Logo
Getu Temesgen
" ለንግሡ ለሚመጡ ምዕመናን ማረፊያ የሚኾን ሰፊ ቦታ ተዘጋጅቷል ! " - የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
#ethiopia | በግሸን ደብረ ከርቤ ለሚከበረው የመስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በግሸን ደብረ ከርቤ የመስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም የንግሥ በዓል መስከረም 21 ይከበራል።

የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቆሞስ አባ ብሥራተ ገብርኤል ክፍለ ማርያም ምን አሉ ?

" የ2018 የመስቀል እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግስ በዓል / የግሼን ደብረ ከርቤ በዓል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው።

የደብሩ አሥተዳደር ሰበካ ጉባኤ፣ ማኅበረ ካህናቱ እና የአጥቢያው ምዕመናን በተለየ ሁኔታ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ ነው።

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢዎች በድምቀት ይከበራል ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት በግሸን ደብረ ከርቤ ደግሞ በዓሉ የተለየ ድምቀት አለው።

በበዓሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከውጭ የሚመጡ አማኞች እና ጎብኝዎች ይገኛሉ። ለጎብኝዎቹ ምቹ የኾነ መሥተንግዶ ለማቅረብ እየሠራን ነው። ለንግሡ ለሚመጡ ምዕመናን ማረፊያ የሚኾን ሰፊ ቦታ ተዘጋጅቷል።

ከባለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ መንገዱን ምቹ ለማድረግ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንገዶች አሥተዳደር አማካኝነት መንገዱን የመጠገን ሥራ ተሰርቷል።

ለመኪኖች መቆሚያ የሚኾኑ አራት መናኸሪያዎች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ የሚገኙ ምዕመናን እና ጎብኝዎች በዓሉን በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን። "
#eotctv

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.