ማርበርግ ቫይረስን አስመልክቶ ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የተላለፈ መልዕክት
እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ (ዘጸአት 15:26)።
ማርበርግ ቫይረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጅንካ ከተማ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፣ ይህ ወቅት በበሽታው ሕይወታቸውን ካጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች እና በቫይረሱ ተይዘው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተጎጂዎች ጎን ቆመን በአንድነት ድምፃችንን ወደእግዚአብሔር የምናሰማበት ጊዜ ነው።
ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ብንጮህ ይሰማናል፣ ይፈውሰናል፣ ጤናችንንም ይመልስልናል። እንደዚህ አይነት ፈታኝ ክስተቶች ለምን እንደሚከሰቱ ባናውቅም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ግን እንደማይለየን እናውቃለን። "እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ" (ዘጸአት 15:26) እንዳለ የፈውስ እጁ የታመሙትን ወገኖቻችንን ይዳስስልን፣ ያዘኑትን ያጽናናልን፣ ያረፉትን እረፍተ ነፍስ ይስጥልን፣ የዚህን ቫይረስ ስርጭትንም በምሕረቱ ያቁምልን። በጾምና በጸሎት ከመትጋት ባሻገር ማንኛውንም የጤና ባለሞያዎች እና የጤና ሥነ ምግባር የሚያዘውንና የሚፈቅደውን ሁሉ በማድረግ ለራሳችሁ: ለቤተሰቦቻችሁ: ለማኅበረሰባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የየድሻችሁን እንድትወጡ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት!
©EOTCTV

9 months ago