16 hours ago
አርትስ ፕላስ እና ተራኪ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን አጋርነት መስረቱ
#ethiopia | አዲስ አበባ - አርትስ ፕላስ የድምፅ መጻሕፍትን ለአድማጮች በማቅረብ ከሚታወቀው ተራኪ መተግበሪያ ጋር የይዘት ስምምነት ተበየነ። ይህ ስምምነት በተራኪ መተግበሪያ ላይ የሚገኙ የድምፅ መጻሕፍትን በአርትስ ፕላስ በኩል ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።
ተራኪ መጻሕፍትን በድምፅ በማቅረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኘ ሲሆን፣ በዚህ ትብብር አማካኝነት ይዘቶቹን ለተጨማሪ ተጠቃሚዎች ማቅረብ ያስችለዋል።
በትብብሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በተራኪ የሚገኙ የልጆች የድምፅ መጻሕፍት በአርትስ ፕላስ መተግበሪያ ላይ ይቀርባሉ። እነዚህ ይዘቶች በአርትስ ፕላስ ኪድስ ምድብ ስር የሚስተናገዱ ሲሆን፣ ለሕፃናት እና ለታዳጊዎች በጎ ሥነ ምግባርን፣ እውቀትን እና የፈጠራ ክህሎትን የሚያጎለብቱ ይሆናሉ።
የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ይህ አጋርነት የሀገሪቱን የኪነ ጥበብ እና የፈጠራ ዘርፍ ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
አርትስ ፕላስ በቅርቡ አገልግሎቱን በይፋ የሚጀምር ሲሆን፣ በሂደቱ ስለሚካተቱ መጻሕፍት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ወደፊት ይፋ ይደረጋሉ።
ድረ ገጽ https://artsplus.tv/
አንድሮይድ https://play.google.com/st...
አይኦኤስ https://apps.apple.com/app... #artsplus #teraki #audiobooks #ethiopianliterature #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድገው "ArifSchool" በይፋ ተዋወቀ!
#fastmereja : የሀገሪቱን የትምህርት ዘርፍ የእሴት ሰንሰለት በቴክኖሎጂ ለማቀናጀትና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ብሄራዊ ስትራቴጂን ግቦች ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀው "ArifSchool" የተሰኘ የተቀናጀ የዲጂታል ትምህርት ስነ-ምህዳር በዛሬዉ እለት ይፋ ተደርጓል።
በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ጥምረት በአራት ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂና የትምህርት ተቋማት ማለትም በአሪፍፔይ (Arifpay)፣ ኤአይቲ (AIT)፣ ገበያ (Gebeya - Dala Studios) እና ኤጁኬሽን ማተርስ (EducationMatters) መካከል የተመሰረተ ነው።
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ የትምህርት ቤት አስተዳደርን፣ የፋይናንስ ግብይትን፣ በሰው ሰራሽ አስተዋፅዖ (AI) የታገዙ የመማሪያ መሳሪያዎችን እና የስነ-ምህዳር ምክር አገልግሎትን በአንድ ጥላ ስር የሚያገናኝ ስለመሆኑ ተገልጿል።
በማስተዋወቂያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ እያንዳንዱ ተቋም በዘርፉ ያለውን ልምድና ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ ያቀረበ ሲሆን የትምህርት ቤት ክፍያዎችን፣ የወላጆችን መዋጮ እና የሰራተኞችን ደሞዝ በዲጂታል መንገድ በማዘመን የትምህርት ቤቶችን የፋይናንስ አስተዳደር ሸክም እንደሚቀንስ የተገለፀ ሲሆን ይህም የሀገሪቱን የዲጂታል ክፍያ በ2030 ሰባት እጥፍ ለማሳደግ ከተቀመጠው ብሄራዊ ግብ ጋር የተናበበ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ብሄራዊ የትምህርት ደረጃን የጠበቀ የትምህርት ቤት ማኔጅመንት እና የኢ‐ለርኒንግ መድረክን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የተማሪዎችን ክትትል፣ የክፍል መርሃ-ግብር፣ ምዘና እና ምናባዊ ክፍሎች (Virtual Classrooms) በስርዓት ለመምራት ያስችላል፣ተማሪዎችና መምህራን የራሳቸውን የፈጠራ ስራዎች፣ የታሪክ መጽሃፍት፣ የዝግጅት ማቅረቢያዎች እና ድረ-ገጾች እንዲያዘጋጁ የሚያስችሉ የጄነሬቲቭ ኤአይ (Generative Al) ቴክኖሎጂዎችን የሚያበረክት መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪ የቴክኖሎጂውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የአቅም ግንባታ፣ የስልጠና ድጋፍ፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና የለውጥ አመራር (Change Management) ስራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል።
ይህ ዘመናዊ መፍትሄ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚከናወን ሲሆን፤ በገጠርም ሆነ በከተማ ለሚገኙ የመንግስት፣ የግል እና የህዝብ ትምህርት ቤቶች እኩል ተደራሽ እንዲሆን ተደርጎ መቅረጹ ተገልጿል።
በዛሬዉ እለት ይፋ በተደረገዉ አዲስ ቴክኖሎጂ አራቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራርመዋል።

5 months ago
Exciting News !!
Zewotir Joined Arts TV / Arts Plus.
Zewotir Desalegne joins us to lead and host an international diplomatic podcast crafted to amplify Africa’s voice on the global stage.
This is more than a show. It’s a conversation that matters.
Stay tuned for the launch and a new wave of fresh content.
📽️ Arts Plus : Download the App Now and Start Watching
🌐 ድረ ገፅ: https://artsplus.tv/
📱 Android (Google Play): https://play.google.com/st...
🍎 iOS (App Store): https://apps.apple.com/app...
#artsplus #ethiopian #ethiopiancinema #africanmovie #movie

7 months ago
ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT) የ9ኛ ዙር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ!
#fastmereja I በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የላቀ የሰው ኃይል በማፍራት ቀዳሚ የሆነው ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)፤ 350 ወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በኦሮሚያ ባህል ማዕከል አዳራሽ ታላላቅ የክብር እንግዶች፣ የቴክኖሎጂ መሪዎች እና ወላጆች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ።
ተመራቂዎቹ ላለፉት ወራት በተግባር የታገዘ (Project-Based) ከፍተኛ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ሲሆን፣ በገበያው እጅግ ተፈላጊ በሆኑት የሚከተሉት ዘርፎች በቂ ክህሎት እና እውቀት ጨብጠዋል፡-
✅ Full-Stack Web Development (ዌብሳይትና ሲስተም ልማት)
✅ Python & Data Science (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዳታ ሳይንስ)
✅ Mobile App Development (የሞባይል መተግበሪያ ልማት)
✅ Cyber Security (የሳይበር ደህንነት)
✅ Digital Marketing & Graphics Design
✅ Video Editing & Basic Computer Skills…
በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ተወካይ አቶ ኪዳኔ ይብጌታ፤ "ዓለም አሁን የምትመራው በቴክኖሎጂ ነው። እኛ ሀገር ቡና ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ እንደሚገኘው ሁሉ፤ እነዚህን ብቁ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለአለም ገበያ በማብቃት (Exporting Talent) ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆን እንችላለን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት እና ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙት ዶ/ር ቢላል ከማል በበኩላቸው፤ "የወደፊቱ ጊዜ የ AI እና የዳታ ነው። ዛሬ የተመረቃችሁ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር (Digital Ethiopia 2030) ወሳኝ ሚና ትጫወታላችሁ" በማለት አደራ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ከአሪፍ ፔይ (ArifPay) እና ከአዲስ ቬሪፋይ (Addis Verify) የተጋበዙ የዘርፉ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በፓናል ውይይት ተሳትፈው ለተመራቂዎች የህይወት እና የሙያ ልምዳቸውን አካፍለዋል።
ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)፤ "ቴክኖሎጂን ከእውቀት ወደ ተግባር" በሚል መሪ ቃል፤ የሀገራችንን ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።
ለተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ! የወደፊት የሥራ ዘመናችሁ የስኬት እና የፈጠራ ይሁንላችሁ!
📍 ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)
"ነገን ዛሬ እንገንባ!"
📞 +251 987 14 3030
🌐 www.mizantechinstitute.com

8 months ago
በዲጂታል የክፍያ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እገዳ በከፊል ተነሳ‼️
- ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች ኃላፊዎች አሁንም በቁጥጥር ሥር ናቸው
የፌዴራል ባለሥልጣናት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ላይ በወሰዱት እርምጃ ታግደው የነበሩ የባንክ ሂሳቦችን በከፊል አንስተዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ የያጉት ፔይ (YagoutPay) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ዓለማየሁን ጨምሮ የ50 ግለሰቦች የባንክ ሂሳቦች እንዲንቀሳቀሱ አዟል። እነዚህ የባንክ ሂሳቦች ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ ህዳር 23 ቀን፣ በዘርፉ የታየ የፋይናንስ ብልሹ አሰራርን ለመመርመር በሚል ታግደው የቆዩ ናቸው።
በተጨማሪም፣ ለዘጠኝ ቀናት የባንክ ሂሳቦቻቸው ተገድበው የነበሩ 10 የዲጂታል ክፍያ (Gateway) ኩባንያዎች እገዳው ተነስቶላቸዋል።
የሚኒስቴሩ የሀብት ማስመለስ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ፀጋ ዋቅጅራ ውሳኔውን ለሁሉም ባንኮች በይፋዊ ደብዳቤ አሳውቀዋል።
እገዳው የተነሳላቸው የክፍያ ተቋማት አሪፍ ፔይ (ArifPay Financial Technologies): አዲስ ፔይ (AddisPay Financial Technologies): ፈናን ፔይ (FenanPay Solutions): ላኪ ፔይ (LakiPay Financial Technologies):
ስታር ፔይ (StarPay Financial Services): ያጉት ፔይ (YagoutPay)
ሳንቲም ፔይ (SantimPay Financial Technologies): ካቻ (Kacha Financial Technology): እና ሲናን ፔይ (Sinan Pay Solutions) ናቸው::
ምንም እንኳን የኩባንያዎቹ የባንክ ሂሳቦች ቢለቀቁም፣ የምርመራው ሂደት ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳንቲም ፔይ፣ የቻፓ ፔይ (Chapa Pay) እና የአሪፍ ፔይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሁንም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን፣ “ከፍተኛ የፋይናንስ ሕገ-ወጥነት” ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደጠቆሙት፣ የምርመራው ዋነኛ ትኩረት የግብር ስወራ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ላይ ነው። የፌዴራል ባለሥልጣናት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግና ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ ቅድሚያ ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ።
seledadotio

9 months ago
የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
#fastmereja I አሪፍ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ከኢትዮጵያ ፊንቴክ ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ፎረም (ETIFT) ጋር በመተባበር በዲኦሎፖል ሆቴል የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ አካሂዷል። የማይክሮ ፋይናንስ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለድርሻ አካላት የተገኙበት ጉባኤ ትኩረቱን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና የገጠር ዜጎችን የሚያገለግሉትን የኢትዮጵያን ወሳኝ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (MFIs) ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ማዋሃድ እንደሆነ ተገልጿል።
ተቋሟቱን ከዲጂታል ጋር የማስተሳሰር ስራው በአሪፍፔይ እየተሰራ ሲሆን ከስራዎቹ መካከል የአሪፋይ ኤምኤፍአይ ስዊች (MFI Switch) አንዱ መሆኑ ተነግሯክ። ይህ አዲስ፣ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሠረተ ልማት ሁሉንም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያለምንም እንከን ከብሔራዊ የክፍያ አውታረ መረብ ጋር ለማገናኘት የተነደፈ ነው።
የአሪፍፔይ ዲጂታል ዋሌት የማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ብድር እንዲቀበሉ እና በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።
በጉባኤው ላይ እነዚህ እና ሌሎች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በጋራ ለማልማት Arifpay እና EtIFT የአጋርነት ስምምነት ፈጽሟል።
አሪፍፔይ በአሁኑ ወቅት ከ120 በላይ ሰራተኛ ይዞ በቀን እስከ 680 ሚሊዮን ብር በአሪፍፔይ በኩል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝበት ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

10 months ago
Arts TV proudly brings you the grand celebration honoring African excellence and Ethiopian pride.
Watch the full ceremony; exclusively on Arts TV tomorrow!
dashenbankofficial @ethiotelecom arifpayet

Sponsored by
Surafel
10 months ago
🇺🇸 የአሪፍ ፔይ ቴክኖሎጂ ሶሊውሽንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረድኤት ጽጌብርሃን የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት ላይ ለመገኘት አሜሪካ ደርሷል
Excitement in the air!! Our guests in DC!
Let us Shine Bright Yellow this Saturday! 💛 3 days left to the Grand African Run.
Lace up, bring your energy, and let’s fill Alexandria with smiles.
📅 Sat, Oct 11 • 9:00 AM (arrive 8:00)
📍 1100 Main Line Blvd, Alexandria, VA
Car prize lottery at the finish — must be at the event to win.
ArifPay is joining us at the Grand African Run!
Come meet the ArifPay team at their booth on October 11 (morning) in Alexandria, Virginia. They’re excited to connect with our community, answer your questions, and show how ArifPay is making everyday payments simpler, faster, and smarter.
📅 October 11 | Morning
📍 Alexandria, VA
#grandafricanrun #arifpay #digitalpayment #communityfirst #runtogether #alexandriava
የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ይፈልጋሉ?
ስኬትን እና የላቀ ስራን አክብረን በምንሸልምበት ፕሮግራማችን ላይ ይገኙ። አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ጋሽ ማህሙድ አህመድ፣ አቶ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን የዘንድሮ ተሸላሚዎቻችን ናቸው።
🎶 በዕለቱ ልዩ የበጎ አድራጎት የሙዚቃ ፕሮግራም ይቀርባል
🍽️ የእራት ግብዣም ይኖረናል
🎤 የአሜሪካ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎች እና የልዑክ ቡድኖች ይገኛሉ
በየአመቱ ልዩ ተሸላሚዎች ከስፖርት፣ ከኪነጥበብ ወይም ከቢዝነስ ዘርፍ ተመርጠው ላደረጉት በጎ አስተዋፅኦ ሽልማት ይበረከትላቸዋል፣ ለስራቸውም ይመሰገናሉ።
📍 ቦታ: Civic Building, 1 Veteran Plaza, Silver Spring, Maryland
🗓️ ቀን እና ሰዓት: ኦክቶበር 12, 5:30 PM
👉 ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ: https://www.eventbrite.com...
#africanimpactaward #celebratingexcellence #communityandachievement

Comments