ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ባለውለታና መንፈሳዊ አባት አጣች። የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ በነበራቸው ሐዋርያዊ አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ፣ በኢየሩሣሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለብዙ ዓመታት ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለEOTCTV እንደገለጸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ሥርዓተ ቀብር ነገ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተማሩበት በመነኮሱበት እና ለረጅም ዓመታት ባገለገሉበት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን።
seledadotio

7 months ago