ማንም ኢትዮጵያዊ የፈለገውን ሀይማኖት እምነት የመከተል የማምለክ መብት
የኢፊድሪ ህገመንግስት
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690
መግቢያ #ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በኢትዮጵያ ያሉ ሀይማኖቶች እኩል መብት ደረጃ በህገመንግስቱ እደል የተሰጣቸው በመሆኑ በእኩልነት ህገመንግስታዊ የእኩልነት መብታቸውን ተጠቅመው የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል የማምለክ መብት እንዳላቸው በህገመንግስቱ አንቀጽ 27 ላይ ተደንግጎ የተቀመጠ ነው። እኛም በዚህ ጽሁፍ ማንም ሰው የፈለገውን ሀይማኖት በግልም ሆነ በአንድነት ሆኖ የማምለክ መብት አለው ሲባል እስከ ምን ድረስ ነው የሚለውን እንመለከታለን።
1. ማንም ሰው
ማንም ሰው ማለት ዘር፣ብሔር በአመለካከት ልዩነት ሳይለይ በፈለገው ሀይማኖት በግሉም ሆነ በቡድን ሆኖ የማምለክ መብት አለው ለማለት ተፈልጎ ነው።
2. የሀይማኖቶች እኩልነት
ሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሀይማኖቶች ሙስሊም፣ክርስትያኑ በሙሉ ህገመንግስቱ በፈቀደላቸው ወይም በሰጣቸው እድል መሠረት በየትኛው ቦታ ሆነው ፈጣሪያቸውን እንደ የእምነታቸው ስረአታቸው ማምለክ ይችላሉ።
3. ከመንግሥት ምን ይጠበቃል?
መንግስት የእኩልነት መብት የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩልነት የማምለክ ስረአታቸውን እድል እንዲጠቀሙ እኩል ምቹ ሁኔታን መጠበቅ አለበት። አንዱን ሀይማኖት አስበልጦ ሌላውን ሀይማኖት አሳንሶ ሳይሆን ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩል የማየት ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህም ህገመንግስታዊ ነው።
4. መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው
በህገመንግስቱ አንቀጽ 11 መሠረት መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውንና አንዱ በአንዱ ጣልቃ በመግባት ስልጣንና አካሄዳቸውን ሊሻማ ሊወስድ ሊያውክ ሌላ ተጽእኖ ሊወስድ፣አላግባብ ሊያስር፣ሊገድል ሌላም አላስፈላጊ ተጽእኖ ከማድረግ ከመቆጠብ ማንም ሀይማኖት በፈለገው ሀይማኖት የማምለክ ሊጠብቅ የመንግስት ግዴታ ሲሆን የሀይማኖት ተቋምም በመንግሥት አሰራር ስልጣን ውስት በመግባት መንግስት በሚሰራው ስራ ላይ ጣልቃ ከመግባት መቆጣብ በህገመንግስቱ የተቀመጠ ግዴታ ነው።
5. ከሀይማኖቶች ምን ይጠበቃል?
ሀይማኖቶች የራሳቸውን እምነት ስረአታቸው በሚፈቅድላቸው መሠረት ሲያካሂዱ የሌላውን ሰው እምነት፣የዜጎችን መብት የመንግስትን ህልውና የሚፈታተን ከተሰጣቸው የመብት ወሰን ሳያልፉ እምነታቸውን የማምለክ ስረአታችን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።
6. አሁን ላይ የእምነት ተከታዮች የማምለክ መብት ተጨባጭ ሁኔታ ምን ይመስላል?
አሁን ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ እና በታወቁ ዜናዎች እንደምንሰማው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ልጆች በተደጋጋሚ ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በተለይም ካህናት፣ቄስ፣ምእመናን ከዚህ በፊት እንደተከሰተው አሁንም በአርሲ የተከሰተ ሲሆን በድጋሚም በወሎ በተመሳሳይ የኦርቶዶክስ ልጆች በጥይት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ህይወታቸው ያለፈ እንዲሁም በርካታ የቆሰሉ እንዳሉም ተገንዝበናል፤ ይህ ኢ ህገመንግስታዊ ድርጊት ነው።
7. የመንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነት እና ግዴታ
ሀይማኖቶች በህገመንግስት የተሰጣቸውን መብት በመጠቀም ስረአቱ በሚፈቅድላቸው ልክ ሊያመልኩ ሊከተሉ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ እንዲሆን ከስጋት ተጠብቀው የመኖር መብታቸው ተረጋግጦ የፈለጉትን ሀይማኖት ስረአት እንዲከተሉ መንግስት የሰላም ጸጥታ ድህንነት ስራ ሊያስጠብቅ ያስፈልጋል።
ከዚህም ባለፈ ዜጎቹ ሲሞቱ የማንኛውም ሀይማኖት ተከታይ ቢሆን ለደረሰባቸው ሞት ዜጎቹ እንደ መሆኑ መጠን ተገቢውን ክብር በመስጠት እውቅና ሊሰጥ ይገባል። ይህ አለመሆኑ የመንግስት ኀላፊነት ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ እና ከዲሞክራሲያዊ ስረአተ መንግስት አካሄድ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ይህን በአንክሮ በመመልከት ሊያስተካክል ይገባዋል።
8. የህግ ምክር
ሀይማኖቶች በህገመንግስቱ አንቀጽ 11፥25፥27 ላይ በተሰጣቸው የማምለክ መብት መሰረት ሀይማኖታቸው በሚፈቅድላቸው ስረአት መሠረት ማምለክ የሚችሉ ሲሆን ይህንን መንግስት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት። ሀይማኖቶችም ይህ መብታቸው ሲጠበቅላቸው በተነጻጻሪ የሌላውን መብቶችን ባከበረ መልኩ ስረአታቸውን ሊፈጽሙ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ/References/
የኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 11፥25፥27
የዩቲዮብ ገጽ
/ eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጽ
/ eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጽ
https://t.me/eotctvcha...
➽ የቲክ ቶክ ገጽ
https://vm.tiktok.com/...
➽ የዩቲዮብ ገጽ Eotc tv 2
• EOTC TV 2 |
➽የትዊተር ገጽ
/ eotct
➽የኢንስታግራም ገጽ
https://www.instagram....
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.facebook.com

5 months ago