26 days ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ አስጀመሩ
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
ሆስፒታሉ በሀገራችን ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትልቅ አማራጭነት የቀረበ ማዕከል መሆኑ ተገልጿል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አቅም ያላቸው ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የመታከም ዕድል ቢኖራቸውም፣ አቅም የሌላቸው ዜጎቻችን ግን በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ሕክምና አግኝተው እንዲድኑ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም ስኬት በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር ዘመኑን የዋጁ ሆስፒታሎች እንዲገነቡና አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።
አክለውም ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
#ethiopia #addisababa #healthsector #oasishospital #healthtourism #ethiopianbroadcastingcorporation

4 months ago
በኦሮሚያ ክልል የካንሰር ታካሚዎችን እንግልት የሚቀንሱ ሁለት ግዙፍ ማዕከላት እየተገነቡ ነው
#ethiopia | በኦሮሚያ ክልል የሚታየውን የካንሰር ሕክምና ተደራሽነት ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ሁለት ዘመናዊ የሕክምና ማዕከላት ግንባታ መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። እነዚህ ማዕከላት በባሌ ሮቤ እና በቡራዩ ከተሞች ነው እየተገነቡ የሚገኙት።
ቁልፍ መረጃዎች፡
* የማጠናቀቂያ ጊዜ፡ የሁለቱም ማዕከላት ግንባታ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
* ዋና ዓላማ፡ ሕክምናው የሚጠይቀውን ከፍተኛ ወጪ መቀነስ እና የአገልግሎት ውስንነቱን በመቅረፍ ለኅበረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ።
* የጤና ቱሪዝም፡ ማዕከላቱ ታካሚዎች ለሕክምና ወደ ውጭ አገር የሚሄዱበትን ወጪ ከመቀነስ ባለፈ፣ በክልሉ የጤና ቱሪዝምን ለማስፋፋት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
የቢሮው ኃላፊ ነጻነት ወርቅነህ እንደገለጹት፣ ማዕከላቱ ሥራ ሲጀምሩ በካንሰር የተጠቁ ዜጎች በአገራቸውና በቅርባቸው ጥራት ያለው ሕክምና እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የላቀ ፋይዳ ይኖራቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #oromia #healthcare #cancertreatment #ethiopia #healthtourism #medicalnews