ ትምህርት እንደሚሆን ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #eotctv #ethiopia #gamo #kucha #legalnews #religiousfreedom #socialmedia #courtruling #newsupdate

ማንም ኢትዮጵያዊ የፈለገውን ሀይማኖት እምነት የመከተል የማምለክ መብት
የኢፊድሪ ህገመንግስት
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690
መግቢያ #ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በኢትዮጵያ ያሉ ሀይማኖቶች እኩል መብት ደረጃ በህገመንግስቱ እደል የተሰጣቸው በመሆኑ በእኩልነት ህገመንግስታዊ የእኩልነት መብታቸውን ተጠቅመው የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል የማምለክ መብት እንዳላቸው በህገመንግስቱ አንቀጽ 27 ላይ ተደንግጎ የተቀመጠ ነው። እኛም በዚህ ጽሁፍ ማንም ሰው የፈለገውን ሀይማኖት በግልም ሆነ በአንድነት ሆኖ የማምለክ መብት አለው ሲባል እስከ ምን ድረስ ነው የሚለውን እንመለከታለን።
1. ማንም ሰው
ማንም ሰው ማለት ዘር፣ብሔር በአመለካከት ልዩነት ሳይለይ በፈለገው ሀይማኖት በግሉም ሆነ በቡድን ሆኖ የማምለክ መብት አለው ለማለት ተፈልጎ ነው።
2. የሀይማኖቶች እኩልነት
ሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሀይማኖቶች ሙስሊም፣ክርስትያኑ በሙሉ ህገመንግስቱ በፈቀደላቸው ወይም በሰጣቸው እድል መሠረት በየትኛው ቦታ ሆነው ፈጣሪያቸውን እንደ የእምነታቸው ስረአታቸው ማምለክ ይችላሉ።
3. ከመንግሥት ምን ይጠበቃል?
መንግስት የእኩልነት መብት የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩልነት የማምለክ ስረአታቸውን እድል እንዲጠቀሙ እኩል ምቹ ሁኔታን መጠበቅ አለበት። አንዱን ሀይማኖት አስበልጦ ሌላውን ሀይማኖት አሳንሶ ሳይሆን ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩል የማየት ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህም ህገመንግስታዊ ነው።
4. መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው
በህገመንግስቱ አንቀጽ 11 መሠረት መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውንና አንዱ በአንዱ ጣልቃ በመግባት ስልጣንና አካሄዳቸውን ሊሻማ ሊወስድ ሊያውክ ሌላ ተጽእኖ ሊወስድ፣አላግባብ ሊያስር፣ሊገድል ሌላም አላስፈላጊ ተጽእኖ ከማድረግ ከመቆጠብ ማንም ሀይማኖት በፈለገው ሀይማኖት የማምለክ ሊጠብቅ የመንግስት ግዴታ ሲሆን የሀይማኖት ተቋምም በመንግሥት አሰራር ስልጣን ውስት በመግባት መንግስት በሚሰራው ስራ ላይ ጣልቃ ከመግባት መቆጣብ በህገመንግስቱ የተቀመጠ ግዴታ ነው።
5. ከሀይማኖቶች ምን ይጠበቃል?
ሀይማኖቶች የራሳቸውን እምነት ስረአታቸው በሚፈቅድላቸው መሠረት ሲያካሂዱ የሌላውን ሰው እምነት፣የዜጎችን መብት የመንግስትን ህልውና የሚፈታተን ከተሰጣቸው የመብት ወሰን ሳያልፉ እምነታቸውን የማምለክ ስረአታችን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።
6. አሁን ላይ የእምነት ተከታዮች የማምለክ መብት ተጨባጭ ሁኔታ ምን ይመስላል?
አሁን ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ እና በታወቁ ዜናዎች እንደምንሰማው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ልጆች በተደጋጋሚ ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በተለይም ካህናት፣ቄስ፣ምእመናን ከዚህ በፊት እንደተከሰተው አሁንም በአርሲ የተከሰተ ሲሆን በድጋሚም በወሎ በተመሳሳይ የኦርቶዶክስ ልጆች በጥይት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ህይወታቸው ያለፈ እንዲሁም በርካታ የቆሰሉ እንዳሉም ተገንዝበናል፤ ይህ ኢ ህገመንግስታዊ ድርጊት ነው።
7. የመንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነት እና ግዴታ
ሀይማኖቶች በህገመንግስት የተሰጣቸውን መብት በመጠቀም ስረአቱ በሚፈቅድላቸው ልክ ሊያመልኩ ሊከተሉ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ እንዲሆን ከስጋት ተጠብቀው የመኖር መብታቸው ተረጋግጦ የፈለጉትን ሀይማኖት ስረአት እንዲከተሉ መንግስት የሰላም ጸጥታ ድህንነት ስራ ሊያስጠብቅ ያስፈልጋል።
ከዚህም ባለፈ ዜጎቹ ሲሞቱ የማንኛውም ሀይማኖት ተከታይ ቢሆን ለደረሰባቸው ሞት ዜጎቹ እንደ መሆኑ መጠን ተገቢውን ክብር በመስጠት እውቅና ሊሰጥ ይገባል። ይህ አለመሆኑ የመንግስት ኀላፊነት ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ እና ከዲሞክራሲያዊ ስረአተ መንግስት አካሄድ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ይህን በአንክሮ በመመልከት ሊያስተካክል ይገባዋል።
8. የህግ ምክር
ሀይማኖቶች በህገመንግስቱ አንቀጽ 11፥25፥27 ላይ በተሰጣቸው የማምለክ መብት መሰረት ሀይማኖታቸው በሚፈቅድላቸው ስረአት መሠረት ማምለክ የሚችሉ ሲሆን ይህንን መንግስት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት። ሀይማኖቶችም ይህ መብታቸው ሲጠበቅላቸው በተነጻጻሪ የሌላውን መብቶችን ባከበረ መልኩ ስረአታቸውን ሊፈጽሙ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ/References/
የኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 11፥25፥27
የዩቲዮብ ገጽ
/ eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጽ
/ eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጽ
https://t.me/eotctvcha...
➽ የቲክ ቶክ ገጽ
https://vm.tiktok.com/...
➽ የዩቲዮብ ገጽ Eotc tv 2
• EOTC TV 2 |
➽የትዊተር ገጽ
/ eotct
➽የኢንስታግራም ገጽ
https://www.instagram....
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.facebook.com

7 months ago
ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ባለውለታና መንፈሳዊ አባት አጣች። የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ በነበራቸው ሐዋርያዊ አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ፣ በኢየሩሣሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለብዙ ዓመታት ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለEOTCTV እንደገለጸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ሥርዓተ ቀብር ነገ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተማሩበት በመነኮሱበት እና ለረጅም ዓመታት ባገለገሉበት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን።
seledadotio

8 months ago
አሳዛኝ ዜና
የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተገደሉ።
የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በምትገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና በርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማኅበራት አገልጋዮች በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተወስደው የቆዩ ሲሆን ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል::
በመልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና በቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው ፣ለዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል::
EOTCTV

Sponsored by
Surafel
8 months ago
የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በታጣቂዎች ተገደሉ።
የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በምትገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና በርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማኅበራት አገልጋዮች በታጣቂዎች ተወስደው የቆዩ ሲሆን ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና የስብከተ ወንጌል አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል::
#eotctv

9 months ago
ማርበርግ ቫይረስን አስመልክቶ ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የተላለፈ መልዕክት
እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ (ዘጸአት 15:26)።
ማርበርግ ቫይረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጅንካ ከተማ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፣ ይህ ወቅት በበሽታው ሕይወታቸውን ካጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች እና በቫይረሱ ተይዘው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተጎጂዎች ጎን ቆመን በአንድነት ድምፃችንን ወደእግዚአብሔር የምናሰማበት ጊዜ ነው።
ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ብንጮህ ይሰማናል፣ ይፈውሰናል፣ ጤናችንንም ይመልስልናል። እንደዚህ አይነት ፈታኝ ክስተቶች ለምን እንደሚከሰቱ ባናውቅም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ግን እንደማይለየን እናውቃለን። "እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ" (ዘጸአት 15:26) እንዳለ የፈውስ እጁ የታመሙትን ወገኖቻችንን ይዳስስልን፣ ያዘኑትን ያጽናናልን፣ ያረፉትን እረፍተ ነፍስ ይስጥልን፣ የዚህን ቫይረስ ስርጭትንም በምሕረቱ ያቁምልን። በጾምና በጸሎት ከመትጋት ባሻገር ማንኛውንም የጤና ባለሞያዎች እና የጤና ሥነ ምግባር የሚያዘውንና የሚፈቅደውን ሁሉ በማድረግ ለራሳችሁ: ለቤተሰቦቻችሁ: ለማኅበረሰባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የየድሻችሁን እንድትወጡ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት!
©EOTCTV

11 months ago
" ለንግሡ ለሚመጡ ምዕመናን ማረፊያ የሚኾን ሰፊ ቦታ ተዘጋጅቷል ! " - የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
#ethiopia | በግሸን ደብረ ከርቤ ለሚከበረው የመስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በግሸን ደብረ ከርቤ የመስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም የንግሥ በዓል መስከረም 21 ይከበራል።
የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቆሞስ አባ ብሥራተ ገብርኤል ክፍለ ማርያም ምን አሉ ?
" የ2018 የመስቀል እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግስ በዓል / የግሼን ደብረ ከርቤ በዓል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው።
የደብሩ አሥተዳደር ሰበካ ጉባኤ፣ ማኅበረ ካህናቱ እና የአጥቢያው ምዕመናን በተለየ ሁኔታ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ ነው።
የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢዎች በድምቀት ይከበራል ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት በግሸን ደብረ ከርቤ ደግሞ በዓሉ የተለየ ድምቀት አለው።
በበዓሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከውጭ የሚመጡ አማኞች እና ጎብኝዎች ይገኛሉ። ለጎብኝዎቹ ምቹ የኾነ መሥተንግዶ ለማቅረብ እየሠራን ነው። ለንግሡ ለሚመጡ ምዕመናን ማረፊያ የሚኾን ሰፊ ቦታ ተዘጋጅቷል።
ከባለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ መንገዱን ምቹ ለማድረግ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንገዶች አሥተዳደር አማካኝነት መንገዱን የመጠገን ሥራ ተሰርቷል።
ለመኪኖች መቆሚያ የሚኾኑ አራት መናኸሪያዎች ተዘጋጅተዋል።
በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ የሚገኙ ምዕመናን እና ጎብኝዎች በዓሉን በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን። "

በግሸን ደብረ ከርቤ ለሚከበረው የመስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

Comments